Home › View all posts by BBC Amharic
Blog Archives
ከአስር ዓመታት በፊት የተቀሰቀሰው የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት የአገሪቱን ዜጎች አገራትን እንዲሰደዱ አድርጎ ኢትዮጵያን ጨምሮ እግራቸው ወደመራቸው አገር ለመሰደድ ተገደዋል።
ጦርነቱ ሲነሳ ገና የስድስት ዓመት ታዳጊ የነበረው ኻሊል ከወላጆቹ ጋር ነበር ለስደት የወጣው። ኋላ ላይ ግን ከቤተሰቡ ተለይቶ የአስራ አንድ አገራትን ድንበሮች እያቆራረጠ ሰርቢያ ደርሷል።
ቤተሰቡ ደግሞ ከቱርክ ሆነው በሕጋዊ መንገድ ወደ ኔዘርላንድስ በመሻገር ለመኖር የሚያስችላቸው ፈቃድ በማግኘታቸው መጨረሻ ላይ ከቤተሰቡ ጋር ለመቀላቀል ችሏል።
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወላጆቻቸው በውጭ አገራት ቢወለዱም በአሜሪካ የተወለዱ ልጆቻቸው ዜግነት የሚያገኙበትን መብት እሽራለሁ አሉ።
ሁለት ሳይንቲስቶች 563 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ኮምፒውተሮች መካከል ግንኙነት ፈጠሩ። መልዕክት እየተየቡም መላላክ ጀመሩ። በመሃል ላይ ለኢንተርኔት መፈጠር አንድ ምክንያት የሆነውን የግንኙነት መቀወረጥ አጋጠማቸው። ሁለቱ ሳይንቲስቶች ከ55 ዓመታት በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ በተለይ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ የኑሮ ውድነት እየናረ መሆኑን ነዋሪዎች ያማርራሉ። የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣ የሸቀጦች እና የትራንስፖርት ዋጋ በከፍተኛ መጠን በከተማዋ ውድ ሆነዋል። በሌላ በኩል ከተማዋ በመሠረተ ልማት እየተሻሻለች እና እያደገች ሲሆን፣ በከተማዋ ለመኖር ዋጋው የሚቀመስ አልሆነም። ከዚህ አንጻር በኑሮ ውድነት አዲስ አበባ በአሁኑ ጊዜ ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች አንጻር ስንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች?
የዘጋቢ ፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጆች ማክስ ደንካን እና ዘንየን ዩ ናቸው። ከፕሮዲውሰሮቹ አንዷ ታማራ ማርያም ዳዊት ናት። ‘ሜድ ኢን ኢትዮጵያ’ በዋርሶው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል፣ በትሪቤካ ፊልም ፌስቲቫል፣ በሼፊልድ ኢንተርናሽናል ዶክመንተሪ ፌስቲቫል እና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ዕውቅና አግኝቷል። ፊልሙ የቻይና ባለ ሃብቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ሥራ አጥነትን፣ ባህልን፣ ቤተሰብን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የአርሶ አደሮች የተጠቃሚነት ጥያቄን በዋናነት ይዳስሳል።
ናሲም ስቃይ ከሚያደርሱባት ሰዎች ውጭ ሌላ ሰው አይታ አታውቅም። ብዙ ጊዜ “በቃ እዚህ ሞቼ ማንም ሳያውቀው ተረስቼ ልቀር ነው?” ብላ ታስባለች። በአስከፊው ኢቪን እስር ቤት ሕይወት ለናሲም እና ለሌሎች ሴት እስረኞች ምን ይመስላል?
በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የሚሠሩ ባለሱቆች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።መንግሥት ሱቃቸው በር ላይ የደኅንነት ካሜራ (ሲሲቲቪ) እንዲያስገጥሙ መመሪያ ሰጥቷል።በከተማው ያለውን የኢስላሚስት ታጣቂ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነው የደኅንነት ካሜራው ያስፈለገው።ሆኖም ግን ነጋዴዎቹ ካሜራ ካስገጠሙ በአል-ሻባብ ታጣቂዎች ዒላማ ተደርገው ስለሚገደሉ ይፈራሉ።የደኅንነት ካሜራዎችን ካላስገጠሙ ደግሞ ፖሊስ ያስራቸዋል።
የጃፓኑ ፍርድ ቤት በመስከረም ወር በዓለም ላይ ረዥም ዓመት የቆየውን የሞት ፍርደኛ፣ ኢዋዎ ሃካማታን፣ ንፁሕ ነው ብሎ ሲፈርድ ደስታና ሐዘን ተቀላቅለው የተደበላለቀ ስሜት ፈጥረው ነበር።
ዶ/ር ፋቲያ ካሚስ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ቤተ ሙከራ ምርምር እያደረገች ነው።እሷ የምትመራው ቡድን ፕላስቲክ የሚበላ ነፍሳት ላይ ነው ጥናት የሚሠራው። "ጠዋት ስንገባ ሁላችንም ደስ አለን። ፕላስቲኩ ተፈርፍሯል" ትላለች።ጥቁሩ ነፍሳት ፕላስቲኩን መብላቱ ትልቅ ድል ነው። ነፍሳቶቹ ፕላስቲኩን ከበሉ በኋላ ማብላላት ይችላሉ።
አብዛኛዎቹ አደጋዎች ከሜታኖል ጋር የተገናኙ ናቸው። ሜታኖል በሕገ ወጥ የአልኮል ምርቶች ውስጥ በብዛት የሚጨመር መርዛማ ውህድ ነው። ሜታኖል የሚጨመረው አልኮሉ በሚመረትበት ወቅት ሲሆን፣ በማጣራቱ ሂደት ደግሞ ክምችቱ ክፍ ይላል።
በየዕለቱ ልክ ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ52 ደቂቃ ላይ በሰርቢያ የሚገኙ መንገዶች ለ15 ደቂቃዎች ዝግ ይደረጋሉ። መኪኖች ይቆማሉ፤ ህዝቡ ጸጥ ይላል።
ይህም በህዳር ወር በሰርቢያ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ኖቪ ሳድ በባቡር ጣቢያ ላይ ጣሪያው ወድቆ ህይወት መቅጠፉን ለማሰብ የሚደረግ ነው።
ጆርጂያ፣ ሰርቢያ፣ ግሪንላንድ እና ሞሮኮ ጎብኝዎችን ለመሳብ ብዙ ጥረት እያደረጉ ነው። ለመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ጎብኚዎች ወደእነዚህ ሀገራት ለመግባት ቪዛ ያስፈልጋቸዋል? እንዴትስ ሊያገኙ ይችላሉ?
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለተለያዩ ሙያተኞች ቪዛ በመስጠት ወደ አሜሪካ የሚወስደውን የስደተኞች ፕሮግራም በተመለከተ ድጋፋቸውን ለኤለን መስክ እና ቪቬክ ራማስዋሚ ሰጡ።
ባለሥልጣናት እንደሚሉት ይህ መረጃ አንድ ዓመት ገደማ ሆኖታል፤ ባለፈው አንድ ዓመት ደግሞ የቤት ኪራይ እና በድንበር የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከፍ ብሏል።
የማኅበራዊ ሚዲያው ዓለም እጅግ ዘግናኝ እና አሰቃቂ የሚባሉ ጭንቀት የሚለቁ እንዲሁም ሕጋዊ ያልሆኑ ምሥሎች የሚለጠፉበት መድረክ ነው። ሰዎች ሲታረዱ፣ በጅምላ ሲገደሉ፣ ሕፃናት ስቃይ ሲደርስባቸው የሚያሳዩ ቪዲዮዎች እና የጥላቻ ንግግሮች . . . ይለጠፋሉ። እነዚህን ይዘቶች ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከመድረሳቸው በፊት የሚቆጣጠሩ ሰዎች አሉ።
የቢቢሲ የሩሲያ አርታኢ ስቲቭ ሮዘንበርግ በትውስታ ወደ 1999 ይጓዛል። ወቅቱ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ነበር። በሩሲያ አዲስ ፕሬዝዳንትም የተሾመበት ጊዜ ነበር። ስቲቭ ትዝታውን እንዲህ ያካፍላል።
ስጦታ የሚለዋወጡት የሰው ልጆች ብቻ አይደሉም። በእንሰሳት ዓለምም የተለመደ ነው። ስኮርፒዮንፍላይ የተባለችው በራሪ ነፍሳት ከፍቅረኛዋ የሚሰጣት ስጦታ ምራቅ ነው። ይህም ለስሪያ የሚጋብዝበት መንገድ ነው።ሌሎች እንደ ቀንድ አውጣና የአፈር ትል ባሉ ነፍሳትና ትላትሎች ዘንድም የተለመደ ነው። በአብዛኛው ከስሪያ ጋር የተያያዘ የስጦታ ልውውጥ ያከናውናሉ። በአእዋፍት ዘንድም ይስተዋላል።
