የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ ከ2001 እስከ 2023 የኢትዮጵያ ጠቅላላ አገራዊ ምርትና ምርቱ ለዜጎች የሚያስገኘው የነብስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ እንደሄደ በጥናት ማረጋገጡን መግለጡን ሸገር ዘግቧል። ማኅበሩ በተለይ ከአውሮፓዊያኑ ከአውሮፓዊያኑ 2016 ጀምሮ የነብስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ መምጣቱንና በአንጻሩ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱንና እንደገለጠ ዘገባው ጠቅሷል። የማዳበሪያ አጠቃቀም ከዓለማቀፍ መስፈርት አንጻር ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የግብርናው ዘርፍ ያገኘው ብድር 7 ነጥብ 8 ከመቶ ብቻ መኾኑንም ተቋሙ ገልጧል ተብሏል። የጥሬ እቃ እጥረት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የውሃ አቅርቦት እጥረትም ለአምራቹ ዘርፍ ፈተና እንደኾነ ተገልጧል። ግጭቶችም ኦኮኖሚው እንዲቀዛቀዝና ኢንቨስትመንት እንዲዳከም ምክንያት ሆነዋል ተብሏል።