Blog Archives
ከህወሓት መሰረዝ በኋላ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እጣፈንታ ምንድነው ?
“ የህወሓት ሙሉ በሙሉ ህጋዊ ሰውነት ማጣት የፕሪቶሪያውን ስምምነት አይሽረውም፡፡ በህወሓት የተፈረመውን የፕሪቶርያ ስምምነት የሚፈፅም አካል በዛው ስምምነት ተወልዷል እሱም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነው ” – አቶ ያሬድ ኃይለማርያም
የህወሓት ከፓርቲነት መሰረዝና የህግ ባለሙያ አስተያየት !
የህወሓት ጉዳይ ፖለቲካዊ መፍትሔ ነበር የሚያስፈልገው ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ህወሓትን ከፖለቲካ ፓርቲነት ሰርዞታል።
ይህን አስመልክቶ አንድ የህግ ባለሙያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሙያዊ ማብራሪያ የሰጡት የህግ ባለሙያውና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ሲሆኑ የህወሓት ጉዳይ በደረቅ ህግ ሳይሆን በፖለቲካዊ መንገድ መታየት ነበረበት ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ ዕድሜ፣ የአመሰራረት ታሪክና ቁመና እንዳላቸው የገለፁት ባለሙያው፣ እነዚህን ፓርቲዎች በአንድ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ በአንድ ህግ ብቻ ማየት ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በራሱ የሕወሓትን እጣፈንታ መበየን ሲገባው፣ ይህን ጉዳይ ጨምሮ ስምምነቱ ያላያቸውና ያልተብራሩ በርካታ ጉዳዮች አሉ ያሉት ባለሙያው፣ ስምምነቱ ጥቅል ጉዳዮችን በቻ የያዘ ስለሆነ፣ በሌሎች ሰነዶች መብራራት ነበረበት በማለት ገልፀዋል፡፡
የህግ ባለሙያው በዝርዝር ምን አሉ ?
” ምርጫ ቦርድ በህወሓት ላይ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ህጉን የተከተሉ ሲሆኑ፣ በህወሓት የሚነሱት ጉዳዮች ደግሞ ፖለቲካዊ ናቸው፡፡
‘ እንደ አዲስ ፓርቲ መመዝገብ የለብኝም፣ ለረዥም ጊዜ የነበረ ፓርቲ ነው፣ እንደነባር ፓርቲ ነው የምንቀጥለው እንጂ ዛሬ እንደሚመሰረት አዲስ ፓርቲ አዲስ ምዝገባ ማድረግ
በ2024 ምን ያህል ሰዎች ተፈናቀሉ ?
ዓለም አቀፉ የተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል (IDMC) ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2024 በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች (IDP) ቁጥር የተመዘገበበት ሆኗል ሲል በዓመቱ 83.4 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጿል ።
በተለያዩ አከባቢዎች የተነሱ ግጭቶችና አመጾች መበራከት የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ለማሳየቱ ምክንያት ነው ሲባል በዚህ ብቻ ለ73.5 ሚሊዮን ሰዎችን ተፈናቅለዋል።
በዓመቱ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በአንጻሩ ለ 9.8 ሚሊዮን ሰዎች በምክንያትነት ተቀምጧል።
ሱዳን በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛውን ድርሻ በዓመቱ የያዘች ሲሆን 11.6 ሚሊየን ሱዳናዊያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ሶሪያ፣ ጋዛ እና ዩክሬን በከፍተኛ ሁኔታ ዜጎቻቸው የተፈናቀሉባቸው ሀገራት ናቸው።
29 ሃገራት በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ዜጎቻቸው እንደተፈናቀሉ መግለፃቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ በ2024 የተመዘገበው የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥርም ከፍተኛው እንደሆነ አንስቷል
ድርጅቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሪፖርቱ ውስጥ ያካተተ ሲሆን በ 2024 2.4 ሚሊየን በላይ ዜጎች በሀገር ውስጥ መፈናቀላቸውን ሲገልጽ ከ80 በመቶ በላዩ የተፈናቀሉት ከግጭት ጋር በተያያዘ መሆኑን አስታውቋል።
በ2023 በአለም አቀፍ ደረጃ የውስጥ ተፈናቃይ የነበሩ ሰዎች ቁጥር 75.9 ሚሊየን ነበር። https://www.internal-displacement.org/countries/ethiopia/
የአማራ ክልል ዳኞች በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ “ሃሳብ እንዳይሰጡ” የሚከለክል ደንብ ወጣ
በአማራ ክልል የሚገኙ ዳኞች፤ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት ወይም “አወዛጋቢ በሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ “በየትኛውም” ማህበራዊ ሚዲያ “ሃሳብ እንዳይሰጡ” የሚከለክል ደንብ ጸደቀ። ደንቡ በክልሉ የሚገኙ ዳኞች “ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን “እንዳይጠቀሙ”፣ “እንዳይከተሉ” እና “አባል እንዳይሆኑ” ይከለክላል።
የዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎችን የስነ-ምግባር እና የዲሲፕሊን የሚመለከተው ይህ ደንብ የጸደቀው ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ግንቦት 5፤ 2017 ነው። ደንቡን ያጸደቀው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች አስተዳደር አብይ ጉባኤ፤ ደንቡ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፏል።
የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ለማሻሻል በ2014 የወጣው አዋጅ፤ ለዳኞች እና ለጉባኤ ተሿሚዎች የስነ ምግባር እና የዲሲፒሊን ደንብ የማውጣት ስልጣን የሰጠው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ላለው አብይ ጉባኤ ነው። እስካሁን በስራ ላይ የቆየው የስነ ምግባር እና የዲሲፒሊን ደንብ የወጣው በ2007 ዓ.ም ነበር።
ይህ ደንብ “በርካታ ጉዳዮችን ያካተተ ቢሆንም ግልጽነት የጎደላቸው ጉዳዮችን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ” በአዲስ መልክ እንዲዘጋጅ መደረጉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። አዲሱ ደንብ እንዲዘጋጅ ከተደረገባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ በቀድሞው ደንብ ያልነበረ “የዳኞች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን” ማካተት በማስፈለጉ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
🔴 ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15924/
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ፖለቲካ
ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል።
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትላንት ማክሰኞ ግንቦት 5፤ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የምስረታውን የወርቅ ኢዮቤልዮ ባለፈው የካቲት ወር ያከበረው ህወሓት ከፓርቲነት የተሰረዘው፤ ቦርዱ ያዘዘውን “የእርምት እርምጃ” ተግባራዊ ባለማድረጉ መሆኑን ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፤ ባለፈው የካቲት ወር መጀመሪያ ለፓርቲው የሰጠው ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ቦርዱ ይህንን ቀነ ገደብ ባሳወቀበት መግለጫው፤ ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል “የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን” በሶስት ወራት ውስጥ እንዲያካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
ቦርዱ ህወሓትን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ ያዘዘው፤ “በአመጽ እና በህገ- ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ” የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንደሚዘገቡ የሚያስችለው አዋጅ (https://ethiopiainsider.com/2024/13159/)በሚያስቀምጠው ድንጋጌ መሰረት ነው። ይህ አዋጅ “በልዩ ሁኔታ” የሚመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያካሄዱ በምርጫ ቦርድ ሊታዘዙ እንደሚችሉ ይደነግጋል።
ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ በነሐሴ 2016 ዓ.ም ለህወሓት የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠው ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲው “የቦርዱ ታዛቢዎች” በተገኙበት በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር። ቦርዱ የቅደመ ጉባኤውን የዝግጅት ስራዎች ለመከታተል እንዲረዳው፤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማካሄዱ 21 ቀናት በፊት ለመስሪያ ቤቱ እንዲያስታውቅም ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15908/
የጤና ባለሙያዎችን የሥራ ማቆም አድማ ተከትሎ፣ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ባንዳንድ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ጸጥታ ኃይሎች መሠማራታቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሠምታለች። በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ የሙከጡሪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች፣ የክልሉ ፖሊስና ሚሊሺያ ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ መግባታቸውን ምንጮች አስረድተዋል። በፍቼ አጠቃላይ ሆስፒታልም፣ የጸጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴ መኖሩን ዋዜማ ተረድታለች። ምዕራብ ጉጂ ዞን ሃምበላ ወረዳ የአምስት ጤና ጣቢያዎች የጤና ባለሙያዎች፣ በጸጥታ ኃይሎች ጫና አድማ ማድረግ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ባንዳንድ ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች አድማ እንዳያደርጉ፣ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ማስፈራሪያ ሲፈጽሙ እንደነበርም ተነግሯል።
