Blog Archives

“ጦርነት ያብቃ፣ ሠላምና ዲሞክራሲ ይስፈን” የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓረቲዎች ኮክሰ

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ኹኔታ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን “ተስፋ ሰጪ ነገሮች የማይታዩበት” ነው ሲል የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓረቲዎቸ ስብስብ – ኮክሰ ሥጋቱን ገለፀ። በቅድሚያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የአሰራርና ተቋማዊ” ያላቸው ችግሮች እንዲፈቱ የጠየቀው ኮከስ በተቋሙ “እውነተኛ ሪፎርም ከሌለ ተዓማኒ፣ አካታች፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሊኖር አይቸልም” ብሏል። በዋናነት 8 የፓለቲካ ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ያደርጉበታል የተባለው ኮከስ ስለ ምርጫ ከመታሰቡ በፊት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ጦርነት እና ግጭቶች እንዲቆሙ፣ ሰላም እንዲሰፍን እና በተለይ ከኤርትራ ጋር እየተስተዋለ ያለው ውጥረት እንዲፈታ ጠይቋል። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓረቲዎቸ ስብስብ – ኮክሰ ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግጭጦች እንዲቆሙ ደጋግሞ ቢጠይቅም አሁንም ለሀገር ደኅንነት ሥጋት ሆነው መቀጠላቸውን ገልጿል። የዚህ ስብስብ አባል ፓርቲ የሆነው የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል ሞጊሶ “ጦርነት ይብቃ” የሚለው አሁንም ዋና የጥሪያቸው ጭብጥ መሆኑን ገልፀዋል። “ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ከተፈለገ ጦርነት መቆም አለበት። ይሄ ነገር እየሰፋ በሄደ ቁጥር ይቺ ሀገር እያየን ልትፈርስ ትችላለች”። ኮከስ ቀጣዩን ምርጫ ለማከናወን አስቻይ ኹኔታ የለም ብሏል ኮከስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከጅምሩ “የነጻነት እና የገለልተኝነት” ጥያቄዎች እንደሚነሱበት በመጥቀስ አሁንም አሉበት ያላቸው “የአሰራርና ተቋማዊ ችግሮች” እስካልተፈቱ ድረስ “ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ሊኖር አይችልም” ብሏል፡፡ “እውነተኛ ሪፎርም ከሌለ ተዓማኒ፣ አካታች፣ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ”  ሊኖር እንደማይችልም አቋሙን ይፋ አድርጓል። “ሕዝብ ሰላማዊ ባልሆነበት ኹኔታ ዲሞክራሲን አይደለም የሚመርጠው። ሕዝብ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አሜሪካ ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊ አብርሃም ታደሰ በርግጥ አስገድዶ ደፈረ ? ሐቁ ምንድነው ?

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ ተቀሰቀሰ

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ 14 ወረዳዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ መቀስቀሱን ዋዜማ ሰምታለች። ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤው ላይ መሆኑን ያስረዱት ምንጮች፣ ይህንኑ ተከትሎ በቅርቡ እንደ አዲስ በተዋቀረው የምስራቅ ቦረና ዞን መቀመጫ ነጌሌ ቦረና ከተማ እና የቦረና ዞን መቀመጫ በሆነችው ያቤሎ ከተማ፣ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች ከዛሬ ማለዳ አንስቶ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆኑን ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመልክታል። ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ በምክር ቤቱ የተወሰኑት 14ቱ ወረዳዎች በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ቦረና፣ ባሌ፣ ሐረርጌ እንዲሁም ከድሬደዋ አካባቢዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው እንደሆኑ ምንጮች ነግረውናል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 21፣ 2017 ዓ፣ም እኩለ ቀን ድረስ በፌዴራልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ የተባለ ነገር የለም። [ዋዜማ]
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በትግራይ ላይ ወታደራዊ ዛቻ …. በኢትዮ ሱዳን ኮሪደር የተሰማራው የኮማንዶ ጦር

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኤኮኖሚ

እነ ታማኝና ብርሐኑ ነጋ የካዷትን አገር የተሸከመው ፖለቲከኛ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ይድረስ ለአስቂኙ ኢታማዦር- ከፋኖ አመራሮች የተላከ ጦማር

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በIMF የተማረሩ ሀገራት! በመጨረሻ IMF ኢትዮጲያ ደርሷል

በIMF የተማረሩ ሀገራት! በመጨረሻ IMF ኢትዮጲያ ደርሷል! በ IMF ድጋፍ ዙሪያ ክርክር አለ! ለሀገራት ይጠቅማል እና ይጎዳል! ከ IMF ድጋፍ ተከትለው ስለሚመጡ የጉዳት ማስረጃዎች ከጥቅሙ ይበዛሉ! ከ IMF ጋር ሪፎርም በማድረግ ከፍተኛ መማረር ውስጥ ስለገቡ ሀገራት እና ምክንያት በምሳሌ እመለከታለን! ኢትዮጲያ ከIMF ጋር የቅርብ ሪፎርም አካል ነች! የአንድ ዓመቱን ምልክት ከሌሎች ሀገራት ጋር እያነጻጸርን እመለከታለን!  https://youtu.be/T631z06d49g
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃ ጉሊት የምትቸረችረው የደምቢዶሎዋ መምህርት

አባይነሽ ሐምቢሳ በደምቢዶሎ ከተማ በሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ተመርቃ መንገድ ላይ አትክልት እና ፍራፍሬ በመቸርቸር የምትተዳደረው መምህርት ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቶ በርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል። አባይነሽ ሐምቢሳ የተባለችው ይህች መምህርት ከደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ በሒሳብ የትምህርት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪዋን ያገኘችው በማዕረግ ነው። ይህች መምህርት ላለፉት ዓመታት ትምህርት በሚዘጋበት በክረምት ወቅት እንዲሁም በእረፍት ቀኗ ቅዳሜዎችን መንገድ ላይ በመቸርቸር ነው ኑሮዋን የምትደግፈው። ለ13 ዓመታት በመምህርነት ያገለገለችው አባይነሽ በየወሩ የምታገኛት 7,500 ብር ደመወዝ ካለው የዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ ኑሮዋን መደጎም ስላዳገታት ነው ወደ ጉሊት የወጣችው። “የማገኘው ደሞዝ ልጆቼን ለማስተዳደር፣ ማኅበራዊ ሕይወቴን ለመደገፍ፣ ለትምህርት፤ ለአጠቃላይ ለኑሮዬ በቂ አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ለመንግሥት ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ በቂ አይደለም፤ ያለውን የኑሮ ውድነትን ያገናዘበ አይደለም” ትላለች። ከማስተማር ሥራዋ ጎን ለጎን ትምህርቷን በከፍተኛ ደረጃ መቀጠሉ አስፈላጊ ሆና ያገኘችው አባይነሽ፣ የማስተርስ ትምህርቷን ለመደጎምም ሌላኛው አማራጩ ጉሊት ነበር። “በወር ደሞዜ የትምህርቴን ከፍዬ፣ ኑሮዬን ደግፌ፣ ለልጆቼ አውጥቼ አይሆንም” ስትል የአራት ልጆች እናት የሆነችው አባይነሽ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጻለች። በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ዩብዶ ወረዳ የተወለደችው አባይነሽ የጉሊት ችርቻሮዋን የጀመረችው ከሁለት ዓመታት በፊት ነው። ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ እና አቮካዶ የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን ከደምቢዶሎ ከ20 አስከ 25 ደቂቃ በእግር የሚያስኬድ መንገድ ከሚጠይቀው ስፍራ ተሸክማ አምጥታ በከተማዋ ትችረችራለች። ገበያ በደራበትም ቀንም ከ200 አስከ 500 ብር ታገኛለች። “ከማገኘው ትርፍ 100 ወይም 200 ብር አስቀምጬ ቀሪውን ደግሞ ለቤተሰቤ የሚያስፈልጉ እንደ ሳሙና፣ ስኳር ወይም
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ፋኖ በአርማጭሆ ሙሉ ክ/ጦር ደመሰሰ! ….. ሁለቱ ክልሎች ውጊያ ጀመሩ!

