ግብፅ “የግድቡን ጉዳይ ወደ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት እወስዳለሁ” ማለቷን ኢትዮጵያ አጣጣለች

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምክንያት “በታችኛው ተፋሰስ የሚኖሩ የሚሊዮኖችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥላለች” ብለው በመክሰስ አገራቸው ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እንደምትወስድ ተናገሩ።

በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ ተወካይ ዮሴፍ ካሳዬ ለግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ምላሽ፤ “ግብፅ ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያደረገችው ንግግር መሠረት አልባ እና አሳሳች ነው” ሲሉ አጣጥለዋል።

ግብፅ “ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተዓማኒ ያልሆኑ ክሶችን በተደጋጋሚ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አቅርባለች” ሲሉም አክለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9rmpxe88do