ከአራት ዓመታት በፊት በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የአፍሪካ አገራትን በማንቋሸሽ እና በጸያፍ ዘለፋዎች በመንቀፍ ይታወቃሉ ትራምፕ። “የአሜሪካን ታላቅነት በድጋሚ ለማምጣት” በተደጋጋሚ የሚምሉት ትራምፕ በፀረ-ስደተኝነት፣ በፀረ- ሙስሊም ንግግራቸው እና አቋማቸው ይታወቃሉ። ከሥልጣን ወርደው ለሁለተኛ ጊዜ በመመረጥ ታሪክ የሠሩት ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ለመሆኑ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ኢትዮጵያውያን እንዴት ተመለከቱት?
ጄዲ ቫንስ ምናልባትም የወደፊቱ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ሊሆን ይችላል። ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ በቀሩት የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትኩረት ከሳቡ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ነው። በምርጫው ላይ ተጽእኖ ሊኖራቸው የሚችሉ የተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮች ይነሱበታል።
ትራምፕ ወደ ፖለቲካው ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ ስማቸው ገናና መሆኑ እና ከዚህ ቀደም ለየት ባለ መልኩ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ጉምቱ ፖለቲከኞችን እንዲረቱ ሳያደርጋቸው አልቀረም። የ78 ዓመቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ድጋሚ መንበረ-ፕሬዝደንቱን ለመቆጣጠር እየተወዳደሩ ይገኛሉ።
በአሜሪካ ምርጫ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ብቻ አይደሉም ዋነኛዎቹ መጠንጠኛዎቹ። የክርስትና ሃይማኖትም በአገሪቱ መንግሥት ውስጥ ጉልህ ሚና እንዲኖረው ጥረት የሚያደርጉ ቡድኖች አሉ። በተለይ ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ ወደ ዋይት ሐውስ የሚመለሱ ከሆነ ለዚህ አቋም አራማጆች ታላቅ ድል ነው። ከእነዚህም መካከል ትራምፕ “ከእግዚአብሔር የተላኩ ናቸው” ብለው የሚያምኑ እንዳሉ ሁሉ፤ ይህ እንቅስቃሴ ለአሜሪካ ዓለማዊ ፖለቲካ እና ዴሞክራሲ ስጋት ነው የሚሉ አሉ።
በአሜሪካ ምርጫ የቅስቀሳ ዘመቻ ወቅት ስደት ዋነኛ ጉዳይ ነው። ሁለቱም ዕጩ ፕሬዚዳንቶች የዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስም ሆኑ የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በድንበር በኩል የሚገቡ ስደተኞችን ማስቆም ዋና ተግባራቸው እንደሚሆን ቃል ገብተዋል። በዚህም ምክንያት አፍሪካውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሕዝቡ ፊቱን ሊያዞርብን ይችላል የሚል ስጋት ገብቷቸዋል።
በአሜሪካ የምርጫ ታሪክ ከፍተኛ ፉክክር ከተደረገባቸው አንዱ በሆነው የዘንድሮ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። አወዛጋቢው ትራምፕ ከየት ተነስተው አሁን ካሉበት እንደደረሱ በፎቶግራፎች ይመልከቱ።
45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋይት ሐውስ በጆ ባይደን ተሸንፈው ከተሰናበቱ ከአራት ዓመታት በኋላ 47ኛው ፕሬዝዳንት ለመሆን ተመርጠው በመጪው ጥር ወደ ዋይት ሐውስ ይመለሳሉ። ለዚህም አሜሪካውያንን አመስግንው ያለዕረፍት እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል።
ለአንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያው የሥልጣን ዘመን በሁለተኛው ዙር እንዴት ሊሆን እንደሚችል ጥሩ ማሳያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል ይላሉ። ዶናልድ ትራምፕ አሁን ሥልጣን መልሰው ሲጨብጡ በመጀመሪያው የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ማድረግ ካቆሙበት እንደሚቀጥሉ ብዙዎች ያምናሉ።
ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ዕውን ሲሆን፣ በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እንኳን ደስ አለዎት የሚሉ መልዕክቶች እና ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። ትራምፕ ከአራት ዓመታት በፊት ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ በአፍሪካ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ያለመ ዕቅድን ተግባራዊ አድርገዋል። ይህም እሳቸው ሥልጣን ከለቀቁ ከሦስት ዓመታት በኋላ በሥራ ላይ ይኛል። ነገር ግን በርካታ አዲስ ነገሮች ባሉበት በአሁኑ ውቅት ትራምፕ ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በምን ዓይነት መልኩ ሊይዙት ይችላሉ?
በሰሜናዊ ዚምባብዌ አንበሶች እና ዝሆኖች በሚኖሩበት ፓርክ ውስጥ ለአምስት ቀናት የቆየ አንድ የስምንት ዓመት ህጻን በህይወት መገኘቱን የአገሪቱ የፓርላማ አባል ገለጹ።
የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር እና የፒው የቅርብ ጊዜ ጥናት መረጃ እንደሚያሳየው እስከ 2022 ድረስ በአሜሪካ ወደ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ነበሩ። ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 3.3 በመቶ የሚሆነው ይይዛሉ። እናም ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ቃል እንደገቡት ሕገ ወጥ ያሏቸውን ስደተኞች ከአሜሪካ ማባረር ይችላሉ?
ያለፈው ዓመትን የፓሪስ ኦሊምፒክ ያደምቃሉ ተብለው ከተጠበቁ አዳዲስ ፈጠራዎች አንዱ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የበራሪ ታክሲዎች አገልግሎት መጀመር ነበር። በኤሌክትሪክ የሚሠሩት በራሪ ታክሲዎች ሳይንደረደሩ የሚነሱ እና ሲያርፉም በአንዴ የሚቀመጡ እንደ ሄሊኮፕተር የሚያገለግሉት በራሪዎች ሲሆኑ ወጪ፣ ድምጽ እና የአየር ብክለትን የሚቀንሱ ናቸው ተብለው ነበር። ምን ገጠማቸው?
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ወረራ ሦስተኛ ዓመቱ እየተቃረበ ነው። ሰሞኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያልተጠቀመችባቸውን አዳዲስ መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ አውላላች። አዳዲሶቹ ሚሳዔሎች ፍጥነታቸው እና የሚጓዙት ርቀት እስከ ዛሬ ከተጠቀመቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ በከፍተኛ እጥፍ ከፍ ያለ ነው። ሩሲያ በዓለም ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና ሚሳዔሎች ከታጠቁ አገራት መካከል በቀዳሚነት የምትጠቀስ ናት። ለመሆኑ ሩሲያን እንድትፈራ ያደረጓት እና በይዞታዋ የሚገኙ ምን ያህል የኒውክሌር አረሮች ታጥቃለች?