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በምን ኹኔታ የሚገለጽ ነው?

"ለምሳሌ ቁርስ በልቶ ምሳ የማይደግም ሰው ሊኖር ይችላል። ሲቀጥል ደግሞ አንድ ነገር ሲጨምር እየጨመረ ነው እንጂ እየቀነሰ አይመጣም"። አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በምን ኹኔታ የሚገለጽ ነው? አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በምን ኹኔታ የሚገለጽ ነው?  
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ፈተና

የሰሜን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክ (ከማኅደራችን) የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ፈተና  
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

የፌዴራል ገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ሥራ ላይ ከዋለ የውጭ ኢንቨስትመንት ሊጎዳ እንደሚችል ተነገረ

የፌዴራል ገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ ከተደረገ የአገሪቱን የውጭ ኢንቨስትመንት ሊጎዳ እንደሚችል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳሰበ፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ የጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በጠራው የምክክር መድረክ የንግድ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የሒሳብ ባለሙያዎች፣ የፌዴራልና ክልል መንግሥታት ተወካዮች፣ የሙያ ማኅበራት፣ የንግድ ተቋማትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ነው ማሳሰቢያው የተሰጠው፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በውይይት መድረኩ ከተገኙ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን፣ ድርጅቱን ወክለው የተገኙት አቶ ዳዊት ፍሰሐ በረቂቅ ሕጉ ላይ ቢስተካከሉ ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡ አንድ ድርጅት እየከሰረ መቀጠል እንደማይችልና ኪሳራው ከቀጠለ እንደሚዘጋ በረቂቅ ሕጉ ላይ መጠቀሱን ገልጸው፣ ነገር ግን እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላለ ልዩ የኢንቨስትመንት ባህሪ ላለው ተቋም የማይሠራ በመሆኑ ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ያለን የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለ15 ዓመታት የሚል ነው፡፡ ይህ ፈቃድ በየ15 ዓመት እንደሚታደስ ሆኖ ለ30 ዓመት የሚቆይ ነው ብለን ነው የምናስበው፡፡ ኢንቨስትመንታችን በሙሉ ለ30 ዓመታት መቆየትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው፡፡ ኢንቨስትመንታችን ትርፍ አለ ብለን በምናስብባቸው ቦታዎች ሁሉ አይደሉም፡፡ በየቦታው ታወሮችን መገንባትን ጨምሮ ብዙ ካፒታል የሚያስወጡ ሥራዎች አሉብን፡፡ የኔትወርክ ሽፋን ለማስፋት የመገንባት ግዴታዎች አሉብን፡፡ በአራት ዓመታት ውስጥ ለመሠረተ ልማት ማስፋፊያና ግንባታ ከ350 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርገናል፡፡ ይህን የምናደርገው በረዥም ጊዜ ትርፍ ይመጣል በሚል ዕቅድ ነው፤›› ብለዋል፡፡ አቶ ዳዊት አክለውም፣ ‹‹ኢንቨስት የምናደርገው ትርፍ በሚገኝባቸው ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ስለፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጠቡ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክተው ስላደረጉት ንግግርም ሆነ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠርተው ስለነበራቸው ውይይት ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታው ሀደራ አበራ (አምባሳደር)፣ ከአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ ጋር ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት ማድረጋቸውን ገልጾ ነበር፡፡ ውይይቱን በተመለከተም ሆነ የፕሬዚዳንት ትራምፕን ንግግር አስመልክቶ ሪፖርተር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመለከታቸውን ኃላፊዎች ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ያልተሳካ ሲሆን፣ በዋትስአፕ ጥያቄ የቀረበላቸው አምባሳደር ማሲንጋ ከሚኒስትር ደኤታው ጋር ስለነበራቸው ቆይታም ሆነ ስለትራምፕ ንግግር ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለጽ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰኔ ወር ውስጥ ‹‹ትሩዝ›› በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ በከፍተኛ መጠን ወደ ግብፅ የሚፈሰውን ውኃ ለሚገድበው ለግዙፉ የህዳሴ ግድብ አገራቸው ‹‹በሞኝነት›› የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን አስታውቀው፣ ነገር ግን በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ሰላም እንዲወርድ ጥረት ማድረጋቸውን በመጥቀስ፣ የሰላም ኖቤል ሽልማት ይገባቸው እንደነበር መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ትራምፕ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ ፒት ረትና ከተለያዩ ሹማምንቶቻቸው ጋር በዋይት ሐውስ ሲወያዩ፣ በዓለም ግዙፍ ከሆኑ ግድቦች አንዱ የሆነውና ‹‹ከግብፅ ወጣ ብሎ የሚገኘው›› ያሉትን የታላቁ የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ትልቅ ችግር መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ በዚህኛውም ንግግራቸው አገራቸው አሜሪካ ግድቡን ፋይናንስ ማድረጓን ጠቅሰው፣ የግድቡ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ችግሩ ለምን እንዳልተፈታ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ትራምፕ የዓባይ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ውስጥ የሚሰሩ ከ40 በላይ ሰራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ተገኙ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ውስጥ የሚሰሩ ከ40 በላይ ሰራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ተገኙ “ሐሰተኛ ማስረጃ ይዘው ከተገኙት ውስጥ እንደ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴዎች ባለሙያዎች እና ዳይሬክተሮች ይገኙበታል” የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል ከሆኑ በፅሁፍ የተዘጋጀውን ይህን መረጃ ይከታተሉ ⤵️ https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/40?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ትራምፕ አሜሪካ የኢትዮጵያውን ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በገንዘብ ደግፋለች ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ የኢትዮጵያውን ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በገንዘብ ደግፋለች ሲሉ ርግጠኝነት በሌለው መልኩ ትናንት በድጋሚ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ግድቡ ወደ ናይል ወንዝ የሚሄደውን ውሃ ይዘጋዋል በማለትም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፣ አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ እየሠሩበት መኾኑንና ችግሩ መፍትሄ እንደሚያገኝ በደፈናው ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ “መፍትሄ” ያሉት ምን እንደኾነ ግን አላብራሩም። መንግሥት፣ ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካኹን ቀደምም ይኹን ትናንት ለተናገሩት አወዛጋቢና አሳሳች አስተያየት፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡ ኮንፌዴሬሽን ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት እንደሆነ የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል፡፡ ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው ብለዋል፡፡ ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል፣ ልብስ ይለብሳል ፣ ህክምና ይሄዳል ብለዋል፡፡ ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ያሉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉ ጥያቄ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የኢትዮጵያ የዓመቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲመዘን

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የዓመቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲመዘን የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ እንቅስቃሴማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ ከምዕራባዊያን ሀገራት እና ተቋሞቻቸው ጋር ባላት ግንኙነት “ተቀባይነቷ የጨመረበት” ዓመት መሆኑን የጠቀሱ አንድ የዘርፉ ተንታኝ፣ የገንዘብ ተቋማት እያደረጉት ያለውን የብድር ድጋፍ አስረጂ አድርገዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት “አስጊነቱ አሁንም የቀጠለ” እና በጥቅሉ ሲመዘን “አድገናልም፣ ወድቀናልም የሚያስብል ኹኔታ ያልተፈጠረበት” ነው ብለዋል። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል ዐቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በኩል እንዳለው የተቋሙ የዚህ ዓመት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ “ውጤታማ” ነበር። ቃል ዐቀባዩ ለዚህ ዝርዝር ጉዳዮችን የጠቀሱ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው። “የዲፕሎማሲ ግንኙነታችንን በማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን በማሳደግ፣ ከጎረቤት ሀገሮች እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ትብብር እንዲቀጥል፣ ቀጣናዊ ትስስርን፣ አሕጉራዊ እና አለማቀፋዊ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል”።የሰላም
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የውጭ ምንዛሬ ተመን የ36.9 ቢልዮን ብር ኪሳራ እንዳስከተለበት ታወቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር ተያይዞ የመጣው አዲስ የውጭ ምንዛሬ ተመን የ36.9 ቢልዮን ብር ኪሳራ እንዳስከተለበት ታወቀ “ባንኮች በእንዲህ አይነት የምንዛሬ ተመን ለውጥ ወቅት ኪሳራ እንደሚያጋጥማቸው ቢታወቅም የዚህ የኪሳራ መጠን ግን እጅግ ከፍተኛ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል” የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል ከሆኑ በፅሁፍ የተዘጋጀውን ይህን መረጃ ይከታተሉ ⤵️ https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/369?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

ሲቪል ማህበራት ለምርጫ ጉዳይ ከውጭ ምንጮች የገንዘብ ድጋፍ እንዳይቀበሉ ታገደ

መንግሥት፣ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለፖለቲካ ቅስቀሳ’፣ ለመራጮች ትምህርትና ለምርጫ ታዛቢነት ሥራዎች ከውጭ ምንጮች የገንዘብ ድጋፍ እንዳይቀበሉ የሚከልክል ድንጋጌ በማካተት የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል። ማሻሻያው፣ በውጭ ድርጅቶችና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች የተመሠረቱ አገር በቀል ድርጅቶች፣ በኢትዮጵያዊያን ለተቋቋሙ አገር በቀል ድርጅቶች የገንዘብ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ እንደማይሠጡ እንደሚያግድም ዘገባው ጠቅሷል። በሥራ ላይ ባለው አዋጅ በተጣለበት ዕገዳ ቅር የተሠኘ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ቅሬታውን ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅርብ ይችላል ተብሎ የተደነገገው መብት፣ የመጨረሻው ውሳኔ ሠጭ የባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ ነው በሚል አንቀጽ መተካቱንም ዘገባው አመልክቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ብሔራዊ ባንክ 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ገጠመው

ብሔራዊ ባንክ በፈረንጆቹ 2024 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት መረጋገጡን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ባንኩ ኦዲት የተደረገው፣ መንግሥትና ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት በደረሱበት ስምምነት መሠረት ነው። ባንኩ ወርቅ የገዛበትና የሸጠበት ዋጋ ልዩነት መስፋቱ፣ ባንኩ ለመንግሥት አበድሮ ያልተመለሰለት ገንዘብ፣ የብር የመግዛት እቅም መዳከምና ከዓለማቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ያለበት ዕዳ በውጭ ምንዛሬ የሚከፈል መኾኑ ለኪሳራው አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል። ባንኩ ለመንግሥት ባንኮች 134 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር፣ ለግል ባንኮች 13 ቢሊዮን ብር እና ለመንግሥት 687 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር አበድሮ ገና አልተመለሰለትም ተብሏል
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በኦሮሚያ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከ500 ብር ጀምሮ በግዳጅ መዋጮ ተሰበሰበ

በኦሮሚያ ክልል አዋሽ ቢሾላ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ለሁለት ወራት የመሠረታዊ ውትድርናና ፖለቲካዊ ሥልጠና ሲወስዱ ለነበሩ የክልሉ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል ለማድረግ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከ500 ብር ጀምሮ በግዳጅ መዋጮ እንደተሰበሰበ ዋዜማ ሠምታለች። አመራሮቹ፣ ሥልጠናውን አጠናቀው ትላንት ወደየመጡባቸው አካባቢዎች መመለሳቸውን ዋዜማ ተረድታለች። መዋጮውን ለማዋጣት ፈቃደኛ ባልኾኑ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ሰደረግባቸው እንደነበርም ምንጮች አስረድተዋል። ከ17 ሺሕ በላይ ሠልጣኝ አመራሮች መካከል ስድስቱ በሥልጠናው ክብደትና በአካባቢው ሞቃት የአየር ጠባይ ሳቢያ ስድስቱ ሕይወታቸው ማለፉንና 200 ያህሉ ከካምፑ መጥፋታቸውን ዋዜማ ቀደም ሲል መዘገቧ አይዘነጋም።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት በአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ይዛለች።

ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት በአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ይዛለች። የኢኮኖሚስት ኢንተሌጀንስ ዩኒት ዓለማቀፍ የኑሮ ውድነት የ2025 ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከዓለም አገራት በ46 ነጥብ 5 ነጥብ 53ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ሪፖርቱ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ለምግብና ትራንስፖርት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በአፍሪካ ቀዳሚ እንደኾኑ ገልጧል። በአገሪቱ ውስጥ ለሥራም ይሁን ለግል ጉዳይ ትራንስፖርት መጠቀም ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል ተብሏል።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በመንግስት እየቀረበ ያለው የደሞዝ ግብር መጠን እና ኢሠማኮ ያቀረበው መነሻ የሰማይ እና የምድር ያህል ልዩነት አለው!

ኢሠማኮ፣ ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8 ሺሕ 384 ብር የኾኑ ሠራተኞች ከደመወዝ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ ኢሠማኮ፣ በወር ከ8 ሺሕ 384 ብር እስከ 22 ሺሕ 974 ብር የሚያገኙ ሠራተኞች 10 በመቶ፣ ከ22 ሺሕ 975 እስከ 44 ሺሕ 530 ብር የሚከፈላቸው 15 በመቶ፣ ከ44 ሺሕ 531 እስከ 72 ሺሕ 336 ብር የሚከፈላቸው 20 በመቶ እንዲኹም ከ72 ሺሕ 337 እስከ 107 ሺሕ 449 ብር የሚከፈላቸእ የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መጠየቁን ዘገባው ጠቅሷል። ከ107 ሺሕ 450 እስከ 150 ሺሕ 107 ብር ባለው ደመወዝ ላይ 30 በመቶ ግብር እና ከ150 ሺሕ 108 ብር በላይ ደሞዝ ላይ ደሞ 35 በመቶ ግብር እንዲጣል ኢሠመኮ ጠይቋል ተብሏል። አዲሱ ግብር የሚከፈልበት የደሞዝ መጠን! የኢሠማኮ አማራጭ ቁጥሮች! በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሰራተኞች የደሞዝ ግብር መጠን በገንዘብ ሚኒስትር ረቂቁ ቀርቦ ውይይት ላይ ነው! ነገር ግን በመንግስት እየቀረበ ያለው የደሞዝ ግብር መጠን (ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ደሞዝ) እና የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ያቀረቡት መነሻ የሰማይ እና የምድር ያህል ልዩነት አለው! የተቀመጠውን የደሞዝ እና የግብር መጠን በዝርዝር ከነምክንያቱ እንመልከተው…. https://youtu.be/dAydraFIzwk
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በጎንደር ጠንካራ ውጊያ እየተደረገ ነው