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን ጨምሮ በተለያዩ ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቋል። የጎንደርና ጎባ ሆስፒታሎች አስተዳደሮች፣ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሥራቸው ባስቸኳይ ካልተመለሱ ርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል። ማኅበሩ፣ በአድማው ወቅት የድንገተኛ፣ የጽኑ ሕሙማን፣ የጨቅላ ሕጻናትና የማዋለጃ ክፍሎች ብቻ አገልግሎት እንደሚሠጡ ገልጧል። የጤና ባለሙያዎች እየታሠሩና ዛቻ እየደረሰባቸው እንደሚገኙ የገለጠው ማኅበሩ፣ በእስር ላይ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ባስቸኳይና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል። የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ በቀጣዩ ዓመት ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ በጀት ለመመደብ ዝግጅቶች እየተደረጉ መኾኑን ትናንት ምሽት ለብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረው ነበር።
በተያያዘ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ መንግሥት የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዮናታን ዳኘውንና ከሥራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ የታሠሩ ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን ከእስር እንዲፈታ ጠይቋል። አምነስቲ፣ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ ነጻነትን እንዲያከበርና የጤና
በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል
– ስልክ እና ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ይዘው እንዳይመጡ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል
“በየትኛውም ሴክተር የሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ ተምሮ እንዳልተማረ በመሃይም ካድሬዎችና የቢሮ ኃላፊዎች መብቱ እየተረገጠ፤ እንዳይረጋጋ በመንግስት የታቀደ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየደረሰበት ይገኛል። የሰሞኑ የጤና ባለሙያዎችም ጥያቄ የሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ጥያቄ ነው፤ ከእንግዲህ መሃይም ሹመኞች እራት እንዲበሉ ሻማ ይዘን የምንቆምበት ወቅት አልፏል”- መምህራን
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/73e?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
አቶ ጌታቸው ረዳ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች “በዘረፋ እና በሰዎች ንግድ ላይ ተሳትፈዋል” ሲሉ ወነጀሉ
የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች “በወርቅ ቁፋሮ እና ንግድ”፣ “የመንግስት ገንዘብ በመዝረፍ” እንዲሁም ”በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፈዋል” ሲሉ ወነጀሉ።
አቶ ጌታቸው ረዳ ከፋና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በስም ጠቅሰው የወነጀሏቸው ሶስቱ አመራሮች፤ ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ፣ ብርጋዴር ጀነራል ሃይለስላሴ ግርማይ እና ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ ናቸው።
ትላንት ሰኞ ግንቦት 4፤ 2017 ምሽት በፋና ቴሌቪዥን የተላለፈው የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ክፍል አንድ ቃለ መጠይቅ፤ ስለ እርሳቸው የፖለቲካ ተሳትፎ አጀማመር፣ በትግራይ ክልል ስለ ተካሄደው ጦርነት፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች እና የትግራይ ሰራዊት አዛዦች “ፈጽመዋቸዋል” ስላሏቸው ወንጀሎች የዘረዘሩበት ነበር።
አቶ ጌታቸው ተፈጽመዋል ካሏቸው ወንጀሎች ቅድሚያውን የሰጡት ለወርቅ ንግድ ነው። በትግራይ ክልል በህገወጥ መንገድ የሚካሄደው የወርቅ ንግድ የተጀመረው፤ ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነትን ከተፈራረሙ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. በኋላ የሚመስለው በርካታ ሰው እንዳለ አቶ ጌታቸው በቃለ መጠይቃቸው ላይ አንስተዋል።
ሆኖም በክልሉ ህገወጥ የወርቅ ቁፋሮም ሆነ ንግድ የተጀመረው፤ የትግራይ ጦርነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ጭምር እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ይፋ አድርገዋል።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15872/
” እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል ” – አቶ ጌታቸው ረዳ
በትግራይ ያለው ህገወጥ የወርቅ ንግድ ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ የጀመረ ሳይሆን በጦርነቱ ጊዜም ሳይቀር ሲሰራ የነበረ እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ።
አቶ ጌታቸው፤ “ብዙ ሰው የወርቅ ንግድ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረምን በኃላ የጀመር ይመስለዋል” ያሉ ሲሆን ግን ጦርነቱም እየተካሄደ ንግዱ ነበር ብለዋል።

“እኔ የማምንበትን ትግል ነው ያካሄድኩት ብዬ አምናለሁ በዛ በማምንበት ትግል ውስጥ የትግራይን ህዝብ አጀንዳ ይዘው የታገሉ ብዙ የጦር መኮንኖች አሉ ለሰሩት ስራ ያለኝ ክብር በፍጹም አይቀንስም ግን ደግሞ ገና ገና ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይበላ በነበረበት ወቅት ሳይቀር ምሽግ ለመቆፈር ብለን የወሰድነው ኤክስካቫተር ወርቅ ለመልቀም ይጠቀሙበት የነበሩ አዛዦችም ነበሩ” ሲሉ አጋልጠዋል።
“ሲዋሹ በጣም ነው የሚገርመኝ” ያሉት አቶ ጌታቸው “እኔ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል እስካሁን የታገስኩትም ይበቃኛል” ብለዋል።
አቶ ጌታቸው “የኤርትራን ሰራዊት እናፍርሰው” በሚል አላማ ዘመቻ የጀመረና ዘመቻውን የሚመራው አመራር ሰዎችን እያፈነ ገንዘብ ሲበስብ እንደነበር ተናግረዋል።
“ሰው ሲሸጡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፤ ኤርትራዊ መሸጥ ‘ ንብረት ‘ ነው የሚባለው ወርዷል ወይ ? ይባላል፤ ታፍንና ይዘህ 27 ወጣት አንድ ቤት ትዘጋና ቤተሰቦች አላቸው ውጭ ሀገር የሚባሉት ሰዎች አካውንት እየተጠየቀ እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 4000 ዶላር እንዲያስገባ ተደርጎ (20 ሰው ካፈንክ 80 ሺህ ዶላር ታስገባለህ) በዚህ የውጭ አካውንት ከፍተው በሺዎች የሚቆጠሩ
በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃኪሞች የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።
በአዲስ አበባ በሆስፒታሎች ዙሪያ መረጃ ቲቪ ባደረገው አሰሳ ዛሬ ክፍት የሆኑት የህክምና ክፍሎች ፤ ድንገተኛ ክፍል፣ ፅኑ ህሙማን ክፍል፣ የጨቅላ ህፃናት ክፍል፣ የማዋለጃ ክፍል ብቻ ናቸዉ። ሌሎች የሕክምና ክፍሎች አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ተረጋግጧል።
የአብይ አገዛዝ ለሃኪሞች ጥያቄ መልስ ሰጥቶ እና የታሰሩትን ሃኪሞች ከፈታ አድማው ሊቆም ይችላል ተብሏል። አድማውን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲቀላቀሉት ጥሪ እየተደረገ ይገኛል። ሲል በሆስፒታሎቹ የተዘዋወረው የመረጃ ቲቪ ሪፖርተር አስታውቋል።

የአድማው አስተባባሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት የመንግስት ሚዲያዎች እንደተለመደው አንዳንድ አስገድደው ወደሚያሰሯቸው ተቋማት በመሄድ ምንም የስራ ማቆም እንደሌለ እና እንደወትሮው አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ሊዘግቡ እና ፕሮፖጋንዳ ሊሰሩ ይችላሉ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት ምንም ግራ መጋባት እንዳይኖር። ዛሬ በተለያዩ ምክንያቶች ማቆም ያልቻላቹ ከከሰዓት ወይም ከነገ ጠዋት ጀምሮ አድማውን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።በ ER, ICU, LW እየሰራቹ ያላቹ ጤና ባለሞያዎች Cold Case እንድታዩ ለማስገደድ ከሞከሩ ወይም የታጠቀ ሀይል የስራ ቦታቹ ካለ እንዲሄዱላቹ አሳውቁ ካልሆነ ጥላቹ ወደ ቤታችሁ ሂዱ። በወታደር ተገዶ የሚሰራ ህክምና የለም። ብለዋል ።
የአድማው አስተባባሪዎች አክለውም በዛሬው ቀን የሚጠራ ማንኛውም ስብሰባ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን በስብሰባው ባለመሳተፍ የራሳችሁን ግዴታ እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን ፤ Stay Home , Stay Safe ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። #MerejaTv
አምነስቲ ኢንተናሽናል የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ከእስር እንዲፈታ ጠየቀ
(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮናታን ዳኘው ከእስር እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ማምሻውን ጠየቀ።
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/3e4?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ኤኮኖሚ

የፎቶው ባለመብት, sm
የምስሉ መግለጫ, ዶ/ር በርናባስ ሳሙኤል፣ ዮናታን ዳኛው፣ ዶ/ር ሀብታሙ ጌታቸው እና ዶ/ር መላኩ አልማው
