ግንቦት 27/2017 ዓ.ም
- የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ጎንደር ቀጠና አዲስ የተደራጀው ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር በጎንደር ኮማንዶ በላይ የተሰኘ ንዑስ ልዩ ኦፕሬሽን ጀመረ።
- የዘመቻ ቋራ ቃል ኪዳን አካል የሆነ ንዑስ ልዩ ኦፕሬሽን እየተደረገባቸው የሚገኘው …

፩ኛ የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር የጎንደር ብርጌድ፣የቃኘው ብርጌድና የዓፄ ፋሲለደስ ብርጌዶች በጥምረት ጎንደር ከተማ ምስራቃዊ አቅጣጫ ዘልቀው በመግባት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ብርቱ ውጊያ በማድረግ የጠላትን ምሽግ እየሰበሩ እየገሰገሱ ነው።
መረጃው እስከደረሰበት ሰዓት ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን በከተማው በጥብቅ ጥበቃ ስር የሚገኘው የአገዛዙ ሹመኛ እየራደ ይገኛል።

፪ኛ በጎንደር ከተማ ደቡባዊ አቅጣጫ የዓፄ ቴዎድሮስ አይሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ብርኃላ የተባለ የጠላት ምሽግን በማፈራረስ በጥልቀት ለመግባት እየተዋጋ የሚገኘው የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የታድሎ ብርሃን አካል ብርጌዶች ናቸው።በዚህ የጎንደር ከተማ አስ/ር ጠዳ ክ/ከተማ እየተደረገ በሚገኘው ተጋድሎ የኦህዴድ ብልፅግና ጨፍጫፊ ታጣቂ በጀግናው ሰራዊታችን ብርቱ ክንድ እየተደቆሰ ይገኛል።

፫ኛ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አዳሩን ማክሰኝት ከተማን ጠላትን ደምስሶ ሰብሮ በመቆጣጠር የወረዳውን ፖ/ጣቢያ በመስበር ከ70 በላይ የግፍ እስረኞችን ማስለቀቅ የቻለው የአፋብኃ ጎንደር ቀጠና የዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ነው።አሁንም ከተማውን በመቆጣጠር ቀሪ ተልዕኮዎቹን በመፈፀም ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጎንደር ከተማ 40 ኪ.ሜ ርቀት የተወሰደ ስኬታማ ኦፕሬሽን ነው።የንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር አሃድም ተሳታፊ ነው።

፬ኛ የዳ/ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የመብረቅና የሻለቃ ፋናዬ ውቤ ክ/ጦሮች በደ/ጎንደር ዞን የሊቦ ከምከም ወረዳ አዲዘመን ከተማ ዘልቀው በመግባት በከተማው የመሸገውን ወራሪ አራዊት ሰራዊት እየተገረፈ ነው።
በሁሉም ግንባሮቼ ውጊያው ተፋፍሞ ቀጥሏል።
እየተደረጉ የሚገኙት ኦፕሬሽኖች ከጎንደር ባ/ዳር ዋና አውራ ጎዳና ላይ የሚገኙ ከተሞች የሚደረጉ በመሆናቸው ህ/ሰቡ በከተሞች እና ጥቁር አስፓልት መንገዶች ጥንቃቄ እንዲያደርግም መልዕክት ተላልፏል።
አገዛዙ በጎንደር ከተማ ያሰባቸውን የፖለቲካ ሻጥሮች አስገዳጅ ሰልፎችና የአደባባይ ትርዒቶች የማያቆም ከሆነ ህዝባችን ከእንግልት ለመታደግ ሲባል በየትኛውም ቦታና ሰዓት አስፈላጊውን ርምጃ አጠናክረን የምንቀጥልም ይሆናል።
አፋብኃ ጎንደር ቀጠና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!