Home › View all posts by DW Amharic
Blog Archives
በተለያዩ ጊዜያት ከኦነግ ጋር የተደረጉ ድርድሮች ፤ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ጋር የተደረገ ድርድር እና ስምምነት ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፣ ከህወሓት ጋር እንዲሁም በቅርቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አንድ ክንፍ ጋር የተደረጉ ድርድሮች እና ስምምነቶች ተጠቃሾች ናቸው ።
ፕሬዝዳንት ተመራጩ ዶናልድ ትራምፕ ካናዳን፣ ግሪንላንድንና የፓናማ ካናልን ወደአሜሪካ ግዛትነት የመጠቅለልን ሃሳብና ዛቻን እያንሸራሸሩ ነው። ይሄው ሃሳባቸው ከየሃገራቱ ተቃውሞና ግራ መጋባትን አስተናግዷል። የፖለቲካ ተንታኞች ይሄንኑ ቃላቸውን እንደ ጸብ አጫሪነት አልያም እንደ መደራደርያ መሳርያነት እየተጠቀሙበት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተፎካካሪያቸው ከማላ ሐሪስን በሰፊ የድምፅ ልዩነት ካሸነፉ በኋላ ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን ሰጥተዋል ። በፕሬዚደንትነት ቃለ መሐላ ከመፈጸማቸው አንድ ወር ግድም ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ በዋናነት ምን አሉ? ቃለ-መጠይቅ
ኢትዮጵያን የሚመራዉ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳርን ከማስፋት ኤኮኖሚን ከማሳደግ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር ድጋፍም ተቃዉሞም እየተሰማበት ዛሬ ደርሷል። ከ 15 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች እንዳሉት የሚገልፀዉ ብልፅግና መነሻና መዳረሻ ርዕዮተ ዓለሙ እንዴት ይገለፃል? ስኬት እና ድክመቱስ እንዴት ይለካል? አስተያየቶን ይፃፉልን።
በአማራ ክልል በመካለከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት የክልሉን ነዋሪ ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጓል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰላማዊ ሰዎችም በግጭቱ የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን የመብት ተሟጋቾች የሚያወጧቸው መረጃዎች ያሳያሉ።ያም ሆኖ ይህንን ሰቆቃ ለማስቆም በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የንግግር ፍንጭ አልታየም።
በመጪው ጥር ከኃላፊነታቸው የሚሰናበሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር አንቶኒ ብሊንከን በዩክሬን ጉዳይ ከአውሮጳ መሪዎች ጋር ዛሬ ብራስልስ አስቸኳይ ውይይት አድርገዋል ። አንቶኒ ብሊንከን የአውሮጳ መሪዎችን እንዲህ በጥድፊያ ያነጋገሩት በዘንድሮ የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚደንትነት መንበረ-ሥልጣኑን ከመረከባቸው አስቀድሞ ነው ።
የመተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በተለያዩ ድረ ገፆች የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2024 ዓ/ም ተጠቃሚዎች አውርደው የተጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ናቸው። በቻይናው ኩባንያ ባትዳንስ የተሰራው እና በአሜሪካ የመዘጋት አደጋ የተጋረጠበት ቲክቶክ /TikTok/ በ2024 በብዛት የተጫነ መተግበሪያ ሆኗል።
ተመራጭ ፕሬዝዳንት ትራም እራሳቸውም ሰኞ እለት ለአንድ ሜዲያ በሰጡት አስተያየት ፕሬዝዳንት ፑቲንም ከሳቸው ጋር መገናኛኘቱን እንደሚፈለጉትና ከሰኞው በዓለ ሹመት በሗላ እንደሚገናኙ ያላቸው እመነት በመግለጽ ይህ ሁለቱንም በተለይም ዩክሬንን እያወድመ ያለ ጦርነት ባስችኳይ መቆም እንድላበት እንደሚያምኑ አስታውቀዋል።
የውጭ ዜጎች እድሉን ካገኙና ከተጣጣሩ በጀርመን ስኬታማ መሆን መቻላቸው ማሳያ የሆኑት አቶ ሳምሶን በአሁኑ ጊዜ ስደተኞች በምርጫ ዘመቻ ወቅት ስማቸው መጉደፉና ስብእናቸውም ዝቅ ተድርጎ መቅረቡ በጣም ይሰማቸዋል።ስደተኛን የሚጠሉት ቀኝ አክራሪዎች ጀርመን ውስጥ እየተጠናከሩ መምጣታቸው ከሚያሳስባቸው አንዱ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር ሳምሶን በቀለ ናቸው።
ኢትዮጵያውያን በቤት እና በመሬት ግብር የሚከፍሉበት የንብረት ታክስ በተቃዋሚዎች ትችት ቢገጥመውም ጸድቋል። ተቃዋሚዎች አዲሱ ታክስ በሸማቾች ላይ ጫና እንደሚፈጥር አስጠንቅቀዋል። መንግሥት “ፍትኃዊ የሀብት ክፍፍል የሚያሰፍን” ያለው የንብረት ታክስ በክልሎች ይሰበሰባል። ለመሆኑ በንብረት ታክስ ማን ስንት ይከፍላል? የማይከፍሉትስ እነ ማን ናቸው?
አቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል ለወጣት ኢትዮጵያውያን የተስፋይቱ ምድር ተደርጋ በምትታየው በደቡብ አፍሪቃ በደላሎች የሚፈጽምባቸው በደል መክፋቱን ገልጸዋል።። በሕገ ወጥ መንገድ ደቡብ አፍሪቃ ከደረሱ በኋላ ለእገታ የሚዳረጉት አስቀድሞ ከደላሎች ጋር የተስማሙበትን ውል በጊዜው አላሟሉም የሚባሉት ኢትዮፕያውያን መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ ተሽከርካሪውን ከባንክ ብድር ወስዶ መግዛቱን ጠቅሶ በቤንዚን እጥረቱ ምክንያት ሰርቶ ብድር መመለስ እንዳልቻለ ገልጧል፣ አንዴ ነዳጅ ከቀዳ ሌላ ጊዜ ለመቅዳት ሳምንት እንደሚጥብቅ አመልክቷል፣ ያን ላለማድረግ ደግሞ በውድ ዋጋ ከህገወጥ ነጋዲዎች ቤንዚን ገዝቶ እንደሚሰራ ነው ያስረዳው።
የትናንትናውን ጨምሮ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ በተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ሳቢያ ከእልቅልፋችን እየቀሰቀሰን ሰላም አሳጥቶናል በማለት የሚያማርሩ የህብረተሰብ አካላት ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