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው እንዲሁም ሦስት የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተሮች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በአማራ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በቀናት ልዩነት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር አምስት ደርሷል። በአዲስ አበባ ከተማ ሌሎች አምስት የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከሁለት ቀን እስር በኋላ ተለቅቀዋል።
የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ ድጋፉን የገለጸው የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዮናታን የታሰሩት ትናንት እሁድ ግንቦት 3/2017 ዓ.ም. እንደሆነ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መለስ ባታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በ2015 ዓ.ም. የተመሠረተውን ማኅበር የሚመሩት አቶ ዮናታን፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን በሚገኘው ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ መሆናቸውን አቶ መለሰ ገልጸዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደሚናገሩት አቶ ዮናታን እሁድ ከሰዓት የተያዙት ከመኖሪያ ቤታቸው ነው። “ከመያዙ በፊት ከትናንት ወዲያ [ቅዳሜ] የሚሠራበት ሆስፒታል አካባቢ እና በሚኖርበት ሰፈር [በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ] ለምርመራ እንደሚፈለግ ደውለው እንዳስታወቁት ነግሮኝ ነበር” የሚሉት አቶ መለስ፤ ይህ ከሆነ ከአንድ ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
ከማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጋር አጭር የስልክ ንግግር ማድረጋቸውን የሚጠቅሱት አቶ መለስ፤ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝ እና “ብዙ ችግር እንዳልደረሰበበት” ከራሱ መስማታቸውን ገልጸዋል። ይሁንና የስልክ ጥሪው በመቋረጡ ምክንያት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የታሰሩበትን ምክንያትም ሆነ ስለተደረገባቸው ምርመራ በዝርዝር መነጋገር እንዳልቻሉ
“. . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል” እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
የምርመራ ዘገባ ጫንጮ ላይ የከተሙ ‘ሪጴ ሎላ’ የተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት አነጋጋሪ ድርጊት ላይ ምርመራ አርገናል
(መሠረት ሚድያ)- ከአዲስ አበባ 40 ኪ/ሜ ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የጫንጮ ከተማ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰላም ርቋታል። ተስማሚ አየር እና መልካም ገፀ ምድር ያላት የኦሮሚያ ክልሏ ጫንጮ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) እና በመንግስት ሀይሎች መካከል በሚደረግ ግጭት ምክንያት ፀጥታዋ ደፍርሷል።
ታድያ በከተማዋ ተወልደው ያደጉትም ይሆን ከሌላ ቦታ ወደ ከተማዋ ሄደው የሚኖሩ ነዋሪዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ‘ሪጴ ሎላ’ በተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት አበሳቸውን እያዩ እንደሆነ መሠረት ሚድያ ባደረገው ክትትል ደርሶበታል።
“የምኖረውም ተወልጄ ያደኩትም እዚሁ ጫንጮ ከተማ ነው፣ ለስራ የተሰማራሁትም በሞባይል ሽያጭ ላይ ነው” የሚለው አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከተማውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ እነዚህ ‘ሪጲ ሎላ’ የተባሉት የመንግስት ሀይሎች የጫንጮን ነዋሪ እያሰቃዩ እንደሆነ ይናገራል።
“እኔ ላይ የደረሰውን ለመናገር፣ አንድ ቀን ሶስት ሆነው መጡና ብር አምጣ አሉኝ። ካሽ የለኝም ስላቸው ‘ካዝና ውጥ ይጠፋል? እናየዋለን!’ ሲሉኝና ሲቆጡ የእቁብ ብር ነው ስል አንዱ በጥፊ መታኝና 3,000 አርግ አለኝ፣ ሰጠኋቸው። የሆነውን ለጓደኞቼ ስናገር እኔንም፣ እኔንም 4,000 ብር ምናምን ወሰዱብን አሉኝ” በማለት ሁኔታውን አስረድቷል።
ይህን ተከትሎ የጫንጮ ከተማ የፀጥታ ሀላፊ ጋር ሄደው ሲያመለክቱ “ከአቅማችን በለይ ነው፣ የኛን ፖሊስ ራሱ ደበደቡብን፣ ዝም በሉ በቃ” ብሎ ምላሽ እንደሰጣቸው አክሎ
በባህር ዳር አየር ማረፊያ ከሰሞኑ የተጧጧፈው የመንገደኞች የጉዞ ትኬት ዝርፊያ እና ሽያጭ
(መሠረት ሚድያ)- በአውቶቡስ መናኸርያዎች፣ በባቡር ጣብያዎች ወይም በታክሲ ተራዎች አካባቢ ዝርፊያ ሲፈፀም ሰምተው ይሆናል፣ ዛሬ ግን የምናስነብባችሁ በአየር ማረፊያ እየተስተዋለ ያለ የአውሮፕላን ትኬት ስርቆትን ነው።
https://tinyurl.com/46t9u5ky
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ ህይወት በምን ምክንያት አለፈ?
