የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (ኤ ኤፍ ፒ) ወደ ትግራይ እንዳይጓዝ ተከለከለ

የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (ኤ ኤፍ ፒ)፣ የኢትዮጵያ ዘጋቢው ለዘገባ ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ መከልከላቸውን ገለጠ። ዘጋቢው ትናንት ወደ ትግራይ ሽሬ ከተማ እንዳይጓዙ የተከለከሉት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ፍቃድ የላቸውም በሚል ምክንያት መኾኑን የዜና ምንጩ ጠቅሷል። የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የጸጥታ አካላት ዘጋቢውን ከጉዞ ያገዷቸው፣ በዚህ ሳምንት አዲስ መመሪያ ደርሶናል በማለት ነው ተብሏል። የዜና ወኪሉ፣ የጉዞ እገዳው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኀን ላይ እየጣሉት ያለው ገደብ ማሳያ ነው በማለት ውሳኔውን ተቃውሟል።