ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል።
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከትላንት ማክሰኞ ግንቦት 5፤ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የምስረታውን የወርቅ ኢዮቤልዮ ባለፈው የካቲት ወር ያከበረው ህወሓት ከፓርቲነት የተሰረዘው፤ ቦርዱ ያዘዘውን “የእርምት እርምጃ” ተግባራዊ ባለማድረጉ መሆኑን ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፤ ባለፈው የካቲት ወር መጀመሪያ ለፓርቲው የሰጠው ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ቦርዱ ይህንን ቀነ ገደብ ባሳወቀበት መግለጫው፤ ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል “የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን” በሶስት ወራት ውስጥ እንዲያካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
ቦርዱ ህወሓትን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ ያዘዘው፤ “በአመጽ እና በህገ- ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ” የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንደሚዘገቡ የሚያስችለው አዋጅ (https://ethiopiainsider.com/2024/13159/)በሚያስቀምጠው ድንጋጌ መሰረት ነው። ይህ አዋጅ “በልዩ ሁኔታ” የሚመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያካሄዱ በምርጫ ቦርድ ሊታዘዙ እንደሚችሉ ይደነግጋል።
ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ በነሐሴ 2016 ዓ.ም ለህወሓት የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠው ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲው “የቦርዱ ታዛቢዎች” በተገኙበት በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር። ቦርዱ የቅደመ ጉባኤውን የዝግጅት ስራዎች ለመከታተል እንዲረዳው፤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማካሄዱ 21 ቀናት በፊት ለመስሪያ ቤቱ እንዲያስታውቅም ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15908/