Home › View all posts by Konjit Sitotaw
Blog Archives
ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ወታደራዊ አዛዥ እና የግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ አጠር ያለ መግለጫ!!
ይህን የአማራ ፋኖ ትግል የጀመርንበት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩንም ዋነኛ ምክንያታችን አማራ በመሆናችን ብቻ በወለጋ ፣ በነቀምት ፣በሻሸመኔ፣ በጉራፈርዳ ፣በመተከል እና በሌሎች አካባቢዎች በጃምላ ተጨፍጭፈናል በጅምላ ተገለናል ፣ በጅምላ ተፈናቅለናል በዚህም ምክንያት አማራ የመዳኛ መንገዱ ክንዱና ነፍጡ መሆኑን አዉቀን ዱር ቤቴ ካልን 3 እና 4 ዓመታትን አሳልፈናል። በዚህም ቆይታችን ዱላ ይዘን ወጥተን ከክላሽ እስከ እስከ ዲሽቃ ከዲሽቃ እስከ ሞርተር እና ሌሎች ካባድ መሳርያዎችን ታጥቀናል። ይህን ሁሉ መሳርያዎች ይዘን እየታገልን ባለንበት ወቅት በ አባታችን ብ/ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ስም ሲነግድ የነበርዉ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሃቤ በትላንትናዉ ዕለት ለዚህ ፋሽዝም ስርዓት እጅ ሰጠ የሚል ዜና ሰምተናል። ኮረኔል ፈንታሁን ለአገዛዙ እጅ ሰጠ አልሰጠ የአማራ ፋኖ ትግል አይቆምም ምክንያቱም ይህ ትግል ለግለሰቦች ስንል ሰላልወጣን። እኛ ግን የጀኔራል አሳምነዉ ልጆች የአባታችን የአደራ ቃል ተወጥተን የአማራን ትንሳኤ እናበስራለን።
አሁንም በዚህ ትግል እሚነግድ ካለ መንገዱ ክፍት ነዉ እንክርዳዶቹ ከስንዴዉ እንድትለዩልን እንፈልጋለን።
ይህን ትግል ስንጀምር ላንጨርስ አልጀመርነዉም አማራነት ያሸንፋል ድል ለፋኖ ድል ለአማራ!!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የግዙፉ ላስታ አሳምነው ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!
“በደብረ ማርቆስ ከተማ 670 መምህራን ታፈኑ”
206ኛ ኮር በመማማር ማስተማር ሒደቱ ከመምሕራን ጋር ለመዋያየት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስተው ወደ ስብሰባ ሲሔዱ የነበሩ 670 መምህራን እና ዕርሰ መምህራን በአገዛዙ ሰራዊት ታፍነዋል።
ከ25 በላይ መኪና በማዘጋጀት ከ206ኛ ኮር አመራሮች ጋር ለመወያየት ያቀኑት 670 መምህራን ከህዳር ወር ጀምሮ የሁለት ወር ደሞዝ በአምባገነኑ ስርዓት ተነጥቀዋል። ትግሉን በማጠልሸት ተጠምዶ የነበረው የምስራቅ ጎጃም ካድሬ ትናንት ጥር 03/2018 ዓ/ም ከጠዋት ጀምሮ ኬላ ዘርግቶ መምህራንን በማጎር የተጠመደ ሲሆን ከ74 በላይ መምህራን በከፍተኛ ድብደባ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተረጋግጧል።
“አንበሳ ምን ቢርበው ሳር አይግጥም!!”
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆነው ሻለቃ ሀብታሙ ደምሴ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ያስተላለፈው መልዕክት!!
የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋን ተከትሎ ለህዝባችን የደህንነት ዋስትና ለመሆን ዱር ቤቴ ብለን ጠብመንጃ አንስተን ወደ ጫካ እና በርሃ የገባነው ህዝብን የማዳን አላማን አንግበን መሆኑ ይታወቃል። በበኩላችን የምንሞትለትን አላማ ጠንቅቀን ስለምንረዳ ይህን አላማ ለማሳካት የሚያስችል ፅናት ተላብሰን ትግላችንን ቀጥለናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅርብ ወራጆች ደግሞ በየተራ ወደ ጠላት እየገቡ መሆናቸውን ታዝበናል።
ትግል ያለ አላማ እና ፅናት እንደማይሰምር ሁሉ፤ አላማ ቢስ የሆኑ ልፍስፍሶች ወደ ጠላት ሲገቡ ልንረዳው የሚገባ ነገር ቢኖር የትግሉ ሜዳ እየፀዳ መምጣቱን ነው። በትግሉ ሜዳ ላይ በፅናት መቆየት የሚችሉት አላማ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን ልንገነዘብ ይገባል። አላማ ከሌላቸው ብዙኃን ይልቅ አላማ ያላቸው ጥቂቶች ለድል ይበቃሉ። የአማራ ህዝብ አሁን ላይ እየሆነ ባለው ነገር ሳይደናገር እና ሳይደናገጥ በእኛ በልጆቹ ሙሉ እምነት እንድኖረው የምናሳስበው የፀና ህዝብ አሸናፊ እንደሚሆን ስለምናውቅ ጭምር ነው። የትግሉ ሂደት መሰናክል የበዛበት መሆኑን አምነን መሰናክሎችን ሁሉ በፅናት ለማለፍ ቆርጠን እንደ ህዝብ መነሳት ይገባናል። ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አማራዊ አንድነታችንን ማንበር ስንችል እና የጋራ መግባባት ላይ ስንደርስ ነው።
ባቡሩ ሲጓዝ በየፌርማታው የሚወርዱ ተሳፋሪዎች እንደሚኖሩ ተገማች ነው። ይህን ትግል እንደ ባቡር ቆጥረነው በየፌርማታው የሚወርደው ተሳፋሪ ጉዳይ ሊያሳስበን እንደማይገባ ለማስታወስ እንወዳለን::
በጣም የሚገርመው ነገር ቢኖር ወደ ጠላት የሚገቡ አካላት ለክዳታቸው
ከ10 ወራት በፊት የሀገሪቱ የህክምና ባለሙያዎች የመብትና የስራ ላይ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች አንስተው መንግስት ምላሽ እንዲሰጣቸው ሲሟገቱ ነበር።
አስከትለውም ግንቦት ወር ላይ ሀገር አቀፍ አድማ በማድረግ በመንግስት ላይ ግፊት ለማድረግ ሞክረዋል።
የህክምና ባለሙያዎቹ አንስተዋቸው ከነበሩት ጥያቄዎች ምን ያህሉ ምላሽ አገኙ? ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅተናል አንብቡት
https://cutt.ly/2tjCtTR7
በፌዴራል ደረጃ ከተመዘገቡት 470ሺ የንግድ አና አገልግሎት ሰጪ የግል ድርጅቶች ውስጥ 370ሺ ስራ አቁመዋል ….. አስደንጋጩን ሪፖርት እነሆ
