Blog Archives

የሊቅ ዐቢይ አስቸጋሪ ምርጫ። የግል አስተያየት (ከኀይሌ ላሬቦ)

የሊቅ ዐቢይና የነለማ ቡድን ተብሎ የሚጠራውን አንጃ ደጋፊዎች፣ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ የአንድነት ጐራ ናቸው ብል ስሕተት አይመስለኝም። የነለማ ቡድን ግን ሁሉም የኢሕአዴግ አባላት ናቸው። የዚህ ቡድን ደጋፊዎች ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢሕአዴግ በመልካም እንተርጉም ካልን ሆድና ጀርባ፣ በመጥፎ እናስመስል ከተባለ ደግሞ እባብና ርግብ መሆናቸውን ነው። ምንም ብንመኝ፣ ሁለቱ በፍጹም አብረው ሊኖሩም ሊደመሩም አይችሉም። “መደመር” የሚለው የሊቅ ዐቢይ ፈሊጥ ለነዚህ ሁለቱ በፍጹም አይሠራም። ባንድ አልጋ እንኳን ቢተኙ፣ ሕልማቸው ተጻራሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዘመን ተሻጋሪና ለማንም የማይበገር፣ ሌላውን ጐረቤቱንም ሆነ አካባቢውን እያሰፋና እያቀፈ የሚሄድ፣ እንከን የለሽ ስብጥርና ጒንጒን ማንነት ነው። ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት የሚታወቁት በተፈጥሯቸው ማንንም አስተናጋጅና ዐቃፊ በመሆናቸው ነው። የኢትዮጵያዊነት ዐቃፊነት፣ ኢትዮጵያ ከተባለው ግዙፍ ምድር መጥቆ ወሰኑንና ድንበሩን ዐልፎ፣ ለሌላውም ዓለምና ሕዝብ ተትረፍርፏል። የዓለም፣ በተለይም ጭቁንና ጥቊር፣ ሕዝብ በምዕራባውያን መብቱ ተጨፍልቆ ይኖር በነበረበት ወቅት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግሉን ድምፅ፣ በያለበት ሲያክላላው፣ ሲያስተጋባው፣ ሲያክለውና ሲያንረው ቈይቶ፤ የኋላ ኋላ ግቡን ለመምታት የበቃው በኢትዮጵያዊነት ዙርያ በመሰለፍና በመሰባሰብ ነው። ኢሕአዴግ በተቃራኒ በባሕርዩ ከፋፋይ፣ በልዩነት ላይ ያተኰረ፣ በጥላቻ መሠረት ላይ የተካበ፣ የጐጠኞችና የአገር ከሓጂዎች ጥርቅማጥርቅም ነው ማለት ይቻላል። ብዙዎች የሚሳሳቱት ኢሕአዴግን እንደፖለቲካ ድርጅት እያዩ ነው። ኢሕአዴግ የተፈጠረው የኢትዮጵያን ጥፋት ከኋላ ሁነው ይሸርቡ በነበሩት በውጭ ኀይሎች ሤራና ምክር ሲሆን፣ በእጁ ጠፍጥፎት ህልውና የሰጠው ግን፣ የታላቂቷ ትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ (ሕወአት) ነው። ሕወአት በኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት አያምንም።
Tagged with: , , , , , , , , , , , , ,
Posted in Ethiopian News

የህወሓት ህልም የሞንጆሪኖ ቅዠት

የህወሓት ህልም የሞንጆሪኖ ቅዠት ፦ $bp("Brid_45999_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-1342151145932603.mp4", name: "የህወሓት ህልም የሞንጆሪኖ ቅዠት", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/FB_IMG_1534863512975.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); ” ኢትዮጵያ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን አቅጣጫ ስታ በውድቀት ቁልቁለት ላይ ተቀምጣለች ፤ … መፍትሄው ደግሞ ወደ ቦታችን መመለስ ነው ። ” . ታጋይ ወ/ሮ ፈትለወርቅ/ሞንጆሪኖ/ በ6ኛው የመለስ ሙት አመት የተናገሩት ። . . ለመሆኑ ወ/ሮ ሞንጆሪኖ በማን ፈቃድ ነው እንደገና ወደ ቦታቹ የምትመለሱት ?….ከዚያ ከደደቢት የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጨለማ የወጣው ሕዝብ ዳግም ወደዚያ ገሃነም ለመግባት እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ይመስሎታል ? … ለማነኛውም ይህ ሐሳብዎ ቅዠት ስለመሆንና አለመሆኑ እስቲ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያብሰልስሉት ። . አብዮታዊ ዲሞክራሲያቹ ሞቷል ፤ የመተ ደግሞ ሲነሳ አላየንም ። . ” አንሰራርተን ዳግም በቤተመንግስት እንከሰታለን ። ” ብሎ የማመን መንፈስ ካላቹ ፤ … ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ” መለስን ከሞት አስነሳለሁ ። ” በማለት ሲያውጅ የነበረውን እስራኤል ዳንሳም እመኑት ። ሜሮን ፋሲል
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ማሻሻያዎችን ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ

