አፋብን ያቀረበውን የምህረት አዋጅ የተቀበሉ 14 የሚኒሻና አድማብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ!

አፋብን ያቀረበውን የምህረት አዋጅ የተቀበሉ 14 የሚኒሻና አድማብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ባወጣው የምህረት አዋጅ መሰረት የብልፅግና አገዛዝ ስልጣን ማስጠበቂያ የነበሩ 14 የሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት በበላይ ዘለቀ ዕዝ ሜ/ጀኔራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክ/ጦር ስር የአንዳቤት ብርጌድን መቀላቀላቸውን ክፍለጦሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

የምህረት አዋጅን የተቀበሉት የአገዛዙ ወታደሮች “በተሳሳተ መንገድ ከጨፍጫፊው ስርዓት ጋር ተሰልፈን ሕዝባችንን ስንገድል፣ ስናስገድል እና ስናሰቃይ በመቆየታችን ተፀፅተናል” ያሉ ሲሆን፡ አሁን ላይ ግን ለህዝባችን ውድ ሕይወታችንን በመገበር ጭምር ለመካስ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

በተጨማሪም ወታደሮቹ የምህረት አዋጁን በማቅረብ ሕይወታችን ለታደገላቸው ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የምህረት አዋጁን የተቀበሉ ታጣቂዎች ስም ዝርዝር፦
1.በላይ ባንቴ ➞ ሚኒሻ
2.ሃብታሙ ካሴ ➞ሚኒሻ
3.ቢሆነኝ ተረፈ ➞ሚኒሻ
4.መንግስቱ አዳምጤ ➞አድማ ብተና
5.ተመስገን ተረፈ ➞ሚኒሻ
6 ሸጋው ማለደ ➞ሚኒሻ
7.ስማቸው ውበት➞ሚኒሻ
8.ተመስገን ሉሌ ➞ሚኒሻ
9.እንየው አስፌ ➞ሚኒሻ
10.ጌጡ ገብሩ ➞ሚኒሻ
11.አብራራው አማረ ➞አድማ ብተና
12.አብቧል ውዱ ➞አድማ ብተና
13.አዳምጤ እንደሻው ➞ሚኒሻ
14.ቸርነት አዳሙ ➞ሚኒሻ ናቸው።

በጉና ክፍለጦር ስር የአንዳቤት ብርጌድን የተቀላቀሉት የሚኒሻና የአድማ ብተና አባላቱ፡ በክፍለ ጦሩና በአንዳቤት ብርጌድ አመራሮች እንዲሁም በአንዳቤት ወረዳ የፋኖ ጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር አካላት ተከታታይ የሆነ  የፖለቲካ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሰፊው ከተሰጣቸው በኋላ የተቋሙን ፎረም በመሙላት የብርጌዱን ሰራዊት በይፋ እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል ሲል ጉና ክፍለ ጦር በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ጨምሮ ገልጿል።