https://miniliksalsawi.substack.com/p/ethiopia-out-of-470000-federally
… የድርጅቶች በዚህ ደረጃ መዘጋት የመንግስት ገቢን በመቀነሱ ምክንያትም በቀሩት ጥቂት ድርጅቶች ላይ የሚያሳድረው የግብር ጫና በሂደት ቀሪዎችንም ከገበያ ሊያሰወጣ የሚችል ክስተት መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚገባ ነው። ……..በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ኤክስፐርቶች ተጠንቶ የቀረበን ሪፖርት በመንተራስ ቅዳሜ የወጣው የእንግሊዘኛ ሪፖርተር ሳምንታዊ ጋዜጣ በፌደራል ደረጃ ተመዝግበው ከሚገኙና በተለያየ ሙያና ዘርፍ ከተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች መካከል 80% የሚሆኑት እንደተዘጉና በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ቁጥር ከ100 ሺህ እንደማይበልጡ ዘግቧል።…… ለረጅም ዓመታት ፈጣን እድገት በማሳያት 470 ሺህ ደረሰው ከነበሩት በፌደራል ደረጃ የተመዘገቡ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች መካከል 370 ሺዎቹ በ2025 መዘጋታቸውን በዘገባው ላይ አክሏል። ….. ሪፓርተር መሰረት ባደረገው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ኤክስፐርቶች ጥናት መሰረት በ2025 ከ370 ሺህ በላይ ድርጅቶች ከፌደራል መዝገብ ተሰርዘዋል ማለት ምን ያህል የስራ እድል፣ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የመንግስት ገቢዎችን እንደሚቀንስና ከአገልግሎት አሰጣጥና ከአቅርቦት አኳያም በምን ያህል ደረጃ የምርት አቅርቦትና ስርጭት ሚዛንን እንደሚያዛባ መረዳት ይቻላል። #MinilikSalsawi
https://miniliksalsawi.substack.com/p/ethiopia-out-of-470000-federally
::
ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ መምሪያ አሃድ ከሆኑት መካከል ለወራት የሰለጠኑ ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎች የዕዝ የኮርና የክፍለጦሩ አመራሮች በተገኙበትና መልክት ባስተላለፉበት ሁኔታ ተመርቀዋል::
ከፍተኛ የዕዙ አመራሮችም የተጀመረውን የፖለቲካ ትጥቅ ትግል ከግብ ለማድረስና የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብሎም ቀጣይነት ያለው ነፃነት ለመጎናፀፍና የሃገራችን ባለቤት ለመሆን በፅናትና ቁርጠኝነት መታገል ብቻኛ አማራጭ መሆኑን ለተመራቂዎች አስገንዝበዋል::
ልዩ ኮማንዶ ፋኖዎችን ያስመረቁት በልዩ ዘመቻ መምሪያው ስር የሆነው አሃድ ወታደራዊ አዛዥና ምክትል ወታደራዊ አዛዥ የሆኑት አርበኞችም ለተመራቂዎች መልክታቸውን አስተላልፈዋል::
የልዩ ዘመቻ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ዛሬ የተመረቃችሁ ምኒልክ ዕዝ የልዩ ዘመቻ እንደስማችሁ ልዩ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ለበርካታ ወራት ፀሀዩን:ብርዱን:ቁሩን በርካታ ውጣውረዱ ሳይበግራችሁ ባልተመቻቸ ሁኔታ ተቋቁማችሁ ለዚህች ልዩ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ የናንተ ስልጠና ለየት የሚያደርገው ያኔ በጣት በምንቆጠረበት ጊዜ ሳይሆን አሁን በሺዎች ብሎም በሚልዮኖች በትጥቅም ይሁን በሰው ኃይል አቅማችን እንዲሁም የማድረግ አቅማችን ትልቅ የስኬት ጫፍ ላይ ባለንበት ጊዜ መቀላቀላችሁ በተጨማሪም የዚህን አንባገነን ስርዓት ግፍ በደል እና ሰቆቃ አድራሽነት ማንም ሳይጎተጉታችሁ እያንዳንዳችሁ ቤት አንኳኩቶ የገባ በመሆኑ ያለማንም ቀስቃሽ በቃኝ አሻፈረኝ ብላችሁ ይህን ትልቅ የትጥቅ ትግል የተቀላቀላችሁ መሆኑ ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ለየት ያደርገዋል።
እንሰባሰባለን እንደራጃለን እንሰለጥናለን እንታጠቃለን ተዋግተን ይህን አንባገነን ፀረ_አማራ ስርዓት ከትክሻችን ላይ አሽቀንጥረን እንጥላለን።
የአማራ ተጋድሎ አካሄድ እና መስመር⚡️:-
👉 የተጋድሏችን
መነሻ:-የአማራ ህልውና አደጋ ነው።
መዳረሻው:- አደጋውን ቀልብሶ ህዝቡን ከባርነት አውጥቶ ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር የሃገሪቱን በትረ ስልጣን
ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የአደረጃጀት ማሻሻያ መጠናቀቅ በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ሕዝብ እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ረጅም እና ግርማዊ የትናንት ታሪክ ባለቤት መሆናችንን በሙሉ ባለቤትነት የምናምንበት ጉዳይ ነው። ለረጅም ዘመናት በፈተናዎች መካከል ሁሉ የረጋ ስርዓት መገንባትም ተችሎ ነበር። ሆኖም ከሺህ ለሚበልጡ ዓመታት በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የስልጣኔ ግጭት በወለደው የትውልዶች ጦርነት በዘመናዊው ታሪካችን በቀጥታ አማራን ጠላት በማድረግ ባደረገው ዘመቻ በውስጣዊ ድክመቶች ታግዞ የሀገረ መንግስት ግንባታውን በማቋረጡ ሀገራችንን ላልተረጋጋና ለሚለዋወጥ ስርዓት ህዝባችንንም ለከፋ የመጥፋት (ህልውና) አደጋ አጋልጦታል። ይህንን በራሳችን ወገኖች ኢትዮጵያዊያን ባለቤትነትና ቅጥረኝነት የሚመራ ውስብስብ ሀገራዊ እና ህዝባዊ አደጋ ለመረዳትና ለመግባባት ብሎም መፍትሔ ለማበጀት ብዙ ማገዶ ፈጅቷል።