(መሠረት ሚድያ)- የህግ መምህር የነበረው አቶ ታዘባቸው ሙላት ያስተምርበት ከነበረው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 29/2017 ዓ/ም ቀን ተጨማሪ ኮርስ ለመስጠት ነበር ወደ ዩኒቨርሲቲው ሌላኛው ካምፓስ ወደሆነው ቡሬ ካምፓስ ከሰዓት ገደማ ያቀናው።
https://tinyurl.com/w3y7c999
ዘንድሮ 47 ቢሊዮን ብር የከሰረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ትርፋማነት እንደሚሸጋገር የኩባንያው ኃላፊዎች ገለጹ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ኪሳራ ቢያጋጥመውም፤ በሁለት ዓመታት ውስጥ ወደ ትርፋማነት ይሸጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የእናት ኩባንያው ኃላፊዎች ተናገሩ። መቀመጫውን በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ያደረገው ሳፋሪኮም ኩባንያ፤ እስከ መጋቢት ወር ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካገኘው 3 ቢሊዮን ዶላር የአገልግሎት ገቢ 10 በመቶ ገደማ የሚሆነው የኢትዮጵያ ገበያ ድርሻ እንደሆነ አስታውቋል።
ኩባንያው የሚመራበት በጀት ዓመት መጠናቀቁን በማስመልከት ባለፈው ሐሙስ ይፋ የተደረገ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ባለፈው ዓመት 2.7 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን ዘንድሮ 7.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ270 ፐርሰንት እድገት ቢያሳይም፤ 47 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኪሳራ እንደገጠመው ዋና ስራ አስፈጻሚው ዊም ቫንሔለንፑት ገልጸዋል።
“ይህ ኪሳራ በአብዛኛው ኩባንያው በሚገኝበት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ ከምንጠብቀው ጋር የተስማማ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በሐምሌ 2016 ዓ.ም. ተግባራዊ ያደረገው የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት ለውጥ በኩባንያው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ጠቁመዋል።
የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት ለውጡ፤ በአጭር እና መካከለኛ ጊዜ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመቋቋም “እርምጃዎች መወሰዳቸውን” የሳፋሪኮም ኃላፊዎች አብራርተዋል። እርምጃው በውጭ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተቀጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን መቀነስን የካተተ ነው።
🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15849/

በኢትዮጵያ ኢመደበኛ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑ፣ መልካም አስተዳደር ለአፍሪካ ቀንድ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተነገረ፡፡
‹‹የከተሞች መደበኛ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ገጽታዎችና የአስተዳደር ቅኝት›› በሚል መሪቃል በተዘጋጀው መድረክ፣ ‹‹የከተሞች መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ገጽታና ባህሪያት በኢትዮጵያ›› በሚል ሐሳብ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት መካነ ጥናት ኮሌጅ አባል ቻላቸው ጌታሁን (ዶ/ር)፣ ‹‹58 በመቶ የዓለማችንን የሥራ ዕድል የሚፈጥረው መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ነው፤›› ብለዋል።
