የአፋብን ምኒልክ ዕዝ እና አሳምነው ዕዝ አሃዶች በጥምረት ወረኢሉ ከተማና በዙሪያው ድል አስመዘገቡ::
አፋብን ምኒልክ ዕዝ እና አፋብን አሳምነው ዕዝ በጋራ በመሆን የአረመኔው አብይ አህመድን ጡት ቁራጭ ኃይል በወረኢሉ እና በሰኞ ገብያ ሁለቱ ዕዞች ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሌሊት 7:00 በዘለቀ ውጊያ በጥምረት የጠላትን ምሽግ በአስደናቂ ሁኔታ በመስበር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተቀናጅተዋል።
ምኒልክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር እና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያቆብብ 1ኛ ኮር በጥምረት ታሪካዊቷ ወረኢሉ ከተማ እና ሰኞ ገበያ ከተማ ላይ በርካታ የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ መከላከያና ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራ ሆድ አደር ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል::
አመራርና የጦር መኮንኖች ጭምር የተደመሰሱ እንዳሉ የውስጥ ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን ከሞት የተረፉት አንድ አንቡላስና አንድ ኦራል ቁስለኛ ወደ ደሴ ተወስደዋል።በዚህ የተበሳጨው ወንበዴ ቡድን በከተማ ዙሪያ ያሉ ደኖች ፋኖን ይደበቅባቸዋል በሚል ጭንቀት እያቃጠለቸው ይገኛል::
©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!