የአማራ ሕዝብ ራሱን በመዘንጋትና ሀገሩን በማስቀደም እየኖረ በራሱም ሆነ በሀገሩ ላይ የተፈጠረውን ታላቅ ተቃርኖ በጊዜው ባለመረዳቱ ራሱን ያገኘው ሀገሩን ተነጥቆ ሀገር አልባ ሆኖ እንዲሁም መንግስት መር በሆነ የዘር ማጥፋት በከፋ የመጥፋት አደጋ ውስጥ ሆኖ ነው። በእርግጥ አማራው በመጥፋት ላይ ያለ ህዝብ ነው። ይህንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስ ብሎም ሁለንተናዊ ህዝባዊ ጥቅሞቹን ለማስከበርና የተቋረጠ የሀገር ግንባታውን ዘመኑን በሚመጥን መልኩ ለማደስ፣ የቀጠለና አዲስ ስልጣኔ ለመገንባት አዲስ አማራዊ አብዮት በማካሄድ ላይ እንገኛለን። የዚህ ህዝባዊ ቁጣ መነሻ ምክንያት የህልውና አደጋው ቢሆንም አደጋውን ከመቀልበስ ባሻገር ግዙፍ ራዕይ የቀነበበ ህዝባዊና ሀገራዊ እንዲሁም ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ መሻቶችን ቀርጿል።
የህልውና ትግሉ ባለፉት ከ30 በላይ ወራት ራሱን በማጠናከርና ጠላትን በማዳከም እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ
ኢሰመኮ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መያዝ ከሚችለው የተጠርጣሪዎች ቁጥር በላይ በመያዙ ከፍተኛ መጨናነቅ ተፈጥሯል አለ። ኢሰመኮ፣ ማረሚያ ቤቱ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ተጠርጣሪዎችን ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ለይቶ አለመያዙ “አሳሳቢ” እንደሆነ ገልጧል። በማረሚያ ቤቱ የተወሠኑ ዞኖች ለተጠርጣሪዎች በቂ የመንቀሳቀሻ ቦታ እንደሌለና ተጠርጣሪዎች እንዲይዙት የሚፈቀድላቸው ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን 200 ብር ብቻ መሆኑ አስፈላጊ ሸቀጦችን ለመግዛት በቂ እንዳልሆነ የጠቀሠው ኢሰመኮ፣ ማረሚያ ቤቱ ላንድ ተጠርጣሪ የእለት ቀለብ የመደበው 35 ብርም ምግብ ለማቅረብ በቂ አይደለም ብሏል። ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ የተጠርጣሪዎችን መጨናነቅ ለመቀነስ፣ ፍርድ የተሠጣቸው እስረኞች በአፋጣኝ ወደ ቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ ቀደም ሲል የተላለፈው ውሳኔ በፍጥነት ይተግበር በማለት አሳስበዋል።
የቀድሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፌደራል ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰኘ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት መመስረታቸውን ዋዜማ ሰምታለች። ዝርዝሩን ያንብቡት–https://cutt.ly/5tjxHaCx
በምስራቅ በለሳ ግንባር ፋኖ የአገዛዙን አከርካሪ የሰበረበት ትንቅንቅ!
በአፋብኃ ሰሜን ዐምሓራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ስር ከሚገኙት ከኮሩ ተወርዋሪ ኃይል፣ ከአፄ እያሱ ክ/ጦር፣ ከዞዝ አምባ ክ/ጦርና ከንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር እንዲሁም ከጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ጥር 01/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ በወሰዱት እርምጃ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ታላቅ ድል ተቀዳጅተው መዋላቸውን መረብ ሚዲያ ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
ውጊያው የተደረገው በምስራቅ በለሳ ጣይመን ከተማ ሲሆን፡ በዚህም የፋኖ አባላቱ በከተማ ውስጥ የሚገኘውን የአገዛዙ ወታደራዊ ካምፕን ጥሰው ገብተው በሦስት አቅጣጫ ተኩስ በመክፈትና ሁለት ትላልቅ ምሽጎችን በመስበር ነው በጠላት ላይ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራ ማድረስ የቻሉት።
በውጊያው 37 የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት አባላት ሲገደሉ 35 የአገዛዙ ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል ያለው ኮሩ፡ በለስ የቀናቸው 25 ወታደሮች ደግሞ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸውን አሳውቋል።
ከንጋት ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን በዘለቀው አማራዊ ጀግንነትን ከጦር ሣይንስ እውቀት ጋር ያጣመረ ነው በተባለው በዚህ ከባድ ተጋድሎ ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ከተደረጉት በተጨማሪ፡ ሦስት ብሬን፣ 55 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 1ሺ የብሬን ተተኳሽ፣ 2ሺ የክላሽ ተተኳሽ፣ 100 የእጅ ቦምብ እና ሁለት ወታደራዊ መገናኛ ራዲዮ በፋኖ መማረኩን መረብ ሚዲያ ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
ቁስለኛ ወታደሮች ለሕክምና ወደ ጓህላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ወደ አርባያ ሆስፒታል ተወስደዋል ነው ያለው ኮሩ ባወጣው
በአገዛዙ በድሮንና በመድፍ የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችንና የሁለት ዕዝ ሰራዊትን ከሚኒሻና አድማ ብተና አባላት ጋር አጣምሮ አስልፎ የተዋጋበትና፡ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት “ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም” የተባለበትን ሽንፈት የተከናነበበት አውደ ውጊያ!
