የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ የዓመቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲመዘን
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ እንቅስቃሴማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያ ከምዕራባዊያን ሀገራት እና ተቋሞቻቸው ጋር ባላት ግንኙነት “ተቀባይነቷ የጨመረበት” ዓመት መሆኑን የጠቀሱ አንድ የዘርፉ ተንታኝ፣ የገንዘብ ተቋማት እያደረጉት ያለውን የብድር ድጋፍ አስረጂ አድርገዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት “አስጊነቱ አሁንም የቀጠለ” እና በጥቅሉ ሲመዘን “አድገናልም፣ ወድቀናልም የሚያስብል ኹኔታ ያልተፈጠረበት” ነው ብለዋል።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል ዐቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በኩል እንዳለው የተቋሙ የዚህ ዓመት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ “ውጤታማ” ነበር። ቃል ዐቀባዩ ለዚህ ዝርዝር ጉዳዮችን የጠቀሱ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው። “የዲፕሎማሲ ግንኙነታችንን በማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን በማሳደግ፣ ከጎረቤት ሀገሮች እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ትብብር እንዲቀጥል፣ ቀጣናዊ ትስስርን፣ አሕጉራዊ እና አለማቀፋዊ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል”።የሰላም ማስከበር እና የባሕር በር ጉዳዮች እያነቃነቁት ያለው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ
ስማቸውን ሳይጠቅሱ ምልከታቸውን ለዶቼ ቬለ ያጋሩ አንድ የዘርፉ ተንታኝ የሀገሪቱን የዓለም አቀፍ ግንኙነት በሦስት ፈርጅ ከፍለው ነው የዳሰሱት። የመጀመርያው ኢትዮጵያ ከምዕራብ ሀገራት እና ተቋሞቻቸው ጋር ያላትን ግንኙነት የተመለከተው ነው። “ከምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ የኢትዮጵያ ተቀባይነት የጨመረበት፣ ተሰሚነቷ ከፍ ያለበት ኹኔታ ነው የምናየው”። ተንታኙ እንደሚሉት ሁለተኛው የግንኙነት ደረጃ መመዘኛ ፈርጅ ባደረጉት ከጎረቤት እና በአቅራቢያ ካሉ ሀገራት ጋር ባለ ትስስር ግን ኢትዮጵያ ብርቱ ሥራ የሚጠበቅባት እንጂ በዚያ ደረጃ የሚገለጽ ስኬታማ ሥራ የሠራችበት ዓመት አይደለም።መንግሥት 125 ኢትዮጵያውያንን ከሊባኖስ መለሰ

“ከጎረቤት ሀገራት ጋር የነበራት ግንኙነት አስጊነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳምንት በፊት በፓርላማው በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ “ጥንቃቄ የተሞላበት” የዓለም አቀፍ ግንኙነትን መከተል እንደምትቀጥል ብሎም “አማካኝ” ያሉትን ስፍራ ሳትለቅ መጓዝ እንዳለባት ጠቅሰው ነበር። የብሪክስ ተሳትፎ እንደ ስኬት ታይቶ ሊሆን እንደሚችል የገለፁት የዲፕሎማሲ ተንታኙ ይህ ጉዳይ ይልቁንም የበለጠ የቀረጥ ጫና እንዳያስከትል እና ተሻሽሏል የሚባለውን ከአሜሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዳይጎዳ ሥጋታቸውን ጠቅሰዋል። “የትኛው ዓለም አቀፍ ውል እና ድንጋጌ – ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚያስገኝ ተገኝቶ ነው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ውጤታማ ነበር ባለፈው ዓመት ልንል የምንችለው? ትንሽ ግራ አጋቢነት ይኖረዋል ለእኔ እንደ አንድ ባለሙያ ስፈትሸው” በማለት ሞግተዋል። DW Amharic