በጎንደር ጠንካራ ውጊያ እየተደረገ ነው ግንቦት 27/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ጎንደር ቀጠና አዲስ የተደራጀው ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር በጎንደር ኮማንዶ በላይ የተሰኘ ንዑስ ልዩ ኦፕሬሽን ጀመረ። የዘመቻ ቋራ ቃል ኪዳን አካል የሆነ ንዑስ ልዩ ኦፕሬሽን እየተደረገባቸው የሚገኘው … 🔸፩ኛ የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር የጎንደር ብርጌድ፣የቃኘው ብርጌድና የዓፄ ፋሲለደስ ብርጌዶች በጥምረት ጎንደር ከተማ ምስራቃዊ አቅጣጫ ዘልቀው በመግባት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ብርቱ ውጊያ በማድረግ የጠላትን ምሽግ እየሰበሩ እየገሰገሱ ነው። መረጃው እስከደረሰበት ሰዓት ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን በከተማው በጥብቅ ጥበቃ ስር የሚገኘው የአገዛዙ ሹመኛ እየራደ ይገኛል። 🔸፪ኛ በጎንደር ከተማ ደቡባዊ አቅጣጫ የዓፄ ቴዎድሮስ አይሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ብርኃላ የተባለ የጠላት ምሽግን በማፈራረስ በጥልቀት ለመግባት እየተዋጋ የሚገኘው የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የታድሎ ብርሃን አካል ብርጌዶች ናቸው።በዚህ የጎንደር ከተማ አስ/ር ጠዳ ክ/ከተማ እየተደረገ በሚገኘው ተጋድሎ የኦህዴድ ብልፅግና ጨፍጫፊ ታጣቂ በጀግናው ሰራዊታችን ብርቱ ክንድ እየተደቆሰ ይገኛል። 🔸 ፫ኛ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አዳሩን ማክሰኝት ከተማን ጠላትን ደምስሶ ሰብሮ በመቆጣጠር የወረዳውን ፖ/ጣቢያ በመስበር ከ70 በላይ የግፍ እስረኞችን ማስለቀቅ የቻለው የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና የዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ነው።አሁንም ከተማውን በመቆጣጠር ቀሪ ተልዕኮዎቹን በመፈፀም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጎንደር ከተማ 40 ኪ.ሜ ርቀት የተወሰደ ስኬታማ ኦፕሬሽን ነው።የንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር አሃድም ተሳታፊ ነው። 🔸 ፬ኛ የዳ/ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የመብረቅና የሻለቃ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ከፋኖ ጋር ጦርነቱ ይቀጥላል ( ጄኔራሉ )……. ;አደጋው የከፋ ይሆናል (አቡነ ማትያስ)


Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ላይ ያለው የዋጋ ንረት ለሴቶች ፈተና ሆኗል።

በሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ላይ ያለው የዋጋ ንረት ለሴቶች ፈተና ሆኗል። የአንድ ሞዴስ ዋጋ ከ50 እስከ 60 ብር ፤ አንዳንድ ቦታዎች እስከ 70 ብር ድረስ እየተሸጠ ስለመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሱት መልዕክቶች ያሳያሉ። ከመጡ መልዕክቶች አንዱ ” የንጽህና መጠበቂያ ለሴቶች መሰረታዊ ነገር ነው ነገር ግን በዋጋ ውድነት ምክንያት ለመግዛት ከፍተኛ ችግር እያየን ነው። መቼ ይሁን ይሄ ችግር የሚፈታው ? በተደጋጋሚ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር ግን ምንም መፍትሄ አልተገኘም ” ይላል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን ይላል ? የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ዋጋው በየጊዜው እየተወደደ መጥቷል። ለዚህ ተብሎ የሚመደብ በጀት ባለመኖሩም አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ እንቅፋት እንደሆነ ተገልጿል። በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ጽርሰት ባለሙያ የሆኑት ወይዘሪት ማኅሌት አማረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት በየጊዜው የዋጋ ንረቱ እየጨመረ ያለው በግብአት አቅርቦት ችግር ነው ሲሉ ተናግረዋል። ለዚህም ከውጪ ሀገር ከሚመጡ ግብአቶች ላይ የነበረውን ቀረጥ ከ30 ወደ 10 ዝቅ ቢደረግም ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን አስረድተዋል። ” አሁን ባለው የገበያ ዋጋ አንድ ሞዴስ ከ50 እስከ 60 ብር ነው ” ያሉት ባለሙያዋ በዚህም ሴቶች ለወር አበባ ብለው የሚያስቀምጡት ገንዘብ ባለመኖሩ ለችግር እንደሚጋለጡ አንስተዋል። አክለውም ” የንፅህና መጠበቂያዎች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ቢሆንም እንኳ በተለይም ጥሬ እቃው ከውጪ የሚመጣ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ከታክስ ነፃ ሆኖ እንዲገቡ ለማስቻል ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር የማመቻቸት ሥራዎች እየተሰሩ ነው ” ብለዋል። ” የንፅህና መጠበቂያዎች እንደ አንድ የህክምና ቁሳቁስ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

የአዲስ አበባው ታላቅ ‘የማፊያ ስራ’!

(መሠረት ሚድያ)- አራት ኪሎ የሚገኘው ‘አምባሳደር ህንፃ’ ላይ ይገኝ የነበረው የድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ሲገባ በመጀመርያ ቀልብን የሚስበው በብዙ የመንግስት ቢሮዎች ውስጥ እንደሚደረገው በትልቁ ታትሞ እና በፍሬም ተዘጋጅቶ የተሰቀለው የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ፎቶ ነው። ድርጅቱ ቢሮው ብቻ ሳይሆን ማስታወቂያውም ቀልቢ ሳቢ ነበር። “ልጄ ውጭ ሀገር ሄዳ ነው ትምህርቷን መከታተል የምትፈልገው፣ አገሯን የምታስጠራ ምሁር እንድትሆንልኝ እፈልጋለሁ” ትላለች ዝነኛዋ የማስታወቂያ ባለሙያ ሙሉአለም ታደሰ ከሌላኛዋ ታዋቂ የሚድያ ሰው ዳናይት መክብብ ጋር በመሆን በጋራ የሰሩት የዚህ ድርጅት ማስታወቂያ። ይህ ዛሬ የምናቀርብላችሁ የከባድ ማጭበርበር ድርጊት ዋና ተዋናይ ቀላል ሰውም አይደለችም። ከጥቂት አመታት በፊት በአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ላይ ከ ‘ተስፋ ሰጪ’ ‘እና ‘ስራ ፈጣሪ’ አምስት የሀገራችን ግለሰቦች አንዷ ሆና ቀርባለች፣ በተጨማሪም ከሴቶች እና ህፃናት ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጌጎ ተስፋዬ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላታል። ግለሰቧ ቤተልሄም ታደሰ ይማም ትባላለች፣ ታድያ ተሸላሚ ያረጋት ስራዋ ምን ይሆን? ድርጅቷ ከ120 ሚልዮን በላይ ብርስ ከህዝብ እንዴት ማጭበርበር ቻለ? ቤተልሄም ታደሰ ይማም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለስራ ወይም ለትምህርት ወደ ውጪ ሀገር ሰው እንልካለን በማለት ገንዘብ የሚሰበስቡ ድርጅቶች መብዛታቸውን ብዙ ሰው ታዝቧል፣ ከነዚህም አንዱ Aim Ultra Consultancy የተባለው ድርጅት ነው። “እኔ Aim Ultra ን ለደቂቃ እንኳን አልተጠራጠርኩም። ማስታወቂያውን ታዋቂ ሰዎች በቲቪ እና በሶሻል ሚድያ ሲሰሩ ስላየሁ እውነት ይሆናል ብዬ ከቤተሰብ ያገኘሁት ገንዘብ ላይ ከብድር እና ቁጠባ ተጨማሪ በመበደር 520,000 ብር ከፈልኩ”
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