የሱስ ሕክምና ማዕከል ባለሙያዎች የወሲብ ፊልም በመመልከት ሱስ ተጠምደው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ይገልጻሉ። አሁን በየዕለቱ ከወሲብ ፊልም ዕይታ ሱስ ጋር ከሚታገሉ ሰዎች፣ እርዳታ እፈልጋለሁ የሚል በርካታ ጥያቄዎችን እየቀረቡ ነው። ይህ ሱስ በአካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጤና እንዲሁም በማኅበራዊ ሕይወት ላይ ከባድ ተጽእኖ እንዳለው ይነገራል።
ማኅበራዊ ሚዲያው በተለይ ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ተጨማሪ ገቢ ማግኛ መንገዶችን በሚያስተዋውቁ ሰዎች የተሞሉ ናቸው። እውን በእነዚህ መንገዶች በመጠቀም ገቢን ማሳደግ ሕይወትን መለወጥ ይቻላል?
ማርገዛቸውን ሳያዉቁ ከወራት በኋላ ወይም ምጥ ሲጀምራቸው ወይም ሊወልዱ ሳምንታት ሲቀራቸው የሚታወቅ እርግዝና እንዳለ ሰምተው ያውቁ ይሆን?
ብዙዎች የካናዳ ቪዛ ለማግኘት ኤጀንቶች እና የጉዞ ወኪሎች ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ይቀጥራሉ። ሆኖም ግን ሐሰተኛ ሰነድ ከማስገባት አንስቶ ቪዛ ጠያቂዎች አካውንታቸውን እንዳያዩ ማገድ እንዲሁም የሌሎችም የማጭበርበሪያ መንገዶች ሰለባ ይሆናሉ። በዚህም ሳቢያ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ከመጭበርበራቸው ባሻገር ወደ ካናዳ እንዳይገቡ የሚያደርግ ዕግድም ይገጥማቸዋል።
የብራዚል የምክር ቤት አባል በድጋሚ ባለመመረጧ የወሰደችውን የሽንት ቤት መቀመጫ መለሰች።
ባለፉት ወራት በተለይ በታላቁ ስምጥ ሸለቆ በሚገኘው የአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው። በአዋሽ፣ መተሐራ እና አቦምሳ አካባቢዎች የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተማዎች እየተሰማ ይገኛል። ለመሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ አሊያም ንዝረት ሲከሰት ምን ልናደርግ ይገባል?
በጃፓኗ ቶኪዮ የሞተር ብስክሌት ክብደት እና ስፋት ያለው ብሉፊን የተባለ ቱና በ207 ሚሊዮን ዩን ተሸጧል።
ገንዘቡ ወደ ዶላር ሲመነዘር 1.3 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ነው።
ብዙም ያልተለመደ ካንሰር እንዳለባት በመታወቁ ስምንት የአካል ክፍሎቿ እንዲወገድላት የተደረገች ሴት ህክምናዋን ጨርሳ ወደ ሥራዋ ተመለሰች።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የ2024 ምርጥ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ካካተቷቸው መጻሕፍት መካከል የዲናው መንግሥቱ 'Someone Like Us' ይገኝበታል። ኦባማ እአአ በ2019 የዲናውን 'How to Read the Air' የተባለ ልብ ወለድ የዓመቱ ምርጥ መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ አስገብተዋል። ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊው ዲናው ማነው?
