በጋሞ ዞን ከዘይሴ ወረዳ በእርሻ ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች እና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪሎች ተገደሉ

ኢሰመጉ፣ የፌደራሉ እንዲሁም የአማራ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስታት በክልሎቹ በንጹሀን ላይ እየደረሠ ላለው የሰብዓዊ መብት ጥሠት በቂ ትኩረት እንዲሠጡ ጠየቀ። ኢሰመጉ፣ በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ከመንግስት የጸጥታ አካል በተተኮሠ ከባድ መሳሪያ እናቶችና ሽማግሌዎችን ጨምሮ ቁጥራቸዉ ያልታወቁ ንጹሃን ጥር 26 ቀን መገደላቸውን ገልጧል። በጋሞ ዞን ከዘይሴ ወረዳ የልዩ ወረዳነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ጥር 19 ቀን በእርሻ ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮችን መግደላቸውንና በተያዘው ወርም ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪሎች እንደተገደሉ ኢሰመጉ ጠቅሷል፡፡ ኢሰመጉ፣ ከዘይሴ ወረዳ ከወራት በፊት በጸጥታ አካላት የተያዙ አምስት የኢዜማ አባላትም እስካሁን የት እንደደረሱ አይታወቅም ብሏል።