ሕወሓት በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ማሻሻያዎችን ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በመተዳደርያ ደንቡ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ ለማድረግ ረቂቅ ሰነድ ማዘጋጀቱን፣ ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ በሚካሄደው በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔም ተወያይቶ እንደሚያፀድቀው ተጠቆመ፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች ለሕወሓት አባልነት የመመልመያ መሥፈርቶች፣ ለድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለመመረጥ የዕድሜና የአገልግሎት ዘመን ገደቦችን የተመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡ በድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነትን በተመለከተ ሁለት ማሻሻያ ሐሳቦች የቀረቡ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የሚመረጥ ሰው ዕድሜው ከ20 ዓመት በላይ መሆን እንዳለበትና ከአራት የጠቅላላ ጉባዔ ዓመታት (ከስምንት ዓመታት) በላይ ማገልገል እንደማይችል፣ ረቂቅ የማሻሻያ ሰነድ መቅረቡን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነትን በተመለከተ ሌላው በረቂቁ የተካተተው ማሻሻያ፣ ዕድሜው ከ65 በላይ የሆነ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መመረጥ እንደማይችል፣ በማዕከላዊ ኮሚቴ በማልገል ላይ የሚገኝ ከሆነም እንዲለቅ አስገዳጅ የዕድሜ ገደብ ሆኖ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡ የሕወሓት አባል ለመሆን አዲስ የተካተተው መመዘኛ ፍላጎት ያላቸውን በሙሉ ማካተት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው አገር ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ የሚኖር የትግራይ ተወላጅ፣ ወይም በትግራይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የድርጀቱ አባል መሆን እንዲችል በማሻሻያነት ቀርቧል፡፡ ከድርጅቱ መባረርን ከሚያስከትል ጥፋቶች መካከል አዲስ ማሻሻያ ሆኖ እንዲገባ የተደረገው ሐሳብ፣ ከጥቅም ጋር የተገናኘ ቡድናዊ ዝምድናን በመፍጠር አስተሳሰብን በሚቃረን ላይ ጥቃት መሰንዘር፣ ወይም በተቃራኒው ይጠቅማል የተባለ ወገንን ደግፎ መከላከል፣ ከፍተኛ የዲስፕሊን ጥፋትና ከድርጅቱ የሚያስባርር ጥሰት ሆኖ በማሻሻያነት መቅረቡን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ከሕወሓት ጽሕፈት
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኦህዴድና ትህነግ(ሕወሓት) በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው)

ኦህዴድና ትህነግ በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው) ~በእነ አብይ መንግስት ላይ ግንባር ቀደሙ አማፂ ትህነግ/ህወሓት ነው። ለዚህ ስራው የቀን ጅብ የሚል ስም ተሰጥቶታል። ከወንጀሉ ሁሉ በስተጀርባ አለበት እየተባለ ነው። ዶክተር አብይ አህመድ በሚኒሶታ ለተነሳለት ጥያቄ ከአንዲት ከሁለት የትግራይ ተወላጆች የተነሳለትን ጥያቄ ከትህነግ/ህወሓት የመጣ እንደሆነ አድርጎ መልሷል። ዶክተር አብይ አህመድ በሰጠው መልስ ከትህነግ ጋር እልህ ውስጥ እንደገባ በግልፅ ያሳየ ነበር። ~ዶክተር አብይ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ በሶማሊ ክልል ለተፈፀመው ጭፍጨፋም የጅቦቹ እጅ እንዳለበት ከመገመቱ ባለፈ ፌደራል መንግስቱ በገዳዮቹ ላይ እርምጃ እንዳይወስድ በግልፅ መግለጫ የሰጠው ትህነግ ብቻ ነው። ትህነግ እንደፈለገ በሚጋልበው በሶማሊ ክልል ፕሬዝደንት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ፌደራል ስርዓቱን እንደሚያፈርስ አድርጎ ሲያስፈራራ ቆይቷል። ~ዶክተር አብይ አህመድ እና መንግስቱ በሶማሊ ክልል ለተፈፀመው ጭካኔ የሚገባውን ሳያደርግ አልፎታል። ጭራሹን በዚህ ወቅት ዶክተር አብይ በህይወት የመኖሩ ጉዳይ ሲያጠራጥር ቆይቷል። ታፍኗል፣ ታግቷል ከማለት አልፎ በሕይወት አለ ወይ ሲባል ሰንብቶ በይፋ የታየው ደብረፅዮን ጋር ነው። ~ የግል ፀብ ያላቸው ያህል ማዶና ማዶ ሆነው አብይና ደብረፅዮን ከአብይ መጥፋት በኋላ አብረው መታየታቸው እንዲሁ የሚታይ አይደለም። በእርግጥ ዶክተር አብይ አህመድ “አንተም ተው፣ አንተ እረፍ” ብትል ከምትሰማው አሜሪካ ከርሞ ነው የመጣው። እነ ደብረፅዮን ወደ ኤርትራ ቢያንጋጥጡም ኢሳያስ “ከዛው እርጉ” ብሏቸዋል። የትህነግ እና ኦህዴድ ግብግብ የዝሆኖች ግጥሚያ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ደብረፅዮን ከዶክተር አብይ ጋር ብቅ ብሏል ~ዶክተር አብይ አህመድ እና ደብረፅዮን አንድ ላይ የታዩት
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሶማሌ ላንድ ተዘርፈው ከሀገር ሲወጡ የነበሩ 6 ሲኖ ትራክ መኪኖችን በቁጥጥር ስር አዋለች

