ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት በአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ይዛለች።
የኢኮኖሚስት ኢንተሌጀንስ ዩኒት ዓለማቀፍ የኑሮ ውድነት የ2025 ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከዓለም አገራት በ46 ነጥብ 5 ነጥብ 53ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
ሪፖርቱ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ለምግብና ትራንስፖርት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በአፍሪካ ቀዳሚ እንደኾኑ ገልጧል።
በአገሪቱ ውስጥ ለሥራም ይሁን ለግል ጉዳይ ትራንስፖርት መጠቀም ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል ተብሏል።