Blog Archives

ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው።

ጦርነቱ ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ይሁን ? 🇮🇷” ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል (የሆርሙዝ መዘጋት) ” – ኢራን 🇺🇸” አራን ሰርጡን ብትዘጋ መጥፊያዋ ይሆናል ” – አሜሪካ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ለመዝጋት የደኅንነት ምክር ቤቱን ውሳኔ እየጠበቀች ነው። የአለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚቀርብበትን የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲዘጋ የኢራን ፓርላማ ሲወስን የደኅንነት ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሚገኝ የኢራን የዜና አገልግሎት ዘግቧል። አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የጦርነቱ ሂደት ወደ ሌላ አቅጣጫ እያመራ ሲሆን ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የተጠየቁት የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ” ብዙ አማራጮች በእጃችን አለ፤ ሊሆን ይችላል ” ብለው መልሰዋል። የአያቶላህ አሊካሚኒ ከፍተኛ አማካሪም ሃገራቸው በአሜሪካ በተጠቃች በኋላ ኢራን ሰርጡን መዝጋት እንዳለባት እና የአሜሪካን መርከብ ማጥቃት እንዳለባት ሲገልፁ ነበር። የምክር ቤቱ ውሳኔ የአለምን ኢኮኖሚ በተለየ ሁኔታ የነዳጅን ዋጋ ሊያሻቅብ የሚችል ሲሆን የሚሰጠው ውሳኔ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ ምክትል ፕረዚዳንት ጄዲ ቫይንስ ፤ የኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋት መጥፊያዋ እንደሚሆን ገልየዋል። ቫይንስ ሃገራቸው አሜሪካ ወደ ጦርነት ውስጥ የገባችው ከኢራን ጋር ሳይሆን ከኒውኪሊየር ፕሮግራሟ ጋር እንደሆነ ተናግረዋል። በ100% መተማመን የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውኪሊየር ጣቢያዎች አጥፍቷል ወይ ? በሚል ተጠይቀው “ወደ እንደዚህ አይነት የደህንነት መረጃዎች መግባት አልፈልግም፤  የአሜሪካ የምሽቱ ጥቃት ግን የኢራንን ኒውኪሊየር የመታጠቅ አቅም በእጅጉ አዘግይቶታል ” ብለዋል። ጥቃቱን ተከትሎ ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ ልትረብሽ ትችላለች
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አዉሮጳ

ትራምፕ ፣ ኢራን፣ አስራኤል፣ እንግሊዝ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ

ከፋኖ ጋር ጦርነቱ ይቀጥላል ( ጄኔራሉ )……. ;አደጋው የከፋ ይሆናል (አቡነ ማትያስ)


Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የአዲስ አበባው ታላቅ ‘የማፊያ ስራ’!

(መሠረት ሚድያ)- አራት ኪሎ የሚገኘው ‘አምባሳደር ህንፃ’ ላይ ይገኝ የነበረው የድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ሲገባ በመጀመርያ ቀልብን የሚስበው በብዙ የመንግስት ቢሮዎች ውስጥ እንደሚደረገው በትልቁ ታትሞ እና በፍሬም ተዘጋጅቶ የተሰቀለው የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ፎቶ ነው። ድርጅቱ ቢሮው ብቻ ሳይሆን ማስታወቂያውም ቀልቢ ሳቢ ነበር። “ልጄ ውጭ ሀገር ሄዳ ነው ትምህርቷን መከታተል የምትፈልገው፣ አገሯን የምታስጠራ ምሁር እንድትሆንልኝ እፈልጋለሁ” ትላለች ዝነኛዋ የማስታወቂያ ባለሙያ ሙሉአለም ታደሰ ከሌላኛዋ ታዋቂ የሚድያ ሰው ዳናይት መክብብ ጋር በመሆን በጋራ የሰሩት የዚህ ድርጅት ማስታወቂያ። ይህ ዛሬ የምናቀርብላችሁ የከባድ ማጭበርበር ድርጊት ዋና ተዋናይ ቀላል ሰውም አይደለችም። ከጥቂት አመታት በፊት በአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ላይ ከ ‘ተስፋ ሰጪ’ ‘እና ‘ስራ ፈጣሪ’ አምስት የሀገራችን ግለሰቦች አንዷ ሆና ቀርባለች፣ በተጨማሪም ከሴቶች እና ህፃናት ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጌጎ ተስፋዬ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላታል። ግለሰቧ ቤተልሄም ታደሰ ይማም ትባላለች፣ ታድያ ተሸላሚ ያረጋት ስራዋ ምን ይሆን? ድርጅቷ ከ120 ሚልዮን በላይ ብርስ ከህዝብ እንዴት ማጭበርበር ቻለ? ቤተልሄም ታደሰ ይማም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለስራ ወይም ለትምህርት ወደ ውጪ ሀገር ሰው እንልካለን በማለት ገንዘብ የሚሰበስቡ ድርጅቶች መብዛታቸውን ብዙ ሰው ታዝቧል፣ ከነዚህም አንዱ Aim Ultra Consultancy የተባለው ድርጅት ነው። “እኔ Aim Ultra ን ለደቂቃ እንኳን አልተጠራጠርኩም። ማስታወቂያውን ታዋቂ ሰዎች በቲቪ እና በሶሻል ሚድያ ሲሰሩ ስላየሁ እውነት ይሆናል ብዬ ከቤተሰብ ያገኘሁት ገንዘብ ላይ ከብድር እና ቁጠባ ተጨማሪ በመበደር 520,000 ብር ከፈልኩ”
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

