በወግዲ ወረዳ በብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ዝርፊያ ተባብሶ ቀጥሏል!

በወግዲ ወረዳ በብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ዝርፊያ ተባብሶ ቀጥሏል!

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የመንግስት መከላከያ ሰራዊት በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና በደል ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጥተዋል። ሰሞኑን በተለያዩ ቀጠናዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በህጻናት ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶች መድረሳቸውና የገበሬው ምርት መዘረፉ ተገልጿል።
​ትናንት የካቲት 08 ቀን 2018 ዓ.ም በወረዳው ልዩ ልዩ አካባቢዎች አሰቃቂ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።

​ በሰኮሩ ቀጠና ሰአዳ ደሳለው የተባለች ህጻን፣ ለአባቷ ምሳ አድርሳ ስትመለስ “አበራ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በ105ኛው ክፍለ ጦር አባል መደፈሯ ተሰምቷል። ህጻኗ በአሁኑ ወቅት በማከፍታ ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ይገኛል።
​በመነበጢ ስር መርድኒ በተባለ ቦታ፣ 87ኛው ክፍለ ጦር “ፋኖ መጣ” በሚል በከፈተው ተኩስ የ6 ዓመት ህጻን እግሩ ላይ በጥይት ተመትቶ በህክምና ላይ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።

​በዚሁ እለት “ቱሉ የጉርባ” ተብሎ በሚጠራው ተራራ ላይ የሚገኝ የተፋሰስ ደን፣ “ፋኖ ይደበቅበታል” በሚል ሰበብ በመከላከያ ሰራዊቱ እሳት እንዲለቀቅበት ተደርጎ መቃጠሉ ተገልጿል።

​በተለይም “ዘምድ” (025 ቀበሌ) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የገበሬውን ምርት ከጎተራ እያወጡ መጫናቸው ተመልክቷል። በዚህ ቀበሌ ብቻ ከ125 ኩንታል በላይ እህል መዘረፉ የተገለጸ ሲሆን፣ የተጎጂዎች ዝርዝርም እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1 . አድማሱ ጌታነህ : 8 ኩንታል ጤፍ
2. ቱባው ለማ 8 ኩንታል ጤፍ
3. ዘለቀ አየለ 10 ኩንታል ጤፍ
4. ዘላለም    : 80 ኩንታል ጤፍ እና የቤት እቃዎች
5. አለባቸው፡ 3 ኩንታል ጤፍ
6. ሥላሽ መኮነን 7 ኩንታል ስንደ እና4 ኩንታል ጤፍ
7. ስርፋሽ : ሙሉ ሱቅ
8 . ስለሽ መኮነን : 300000 (ሶስት መቶ ሽ) ብር የሚገመት የሱቅ ዕቃ
9. ሰማራ : ወርቅ ጌጣጌጥ እና የቤት እቃዎች
10. አብነው አያሌው : 5 ኩንታል ሰንደ4 ኩንታል ጤፍ በፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ተዘርፈዋል ሲል ምኒልክ ዕዝ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል አሳውቋል።