Blog Archives

ኢትዮጵያ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር አበዳሪዎቿ ጋር መደበኛ የእዳ ሽግሽግ ድርድር ጀመረች

የአዲስ አበባ ከተማ ከፊል ገጽታ የፎቶው ባለመብት, Getty Images ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በፊት ለሸጠችው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ከዓለም አቀፍ የቦንድ ገዢዎች ጋር የእዳ ሽግሽግ እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው መደበኛ ንግግር መጀመሯን ሮይተርስ የዜና ወኪል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘገበ። ሮይተርስ ቀደም ብሎ በብሉምበርግ የወጣውን ዘገባ በማረጋገጥ ከዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ጋር በእዳ ሽግሽግ ዙሪያ በፓሪስ ፈረንሳይ ድርድር መጀመሩን ዘግቧል። አንድ የገንዘብ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ዝርዝር መረጃ ሳይጠቅሱ የመንግሥት ልዑክ ወደ ፓሪስ ማቅናቱን አረጋግጠዋል። “ከቦንድ አበዳሪዎች ጋር የተያዙ አንዳንድ ስብሰባዎች ነበሩ” ሲሉ ለሮይተርስ የተናገሩት ምንጩ የስብስበዎቹ ውጤት መጨረሻ ላይ የሚገለፅ እንደሆነ በመጠቆም ስምምነነት ላይ ግን እንዳልተደረሰ ገልፀዋል። አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው ወዲያ ምላሽ አልሰጡም። የቦንድ አበዳሪዎች ኮሚቴ ተወካዮችም እንዲሁ ምላሽ አልሰጡም። “ለመሠረተ ልማት ግንባታዎች” እንደሚውል የተነገረለት የቦንድ ሽያጭ በ10 ዓመታት ተመልሶ የሚከፈል እና የ6.625 በመቶ ወለድ ያለው መሆኑ በወቅቱ ተነግሮ ነበር። ኢትዮጵያ ያወጣችውን ቦንድ 50 በመቶ የአሜሪካ ባለሃብቶች፣ 35 በመቶ የእንግሊዝ ባለሀብቶች፣ 14 በመቶ የአውሮፓ አገራት ባለሃብቶች እና ሌሎች ገዝተዋል፡፡ በውሉ መሰረት ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም. የቦንድ ብዱሩን ክፍያ መክፈል ያልቻለች ሲሆን፤ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ በኩል የእዳ ሽግሽግ እንዲደረግ መርጣለች። በዚህ አካሄድ የሁለትዮሽ ብድር፣ ዩሮ ቦንድ እና ሌሎች የንግድ ብድሮች አንድ አይነት አመላለስ አላቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከቦንድ ገዥዎች ጋር የእዳ ሽግግር ማድረጊያ መንገዶችን ለመለየት ለወራት ንግግር ሲያደርግ ቆይቷል። በቦንድ ገዥዎች እና በተበዳሪ መንግሥታት መካከል
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ጀርመን, ፖለቲካ

ሆሮ ጉዱሩ :- በአቤዶንጎሮ ወረዳ የታጣቂዎቸ ጥቃት

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ የታጠቂዎች እንቅስቃሴ እና ጥቃት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡ በገጠራማ አካባቢዎች ላይ የነበረው የታጣቂዎች ጥቃት ወደ ከተማ ተዛምተው ትናንት ምሽት ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ታጣቂዎች መግባታቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደጫካ ሸሽተው እንደነበር ተገለፀ፡፡ DW Amharic ፡ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤዶንጎሮ ወረዳ የታጠቂዎች ጥቃት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡ በገጠራማ አካባቢዎች ላይ ይስተዋል የነበረዉ የታጣቂዎች ጥቃት ወደ ከተማ ተዛምቶ  ትናንት ምሽት ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ታጣቂዎች መግባታቸው እና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደጫካ ሸሽተው እንደነበር ዶቼ ቬሌ ያነጋገራቸዉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ከባለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በወረዳው የሚስተዋለው የታጣቂዎች ጥቃት የነዋሪውን የዕለት ተዕለት እንቅስቅስቃሴ እያወከ ነዉ፡፡ የወረዳው አስተዳደር በበኩሉ ትናንት ምሽት ጽንፈኛ ሐይሎች ያላቸው ታጣቂዎቸ በወረዳው ከተማ ተኩስ ከፍቶ እንደነበር አረጋግጧል። ታጣቂዎቹ ጸረ ሽምቅ ተብሎ በሚጠሩ የጸጥታ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲባረሩ መደረጋቸዉንም  አመልክተዋል፡፡ ከወረዳው ዋና ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጫካ ሸሽቶ ቆይተዋል ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር ዋና ከተማ ሻምቡ በ 47 ኪሜ ገደማ ርቀት ላይ በሚትገኘው የአቤዶንሮ ወረዳ ትናንት ምሽት ታጣቂዎች ወደ ወረዳው መግባታቸውን ተከትሎ ከ 3 ሺ በላይ ነዋሪዎች ወደ ጫካ መሸሻቸውን ያነጋርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል። በወረዳው መሰል ጥቃቶች የተደጋገሙ ሲሆን ትናንት ምሽት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኃይል ቱሉ ዋዩ ወደ ተባለው የወረዳው ዋና ከተማ መግባታቸውን በአካባቢው ከሚገኙ ጸረ ሽምቅ ከተባሉ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, ኢትዮጵያ, ጀርመን, ፖለቲካ

የኑርንበርጉ ነዋሪ የኤሌክትሪካል ኢንጅነር ሳምሶን በቀለ ስኬት

የውጭ ዜጎች እድሉን ካገኙና ከተጣጣሩ በጀርመን ስኬታማ መሆን መቻላቸው ማሳያ የሆኑት አቶ ሳምሶን በአሁኑ ጊዜ ስደተኞች በምርጫ ዘመቻ ወቅት ስማቸው መጉደፉና ስብእናቸውም ዝቅ ተድርጎ መቅረቡ በጣም ይሰማቸዋል።ስደተኛን የሚጠሉት ቀኝ አክራሪዎች ጀርመን ውስጥ እየተጠናከሩ መምጣታቸው ከሚያሳስባቸው አንዱ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር ሳምሶን በቀለ ናቸው።
Posted in ጀርመን