አንዳንድ ምግባረ ብልሹ የፀጥታ አካላት በመዲናዋ ነዋሪዎች ላይ በግልፅ ዝርፊያ መፈፀም እንደጀመሩ ታወቀ

አንዳንድ ምግባረ ብልሹ የፀጥታ አካላት በመዲናዋ ነዋሪዎች ላይ በግልፅ ዝርፊያ መፈፀም እንደጀመሩ ታወቀ (መሠረት ሚድያ)- የፀጥታ አካላት በአቅራቢያችን ሲገኙ ደህንነት ይሰማናል፣ ከሌላው ግዜ በተለየ ህግ አስከባሪ እንዳለ ተሰምቶን ሰላም ይታየናል። ይህ የተለመደ ስሜት ግን በቅርብ ግዜያት በተለይ በመዲናዋ አዲስ አበባ እየጠፋ ይገኛል፣ ለዚህ ደግሞ እየበዙ የመጡት ምግባረ ብልሹ የፀጥታ አካላት ናቸው። https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/0be?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በኢትዮጵያ የነብስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ መምጣቱንና በአንጻሩ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱ ተገለጠ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ ከ2001 እስከ 2023 የኢትዮጵያ ጠቅላላ አገራዊ ምርትና ምርቱ ለዜጎች የሚያስገኘው የነብስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ እንደሄደ በጥናት ማረጋገጡን መግለጡን ሸገር ዘግቧል። ማኅበሩ በተለይ ከአውሮፓዊያኑ ከአውሮፓዊያኑ 2016 ጀምሮ የነብስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ መምጣቱንና በአንጻሩ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱንና እንደገለጠ ዘገባው ጠቅሷል። የማዳበሪያ አጠቃቀም ከዓለማቀፍ መስፈርት አንጻር ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የግብርናው ዘርፍ ያገኘው ብድር 7 ነጥብ 8 ከመቶ ብቻ መኾኑንም ተቋሙ ገልጧል ተብሏል። የጥሬ እቃ እጥረት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውሃ አቅርቦት እጥረትም ለአምራቹ ዘርፍ ፈተና እንደኾነ ተገልጧል። ግጭቶችም ኦኮኖሚው እንዲቀዛቀዝና ኢንቨስትመንት እንዲዳከም ምክንያት ሆነዋል ተብሏል።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች፤ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች በትላንትናው ዕለት የጀመሩትን የስራ ማቆም ዛሬም በመቀጠላቸው በከተማይቱ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ተዘግተው ዋሉ። ዳኞቹ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስኪፈቱ ድረስ የስራ ማቆማቸውን እንደሚቀጥሉ የትግራይ ዳኞች ማህበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል። በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች ስራቸውን ለማቆማቸው በዋነኛነት የጠቀሱት ምክንያት “የደህንነት ችግር አለብን” የሚል ነው። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫም፤ በመቐለ ሰባት ክፍለ ከተሞች ባሉ ፍርድ ቤቶች እና በከተማይቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰሩ ዳኞች “በደህንነት ስጋት” ምክንያት ስራ እንዳቆሙ ማሳወቃቸውን አረጋግጧል። የትግራይ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ሃይለስላሴ፤ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው አምስት ጥያቄዎች ከዳኞች ደህንነት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የዳኞቹ የመጀመሪያ ጥያቄ በችሎት የሚመደቡ የጸጥታ አስከባሪዎችን የሚመለከት ነው። 🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15997/
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የአቢይ አገዛዝ ይበቃዋል” ምዕራባውያን………. አፋብኃ ጄኔራል ተፈራን እና ከሰምን ለምን ዘነጋቸው?

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አጥብቀን ስንጠይቅ ‘ይህ እኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግላቸው የሚከታተሉት ፕሮጀክት ነው’ የሚል ማስፈራርያ አዘል ማሳሰቢያ ይሰጠናል

ከኢግል ሂልስ ‘ላጋር ዋን’ ሳይት ቤት የገዙ ደንበኞች ገጠመን ያሉት አነጋጋሪ ክስተት – “ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ቅድሚያ የከፈልነው ገንዘብ እና ቤቱ ራሱ እንደሚወሰድብን ማስጠንቀቂያ ደርሶናል” – “አጥብቀን ስንጠይቅ ‘ይህ እኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግላቸው የሚከታተሉት ፕሮጀክት ነው’ የሚል ማስፈራርያ አዘል ማሳሰቢያ ይሰጠናል” https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/fda?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ፋኖ የአማራ ሕዝብን ያድናል፣ያሸንፋልም” አመራሩ ……… የህወሓት ጥሪና ማስጠንቀቂያ

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ከመረብ ወንዝ አቅራቢያ የተሰማው አዲስ መረጃ!”ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥና አጃቢዎች ተደመሰሱ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ጥያቄ እየጠየቀ ያለን ባለሙያ ለማሸማቀቅ በሚመስል መልኩ እንደማስፈራሪያ መጠቀሙ ከአንድ ትልቅ ኃላፊነት ካለበት ተቋም አይጠበቅም

” ጥያቄ እየጠየቀ ያለን ባለሙያ ለማሸማቀቅ በሚመስል መልኩ እንደማስፈራሪያ መጠቀሙ ከአንድ ትልቅ ኃላፊነት ካለበት ተቋም አይጠበቅም ” – የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ከሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ እና እያካሄዱ ካሉት ከፊል የሥራ ማቆም ጋር በተያያዘ 78 የሚሆኑ ባለሙያዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ባለሙያዎቹና የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣ ” ቀደሞ ከተፈቱት ውጪ አሁን በእስር ላይ የሚገኙት 78 ጤና ባለሙያዎች ናቸው ” ብለዋል። ” ይሄ ማለት እስከ ትላንት የደረሰን ዳታ ነው፤ የዛሬውን አልጨመርንበትም። የተፈቱትን ሳይጨሞር እንቅስቃሴው ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ ታስረው በእስር የሚገኙ ናቸው ” ብለዋል። ዳታው በምን መልኩ ተሰበሰበ ? ትክክለኛነቱን በምን አረጋገጣችሁ ? ለሚለው ጥያቄ ” ዳታው ትክክለኛ ዳታ ነው። ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ አብረዋቸው ከሚሰሩ የሆስፒታል ባለሙያዎች የተበሰቡ፣ ያሉበት እስር ቤት ጭምር የምናውቃቸው ናቸው ” ብለዋል። የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር በበኩሉ ፥ በእስር ላይ ይገኛሉ የተባሉት 78 ባለሙያዎች ዝርዝር እንደደረሰው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። ” የታሰሩ ባለሙያዎች ዳታ በውስጥ ከመረጃ መሰብሰቢያ ቋት የደረሰን መረጃ ነው ” ብሏል። ” እስራቱና ድብደባው ቆሞ መንግስት ነገሩን ቆም ብሎ በማሰብ ጥያቄ እየነሳው ካለው ባለሙያው ጋር እልህ በመጋባት ታች ያለው ህብረተሰብ እንዳይጎዳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ” ሲልም አሳስቧል። ማኅበሩ የትላንቱን የጤና ሚኒስቴር መግለጫ በተመለከተ በሰጠው አስተያየት ፥ ” ጤና ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ከእውነታው የራቀና ትክክለኛ ጥያቄ እያቀረቡ ያሉ ጤና ባለሙያዎችን ‘በሃሰተኛ መረጃ የተወናበዱ’፣ ‘ምንም
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

የጎጃሙ ጥቃትና የፈረስ ቤት ድል ወልዲያ ላይ በፋኖ ስም የተሴረው..

