በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች፤ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ካልተመለሱ የጀመሩትን የስራ ማቆም እንደሚቀጥሉ ገለጹ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች በትላንትናው ዕለት የጀመሩትን የስራ ማቆም ዛሬም በመቀጠላቸው በከተማይቱ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ተዘግተው ዋሉ። ዳኞቹ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስኪፈቱ ድረስ የስራ ማቆማቸውን እንደሚቀጥሉ የትግራይ ዳኞች ማህበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።

በመቐለ ከተማ የሚገኙ ዳኞች ስራቸውን ለማቆማቸው በዋነኛነት የጠቀሱት ምክንያት “የደህንነት ችግር አለብን” የሚል ነው። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫም፤ በመቐለ ሰባት ክፍለ ከተሞች ባሉ ፍርድ ቤቶች እና በከተማይቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚሰሩ ዳኞች “በደህንነት ስጋት” ምክንያት ስራ እንዳቆሙ ማሳወቃቸውን አረጋግጧል።

የትግራይ ዳኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ሃይለስላሴ፤ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረቧቸው አምስት ጥያቄዎች ከዳኞች ደህንነት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የዳኞቹ የመጀመሪያ ጥያቄ በችሎት የሚመደቡ የጸጥታ አስከባሪዎችን የሚመለከት ነው።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15997/