ከላላ ወረዳን ጨምሮ በበርካታ የምዕራብ ወረዳዎች ላይ ታህሳስ 28/2018 ዓ/ ም ከንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት ከባድ ውጊያ መደረጉን በእለቱ መረብ ሚዲያ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገፆቹ መዘገቡ ይታወቃል።
በውጊያው፡ አገዛዙ ከድሮን ጀምሮ በመድፍና በቢኤም እንዲሁም በሞርተርና በዙ23 የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችን እና ከሁለት ዕዝ የተወጣጣ ሰራዊትን አሰልፎ የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን “ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ” የተባለው አባባል ደርሶበት በጥቂት የፋኖ አሃዶች የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋምም ባለመቻሉ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራን ተከናቧል።
ውጊያው የተካሄደው በጃማ፣ በከላላ፣ በልጓማ፣ በደብረዘይት፣ በለገሂዳ፣ ገነቴ፣ በመኃል ሳይንት ደንሳ ከተማ፣ በተንታ አጅባር፣ በመቅደላ ማሻ፣ በጉጉፍቱ፣ ካቤ እና በሰኞ ገበያ ላይ ነው።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሶስት ኮሮች ማለትም ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ ከልጅ እያሱ ኮር እና ከደጋው መብረቅ ኮር፣ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ ከሆነችው ከበላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች እና ከአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥምረት በመፍጠር ነው በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ጥቃት የከፈቱት።
በአገዛዙ በኩል በአየር ወለድ ኮማንዶ መምሪያ የ105ኛ እና የ107ኛ ክ/ጦር ኮማንዶዎችን ጨምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ801ኛ ኮር
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመት ምሕረት፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ ኣምላክ አሜን!
+ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
+ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
+ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
+ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
+ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣
እኛ በሕይወት እንኖር ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም የላከ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓስራ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ልደቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
“ወበዝንቱ ተዓውቀ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር ላዕሌነ እስመ ለወልዱ ዋሕድ ፈነዎ ውስተ ዓለም ከመ ንሕየው በእንቲኣሁ፤ ወዝንቱ ውእቱ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር፡- የእግዚአብሔር ፍቅሩ በእኛ ዘንድ ተገለጠ፤ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነው፤ (፩ዮሓ. ፬፥፱)
በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው እኛ ምሥራቃውያን ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓል፣ የጌታችን የኣምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ነው፤ በዓለ ልደት የእግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ለሰው ልጆች ሁሉ የታወጀበት ዕለት ነው፤ በዚህ ዕለት የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅርና ሰላም ቃላዊ ወይም ተምኔታዊ ኣልነበረም፤ ወይም ደግሞ በርቀት በመልእክት የተላለፈ ኣልነበረም፤
ከዚህ ይልቅ ሰብእናችንን በመዋሐድ፣ በተግባር ሆኖ በመገኘት፣ እንዲሁም ለመሰጠት ዝግጁ በመሆን የተገለጠና የታየ ሰላምና ፍቅር
ለገና በዓል ቤተሰብ ጥየቃ ለመሄድ እየተዘጋጁ የነበሩ 16 ላብ አደሮች መረሸናቸው ተሰማ
ወጣቶቹ ቅዳሜ ምሽት ጎጃም ውስጥ በመንግስት ሀይሎች መረሸናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል፣
የሚድሮክ አካል በሆነው በአየሁ እርሻ ልማት መስሪያ ቤት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውም ታውቋል
ተጨማሪ ያንብቡ: https://meseretmedia.org/p/16
በምስራቅ አማራ ቀጠና እየተገባደደ በሚገኘው ታህሳስ ወር ብቻ አንድ ጄነራል መድፍን ጨምሮ ሦስት የአየር መቃዎሚያ በፋኖ ወድሟል!
በቀጠናው የቀረው የጠላት ሜካናይዝድ መሣሪያም “ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ናት” ነው እጣፈንታው ተብሏል።
በምስራቅ አማራ ቀጠና በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ አደም አሊ(አባናደው) ስም በተሰየመው ወታደራዊ ዘመቻ 3ሺ ሦስት(3003) ወታደሮቹ በፋኖ የተገደሉበት እና 679 ወታደሮቹ ደግሞ የተማረኩበት በአሰፋ ቸኮል የሚመራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ፡ አሁን ደግሞ የዕዙ ሜካናይዝድ ክፍል አለኝ ከሚለው ከባባድ የጦር መሣሪያ መካከል አንዱና አዲሱ የአየር መቃዎሚያ በፋኖ በላውንቸር ተመቶ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
ሰሞኑን የክልሉ ፖሊስ አባላትን ባህርዳር ላይ ሰብስቦ “ፋኖን ያጀገነው እኛ ባለመተባበራችን እንጂ፡ ፋኖ አቅመቢስ ነው” በሚል ሲፎክር በነበረው፡ ከወራት ወዲህ ደግሞ የቅርብ ጓዶቹ “የባዶ ዕዝ አዛዡ” በሚል ስላቅ በሚጠሩት በአሰፋ ቸኮል የሚመራው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ፡ “ዘመቻ አባናደው” ከመስከረም 14/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት ከመካሄዱ በፊት ማለትም ነሐሴ 03/2017 ዓ/ም አንድ ዙ 23(የአየር መቃዎሚያ) ራያ ቆቦ ሮቢት ላይ በፋኖ እንደተማረከበት በእለቱ መረብ ሚዲያ በምስል አስደግፎ መዘገቡ አይዘነጋም።
ይኸው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከዘመቻ አባናደው በኋላ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የነበረ ሲሆን፡ ከመማረክና ከመደምሰስ የተረፉ የዕዙ ሰራዊት አባላትን በቡርቃ ማሰልጠኛ ጣቢያ የአካልና የስነ ልቦና ተሀዲሶ ስልጠና ለወራት በመስጠት ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም አስመርቆ ነበረ።