ለታዳጊ አገሮች 84 በመቶው የሥራ ዕድል የሚፈጠረው ከዚሁ ዘርፍ እንደሆነ በማስረዳት፣ ሴቶችና ሕፃናት ደግሞ መደበኛ ባለሆነ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው ገልጸው፣ ያገቡ ወይም አግብተው የፈቱ ሰዎች ደግሞ በዚህ ዘርፍ በአብዛኛው ሲሳተፉ ይስተዋላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ከገጠር ወደ ከተማ ለሚፈልሰው የሰው ኃይል የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉም አክለዋል። የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ አጠቃላይ ገቢ አንድ ሦስተኛና ከዚያ በላይ የሚሆነው የሚመነጨው ከዚሁ ዘርፍ መሆኑንም አመላክተዋል።
እ.ኤ.አ ከ1992 እስከ 2000 ድረስ ያሉ የጥናት ውጤቶች በአማካይ የሚያመላክቱት ይኼን ነው ብለዋል። ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮጵያ እያደገ መምጣቱ በጥናቱ ተጠቁሟል። በከፍተኛ ደረጃ የሚታየውን የከተማ ሕዝብ ቁጥር ዕድገትና የሥራ ዕድል መንግሥት መር የሆነው ኢኮኖሚ መሸከም እንዳልቻለም፣ በዚህም ዜጎች በቀጥታ ወደ መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ ዘርፍ እንደሚገቡ ገልጸዋል
‹‹የከተሞች መደበኛ ያልሆነ ኢኮኖሚ አስተዳደር በኢትዮጵያ›› በሚል ሐሳብ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናት ማዕከል
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ኤኮኖሚ
በዘጠኝ ወራት ከ37 ሺሕ በላይ ሠራተኞች መልቀቃቸው ተነግሯል
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩ ጦርነት ሸሽተው የወጡ ባለሀብቶች፣ ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ እያቀረቡ መሆናቸውን፣ የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።
ኮርፖሬሽኑ ይህንን የገለጸው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ ሲያቀርብ ነው፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከአገር ሸሽተው የሄዱ ባለሀብቶችን ለረዥም ጊዜያት በኢንተርኔትና በአካል በመገናኘት ኩባንያዎቻቸው ተመልሰው ወደ ልማት እንዲገቡ ጥረቶች ቢደረጉም ፍላጎት አለማሳየታቸውን፣ በኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡
‹‹ኩባንያዎቹ ወደ ሌላ አገር ሄደው ለማልማት ማሽናቸውን ከአገር ይዘው ለመውጣት ጥያቄ በማቅረባቸው፣ እኛ እንደ መፍትሔ እያቀረብንላቸው ያለው አገር ውስጥ የገባና በአጠቃላይ አገራዊ ምርት የተመዘገቡ ማሽኖችን ወደ ሌላ አገር ከሚወስዱ፣ በአገር ውስጥ ወደ ሌላ አካባቢ በማዘዋወር ለማሠራት ጥያቄ አቅርበን እየጠበቅን፤›› ነው ብለዋል።
ነገር ግን ወ/ሮ ሶስና ጌታሁን የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል፣ መቀሌ የነበሩ ኢንቨስተሮች እዚያው መቆየት ካልፈለጉ ቦሌ ለሚ ወይም አዳማ እንዲያለሙ ለማድረግ እየተሠራ ነው የሚለው ምላሽ ትክክል አለመሆኑን፣ ኢንቨስተሮች በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምን እንደጎደላቸው መጠየቅና ችግሩን መፍታት እንጂ ከአንድ አካባቢ አስነስቶ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ መሞከር ትክክል አይደለም ብለዋል። አክለውም ያልተመቹ ጉዳዮች ካሉ ኢንቨስተሮቹ ተጠይቀው መፍትሔ በማፈላለግ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እዚያው ማቆየት እንጂ፣ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ማዘዋወር አግባብ አይደለም በማለት አሳስበዋል፡፡
ይህ በዚህ
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ፖለቲካ
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የተሰጠ መግለጫ – ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም.