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አስቸኳይ የብልጽግና ስብሰባ! ….. በንቅናቄው መንግሥት ሊፈርስ ነው! … በልዩ ኦፕሬሽን ሰብረን ወጥተናል! ….ከባድ ውጊያ ቀጥሏል!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁነን ! ( የሕክምና ባለሙያ )

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

የመጨረሻው ደውል ላይ ነን የሀኪሞች ጥያቄ የመቶ ሚሊዮኖች ጥያቄ ነው!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የመጨረሻው ደውል ላይ ነን የሀኪሞች ጥያቄ የመቶ ሚሊዮኖች ጥያቄ ነው!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ

ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትላንት ማክሰኞ ግንቦት 5፤ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የምስረታውን የወርቅ ኢዮቤልዮ ባለፈው የካቲት ወር ያከበረው ህወሓት ከፓርቲነት የተሰረዘው፤ ቦርዱ ያዘዘውን “የእርምት እርምጃ” ተግባራዊ ባለማድረጉ መሆኑን ገልጿል። ምርጫ ቦርድ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፤ ባለፈው የካቲት ወር መጀመሪያ ለፓርቲው የሰጠው ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ቦርዱ ይህንን ቀነ ገደብ ባሳወቀበት መግለጫው፤ ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል “የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን” በሶስት ወራት ውስጥ እንዲያካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ቦርዱ ህወሓትን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ ያዘዘው፤ “በአመጽ እና በህገ- ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ” የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንደሚዘገቡ የሚያስችለው አዋጅ  (https://ethiopiainsider.com/2024/13159/)በሚያስቀምጠው ድንጋጌ መሰረት ነው። ይህ አዋጅ “በልዩ ሁኔታ” የሚመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያካሄዱ በምርጫ ቦርድ ሊታዘዙ እንደሚችሉ ይደነግጋል። ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ በነሐሴ 2016 ዓ.ም ለህወሓት የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠው ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲው “የቦርዱ ታዛቢዎች” በተገኙበት በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር። ቦርዱ የቅደመ ጉባኤውን የዝግጅት ስራዎች ለመከታተል እንዲረዳው፤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማካሄዱ 21 ቀናት በፊት ለመስሪያ ቤቱ እንዲያስታውቅም ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። 🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15908/
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የሚኒስትሮቹ ኑሮና ደመወዝ፤ ጀኔራሎቹን ያሰሩ ወታደሮች

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የመምህራን ደሞዝ ታገደ! አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በጎንደር የብልጽግና ሰዎች ተጫረሱ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በኢትዮ-ሱዳን ኮሪደር ተዘጋጅተናል ፋኖ

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የጤና ባለሙያዎች አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል።

የጤና ባለሙያዎችን የሥራ ማቆም አድማ ተከትሎ፣ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ባንዳንድ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ጸጥታ ኃይሎች መሠማራታቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሠምታለች። በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ የሙከጡሪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች፣ የክልሉ ፖሊስና ሚሊሺያ ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ መግባታቸውን ምንጮች አስረድተዋል። በፍቼ አጠቃላይ ሆስፒታልም፣ የጸጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴ መኖሩን ዋዜማ ተረድታለች። ምዕራብ ጉጂ ዞን ሃምበላ ወረዳ የአምስት ጤና ጣቢያዎች የጤና ባለሙያዎች፣ በጸጥታ ኃይሎች ጫና አድማ ማድረግ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ባንዳንድ ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች አድማ እንዳያደርጉ፣ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ማስፈራሪያ ሲፈጽሙ እንደነበርም ተነግሯል። የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን ጨምሮ በተለያዩ ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቋል። የጎንደርና ጎባ ሆስፒታሎች አስተዳደሮች፣ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሥራቸው ባስቸኳይ ካልተመለሱ ርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል። ማኅበሩ፣ በአድማው ወቅት የድንገተኛ፣ የጽኑ ሕሙማን፣ የጨቅላ ሕጻናትና የማዋለጃ ክፍሎች ብቻ አገልግሎት እንደሚሠጡ ገልጧል። የጤና ባለሙያዎች እየታሠሩና ዛቻ እየደረሰባቸው እንደሚገኙ የገለጠው ማኅበሩ፣ በእስር ላይ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ባስቸኳይና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል። የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ በቀጣዩ ዓመት ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ በጀት ለመመደብ ዝግጅቶች እየተደረጉ መኾኑን ትናንት ምሽት ለብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረው ነበር። በተያያዘ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ መንግሥት የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዮናታን ዳኘውንና ከሥራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ የታሠሩ ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን ከእስር እንዲፈታ ጠይቋል። አምነስቲ፣ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ ነጻነትን እንዲያከበርና የጤና
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል

በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል – ስልክ እና ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ይዘው እንዳይመጡ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል “በየትኛውም ሴክተር የሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ ተምሮ እንዳልተማረ በመሃይም ካድሬዎችና የቢሮ ኃላፊዎች መብቱ እየተረገጠ፤ እንዳይረጋጋ በመንግስት የታቀደ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየደረሰበት ይገኛል። የሰሞኑ የጤና ባለሙያዎችም ጥያቄ የሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ጥያቄ ነው፤ ከእንግዲህ መሃይም ሹመኞች እራት እንዲበሉ ሻማ ይዘን የምንቆምበት ወቅት አልፏል”- መምህራን https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/73e?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደኤታው ለቀቁ! የሐኪሞች ዐድማ ቀጠለ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የጠላትን አስከሬን በሲኖትራክ ሙሉ ያስጫነ ጀግና ……….. አርበኛ አሸናፊ (ቆጥረህ ጫን) ጋር የተደረገ ቆይታ

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች “በዘረፋ እና በሰዎች ንግድ ላይ ተሳትፈዋል

አቶ ጌታቸው ረዳ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች “በዘረፋ እና በሰዎች ንግድ ላይ ተሳትፈዋል” ሲሉ ወነጀሉ የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች “በወርቅ ቁፋሮ እና ንግድ”፣ “የመንግስት ገንዘብ በመዝረፍ” እንዲሁም ”በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፈዋል” ሲሉ ወነጀሉ። አቶ ጌታቸው ረዳ ከፋና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በስም ጠቅሰው የወነጀሏቸው ሶስቱ አመራሮች፤ ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ፣ ብርጋዴር ጀነራል ሃይለስላሴ ግርማይ እና ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ ናቸው። ትላንት ሰኞ ግንቦት 4፤ 2017 ምሽት በፋና ቴሌቪዥን የተላለፈው የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ክፍል አንድ ቃለ መጠይቅ፤ ስለ እርሳቸው የፖለቲካ ተሳትፎ አጀማመር፣ በትግራይ ክልል ስለ ተካሄደው ጦርነት፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች እና የትግራይ ሰራዊት አዛዦች “ፈጽመዋቸዋል” ስላሏቸው ወንጀሎች የዘረዘሩበት ነበር። አቶ ጌታቸው ተፈጽመዋል ካሏቸው ወንጀሎች ቅድሚያውን የሰጡት ለወርቅ ንግድ ነው። በትግራይ ክልል በህገወጥ መንገድ የሚካሄደው የወርቅ ንግድ የተጀመረው፤ ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነትን ከተፈራረሙ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. በኋላ የሚመስለው በርካታ ሰው እንዳለ አቶ ጌታቸው በቃለ መጠይቃቸው ላይ አንስተዋል። ሆኖም በክልሉ ህገወጥ የወርቅ ቁፋሮም ሆነ ንግድ የተጀመረው፤ የትግራይ ጦርነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ጭምር እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ይፋ አድርገዋል። 🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15872/
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ጄኔራሎቹ ተዘጋጅተናል፣ጦርነቱ ፍትሃዊ ነው ሲሉ አፋብኃ በበኩሉ ሰራዊቱ በውጊያና የደፈጣ ጥቃት አለቀ ብሏል