ለወራት የተሀድሶ ስልጠናው የተሰጣቸው የዕዙ ሰራዊት አባላት፡ ከነ አዛዦቻቸው ሲጠሉት የነበረውን ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን በምረቃ ስነስርዓታቸው ላይ ከላይ እስከታች
በላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር፣በእሸት ክፍለ ጦርና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በላስታና ቡግና ሰንሰለታማ ተራሮች ሲቀጠቀጥ የዋለው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጦር በደረሰበት ሽንፈት ምላሽ ንፁሃንን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ።
መነሻውን ከአይና ቡግና አድርጎ 05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ) ላይ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ንጋት አጥቢያ 12:00 ሰዓት እስከ ቀትር 8:00 ሰዓት ውጊያ የከፈተው የአገዛዙ ሰራዊት በጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድና ሦስተኛና አራተኛ ሻለቃዎች በአይቆፍር ጨረሆና ሆዛ ሜዳ አቅጣጫ የመጣውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል፤በአውደ ውጊያው 35 የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን በአምቡላንስና ፓትሮል እየለቀመ ተመልሷል እንዲሁም ሰባት አባላቱ የአማራን ህዝብ አንወጋም በማለት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል።
በዚህም የተበሳጨው የጁላ ሰራዊት ቡግና ወረዳ የ08 ቀበሌ ንብ ዋርካና የ05 ቀበሌ ቅዱስ ሐርቤ (ጣንቋ)ን ህዝብ በመድፍ፣በአየር መቃወሚያ(ዙ-23) እና በሞርታር-120 ሲጨፈጭፍ ውሏል፤በዚህ ጭፍጨፋ ሦስት ንፁሃን ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ አራት የአርሶ አደር ቤቶች በዙ-23 ሲቃጠሉ ተጨማሪ ዘጠኝ ንፁሃን በከባድ ሁኔታ ቆስለው ህይወታቸው በህክምና እየተጠበቀ ይገኛል።
በጭፍጨፋው በከባድ መሳሪያ አንዲት የ60 ዓመት መነኩሴና የ15 ዓመት ልጃገረድ ለገና በዓልና ለንጉስ ላልይበላ ልደት ክብረ በዓል ወደ ላስታ ላሊበላ ይጓዙ የነበሩ እና ቅዱስ ሐርቤ ሚኒቃባ መንደር ከእናቷ ማዘል ላይ የነበረች እታቱ
በከተማዋ ቦርቸሌ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘው ትልቁ የአየር ወለድ ኮማንዶ ካምፕ የተሰበረ ሲሆን፡ የፋኖ አባላቱ ከምሽግ ምሽግ እየተወረወሩ “የባለምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች” ሲል አገዛዙ የሚያሞካሻቸው ህፃን ደፋሪ፡ ሀብት ንብረት አውዳሚ ፀረ አማራ ኮማንዶዎችን ባፈሙዝ አለንጋ ሲገርፏቸው እንደዋሉ የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
ዝርዝር መረጃውን አድምጡ👉https://www.youtube.com/watch?v=uoJpt2xZmdY
Yared Hailemariam
ታዬን ለመበቀል፣ ቀነኒን ፍትህ በመንፈግ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም የዘቀጠው የፍትህ ሥርዓት።
የፍትህ ሥርዓቱን ለበቀል፣ ለፖለቲካ እና የወገኑለትን ከተጠያቂነት ለማስመለጥ በመንግስት ደረጃ ታስቦበት ሲተገበር ማየት እጅግ ያማል። ሰዎች በማንነታቸውና በሃሳባቸው ብቻ ተፈርጀው፣ ታስረው እና በሃሰት ሽብርተኛ ተብለው ተከሰው በሚጉላሉበት አገር ብዙ ጥፋትና ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ሰዎች ደግሞ ያለጠያቂት በነጻነት ይንቀሳቀሳሉ።
ታዮ ደንድአን በሰንሰለት አስሬ ፍርድ ቤት ካላቀረብኩ ማለት ከፖለቲካ በቀል ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም። አንድ እስረኛ በሰንሰለት ታስሮ ፍርድ ቤት የሚቀርበው እስረኛው አንድም ሊያመልጥ ይችላል ወይም ጉልበተኛ ሆኖ ፖሊሶቹን ወይም ዳኞችን ሊተናኮስ ይችላል ተብሎ ሲታሰብ ነው። ታዬን ማሰር ግን አላማው ማዋረድ፣ ማሸማቀቀ እና ፍትህን መበቀያ ማድረግ ነው። የታዮ ሁኔታ ሲገርመኝ ባለቤቱን ቀነኒን በመግደል ፖሊስ ጠርጥሮና ማስረጃ አሰባስቦ ለአቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርትበት የተላለፈውን ፋይል በመዝጋትና ተጠርጣሪውን በመልቀቅ የወንጀሉን ጉዳይ አባገዳዎች በሽምግልና እና በካሳ እንዲጨርሱት ማድረግ ከነውርም አልፎ የፍትህ ሥርዓቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ማሳያ ነው። ( Yared Hailemariam )
ከወረታ ደብረታቦር ባለው አውራ ጎዳና በአገዛዙ ተደራጅተው በፋኖ ስም ሲዘርፉ የነበሩ ባንዳዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ!
በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር ስር ከነበልባሉ ፎገራ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በወረታ እና በደብረታቦር መካከል ሀገረ ሰላም፣ አርባ አምባ፣ በቆሽ በርና ውር ተብለው በሚጠሩ አከባቢዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ባንዳዎችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ቀጠናውን ማፅዳታቸውን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
ፋኖ፡ አገዛዙ የአማራ ሕዝብን በማሕበራዊና በኢኮንሚያዊ ሕይወቱ እረፍት እንዲነሱለት አደራጅቶ ያሰማራቸው ዘራፊ ወንበዴዎች ላይ የሚወስደውን ጥብቅ እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለክፍለ ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባሎች ፖለቲካዊ ስልጠና ሰጠ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ለተከታታይ ሶስት ቀናት አጠቃላይ ለክፍለጦር፣ለሻለሻለቃ አመራሮችና አጠቃላይ ለሰራዊቱ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ወሮበላው የኦሮምማው ስብስብ አማራን ለማጥፋት በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከአማራ ግዛቶች ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት እያደርገ መሆኑን አለም የሚያቀው ሀቅ ነው።
ሆኖም ይህን የብልፅግና ፋሽስታዊ ስርዐት የአማራ ልጆች በነበልባል ክንዳቸው እየተፋለሙትና እየመከቱ የበላይነታቸው እየወሰዱ ይገኛል። ስለሆነም የአሳምነው አናብስቶች ከትግሉ ጎን ለጎን በተለያዩ ለሰራዊት ፖለቲካዊ ስልጠና ማለትም፦
*የሰራዊት ስነምግባር እና ስነስረዓት መወሰኛ ደንብ
*ጓዳዊ ዝምደና
*ባህል እና ጨዋነት
*ድርጅትና የድርጅት ምንነት