ሶማሌ ላንድ :- ተዘርፈው ከሀገር ሲወጡ የነበሩ 6 ሲኖ ትራክ መኪኖችን በቁጥጥር ስር አዋለች በዛሬው እለት ሰሞኑን ከጅግጅጋ የተዘረፉ 6 ሲኖ ትራክ የጭነት መኪናዎች ከኢትዮጵያ ውጪ ሶማሌ ላንድ ውስጥ ከ80 ኪ/ሜ በላይ እንደተጓዙ አረብ ሲዮ በምትባል ቦታ ላይ በሶማሌ ላንድ የጦር ሰራዊት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተዘረፉት የጭነት መኪናዎቹ ሶስቱ የግለሰቦች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ የትግራይ ልማት ማህበር መሆናቸውን ጎናቸው ላይ በተለጠፉ ፖስተሮች ማረጋገጥ ተችሏል። የሶማሌ ላንድ መንግስት ቀጠናውን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንደሚሰራና – በተለይም በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፅመውን የክልሉ ፕሬዘዳንት አብዲ ኢሌን ከእኩይ ዓላማ ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግስት በሚወስደው እርምጃ ሶማሌ ላንድ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደሚቆም ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መበታተን እና መከባበር ምን እና ምን ናቸዉ? ( ከታየ ደንዳና)

ከታየ ደንዳና መበታተን እና መከባበር ምን እና ምን ናቸዉ? መቀሌ በተካሄደዉ ሰልፍ ላይ ዶር ደብረፅዮን ንግግር ሲያደርጉ “መከባበር ወይም መበታተን” የሚል ሀረግ ተጠቅሟል አሉ። አሉ ያልኩት በቀጥታ ባለመስማቴ ነዉ። ይህ አባባል ማህበራዊ ሚዲያዉ ላይ በሰፊዉ ይመላለሳል። አንዳንዱ ሀረጉን እንደመፈክር በመያዝ ፎክሮ ማስፈራራት ይከጅላል። ሌላዉ ደግሞ በአባባሉ ተናዶ ይከራከራል። “እሰይ ተገላገልን!” የሚሉም በርካታ ናቸዉ። ስለዝህ በጉዳዩ ላይ ግልፅነት መፍጠር ይበጃል! ከመከባበር እንጀምር። መከባበር ለአንድነት መሠረት ነዉ። በዝህ ላይ ዶር ልክ ብሏል። አንዱ ጌታ ሌላዉ ባሪያ ሆኖ አንድነት የለም። ሁላችንም በፍቅር እና በሠላም አብረን ለመኖር መከባበራችን ግድ ነዉ። ችግሩ “መቼ እና በምን ላይ እንከባበር?” የሚለዉ ነዉ። ይህ በደንብ መታወቅ ያለበት ይመስለኛል። አንዳችን የሌላችንን ህጋዊ መብት እና ጥቅም ማክበር ተገቢ ነዉ። ነገር ግን አንዱ ሌላዉ አናት ላይ ወጥቶ “ዉረድልኝ!” ሲባል “ባለሁበት አክብሩኝ!” የሚል ከሆነ ልክ አይመጣም። የሀገር ሀብትን ዘርፎ እና ሰርቆ በዉጭ እና በዉስጥ ካከማቹ በኀላ ” የያዝነዉን ይዘን እንከባበር!” ማለት እንዴት ይሆናል? ዘራፊ፣ ገዳይ እና ሌባ ተሰብስቦ “ስሜን ካነሳችሁ ዋ!” ካለ መከባበር በምን ስሌት ይፈጠራል?መከባበር እዉን የሚሆነዉ በህግ የበላይነት ማዕቀፍ ዉስጥ ነዉ። ይህ ደግሞ ወንጀለኛን ለፍርድ ማቅረብ እና ተጎጂን መካስ ይጠይቃል። ህግን ማክበር እና ማስከበር ለመከባበር መሠረት ይሆናል። ህግ ካልተከበረ ህገ-ወጥነት ህግ ይሆናል። በህገ-ወጥነት ዉስጥ ደግሞ መገፋፋት ይኖራል። ከሁሉም ነገር በፊት በዝህ ጉዳይ መተማመን ያስፈልጋል። ካላከበራችሁኝ ሀገር እበታትናለሁ ማለት ግን አስገራሚ ነዉ።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሓት ወልቃይት ላይ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ ከሽፎበታል!