Fano forces in the Amhara region of Ethiopia have established a central command – Statement, May 9, 2025
https://x.com/merejatv/status/1921085243424899483
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ፖለቲካ
ሩሲያ የናዚ ጀርመን በሁለተኛው የአለም ጦርነት በይፋ የተሸነፈበትን 80ኛ አመት የድል በዓሏን አክብራለች።
በድል በዓሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የቻይናውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።
በተጨማሪ የቡርኪናፋሶው መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ በፕሬዚዳንት ፑቲን ግብዣ የግል አውሮፕላን ከሞስኮ ተልኮለት በፕሮግራሙ እንዲሳተፍ ተደርጓል።
መሪዎቹ ትናንት በክሬምሊን የእራት ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን ዛሬ በዓሉ በአደባባይ በወታደራዊ ትርዒቶች ተከብሯል።
የዛሬው ወታደራዊ ሰልፍ ሞስኮ ወደ ዩክሬን ጦሯን ካዘመተች በኋላ ትልቁ ነው ሲባል ከ10 አመታት በኋላ የበርካታ ሃገራት መሪዎች የተገኙበትም ነው ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ባደረጉት ንግግርም በአሁኑ ወቅት በዩክሬን እየተፋለሙ ያሉ የጦር ሰራዊታቸውን አሞግሰዋል።
በወታደራዊ ሰልፉ ላይ ከ11,500 በላይ ወታደሮቼ እና ከ180 በላይ ወታደራዊ መኪኖች ተካፋይ ሆነዋል።
የሩሲያ የአየር ኃይል ቡድንም የአየር ላይ ትርኢቶችንም አሳይተዋል።
የፑቲን የውጪ ጉዳይ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ይህንን የጋራ በዓላችንን በማስመልከት ፕሬዚዳንት ፑቲን እና ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሃሳብ መለዋወጣቸውን እና የእንኳን አደረሰህ መልዕክት እንደተለዋወጡ ለሚዲያዎች ገልፀዋል።
ሶቪየት ህብረት በሁለተኛው የአለም ጦርነት ንቁ ተሳታፊ የነበረች ሲሆን ከ21 ሚሊየን ሰዎች በላይም በጦርነቱ አጥታለች።
የናዚ ጀርመን በይፋ በሁለተኛው የአለም ጦርነት የተሸነፈበትን ምክንያት በማድረግ ሩሲያ ቀኑን እንደ ድል በዓል የምታከብር ሲሆን ዘንድሮ 80ኛ አመቱን እያከበረች ትገኛለች።
Source: AP , Sputnik
መንግሥት፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደየአገልግሎታቸው ዓይነት “ወጥ ቀለም” እና መለያ ኮድ እንዲኖራቸው እቅድ መያዙን ዋዜማ ሠምታለች። የተሽከርካሪዎች ቀለምና መለያ ኮድ ከከተማ ከተማ የተለያየ ይሆናል ተብሏል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችም፣ ወጥ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ ዋዜማ ተረድታለች። የትራንስፖርት ሚንስትር ዓለሙ ስሜ፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ ለማድረግ እንደተወሰነ ሰሞኑን ባንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸውንም ዋዜማ ተረድታለች።
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ፖለቲካ
Posted in
News,
ኢትዮጵያ,
ፖለቲካ
በአማራ ክልል በመካለከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት የክልሉን ነዋሪ ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጓል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰላማዊ ሰዎችም በግጭቱ የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን የመብት ተሟጋቾች የሚያወጧቸው መረጃዎች ያሳያሉ።ያም ሆኖ ይህንን ሰቆቃ ለማስቆም በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የንግግር ፍንጭ አልታየም።
ኢትዮጵያን የሚመራዉ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳርን ከማስፋት ኤኮኖሚን ከማሳደግ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር ድጋፍም ተቃዉሞም እየተሰማበት ዛሬ ደርሷል። ከ 15 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች እንዳሉት የሚገልፀዉ ብልፅግና መነሻና መዳረሻ ርዕዮተ ዓለሙ እንዴት ይገለፃል? ስኬት እና ድክመቱስ እንዴት ይለካል? አስተያየቶን ይፃፉልን።
በተለያዩ ጊዜያት ከኦነግ ጋር የተደረጉ ድርድሮች ፤ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ጋር የተደረገ ድርድር እና ስምምነት ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፣ ከህወሓት ጋር እንዲሁም በቅርቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አንድ ክንፍ ጋር የተደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ተጠቃሾች ናቸው ።
የመተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በተለያዩ ድረ ገፆች የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2024 ዓ/ም ተጠቃሚዎች አውርደው የተጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ናቸው። በቻይናው ኩባንያ ባትዳንስ የተሰራው እና በአሜሪካ የመዘጋት አደጋ የተጋረጠበት ቲክቶክ /TikTok/ በ2024 በብዛት የተጫነ መተግበሪያ ሆኗል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ ተሽከርካሪውን ከባንክ ብድር ወስዶ መግዛቱን ጠቅሶ በቤንዚን እጥረቱ ምክንያት ሰርቶ ብድር መመለስ እንዳልቻለ ገልጧል፣ አንዴ ነዳጅ ከቀዳ ሌላ ጊዜ ለመቅዳት ሳምንት እንደሚጥብቅ አመልክቷል፣ ያን ላለማድረግ ደግሞ በውድ ዋጋ ከህገወጥ ነጋዲዎች ቤንዚን ገዝቶ እንደሚሰራ ነው ያስረዳው።
የትናንትናውን ጨምሮ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ በተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ሳቢያ ከእልቅልፋችን እየቀሰቀሰን ሰላም አሳጥቶናል በማለት የሚያማርሩ የህብረተሰብ አካላት ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