*የአማራ ህዝብ ምንነት እና *የገጠሙት ፈተናወች እና ያደረጋቸው ተጋድሎወች
*ፋኖነት እና መገለጫ ባህሪያት በሚሉ
አርዕስቶች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ ኢያሱ ሙሉጌታ ፣የአሳምነው ዕዝ ህግ ክፍል ሀላፊ አርበኛ ተስፋዬ ገስጥ እና የአሳምነው ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ ለማ በመሆን ከትምህርት እና ስልጠና መምሪያ በተሰጠው ዕቅድ መሰረት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የሻለቃ አመራሮች እና ለሰራዊት አባላት በበቂ ሁኔታ ስልጠና በመስጠት አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በስልጠናውም የተገኙት የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራር
የህዝቡን አንድነት በማፅናት አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስታወቀ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመልሶ ማደራጀት ትግበራው የህዝብን አስተዳደር የፀጥታና የፍትህ ጥያቄዎችን በመመለስ አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነትን እንዲያረጋግጥ ታስቦ በአዲስ የተዋቀረው ጊዚያዊ መንግስት በ206ኛ ኮር ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች አገልግሎት በመጀመር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ከጠላት ነፃ በወጡ ሁሉም ቀበሌዎች የአስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የፍትህና ህግ አገልግሎት፣ ፀጥታ፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በፍጥነት ምላሽ በመስጠት አመርቂ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን የወረዳው ጊዚያዊ መንግስት ገልጿል።
የህዝብን አስተማማኝ ደጀንነት በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ጊዚያዊ መንግስቱ የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በማረጋገጥ እንደቻሉ በማውሳት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ድርጅታዊ ግዳጅ ከመደበኛ ሰራዊቱ ጎን ተሰልፈው እንደሚወጡም አረጋግጧል።
በመልሶ ማደራጀት ትግበራው ባንዳዎችን በማፅዳት የሰራዊቱን የህዝቡንና የትግሉን ደህንነት በማስጠበቅ የጠላትን እረጅም እጅ እየቆረጠ የሚገኘው 206ኛ ኮር ለደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች፣ በህግና እና ስነ-ስርዓት እንዲሁም በጊዚአዊ መንግስት መመሪያዎች ላይ ከ14ኛ ክ/ጦር አመራሮች ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጧል።
የድርጅቱን ህግ እና ደንብ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የፀደቁ መመሪያዎች ላይ ስልጠና የተሰጣቸው የወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች ህዝቡን ለማስተዳደርና የድርጅታችንን ህግና ደንብ ለማስፈፀም በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ተናግረዋል ።
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ዛሬ ከንጋት ጀምሮ በደቡብ አማራ ሸዋ ቀጠና ደብረሲና ከተማን ጨምሮ በሾላ ሜዳ፣ በአርማኒያና ጭራ ሜዳ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ ፋኖ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ በማድረስ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡ ታወቀ!
ወደ ደብረሲና ከተማ ዘልቀው የገቡት የፋኖ አባላቱ፡ በከተማዋ የአየር ወለድ ኮማንዶዎች የሰፈሩበትን ካምፕ በማፈራረስ በርካታ ኮማንዶዎችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጋቸውን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
ፀረ አማራው የብልፅግና ቡድን የፋኖን ጥቃት ለመመከት ከአየር ኃይልና ባሕር ኃይል ጀምሮ የአየር ወለድ ኮማንዶዎቹን፣ መሠረታዊ ወታደሮቹንና ሌሎች ታጣቂዎቹን ያሰለፈ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ሁሉ ግብስብስ ኃይል የፋኖን ግስጋሴ ሊያስቆም እንዳልቻለ ነው የተነገረው።
“እየዘፈኑ ድህነት እያለቀሱ ክብረት”
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር የተሰጠ መግለጫ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስባቸው ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ በሚገኙ 11 ወረዳዎች ውስጥ የሰርግ ጥሎሽ አምስት ሺህ ብር ብቻ እንድሆን መወሰኑና በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ መመሪያ ማውጣቱ ይታወቃል:: የመመሪያውን ተፈፃሚነት ይከታተል ዘንድ ኮሩ በየወረዳዎች የመደበው ግብረኃይል የሰበሰበው መረጃ እንደሚያስረዳው ህዝባችን ራሱ ያፀደቀውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ያልቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: ወይ መቶ ወይ መተው እየተባለ እስከ መቶ ሺህ ብር ድረስ ጥሎሽ በመጣል ገደብ የለሽ እና ድሀን አግላይ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን ደርሰንበታል:: ሰርግ ምስለት እየዘፈኑ ክስረት ሆኗል:: አላማውንም እየሳተ ነው!
በምድር በሰማይ እሳት እየነደደበት ያለው ህዝባችን በጦርነቱ ከደረሰበት የኢኮኖሚ ድቀት እና የማህበራዊ እረፍት እጦት በተጨማሪ በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ የሆኑ ባህላዊ ክዋኔዎች አሉ:: ከእነዚህ ባህላዊ አሰራሮች አንዱ የሆነው በተጋነነ ድግስ የሚከወን የሰርግ ስነ ስርዓት ነው:: ለሰርግ ብቻ ሳይሆን ለተዝካር እና ሰደቃ ያለ የሌለን ጥሪት አሟጦ የመደገስ ውሳኔ ከሀይማኖት ባሻገር ባህላዊ እየሆነ ነው:: ሐይማኖቶች በሚፈቅዱት መሰረት ተብቃቅቶ ህይወትን መምራትና አላስፈላጊ ወጭዎችን መቀነስ ተገቢ ስለሆነ ይህን ለማድረግ ይቻል ዘንድ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሰርግ ዙሪያ መመሪያ አውጥቷል:: ይህ መመሪያ የሚደነግገው የሰርግ ጥሎሽ ከ 5 ሺህ ብር መብለጥ እንደሌለበት ነው::
መመሪያውን ተላልፎ የሚገኝ አካል 10 ሺህ ብር የሚቀጣ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከ5 ሺህ በላይ