አብይ አሕመድ እና በአውሮፓ የገጠመው ተቃውሞ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የአብይ አህመድ አቀባበል በለንደን ……. የአማራ ፋኖ በእንግሊዝ !

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

ሩሲያ የናዚ ጀርመን በሁለተኛው የአለም ጦርነት በይፋ የተሸነፈበትን 80ኛ አመት የድል በዓሏን አክብራለች።

ሩሲያ የናዚ ጀርመን በሁለተኛው የአለም ጦርነት በይፋ የተሸነፈበትን 80ኛ አመት የድል በዓሏን አክብራለች። በድል በዓሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የቻይናውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች ተሳትፈዋል። በተጨማሪ የቡርኪናፋሶው መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ በፕሬዚዳንት ፑቲን ግብዣ የግል አውሮፕላን ከሞስኮ ተልኮለት በፕሮግራሙ እንዲሳተፍ ተደርጓል። መሪዎቹ ትናንት በክሬምሊን የእራት ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን ዛሬ በዓሉ በአደባባይ በወታደራዊ ትርዒቶች ተከብሯል። የዛሬው ወታደራዊ ሰልፍ ሞስኮ ወደ ዩክሬን ጦሯን ካዘመተች በኋላ ትልቁ ነው ሲባል ከ10 አመታት በኋላ የበርካታ ሃገራት መሪዎች የተገኙበትም ነው ተብሏል። ፕሬዚዳንት ፑቲን ባደረጉት ንግግርም በአሁኑ ወቅት በዩክሬን እየተፋለሙ ያሉ የጦር ሰራዊታቸውን አሞግሰዋል። በወታደራዊ ሰልፉ ላይ ከ11,500 በላይ ወታደሮቼ እና ከ180 በላይ ወታደራዊ መኪኖች ተካፋይ ሆነዋል። የሩሲያ የአየር ኃይል ቡድንም የአየር ላይ ትርኢቶችንም አሳይተዋል። የፑቲን የውጪ ጉዳይ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ይህንን የጋራ በዓላችንን በማስመልከት ፕሬዚዳንት ፑቲን እና ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሃሳብ መለዋወጣቸውን እና የእንኳን አደረሰህ መልዕክት እንደተለዋወጡ ለሚዲያዎች ገልፀዋል። ሶቪየት ህብረት በሁለተኛው የአለም ጦርነት ንቁ ተሳታፊ የነበረች ሲሆን ከ21 ሚሊየን ሰዎች በላይም በጦርነቱ አጥታለች። የናዚ ጀርመን በይፋ በሁለተኛው የአለም ጦርነት የተሸነፈበትን ምክንያት በማድረግ ሩሲያ ቀኑን እንደ ድል በዓል የምታከብር ሲሆን ዘንድሮ 80ኛ አመቱን እያከበረች ትገኛለች። Source: AP , Sputnik
Posted in News, አዉሮጳ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት የማስቆም ዕቅድ

ተመራጭ ፕሬዝዳንት ትራም እራሳቸውም ሰኞ እለት ለአንድ ሜዲያ በሰጡት አስተያየት ፕሬዝዳንት ፑቲንም ከሳቸው ጋር መገናኛኘቱን እንደሚፈለጉትና ከሰኞው በዓለ ሹመት በሗላ እንደሚገናኙ ያላቸው እመነት በመግለጽ ይህ ሁለቱንም በተለይም ዩክሬንን እያወድመ ያለ ጦርነት ባስችኳይ መቆም እንድላበት እንደሚያምኑ አስታውቀዋል።
Posted in አዉሮጳ