ትህነግ/ህወሓት ወልቃይት ላይ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ ከሽፎበታል! ትህነግ/ህወሓት ዛሬ ሀምሌ 22/11-2010 በወልቃይት አዲረመጥ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ ነሸር። ሆኖም የወልቃይት አዲረመጥ ከተማ ሕዝብ ሰፊ የሆነን ተቃውሞ ስላጋጠመው ሰልፉ እንደታሰበ በአደባባይ ሳይካሔድ ቀርቷል። ከ50 በማይበልጡ የትህነግ/ የህወሐት ካድሬዎች በአዳራሽ መወያየታቸው ተገልፆአል። ሰልፉ የከሸፈው የከተማው ሕዝብ አድማ በማድረጉ መሆኑ ታውቋል። በስብሰባውም “የወልቃይት ሕዝም ለምን እምብይ አለ? ብለው መወያየታቸውም ታውቋል። ለዛሬው ሰልፍ የወልቃይት ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች በሰልፉ እንዲገኙ፣ ካልተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዛቻ የደረሰባቸው ቢሆንም ትህነግ/ህወሓት ባሰበው መንገድ ሰልፍ እንደማይሳተፉ መግለፃቸው ታውቋል። “ወልቃይት አማራ ነው! ለውጡ እና የለውጥ ሐይሉም እንደግፋለን!” የሚል መፈክር ይዘን መውጣት የምትፈቅዱ ከሆነ ሰልፉን እንቀላቀላለን በማለታቸው ከትህነግ ካድሬዎች ጋር አልተስማሙም። ሰራተኞቹ “እናንተ በእኛ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። የእኛ ትክክለኛ እና እውነተኛ አቋማችን በማንገልፅበት እና በማይንፀባረቅበት ሰልፍ አንገኝም፣ አንሰለፍምም” በማለት ከሰልፉ ሳይገኙ ቀርተዋል። የትህነግ/ህወሓት ካድሬዎች “ወልቃይት የትግራይ ነው፣ ጎንደር ያሉት የወልቃይት ኮሚቴዎች አይወክሉንም” የሚል መፈክር አሳትመው ሰልፍ ለመውጣት ቢጥሩም ሕዝቡ የስራ ማቆም አድማ በማድረጉ ሰልፉ ሳይሳካ ቀርቷል። ሰልፉ የከሸፈባቸው የትህነግ ካድሬዎች በአዳራሽ ለመወራረት ተገድደዋል ተብሏል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት ሰዎች የጠ/ሚ አብይ አህመድ አመራር ላይ ያላቸውን ተቃዉሞ በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ – በሌብነት እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል።

ወያኔዎች ዘውትር በትግራይ ክልል ድጋፍ ሲዳከምባቸው የሀውዜንን ጭፍጨፋ ካርታ መሳብ ስራቸው ነው ።ግን እስከ መቼ ይቀልዳሉ የሚገርመው ዛሬም የሰማእታትንና የሀውዜንን ካርድ ጆከራን ስበው ማየት ያማል እስኪ ተመልከቱ ዛሬ መቀሌ ላይ የተካሄደው ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ ወይስ የቀብር ስነስረዓት ? ሰላማዊ ሰልፍ ሲከለክሉ የነበሩት የትህነግ አመራሮች እንደዚህ አይነት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ ያመቻቸው የጠሚ አብይ አህመድ አመራር ላይ ያላቸውን ተቃዉሞ በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ። Vicious!!! ባንድ በኩል የቀድሞ ሰልፍ ከልካዮች በተከፈተው ሰልፍ የመውጣት እድል ተጠቃሚ በመሆን ልብ ሳይሉ ለዶ/ር አብይ አመራር እዉቅና ሲሰጡና ከዚህ ቀደም የገነቡት ስርኣት አፋኝ እንደነበር ራሳቸውን ሲያጋልጡ ዋሉ። TPLF በሌብነት እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰልፍ ከልካይ የሆነውን የመለስን ፎቶ እዚህ ላይ በመያዝና እንዲ ያለ ሰልፍ የሚፈቅድን አመራር በተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ የመቃወም አዙርት ዉስጥ ሲዳክሩ ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፍን በሰላማዊ ሰልፍ መቃወም ምን የሚሉት ዝቅጠት ነው። በሌብነት እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል። የኢንሳ ባለስልጣን የነበረውና በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተከሰሰው ቢኒያም ተወልደ የተባለው የሕወሃት ሰው እንዲፈታ ጠይቀዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በርካታዎች የሰልፉ አላማ ያልገባቸውና የተሰጣቸውም መፈክል ያላገናዘቡ ከመሆን ተጨማሪ ለዶክተር አብይ አሕመድ ድጋፍ ሰልፍ አለ የሚል ፕሮፓጋንዳ ከተማ ውስጥ ተሰራጭቶ እንደነበር ተጠቁሟል። በተጨማሪም ስልጣን ላይ እያሉ ሰልፍ ከተካሄደ ሰልፈኞች ይገደሉ ይደበደቡና ይታሰሩ የነበረ ሲሆን በዛሬው የመቀሌ ሰልፍ ላይ ግን ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ተጠብቆ ሀሳባቸውን ገልጸው ወደ ቤታቸው ገብተዋል። በመሆኑም
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሃትና የቀበሌው ፖለቲካው ( ዳንኤል መኮንን )