የፍትህ ሚኒስቴር “የሰው እና ሰነድ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ፤ በማንነታቸው እና በፖለቲካ አቋማችው የታሰሩ ሰዎች ለከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ” ተዳርገዋል ሲሉ የምክርቤት አባል ተናገሩ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ በማንነቱ ሆነ በፖለቲካ አቋሙ የሚታሰርም ሆነ የተሰረ ሰው እንደሌለ ተናገሮ ግን እንድ ሰው የፖለቲካ ግቡን ለማሳካት በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ፖለቲከኛም ፣የመንግስት ሰራተኛም ሆነ የመንግስት ሃላፊ ላይ የህግ ተጠያቂነትን አረጋግጣለሁ ብሏል፡፡
ይህ ጉዳይ የተነሳው የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ በፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ ከምክርቤት አባላት ለተነሱለት ጥያቄዎች የ25 ደቂቃ ምላሽ እና ማብራርያ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የምክርቤት አባሉ አበባው ደስአለው (ዶ/ር) የፍትህ ሚኒስቴር ዋነኛው ስራው ክስ በመመስረት ፣ክሱን ሂደት በመከታታል አፋጣኝ ፍትህ ለዜጎች ማደረስ መሆኑንን አስተውሰው “በማንነታቸው እና በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ከ2 ዓመት ከስድስት 6 ወር በላይ የታሰሩ የአማራ ፖለቲከኞች ፣ጋዜጠኖች ፣እንቂዎች እና የሃይማኖት አባቶች እናንተ የሚጠበቅባችሁን የሰነድ ፣የሰው ማስረጃ እና መስክር ማቅረብ ባለመቻላችሁ ለክፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ተዳርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምክርቤት አባሉ”ማስረጃ እና ምስክር ማቅረብ ካልቻላችሁ የተሰጣችሁን ክስ የማቋረጥ ስልጣን መጠቀም ሲገባችሁ ዜጎች በፍትህ መጓደል የሚሰቃዩት አስከመቼ ነው?”ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
“ከፖለቲካ ጫና ወጥታቹሁስ እውነተኛ ፍትህ የምታሰፍኑት መቼ ነው “በሚል ሌላ ጥያቄም አበባው ደስአለው (ዶ/ር)አክለዋል ፡፡
በማረሚያቤት የሚገኙ አስረኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲያጋጥም ዳኞችም ፍርድ ሲሰጡ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ግን ይህን ትዕዛዝ ሲተገብሩ አይታይም ሲሉ የምክርቤት አባሉ ከስዋል፡፡
በስብዓዊ ተቋት እንደተረጋገጠው በአገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአማራ እና

የፎቶው ባለመብት,GIDA AYANA COMMUNICATION
የምስሉ መግለጫ,ጥቃቱ የተፈፀመበት አካባቢ ከጊዳ አያና ወረዳ ዋና መቀመጫ አያና ከተማ 20 ኪሎ ሜትር ገደማ ይርቃል
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ “በኦሮሚያ ልዩ ኃይል” ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት 19 ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ መቃጠላቸውን እና መዘረፋቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ተቃዋሚዎቹ እናት ፓርቲ እና ኢህአፓ ጥቃቱ “በመንግሥት መዋቅር የተፈጸመ” መሆኑን በመግለጽ ሲያወግዙት የክልሉ እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስካሁን ምንም ያሉት ነገር የለም።
በወረዳው የአማራ ተወላጆች ይኖሩበታል በተባለው ጠጋ ጂጊ (ሻሾ በር) አነስተኛ ከተማ ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም. አንድ መነኩሴን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በስለት እና በጥይት “በአሰቃቂ ሁኔታ” ተደብድበው መገደላቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው አምስት የዐይን እማኞች እና የሟች ቤተሰቦች አስታውቀዋል።
ከጥቃቱ ሁለት ቀናት አስቀድሞ በአካባቢው ለወራት የቆየው የመከላከያ ሠራዊት ለቅቆ ሲወጣ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል የሆነው “የኦሮሚያ ልዩ ኃይል (ልዩ ኮማንዶ)” መግባቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ማክሰኞ ታኅሣሥ 14 ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በአካባቢው የተኩስ ልውውጥ መጀመሩን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ የተኩስ ልውውጡ በማን መካለል እንደተደረገ እንደማያውቁ አንድ ነዋሪ ሲናገሩ፤ ሌላ ነዋሪ ደግሞ መሳሪያ አናስረክብም ብለው ጫካ በገቡ እና ራሳቸውን “ፋኖ” ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች እና በኦሮሚያ ልዩ ኃይል መካከል ውጊያ መደረጉን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱት የፋኖ ኃይሎች ቅርበት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን በአካባቢው ግጭት እንደነበር የሚጠቁም መረጃዎችን አውጥተዋል።
ግጭቱ ከመቀስቀሱ አስቀድመው ስጋት ያደረባቸው እና ከተቀሰቀሰ በኋላ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ቀበሌዎች
የሞዴል ቀነኒ አዱኛን ጉዳይ በባህላዊው የገዳ ስርዓት ለመፍታት የተደረገው ጥረት ያለስምምነት ተቋረጠ
ባለፈው ዓመት ከአርቲስት አንዱዓለም ጎሳ ጋር ትኖርበት ከነበረው ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ ህይወቷ ያለፈው የሞዴል ቀነኒ አዱኛን ጉዳይ በባህላዊው የኦሮሞ አባገዳዎች ስርዓት በእርቅ ለመቋጨት የተደረገው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን አባገዳዎች አስታወቁ፡፡
ጉዳዩን ላለፉት ሦስት ወራት በሽምግልና እና በባህላዊው የፍትህ ስርዓት ለመፍታት ሲጥሩ የቆዩት የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ፤ ጥረቱ በተጎጂ ቤተሰቦች ፈቃደኛ አለመሆን ምክንያት መቋረጡን ዶይቼ ቬለ ለእኔ ነግረውኛል ብሏል፡፡
የሽምግልናው ሂደትና የአባገዳዎች እይታ አባገዳ ጎበና እንደገለጹት፤ ጉዳዩ በመደበኛው ፍርድ ቤት እልባት ባለማግኘቱ የገዳ ስርዓት አባቶች ተጠርጣሪውንና የተጎጂ ቤተሰቦችን በማገናኘት መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። “ሆኖም በአራተኛው ቀጠሮ የሟች አባት አቶ አዱኛ ዋቆ ሂደቱን አፍርሰውብናል” ብለዋል፡፡
አባገዳዎቹ ጉዳዩን ከኦዳቡልቱም አባገዳዎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን በጥልቀት እንደተመለከቱትና “እውነቱ ተገኝቷል” የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የሟች ቤተሰብ ሽምግልናውን ባለመቀበላቸው ምክንያት፣ የተገኘውን እውነት ለጊዜው ይፋ ሳያደርጉ ሂደቱን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አብራርተዋል።

የሟች ቤተሰብ ተቃውሞ