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አቶ ጌታቸው እነ ጀነራል ምግበ በወርቅ ንግድ ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ በስም ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል።

” እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል ” – አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ያለው ህገወጥ የወርቅ ንግድ  ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ የጀመረ ሳይሆን በጦርነቱ ጊዜም ሳይቀር ሲሰራ የነበረ እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ። አቶ ጌታቸው፤ “ብዙ ሰው የወርቅ ንግድ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረምን በኃላ የጀመር ይመስለዋል” ያሉ ሲሆን ግን ጦርነቱም እየተካሄደ ንግዱ ነበር ብለዋል። “እኔ የማምንበትን ትግል ነው ያካሄድኩት ብዬ አምናለሁ በዛ በማምንበት ትግል ውስጥ የትግራይን ህዝብ አጀንዳ ይዘው የታገሉ ብዙ የጦር መኮንኖች አሉ ለሰሩት ስራ ያለኝ ክብር በፍጹም አይቀንስም ግን ደግሞ ገና ገና ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይበላ በነበረበት ወቅት ሳይቀር ምሽግ ለመቆፈር ብለን የወሰድነው ኤክስካቫተር ወርቅ ለመልቀም ይጠቀሙበት የነበሩ አዛዦችም ነበሩ” ሲሉ አጋልጠዋል። “ሲዋሹ በጣም ነው የሚገርመኝ” ያሉት አቶ ጌታቸው “እኔ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል እስካሁን የታገስኩትም ይበቃኛል” ብለዋል። አቶ ጌታቸው “የኤርትራን ሰራዊት እናፍርሰው” በሚል አላማ ዘመቻ የጀመረና ዘመቻውን የሚመራው አመራር ሰዎችን እያፈነ ገንዘብ ሲበስብ እንደነበር ተናግረዋል። “ሰው ሲሸጡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፤ ኤርትራዊ መሸጥ ‘ ንብረት ‘ ነው የሚባለው ወርዷል ወይ ? ይባላል፤ ታፍንና ይዘህ 27 ወጣት አንድ ቤት ትዘጋና ቤተሰቦች አላቸው ውጭ ሀገር የሚባሉት ሰዎች አካውንት እየተጠየቀ እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 4000 ዶላር እንዲያስገባ ተደርጎ (20 ሰው ካፈንክ 80 ሺህ ዶላር ታስገባለህ) በዚህ የውጭ አካውንት ከፍተው በሺዎች የሚቆጠሩ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃኪሞች የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃኪሞች የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል። በአዲስ አበባ በሆስፒታሎች ዙሪያ መረጃ ቲቪ ባደረገው አሰሳ ዛሬ ክፍት የሆኑት የህክምና ክፍሎች ፤ ድንገተኛ ክፍል፣ ፅኑ ህሙማን ክፍል፣ የጨቅላ ህፃናት ክፍል፣ የማዋለጃ ክፍል ብቻ ናቸዉ። ሌሎች የሕክምና ክፍሎች አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ተረጋግጧል። የአብይ አገዛዝ ለሃኪሞች ጥያቄ መልስ ሰጥቶ እና የታሰሩትን ሃኪሞች ከፈታ አድማው ሊቆም ይችላል ተብሏል። አድማውን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲቀላቀሉት ጥሪ እየተደረገ ይገኛል። ሲል በሆስፒታሎቹ የተዘዋወረው የመረጃ ቲቪ ሪፖርተር አስታውቋል። የአድማው አስተባባሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት የመንግስት ሚዲያዎች እንደተለመደው አንዳንድ አስገድደው ወደሚያሰሯቸው ተቋማት በመሄድ ምንም የስራ ማቆም እንደሌለ እና እንደወትሮው አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ሊዘግቡ እና ፕሮፖጋንዳ ሊሰሩ ይችላሉ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት ምንም ግራ መጋባት እንዳይኖር። ዛሬ በተለያዩ ምክንያቶች ማቆም ያልቻላቹ ከከሰዓት ወይም ከነገ ጠዋት ጀምሮ አድማውን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።በ ER, ICU, LW እየሰራቹ ያላቹ ጤና ባለሞያዎች Cold Case እንድታዩ ለማስገደድ ከሞከሩ ወይም የታጠቀ ሀይል የስራ ቦታቹ ካለ እንዲሄዱላቹ አሳውቁ ካልሆነ ጥላቹ ወደ ቤታችሁ ሂዱ። በወታደር ተገዶ የሚሰራ ህክምና የለም። ብለዋል ። የአድማው አስተባባሪዎች አክለውም በዛሬው ቀን የሚጠራ ማንኛውም ስብሰባ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን በስብሰባው ባለመሳተፍ የራሳችሁን ግዴታ እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን ፤ Stay Home , Stay Safe ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። #MerejaTv
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አምነስቲ ኢንተናሽናል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ

አምነስቲ ኢንተናሽናል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ (መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናታን ዳኘው ከእስር እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ማምሻውን ጠየቀ። https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/3e4?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ

ዶ/ር በርናባስ ሳሙኤል፣ ዮናታን ዳኛው፣ ዶ/ር ሀብታሙ ጌታቸው እና ዶ/ር መላኩ አልማው የፎቶው ባለመብት, sm የምስሉ መግለጫ, ዶ/ር በርናባስ ሳሙኤል፣ ዮናታን ዳኛው፣ ዶ/ር ሀብታሙ ጌታቸው እና ዶ/ር መላኩ አልማው   የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው እንዲሁም ሦስት የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተሮች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በአማራ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በቀናት ልዩነት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር አምስት ደርሷል። በአዲስ አበባ ከተማ ሌሎች አምስት የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከሁለት ቀን እስር በኋላ ተለቅቀዋል። የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ ድጋፉን የገለጸው የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዮናታን የታሰሩት ትናንት እሁድ ግንቦት 3/2017 ዓ.ም. እንደሆነ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መለስ ባታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በ2015 ዓ.ም. የተመሠረተውን ማኅበር የሚመሩት አቶ ዮናታን፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን በሚገኘው ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ መሆናቸውን አቶ መለሰ ገልጸዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደሚናገሩት አቶ ዮናታን እሁድ ከሰዓት የተያዙት ከመኖሪያ ቤታቸው ነው። “ከመያዙ በፊት ከትናንት ወዲያ [ቅዳሜ] የሚሠራበት ሆስፒታል አካባቢ እና በሚኖርበት ሰፈር [በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ] ለምርመራ እንደሚፈለግ ደውለው እንዳስታወቁት ነግሮኝ ነበር” የሚሉት አቶ መለስ፤ ይህ ከሆነ ከአንድ ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። ከማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጋር አጭር የስልክ ንግግር ማድረጋቸውን የሚጠቅሱት አቶ መለስ፤ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝ እና “ብዙ ችግር እንዳልደረሰበበት” ከራሱ መስማታቸውን ገልጸዋል። ይሁንና የስልክ ጥሪው በመቋረጡ ምክንያት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የታሰሩበትን ምክንያትም ሆነ ስለተደረገባቸው ምርመራ በዝርዝር መነጋገር እንዳልቻሉ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 47 ቢሊዮን ብር ከሰርኩ አለ