በትግራይ እየተካሄደ ነው የሚባለው ሕገወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጣት አነጋጋሪ ጉዳይ ከሆነ ወራት ተቆጥረዋል። የአካባቢ ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎች እንዲሁም የውጭ ዜጎች ሳይቀሩ ይሳተፉበታል የሚባለው የወርቅ ቁፋሮ አሳሳቢ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጥቅም ላይ በሚውሉ አደገኛ ኬሚካሎች ምክንያት በሰዎች፣ በእንስሳት እና በአካባቢ ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ነዋሪዎች እና አጥኚዎች እየተናገሩ ነው።
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ለካራባኦ ዋንጫ ፍጻሜ መድረስ እንደሚችል ቢያምንም ተጫዋቾቹ የውድድሩን "አስቸጋሪ" ኳስ መላመድ እንዳለባቸው አሳስቧል።
ታዋቂ የሆሊውድ ተዋናዮችን ያሳተፈ 'ዘ አቢሲኒያን' (አቢሲኒያውያን) የተሰኘ የድምጽ ድራማ ተለቅቋል።
ድራማው ጥንታዊ እና የዓለማችን የቁንጮ ማማ ላይ ከደረሱት አንዱ በሆነው የአክሱም ስልጣኔ ላይ የሚያጠነጥን ነው።
አንዲት የጣልያን መንደር ነዋሪዎቿ በጠና እንዳይታመሙ ከለከለች።
ቤልካስትሮ የተሰኘችው መንደር ነዋሪዎች "አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ከሚያስፈልገው ማንኛውም በሽታ እንዳይያዙ" መመሪያ እንደተላለፈላቸው የአካባቢው ከንቲባ አንቶኒዮ ቶርቺያ ተናግረዋል።
የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶ ብር ተሻገረ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማክሰኞ ምሽት፣ ታኅሳስ 29/ 2017 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል።ማሻሻያውን ተከትሎ 91 ብር ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን ብር 101.47 ገብቷል።
በዩናይትድ ኪንግደም፣ በርሚንግሃም በሚገኝ በአንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የልደት በዓልን በአንድ ላይ ያከበሩት ሩሲያውያን እና ዩክሬናውያን ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነትን በተላበሰ መልኩ ዕለቷን አስበዋታል።
ከጥቂት ወራት ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያየ መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦች በተደጋጋሚ መከሰታቸው ተመዝግቧል። እስካሁን ያጋጠሙት ንዝረቶች ዝቅተኛ ኃይል ያላቸው በመሆናቸው በሰው እና በንብረት ላይ የጎላ ጉዳት አላደረሱም። ነገር ግን የርዕደ መሬቱ የጥንካሬ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ በመምጣት ላይ በመሆኑ አሳሳቢ ሆኗል። ለመሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች የሚያደርሱት ጉዳት አስከፊ የሚሆኑት በምን ምክንያት ነው?
ከአፍሪካ ወደ ስፔን እየተጓዘ በነበረና በስደተኞች በተጨናነቀ ጀልባ ላይ ልጅ መወለዱን የስፔን ባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች ገለጹ።
ሀዲስ ዓለማየሁ መሰንቆ ተጫዋች ነው። ስለ መሰንቆ አውርቶ አይጠግብም። ዓለም ሙሉ በአንዱ የመሰንቆ ገመድ ቢተሳሰርለት ምኞቱ ነው። ሀዲስ እና መሰንቆን መለያየት አይቻልም ይላል። ስሙንና የሚወደውን መሰንቆ ገምዶ ራሱን ሀዲንቆ ሲል ይጠራል። የመጀመሪያን አልበሙን በቅርቡ ለቋል። አልበሙ እየፈረሱ ባሉት ቀደምት የአዲስ አበባ ሰፈሮች እና ጎዳናዎች ትዝታ የተሞላ ነው።