በሌላ በኩል የሞዴል ቀነኒ አዱኛ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ፤ የሽምግልና ሂደቱን ያልተቀበሉበትን ምክንያት ሲያስረዱ፣ “በቅድሚያ የልጄ ገዳይ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ካሳ (ጉማ) አንቀበልም” የሚል አቋም እንዳላቸው ገልጸዋል።
አቶ አዱኛ አክለውም፤ “እነሱ (ሽምግሌዎቹ) የሚሉት ‘ደም በእጃችን አለ ግን አልገደልኩም’ ነው፤ እኛ ደግሞ የገደለ ሳይታወቅ እንዴት ጉማ እንበላለን?” በማለት ጠይቀዋል። አባትየው አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ በቅድሚያ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ እውነቱ ከተረጋገጠ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጎርጎርዮሳውያን /Gregorians/ የዘመን አቆጣጠር በነገው ዕለት የሚጀመረውን የ2026 አዲስ ዓመት በማስመልከት ለመላው የዓለም ማኅበረሰብእ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
ታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት
ቅዱስነታቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል፦
ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ለመላው የዓለም ሕዝብ የተላለፈ
አባታዊ መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት፡-
እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።”
(ሉቃ. 2፡11)
የጌታችን ልደት የሰው ልጆች ምኞት የተፈጸመበት ፣ ከሁሉ በላይ የእግዚአብሔር ፍቅርና ማዳን የተገለጠበት በመሆኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ሲያስቡት ይኖራሉ፤ አዲስ ዘመንም ካለፈው ዓመት የቀጠለ የቍጥር ቀመር ሳይሆን እያንዳንዱ ቀን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን እናምናለን፤ በዘመን ላይ ዘመን ሲጨመር ገንዘብ ሊገዛው፣ ሥልጣን ሊያመጣው የማይቻለውን የዕድሜ ስጦታ አግኝተናልና የምስጋና ርእሳችን ነው ። እያንዳንዱ ዘመን ይዞት የሚመጣው በረከት፣ ትምህርትና ብስለት ያለው በመሆኑም በመላው ዓለም ሆናችሁ እንደየዘመን አቆጣጠራችሁ የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ለምታከብሩ፤ እንዲሁም የ2026ን አዲስ ዓመት ለመቀበል ለተዘጋጃችሁ ወገኖቻችን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን ።
በአዲስ ዘመን ተነፋፍቆ የቆየው ወዳጅ የሚገናኝበት ፣ ወደ ቤቱም የሚመለስበት እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዘመን ብዙ ልዩነቶች ዓለምን እያወኩ ይገኛሉ፤ የበዓሉ ዓላማ ግን መገናኘት በመሆኑ ወደ አንድነት
እስራኤል ለሶማሌላንድ ከሰጠችው የነጻ ሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና በኋላ ዛሬ የመጀመሪያውን ስብሰባ ያደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት “የት ደረሰ?” የሚል ጥያቄ አነሳ።
በመደበኛ ስብሰባው ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስም ሆነ ምክትሎቻቸው ከሶማሌላንድ ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።
ጥያቄውን ካነሱት የፓርላማ አባላት አንዱ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ዶ/ር አበባው ደሳለው፤ የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ ሁለት ዓመት ሊሞላው ቀናት እንደቀሩት አስታውሰዋል። የመግባቢያ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ የ20 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ በኪራይ ውል ማግኘት የሚያስችላት እንደነበር አንስተዋል።
በምትኩም ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ በመሆን ለሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅና ለመስጠት ተስማማታ እንደነበር ገልጸዋል። ይሁንና ኢትዮጵያ “የባሕር በሩን ሳታገኝ እና ለሶማሌላንድ እውቅና ሳትሰጥ” በእስራኤል መቀደሟን ዶ/ር አበባው ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና በመስጠት “ሁለተኛዋ ሀገር” ትሆን እንደሆነም የፓርላማ አባሉ ጠይቀዋል።
ዘገባው የኢትዮ ኢንሳንደር ነው!
ከመስከረም 2017 እስከ ነሃሴ 2017 በነበረው ጊዜ ውስጥ ኬንያ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት 953 ሕገወጥ የውጭ ፍልሰተኞች መካከል 70 በመቶዎቹ ወይም 670 ያህሉ ኢትዮጵያዊያን ኾነው ተገኙ።
ከኢትዮጵያዊያን ቀጥሎ በብዛት፣ ሶማሊያዊያን፣ ቡሩንዲያዊያንና ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች በቅደም ተከተል እንደተቀመጡ የአገሪቱ ጋዜጦች የመንግሥትን እንድ ሪፖርት ጠቅሠው ዘግበዋል።
ሪፖርቱ፣ የኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ቁጥር ከፍተኛ የኾነው፣ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በሚካሄዱት ግጭቶች እና በትግራይ በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ እንደኾነ ማውሳቱን ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኹኔታ፣ ድንበር-ዘለል የጦር መሳሪያና አደንዛዥ ዕጽ ዝውውር እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሠርጎ ገብነት ስጋት መፍጠሩም በሪፖርቱ ተጠቅሷል ተብሏል።
በተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ያላቸውን ብሪታንያን፣ ፈረንሳይን፣ ሩሲያንና ቻይናን ጨምሮ 14 የምክር ቤቱ አባላት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ትናንት በጉዳዩ ላይ ባካሄዱት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ አወገዙ። የአሜሪካ ተወካይ በበኩላቸው፣ እስራኤል ከሶማሌላንድ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመመስረት መብት እንዳላት ጠቅሠው፣ አሜሪካ ግን የአንዲት ሶማሊያ ፖሊሲዋን እንዳልቀየረች አረጋግጠዋል። ሶማሊያ ባንጻሩ፣ የእስራኤል ውሳኔ ፍልስጤማዊያንን ወደ ሶማሌላንድ ከማስፈር ጋር የተያያዘ ሊኾን እንደሚችል ጠቁማለች። ጸጥታው ምክር ቤት በእስራኤል ውሳኔ ላይ በአስቸኳይ ስብሰባ እንዲወያይ ጥያቄ ያቀረበችው፣ በምክር ቤቱ ተለዋጭ መቀመጫ ያላት ሶማሊያ ናት። እስራኤል፣ ለሶማሌላንድ የሠጠችው የአገርነት እውቅና በሶማሊያ ላይ የተቃጣ ጠበኛ ድርጊት ተደርጎ መታየት የለበትም ብላለች።