ህወሃትና የቀበሌው ፖለቲካው ( ዳንኤል መኮንን ) በረዥሙ የሀገራችን ታሪክ ባላባቶችና መሳፍንቶች በደናው ጊዜ ያሻቸውን አድርገው ነገር ግን ለስልጣናቸውና ለወንበራቸው ተግዳሮት ሲገጥማቸው ወደ ቀበሌያቸው ተመልሰው እራሳቸውን ለማስመለጥ በህዝባቸው ስም መነገዳቸው አዲስ አይደለም፡፡ ከዘመናዊው ታሪካችን ወዲህ ጀምረን ብናይ እንኳን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መሳፍንት #የእኔ (ህዝቤን ያሉበት ቀን እንኳን የለም) የባላባትነት መብት ካልተጠበቀ ሀገር ትፈርሳለች እያሉ ህዝብ ሲያስጨርሱና ሲያጫርሱ ነበር፡፡ ይህ የመሳፍንቱና የባላባቶች ደካማ አካሄድ እንደ ሀገር ዛሬ ላለንበት ኃላ ቀርነት ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ ዛሬ ግን ይህ የሚሰራ አይመስልም፡፡ የህወሃት የብዝበዛና የመጨቆን ፍላጎትና መብት ስላልተጠበቀ ኢትዮጲያ ወደ ብጥብጥና መበታተን አታመራም፡፡ ህወሃት ከፈለገች በሰላም ወደ ፈለገችበት መሄድ ትችላለልች፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ ዋና አካል የሆነው የትግራይ ህዝብ ግን ስለ ህወሃትን ብሎ ሂድ እንኳን ብትለው የትም አይሄድም ምክንያቱም ልክ እንደ ጥንቱ በህወሃት ዘመንም ባላባቶቹ ህወሃቶች እንጂ የትግራይ ህዝብ ምንም የተለየ ነገር አላገኘም፡፡ የትግራይ ህዝብ ለረዥም ዘመናት ለባላባቶች ጥቅምና ክብር ሲል ውድ ልጆቹን መገበር ሰልችቶታል፡፡ የዶ/ር የደብረ ጺዮን የዛሬው ከንቱ ጩኸት የህወሃት የመጨረሻ ሰአት የጣር ደምጽ እንጂ ምንም የተለየ ትርጉም የለውም፡፡ ያው የአፍሪካ ፖለቲካ ስለሆነ በቶሎ እጅ አይሰጥም፡፡ ትንሽ ይፈራገጥ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የህወሓት ድህረ ገጾች የጥላቻ ዘመቻ

የህወሓት ድህረ ገጾች የጥላቻ ዘመቻ (መንግስቱ ሙሴ) አንዱ አረስት በ tigraionline.com የተለጠፈ እንዲህ ይነበባል። “Abiy Isaias’s futile attempt to isolate the Tigrai people and TPLF will lead to dead end” ከእርዕሱ ግርጌ እንዲህ የሚል ጽሁፍም አለ። “The Abiy administration and Isaias Afwerki’s attempt to isolate the people of Tigrai and the Tigrai state government is futile. Since he was elected by the EPRDF ruling part as a prime minister of Ethiopia, Dr. Abiy Ahmed has been rushing major domestic and foreign policy decisions haphazardly like there is no tomorrow.” ሲተረጎም ቃል በቃል ሳይሆን ዋና መንፈሱ ዶክተር አብይ አህመድ እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የትግራይን ሕዝብ ያገለለ ግንኙነት አድርገዋል ነው። አብይ የተቻኮለ የውጭ ፖሊሲ እና አገራዊ ህግጋትን እየቀየረ ነው ይላል። ወረድ ብሎ በዚሁ እርእስ ስር እጅግ አስገራሚ እና ስላቅ ያስቀምጣል። “Domestically Abiy Ahmed is doing everything he can to consolidate his grip in power by any means necessary including working directly and indirectly with many extremist groups. He is slowly undoing what was achieved in the past 27 years by the previous EPRDF governments and the Ethiopian people in general.” የሀገር ውስጥን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ለመቀየር እና ስልጣኑን በየትኛውም መልክ ለማጠናከር የሚችለውን ሁሉ እየተጠቀመ ነው። አላማውን ዳር ለማድረስ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከጽንፈኛ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ስብሐት ነጋ በዘረፋ የተገነባውን ኤፈርትን ወደ ትግራይ ሕዝብ ይዞታ ማዞር የሚለውን ሐሳብ ተቃወመ።

