ብሔራዊ ባንክ በፈረንጆቹ 2024 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደገጠመው በገለልተኛ ኦዲት መረጋገጡን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ባንኩ ኦዲት የተደረገው፣ መንግሥትና ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት በደረሱበት ስምምነት መሠረት ነው። ባንኩ ወርቅ የገዛበትና የሸጠበት ዋጋ ልዩነት መስፋቱ፣ ባንኩ ለመንግሥት አበድሮ ያልተመለሰለት ገንዘብ፣ የብር የመግዛት እቅም መዳከምና ከዓለማቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ያለበት ዕዳ በውጭ ምንዛሬ የሚከፈል መኾኑ ለኪሳራው አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል። ባንኩ ለመንግሥት ባንኮች 134 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር፣ ለግል ባንኮች 13 ቢሊዮን ብር እና ለመንግሥት 687 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር አበድሮ ገና አልተመለሰለትም ተብሏል