በአማራ ሳይንት ግንባር ድል ተመዘገበ። የኮሎኔል ደሳለኝ አጃቢም አንድ ጥርጥር ክላሽ እና ማካሮቭ ሽጉጥ ይዞ ወደ ፋኖ ተቀላቅሏል።
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ታቦር ሻለቃ ፋኖዎች ወደ ጓሜዳ ቀጠና ለመግባት በርካታ ኃይል ከዙ-23 እና ሞርተር ጋር በተሽከርካሪ ጭኖ የመጣውን ጠላት በመመከት በመልሶ ማጥቃት ታሪክ ሰርተዋል።
ትናንት ማለትም የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም አማራ ሳይንት ወረዳ ውስጥ በተለምዶ መለስ ሳንቃ በር ተብሎ ወደሚጠራው ቦታ በመጠጋት አንድ ዙ23፣ 2 ሞርተር እና 6 ድሽቃ አጥምዶ የታቦር ሻለቃ ፋኖዎችን ጥሶ ለማለፍና ጓሜዳ ታዳጊ ከተማ ለመግባት ያሰበውን የጠላት ኃይል የአማራ ሳይንት አናብስት በጀግንነት ተፋልመው ወደነጣበት የመለሱት ሲሆን በከባድ መሳሪያ በታጀበው በዚህ ትንቅንቅ ከጠላት በኩል ቁጥራቸው ያልታወቀ ወታደሮች ሲቆስሉ የተደመሰሱም እንዳሉ የኮሎኔል ደሳለኝ አጃቢ ተናግሯል።
የታቦር ሻለቃ አባላት በፊት ለፊት እና በጀርባ በኩል ተሰልፈው የጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሰዋል። ከጀርባ በኩል ወደ ሳይንት አጅባር ከተማ በመቅረብ የጎዳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲያደርጉት ጠላት የመሸገበትን ቦታ በብርሀን ፍጥነት በመልቀቅ ወደወጣበት ተመልሷል።
ውጊያው በፋኖ ድል አድራጊነት እንደተጠናቀቀ የጠላትን ኃይል በመክዳት ወደ ታቦር ሻለቃ የተቀላቀለው የኮሎኔል ደሳለኝ አጃቢ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ወደ ፋኖ እንድመጣ ሊያስገድደኝ ችሏል ያለ ሲሆን ሌሎች የቀድሞ ጓዶቹም የውጊያ ሞራል እንደሌላቸው ገልጿል። አጃቢው አክሎም የበፊቱ መከላከያ አሁን ላይ የለም ይልቁንስ አሁን ያለው ህዝብ ጠል እና ዘራፊ እንድሁም ፈሪ ኃይል ነው፤ ይህን ኃይል ደግሞ በቀላሉ ማሸነፍ ይቻላል ሲል ተናግሯል። አፋብን ያወጣውን የምህረት አዋጅ ሰምቶ ወደ ፋኖ መቀላቀሉንም ነው የኮሎኔሉ አጃቢ የተናገረው።
©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!