አቶ ስብሀት ነጋ የኢፈርት ሀብት የትግራይ ህዝብ በአክስዮን ባለቤትነት ይያዝ በሚል አጀንዳ የማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባ ረግጦ ወጣ!!! በመቀለ ከተማ በትግራይ ክልል ርእሰከተማ በስልጣን ያለው የህወሓት ማ /ኮ እና በተለያዬ ምክንያት በጡሮታ ፣በብቃት ማነስ ፣በሙሱና ወዘተ ተሰናብተው የነበሩ ቡዱኖች ተሰብስበው ኤፈርት በማን ባለቤትነት ይያዝ የሚል አጀንዳ በዶክተር ደብረጽዮን ቀርቦ ሲያበቃ ቤቱ ለሁለት ተካፋፈለ ። 1 ኛ . የዶክተር ደብረጽዮን ቡዱን የኢፈርት ደርጅቶች እስከ ኣሁን የሀሜት ምንጭ ሆነው ስለቆዩ ለወደፊት ባለው ጥሬ ገንዘብ የተቸገሩ አካል ጉዳቶኞችና የተዳከሙ ያለኣንዳች ድጎማ የተባረሩ ደካማ ታጋይ ነበር እናቋቁምበት ። 2ኛ የቀረው ሀብት ግን በኣክስዮን ሸር በባለቤትነት በህዝብ እጅ ሆነው ትርፉ በየአመቱ ኦዲት እየተደረገ ሌላ ተቃማት እየፈጠረ የትግራይ ህዝብ መሆኑ በህግ እናስረክበው በነዚ ድርጅቶች የህዋሓት ማ/ኮሚቴ እጁ ማስገባት የለበትም ሲሉ የነስብሀት ነጋ ቡዱን እነ ኣባይ ጸሃዬ ፣ ስዩም መስፈን ስብሀት ነጋና ተከታዮቻቸው ግን የኤፈርት ሀብት በማናቸውም መስፈርት የትግራይ ህዝብ ሀብት አይደሉም በማለት ደረቅ ኣቋም በመያዝ ይህ ሀብት የህወሓት ማክላይ ኮሚትቴ ነው ብለዋል ። በመጨረሻ እነደኩተር ደብረጽዮን የኤፈርት ተቃቋማትና ባገር ውስጥም በማናቸውም ቦታ ይኑር የኢፈርት ባለቤትነት ነበር ፣ ለወደፊትም በህዝብ የአክስዮን ሸር ባለቤትነት ሊሆን ነው ብለው ኣቋም ሲወስዱ ፣ ኣቶ ስብሀት ነጋ ግን እንግዳውስ ተቋሟቱ ወደ የህዝብ ባለቤትነት ይሁኑ ካላቹሁ በእኔ ስም የሚታወቅ እጅግ ቡዙ ሚሊን የሚገመት ከንዘብ በእኔ ስም ኣለኝ ለእናንተ ኣላስረክብም የራሴ ሀብት ነው በማለት ስብሰባ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሕዝብ ላይ ወንጀል የሰራሁት ጌታቸው አሰፋ አስገድዶኝ ነው ሲል የሶማሌ ክልሉ አብዲ ኢሌ ተናገረ።

በሕዝብ ላይ ወንጀል የሰራሁን ጌታቸው አሰፋ አስገድዶኝ ነው ሲል የሶማሌ ክልሉ አብዲ ኢሌ ተናገረ። አብዲ ኢሌ የክልሉን ፓርላማ አመታዊ ስብሰባ ሲከፍት ባደረገው ንግግር በክልሉ የተፈፀመውን ወንጀል በሙሉ በቀድሞ የደሕንነት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ አድርጎታል። የቀድሞ ደሕንነት ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጭንቅላቴ ላይ ሽጉጥ ደቅኖ የሚያዘኝን ነገር ሁሉ እንድፈፅም ያስገድደኝ ነበር ሲል ፓርላማውን በተለሳለሰ አንደበት አጭበርብሯል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚነስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ባለቤትን ወይዘሮ ሮማንን አግቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያስፈራራና እንደፈለገም ያዘው ነበር ሲል የጌታቸው አሰፋ ወንጀል ካላቸው ውስጥ አንዱን ተናግሯል። ዶክተር አብይ ኢትዮጵያን ለማዳን ከፈጣሪ የተላኩ ናቸው ።እንደ ዶክተር አብይና ለማ መገርሳ ጥሩና መልካም ሰወች አይቼ አላውቅም ብሏል አብዲ ኢሌ ። የኔ ስልጣን መልቀቅ በሰፊው እየተናፈሰ ያለው በጌታቸው አሰፋ ተላላኪዎች በኩል ሲሆን ይህን ተገን አድርጎ በክልሉ የገንዘብ ዘረፋ ለማካሔድ ነው ሲል ተናግሯል። የሕወሓት ሰወች በሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እንድናደርስ ተጠቅመውብናል ያለው አብዲ ኢሌ ከአሁን በኃላ በይቅር ባይነት ሁላችንም ተደምረን ወደ ልማት ፊታችንን ማዞር አለብን ብሏል ስብሰባው ነገም ይቀጥላል። Somali Region parliament starts meeting today. Abdi Iley spoke and here is the key messages in his address: – All the mistakes I committed is because of Getachew Assefa, former chief of Intelligence – Getachew Assefa held gun on our head and asked us to do what he wants – He was the
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራ-ጠል ደዌ የህወሃት ብቻ ህመም አይደለም ( መሥከረም አበራ )ቸ

