መንግሥት፣ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለፖለቲካ ቅስቀሳ’፣ ለመራጮች ትምህርትና ለምርጫ ታዛቢነት ሥራዎች ከውጭ ምንጮች የገንዘብ ድጋፍ እንዳይቀበሉ የሚከልክል ድንጋጌ በማካተት የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል።
ማሻሻያው፣ በውጭ ድርጅቶችና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች የተመሠረቱ አገር በቀል ድርጅቶች፣ በኢትዮጵያዊያን ለተቋቋሙ አገር በቀል ድርጅቶች የገንዘብ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ እንደማይሠጡ እንደሚያግድም ዘገባው ጠቅሷል።
በሥራ ላይ ባለው አዋጅ በተጣለበት ዕገዳ ቅር የተሠኘ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ቅሬታውን ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅርብ ይችላል ተብሎ የተደነገገው መብት፣ የመጨረሻው ውሳኔ ሠጭ የባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ ነው በሚል አንቀጽ መተካቱንም ዘገባው አመልክቷል።