በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃኪሞች የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።
በአዲስ አበባ በሆስፒታሎች ዙሪያ መረጃ ቲቪ ባደረገው አሰሳ ዛሬ ክፍት የሆኑት የህክምና ክፍሎች ፤ ድንገተኛ ክፍል፣ ፅኑ ህሙማን ክፍል፣ የጨቅላ ህፃናት ክፍል፣ የማዋለጃ ክፍል ብቻ ናቸዉ። ሌሎች የሕክምና ክፍሎች አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ተረጋግጧል።
የአብይ አገዛዝ ለሃኪሞች ጥያቄ መልስ ሰጥቶ እና የታሰሩትን ሃኪሞች ከፈታ አድማው ሊቆም ይችላል ተብሏል። አድማውን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲቀላቀሉት ጥሪ እየተደረገ ይገኛል። ሲል በሆስፒታሎቹ የተዘዋወረው የመረጃ ቲቪ ሪፖርተር አስታውቋል።
የአድማው አስተባባሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት የመንግስት ሚዲያዎች እንደተለመደው አንዳንድ አስገድደው ወደሚያሰሯቸው ተቋማት በመሄድ ምንም የስራ ማቆም እንደሌለ እና እንደወትሮው አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ሊዘግቡ እና ፕሮፖጋንዳ ሊሰሩ ይችላሉ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት ምንም ግራ መጋባት እንዳይኖር። ዛሬ በተለያዩ ምክንያቶች ማቆም ያልቻላቹ ከከሰዓት ወይም ከነገ ጠዋት ጀምሮ አድማውን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።በ ER, ICU, LW እየሰራቹ ያላቹ ጤና ባለሞያዎች Cold Case እንድታዩ ለማስገደድ ከሞከሩ ወይም የታጠቀ ሀይል የስራ ቦታቹ ካለ እንዲሄዱላቹ አሳውቁ ካልሆነ ጥላቹ ወደ ቤታችሁ ሂዱ። በወታደር ተገዶ የሚሰራ ህክምና የለም። ብለዋል ።
የአድማው አስተባባሪዎች አክለውም በዛሬው ቀን የሚጠራ ማንኛውም ስብሰባ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን በስብሰባው ባለመሳተፍ የራሳችሁን ግዴታ እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን ፤ Stay Home , Stay Safe ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። #MerejaTv