አማራ-ጠል ደዌ የህወሃት ብቻ ህመም አይደለም ዛሬ እግሯ ገደል የገባው ህወሃት ከተፈጠረች ጀምሮ በተቆራኛት አማራ-ጠል ደዌ ስትሰቃይ የኖረች ንኡስ ፍጡር ነች፡፡ይህ በሽታ ግን ህወሃትን ብቻ የሚያሰቃይ አይደለም፡፡ይልቅስ ፈውስ በሌለው የዘረኝነት ልክፍት የተለከፉ ፖለቲከኞችን ሁሉ የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሞት አፋፍ ላይ ያለችውን ህወሃት ከሞት ሊመመልሳት ባይችል እንኳን በጣር የመፈራገጧ ጊዜ እንዲረዝም የሚያስችሏትም የእነዚሁ የበሽታ ተጋሪቿ እርዳታ ይመስለኛል፡፡ የአማራ ጥላቻ በብዙ መንገድ ይገለፃል፡፡ ለምሳሌ የህወሃት ባስልጣናት እና የአረና አክቲቪስቶች የወንዛቸው ልጆች መሳሪያ ተደግፈው ከተቀመጡበት ወንበር በአፍጢማቸው የደፋቸው የኦቦ ለማ እና የጠ/ሚ/ር አብይ ኦህዴድ ሆኖ ሳለ አምርረው እየወቀሱ ያሉት በስንት ግፊያ መላወስ የጀመረውን አማራውን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን እና “አለ ሞቷል?” እያልን ስንወራረድበት የኖርነውን ፓርቲያቸውን ብአዴንን ነው፡፡ የኢንሳው ሰውየ እንደውም “የኦህዴድ እና የኦሮሞዎች ችግር ስስ ነው የብአዴን እና የአማሮች ችግር ነው የደደረው” ብለው መቃብር ብቻ የሚለየውን አማራን ሁልጊዜ የመጥላት በሽታቸውን አስመሰከሩ፡፡ ይህ በሽታ የህወሃቶች እና ትግሬ አክቲቪስቶች ብቻ ስላልሆነ ባለፈው ሳምንት ዶ/ር አወል ቃሲም (ምክንያታዊ ይመስለኝ ነበር) በሃገሩ ላይ ከተደረገው ሰልፍ ሁሉ የባህርዳሩ ሰልፍ ላይ ተይዞ የተወጣው ባንዲራ የአሮጌውን አብሮነት ምልክት አየሁበት ብሎ ተብሰለሰለ፡፡ አዛውንቱ ዶ/ር ነጋሶ ደግሞ ዛሬ የሆነ መፅሄት ላይ ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስ የባህር ዳሩ ሰልፍ የለየለት የህገ-መንግስት ጥሰት ነው ሲሉ “ስለፃፍኩት ተፀፀትኩ” ላሉት ህገ-መንግስት ጠበቃ ሆነው ብቅ አሉ፡፡ በዚህ ቃለ ምልልስ ከዶ/ር ነጋሶ ጋር የተገናኘው ሰውየ ጋዜጠኛ መሆኑን እጠራጠራለሁ! ዶ/ር
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተሃድሶ መድረኩ በኦህዴድ የስልጣን ጥማት በስርዓቱ እና በተቀመጠለት አቅጣጫ ባለመሄዱ ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ ነች ~ ዶ/ር ደ/ፅዮን ገ/ሚካኤል

“ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ ነች” ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት የትግራይ ምክትል ርእሰ መስተዳድር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከትግራይ ከያንያን እና የሚድያ ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ ውለዋል። ዶክተር ደብረፅዮን ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳብ ላይ ሀገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ ቆም ብሎ ማሰብ የምያስፈልግበት ነው ብለዋል። ኢህአዴግ በተሃድሶ ግዜው ያስቀመጣቸው የለውጥ መንገዶች ከሞላ ጎደል መልካም ነገር የታየባቸው ቢሆኑም በጣም በርከት ያሉ ጉዳዮች ደግሞ በተፈለጉበት መንገድ አለመሄዳቸው አብራርተዋል። ዶክተሩ እንዳሉት “ለምሳሌ በእስር የነበሩ ወንጀለኞች የሚፈቱበት አቅጣጫ ያስቀመጥን ቢሆንም የፀጥታ ሀይል የገደለ ይፈታ ግን አላልንም። ምክንያቱም ህገ ወጥነት ነው” ብለዋል። በተሃድሶው ጊዜ ከአራቱ የኢህዴግ አባል ድርጅቶች ተሃድሶው በሚገባ እና ለትግል በሚጋብዝ መልኩ የመራው ህወሓት መሆኑ ገልፀው ግምገማው ደግመው እንድያዩት የተደረጉ ኦሆዴዶች እንደነበሩም ገልፀዋል። ዶክተር ደብረፅዮን በማብራርያቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን እለቃለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በኦሆዴድ የታየ የሀላፊነት መቀያየር ሩጫ፤ ከፍተኛ የስልጣን ጥማትን የምያሳይ እና አሁን እየታየ ላለው ችግር መነሻ መሆኑም ገልፀዋል። በተለይም አሁን አሁን እየታዩ ያሉት የድጋፍ ሰለማዊ ሰልፎች ህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የሚፃረሩ መልእክቶች እየተላለፉበት ያሉ መሆኑም ገልፀዋል። ህገወጥ መልእክቶቹም መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል። ዶክተሩ በንግግራቸው በማነኛውም የአገራችን ህዝብ ያለ የመለወጥ እና የመልማት ፍላጎት በማነኛውም መልኩ መደናቀፍ የለበትም። እሳቸው እንዳሉት ከአማራም፣ ከኦሮሞም፣ ከደቡብም፣ ከሶማሌም፣ ከዐፋርም ወዘተ አብሮ መስራት የምያስችል ዲሞክራስያዊ ሀይል ስላለ ነገሮች የሚስተካከሉበት መንገድ ማፈላለግ ይገባል። ጥንቃዌም
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሱዳን ወረራ ጀርባ ያለው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ሲጋለጥ (ጌታቸው ሺፈራው)