ዘንድሮ 47 ቢሊዮን ብር የከሰረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ትርፋማነት እንደሚሸጋገር የኩባንያው ኃላፊዎች ገለጹ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ኪሳራ ቢያጋጥመውም፤ በሁለት ዓመታት ውስጥ ወደ ትርፋማነት ይሸጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የእናት ኩባንያው ኃላፊዎች ተናገሩ። መቀመጫውን በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ያደረገው ሳፋሪኮም ኩባንያ፤ እስከ መጋቢት ወር ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካገኘው 3 ቢሊዮን ዶላር የአገልግሎት ገቢ 10 በመቶ ገደማ የሚሆነው የኢትዮጵያ ገበያ ድርሻ እንደሆነ አስታውቋል። ኩባንያው የሚመራበት በጀት ዓመት መጠናቀቁን በማስመልከት ባለፈው ሐሙስ ይፋ የተደረገ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ባለፈው ዓመት 2.7 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን ዘንድሮ 7.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ270 ፐርሰንት እድገት ቢያሳይም፤ 47 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኪሳራ እንደገጠመው ዋና ስራ አስፈጻሚው ዊም ቫንሔለንፑት ገልጸዋል። “ይህ ኪሳራ በአብዛኛው ኩባንያው በሚገኝበት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ ከምንጠብቀው ጋር የተስማማ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በሐምሌ 2016 ዓ.ም. ተግባራዊ ያደረገው የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት ለውጥ በኩባንያው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ጠቁመዋል። የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት ለውጡ፤ በአጭር እና መካከለኛ ጊዜ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመቋቋም “እርምጃዎች መወሰዳቸውን” የሳፋሪኮም ኃላፊዎች አብራርተዋል። እርምጃው በውጭ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተቀጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን መቀነስን የካተተ ነው። 🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15849/
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በኢትዮጵያ ኢመደበኛ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ በጥናት ተመላከተ

በኢትዮጵያ  ኢመደበኛ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑ፣ መልካም አስተዳደር ለአፍሪካ ቀንድ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተነገረ፡፡ ‹‹የከተሞች መደበኛ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ገጽታዎችና የአስተዳደር ቅኝት›› በሚል መሪቃል በተዘጋጀው መድረክ፣ ‹‹የከተሞች መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ገጽታና ባህሪያት በኢትዮጵያ›› በሚል ሐሳብ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት መካነ ጥናት ኮሌጅ አባል ቻላቸው ጌታሁን (ዶ/ር)፣ ‹‹58 በመቶ የዓለማችንን የሥራ ዕድል የሚፈጥረው መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ነው፤›› ብለዋል። ለታዳጊ አገሮች 84 በመቶው የሥራ ዕድል የሚፈጠረው ከዚሁ ዘርፍ እንደሆነ በማስረዳት፣ ሴቶችና ሕፃናት ደግሞ መደበኛ ባለሆነ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው ገልጸው፣ ያገቡ ወይም አግብተው የፈቱ ሰዎች ደግሞ በዚህ ዘርፍ በአብዛኛው ሲሳተፉ ይስተዋላል ብለዋል። በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ከገጠር ወደ ከተማ ለሚፈልሰው የሰው ኃይል የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉም አክለዋል። የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ አጠቃላይ ገቢ አንድ ሦስተኛና ከዚያ በላይ የሚሆነው የሚመነጨው ከዚሁ ዘርፍ መሆኑንም አመላክተዋል። እ.ኤ.አ ከ1992 እስከ 2000 ድረስ ያሉ የጥናት ውጤቶች በአማካይ የሚያመላክቱት ይኼን ነው ብለዋል። ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮጵያ እያደገ መምጣቱ በጥናቱ ተጠቁሟል። በከፍተኛ ደረጃ የሚታየውን የከተማ ሕዝብ ቁጥር ዕድገትና የሥራ ዕድል መንግሥት መር የሆነው ኢኮኖሚ መሸከም እንዳልቻለም፣ በዚህም ዜጎች በቀጥታ ወደ መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ዘርፍ እንደሚገቡ ገልጸዋል ‹‹የከተሞች መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ አስተዳደር በኢትዮጵያ›› በሚል ሐሳብ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናት ማዕከል
Posted in News, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የነበሩ ባለሀብቶች ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ እያቀረቡ ነው ተባለ

በዘጠኝ ወራት ከ37 ሺሕ በላይ ሠራተኞች መልቀቃቸው ተነግሯል በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩ ጦርነት ሸሽተው የወጡ ባለሀብቶች፣ ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ  እያቀረቡ መሆናቸውን፣ የኢንዱስትሪ ፖርኮች  ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ ይህንን የገለጸው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ ሲያቀርብ ነው፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከአገር ሸሽተው የሄዱ ባለሀብቶችን ለረዥም ጊዜያት በኢንተርኔትና በአካል በመገናኘት ኩባንያዎቻቸው ተመልሰው ወደ ልማት እንዲገቡ ጥረቶች ቢደረጉም ፍላጎት አለማሳየታቸውን፣ በኢንዱስትሪ ፖርኮች  ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ኩባንያዎቹ  ወደ ሌላ አገር ሄደው ለማልማት ማሽናቸውን ከአገር ይዘው ለመውጣት ጥያቄ በማቅረባቸው፣ እኛ እንደ መፍትሔ እያቀረብንላቸው ያለው አገር ውስጥ የገባና በአጠቃላይ አገራዊ ምርት የተመዘገቡ ማሽኖችን ወደ ሌላ አገር ከሚወስዱ፣ በአገር ውስጥ ወደ ሌላ አካባቢ  በማዘዋወር ለማሠራት ጥያቄ አቅርበን እየጠበቅን፤›› ነው ብለዋል። ነገር ግን ወ/ሮ ሶስና ጌታሁን የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል፣ መቀሌ የነበሩ ኢንቨስተሮች እዚያው መቆየት ካልፈለጉ ቦሌ ለሚ ወይም አዳማ እንዲያለሙ ለማድረግ እየተሠራ ነው የሚለው ምላሽ ትክክል አለመሆኑን፣ ኢንቨስተሮች በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምን እንደጎደላቸው መጠየቅና ችግሩን መፍታት እንጂ ከአንድ አካባቢ አስነስቶ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ መሞከር ትክክል አይደለም ብለዋል። አክለውም ያልተመቹ ጉዳዮች ካሉ ኢንቨስተሮቹ ተጠይቀው መፍትሔ በማፈላለግ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እዚያው ማቆየት እንጂ፣ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ማዘዋወር አግባብ አይደለም በማለት አሳስበዋል፡፡ ይህ በዚህ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ለትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች አዲስ ቀለም እና ኮድ ለሹፌሮቹም ዩኒፎርም ሊዘጋጅ ነው

መንግሥት፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደየአገልግሎታቸው ዓይነት “ወጥ ቀለም” እና መለያ ኮድ እንዲኖራቸው እቅድ መያዙን ዋዜማ ሠምታለች። የተሽከርካሪዎች ቀለምና መለያ ኮድ ከከተማ ከተማ የተለያየ ይሆናል ተብሏል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችም፣ ወጥ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ ዋዜማ ተረድታለች። የትራንስፖርት ሚንስትር ዓለሙ ስሜ፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ ለማድረግ እንደተወሰነ ሰሞኑን ባንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸውንም ዋዜማ ተረድታለች።
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በኢትዮጵያ የንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል?

ኢትዮጵያውያን በቤት እና በመሬት ግብር የሚከፍሉበት የንብረት ታክስ በተቃዋሚዎች ትችት ቢገጥመውም ጸድቋል። ተቃዋሚዎች አዲሱ ታክስ በሸማቾች ላይ ጫና እንደሚፈጥር አስጠንቅቀዋል። መንግሥት “ፍትኃዊ የሀብት ክፍፍል የሚያሰፍን” ያለው የንብረት ታክስ በክልሎች ይሰበሰባል። ለመሆኑ በንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል? የማይከፍሉትስ እነ ማን ናቸው?
Posted in ኤኮኖሚ