በቻይናዋ ከተማ በጉዋንዡ የልብስ ስፌት ማሽን ድምጽ መስማት የተለመደ ነው። ከጠዋት እስከ ማታ ከፋሪባዎች ድምጹ በመስኮት በኩል ይሰማል።ካናቴራ፣ ሱሪ፣ ሹራብ፣ ቀሚስ ይሰፋል። ከ150 አገራት በላይ የሚላክ ምርት ነው።ፓንዩ የተባለው ሰፈር ሼን የሚባል መንደር አለ። በዓለም በፋሽን ውስጥ የሚታወቁ ልብሶች መነሻ ነው።አንድ የፋብሪካው ሠራተኛ "በወር ውስጥ ባሉት ቀናት እሠራለሁ" ትላለች።አብዛኞቹ ሠራተኞች ቢበዛ አንድ ቀን እረፍት ነው የሚያገኙት።
በአውስትራሊያ የምትኖር አንዲት ሴት ለማኅበራዊ ሚዲያ ፕራንክ በሚል በጓደኛዋ አማካኝት ሙሽራ ሆና የተወነችበት የሰርግ ሥነ ሥርዓት ኋላ ላይ የእውነት ነው ተብሎ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ደርሷል።
በደቡባዊ ካሊፎርኒያ፣ ሎስ አንጀለስ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የሰደድ እሳት ለመግታት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተሰማሩ።
ባለፉት ሳምንታት ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአርክቲክ ውቅያኖስ የሚገኘውን እና በዓለማችን ትልቁን የግሪንላንድ ደሴትን 'ለመጠቅለል' ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተዋል
ኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የስቶክ ገበያን ክፍት አድርጋለች። ኢትዮ ቴሌኮም ኢኤስክስን በመቀላቀል የመጀመሪያው የልማት ድርጅት ይሆናል። ሌሎችም ድርጅቶች ይህንን የግብይት መድረክ እንደሚቀላቀሉ ተነግሯል። የኢኤስኤክስ መከፈት ለኢትዮጵያውያን ምን ይዞ ይመጣል? ችግር ላይ ያለውን የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት እንዴት ሊደግፍ ይችላል?
ዶናልድ ትራምፕ የፓናማ ቦይን፣ ጎረቤታቸውን ካናዳን እና ግሪንላንድ ደሴትን በአሜሪካ ይዞታ ሥር ለማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ በይፋ እየተናገሩ ነው። ትራምፕ ይህንን አገራቱን ያስቆጣውን ሃሳብ የሰነዘሩት ለምንድ ነው? ንግግራቸውስ ከምር ነው?
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ኖርዌይ በዓለማችን ቁንጮ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች። ባለፈው ዓመት በአገሪቱ ካሉ አስሩ መኪኖች ዘጠኙ የኤሌክትሪክ መኪኖች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
ሌሎች አገራት ከኖርዌይ ምን መማር ይችላሉ?
በአዋጁ መሠረት “የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ የሚያከማቹ፣ እና ከግብይት ሥርዓት ውጪ ሲሸጡ የተገኙ” ሰዎች፤ ከሦስት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እሥራት እና ከ350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣሉ። ከቅጣቱ በተጨማሪ "ማንኛውም የነዳጅ ውጤቶች አጓጓዥ ተሸከርካሪ ጂፒኤስ የመግጠም ግዴታ አለበት" የሚል አዲስ ድንጋጌ ተካትቶበታል።
የባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር አደራዳራዳሪዎች እንደሚሉት እስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ ደርሰዋል። እስራኤል በሐማስ የተፈጸመባትን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ላይ እያካሄደችው ያለው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ 15 ወራትን ሊያስቆጥር በተቃረበበት ጊዜ ነው ሁለቱ ወገኖች ከስምምነት ለመድረስ መቃረባቸው የተነገረው። ለመሆኑ የተኩስ አቁም ስምምነት ምንድን ነው? የተኩስ አቁም ስምምነት ግጭትን በዘላቂነት ያስቆማል? ወይንስ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ፋታን የሚሰጥ ነው?
ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሽብርተኝነትን በመንግሥት ደረጃ ስፖንሰር ታደርጋለች በሚል የተፈረጀችውን ኩባ ከዝርዝሩ ሊያስወጧት እንደሆነ ተናገሩ።
ወደ ባሕር ለመጥለቅ ጥቅም ላይ የሚውል ጀልባ በግብፅ መገልበጡን ተከትሎ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች የግብፅ ባለሥልጣናትን ከሰዋል። ጀልባው የተገለበጠው ቀይ ባሕር ላይ ነበር። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች እንዳሉት አረብኛ ማንበብ ባይችሉም በአረብኛ የተጻፈ የዓይን እማኞች ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ ተገደዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት "በድልድል እና ምደባ" 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከጥር ጀምሮ ከሥራ ማሰናበቱን ሠራተኞች እና ድርጅቱ ተናገሩ። ድርጅቱም የብቃት ፈተና እና ውድድር ያላለፉ ሠራተኞችን ከሥራ መቀነሱን ገልጾ "የሪፎርም ባሕሪ ነው" ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል።
ናይጄሪያውያን የፍቅር ጓደኛዋ ነው በተባለ ዘማሪ አንገቶ ተቀልቶ ለተገደለችው ሴት ሐዘናቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ እየገለጹ ነው።
የዩናይትድ ኪንግደም የግምጃ ቤት ሚኒስትር ቱሊፕ ሲዲቅ በባንግላዴሽ እየተካካሄደባቸው ባለው የሙስና ምርመራ ጋር በተያያዘ በደረሰባቸው ጫና ከሥልጣናቸው ለቀቁ።
የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ወታደራዊ አገዛዝን ካወጁ በኋላ አመጽ አነሳስተዋል የተባሉትን ፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዮልን ከጠባቂዎቻቸው ጋር ለሰዓታት ከቆየ አስገራሚ ፍጥጫ በኋላ በቁጥጥር ስር አዋሉ።
በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት እስካሁን 24 ሰዎች ሞተዋል። በሎስ አንጀለስ የምትኖረው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት ፈረደ በዚህ ሰደድ እሳት የተነሳ ለተጎዱ ነዋሪዎችን ድጋፍ ከሚሰጡ መካከል አንዷ ናት። በራሷ ተነሳሽነት ከሁለት ልጆቿ ጋር ድጋፍ አድርጋለች። በሰደድ እሳቱ እምብዛም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ እንዳልተጎዳ ተናግራለች።
በኢትዮጵያ አረጋውያን ከቤተሰባቸው ጋር እስከ መጨረሻው ሞኖራቸውን አውሮፓውያኑም ሊወርሱት የሚገባ ባህል ነው የምትለው ቱቱ መላኩ በእንግሊዟ ሬዲንግ ከተማ ፓልመር ፓርክ አካባቢ ካፌና ሬስቶራንት አላት። አብዛኞቹ ደንበኞቿ የዕድሜ ባለፀጋዎች ናቸው። አንድ ሳምንት ከምግብ ቤቷ ከጠፉ አያስችላትም። ስልኳን አንስታ ጤንነታቸውን ትጠይቃለች።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ስለጎረቤት አገራት አወዛጋቢ መልዕክት የሚለጥፉት የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ልጅ ራሳቸውን ከኤክስ አገለሉ።
በግጭት እና በድርቅ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ችግር በቆየው የአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ውስጥ ባጋጠመው ከፍተኛ የምግብ እጥረት ምክንያት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን በወረዳው ያጋጠመውን የምግብ እጥረት የተደረገው ዳሰሳ ጥናት አመለከተ። የወረዳው ባለሥልጣናትም ሰዎች ስለመሞታቸው ከመስማታቸው ውጪ የተረጋገጠ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
በጥዋቱ ቡና የሚጠጡ ሰዎች ከልብ በሽታ ጋር በተያያዘ የመሞት ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቁሟል።
ይህ ቫይረስ በትንኝ የሚተላለፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1930ዎቹ ኡጋንዳ ውስጥ የተገኘ በሽታ ነው። ቫይረሱ በአውሮፓውያኑ 1999 ነው ወደ ምዕራቡ ዓለም የገባው። በአሜሪካ በየዓመቱ ከሁለት ሺህ ባላይ አሜሪካውያን በዚህ ቫይረስ ይያዛሉ፤ 1200 የሚሆኑት ደግሞ ለሕይወት አስጊ ለሆነ በሽታ ይጋለጣል፤ 120 ሰዎች ይሞታሉ።
ስሙ ለዚህ ፅሑፍ ሲባል የተቀየረው የ25 ዓመቱ ሞሐመድ በአውሮፓውያኑ 2028 ጫት ከታገደ ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሞከረው ለቢቢሲ ይናገራል።