ከሱዳን ወረራ ጀርባ ያለው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ሲጋለጥ (ጌታቸው ሺፈራው) ከሶስት ቀን በፊት ሱዳን ውስጥ የሚኖሩ የወልቃይት አማሮች ከሚቀርቧቸው የሱዳን ባለሀብቶች አንድ መረጃ ይደርሳቸዋል። በአንድ ወቅት ባዕከር የሚባል ቦታ መምህር የነበርና በወልቃይት አማሮች ላይ ጥቆማ እያደረገ በማሳሰር ለትህነግ በዋለው ውለታ ትህነግ የፀጥታ ኃላፊ ያደረገው ተኪ ተኩ በአዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደሰነበተ ይነግሯቸዋል። ይህን ጉዳይ እኔም ትናንት ምሽት ዘግቤው ነበር። ተኪ መተኩ ትህነግ ምዕራብ ትግራይ የሚለው ወልቃይት ዞን ፀጥታ ኃላፊ ሲሆን ገዳዲፍ፣ ገላባትና አዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች በመዞር የትህነግ ደህንነቶች ጋር በመሆን የአማራ ገበሬዎች ላይ ጦርነት እንዲከፈት ሲያደራጅ ሰንብቷል። የሱዳን ባለሀብቶች ለሱዳን ጦር ቀለብ እስከቻሉ ድረስ የጠየቁት የሰራዊት ይሰጣቸዋል። የዚህን ውጊያ ዋጋም ተኪ የተባለው የትህነግ የፀጥታ ሀላፊ ገንዘብ ከፍሎ መመለሱን የሱዳን ባለሀብቶች ለወልቃይት ተወላጆች ተናግረዋል። በጉዳዩ መሳተፍ ያልፈለጉት ባለሀብቶች “ከእናንተ ጋር ሊያጋጨን ነው” ሲሉ ቀድመው አሳውቀዋል። የትህነግ የዞን ፀጥታ ሀላፊ ተኪ አስተባባሪነት የተደረገው ዝግጅት ሲጠናቀቅም፣ ለትህነግ ተባባሪ በሆኑ ባለሀብቶች በኩል በሶስት አቅጣጫ ጦርነት ተጀምሯል።በቋራ፣ በመተማ ቁጥር አንድ እና በጓንግ በኩል የታቀደው ጦርነት በቋራና በመተማ በኩል ተጀምሯል። በቋራ በኩል የአማራ ገበሬዎች አንድ የሱዳን ፓትሮልን መማረክ ሲችሉ፣ በመተማ በኩል የተከፈተ ጦርነት የብዙ ገበሬዎችን ህይወት ቀጥፏል። በጓንግ በኩል ገበሬዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተዘጋጀ የሱዳን ጦር እንዳለ ታውቋል። በአማራ ገበሬዎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ያለው የሱዳን ሰራዊት ከባድ መሳርያ የታጠቀ ሲሆን ገበሬዎቹ ያዙት አጭር ርቀት መሳርያ ነው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ መኳንንት ተረጋጉ “ሁሉም አይደለም….” (መስከረም አበራ )

የትግራይ መኳንንት ተረጋጉ “ሁሉም አይደለም….” (መስከረም አበራ ) የትግራይ ህዝብ እና የህወሃት ነገር ብዙዎቻችን “ትግሬ ሁሉ ህወሃት ነው” ወይም “ህወሃት የትግራይን ህዝብ አይወክልም” እያልን ቀለል አድርገን እንደምናወራው ግልፅ ነገር አይመስለኝም፡፡ ነገሩ በጣም በጥንቃቄ እና ሃላፊነት በሚሰማው መንገድ መያዝ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ህወሃት መሄዱ እንደማይቀር ከበፊትም ይሰማኝ ነበርና ህወሃት ሲሄድ የትግራይ ህዝብ ከሌላው ወገኑጋር ባለው መስተጋብር ሊገጥመው የሚችለው ነገር ሳያሳስበኝ አልቀረም፡፡ እናም ስለጉዳዩ ለትግሬ ጓደኞቼ አጫውት ነበር፡፡ በተለይ ከትግራይ ወጡ ብለን አይን አይን እናያቸው የነበሩ አክቲቪስት እና ታጋይ ተብየዎች የታሰሩትም ከተፈቱ በኋላ፣ያልታሰሩትም የህወሃት እግር ወደገደል መግባቱን ካዩ በኋላ ክንብንባቸውን አውልቀው እንደቂጣ የነካከተ ምክንያት እያቀረቡ ህወሃት በካርቦን ሲመስሉ ነገሩ ይበልጥ ያሰጋኝ ጀመር፡፡ ቢቸግረኝ ከሁለት አመት በፊት አንዱን የትግሬ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነው አክቲቪስት “እስኪ ተረጋጋ! አንተኮ ከትግሬም ተቃዋሚ አለ እየተባልክ እንደመድሃኒት የምትጠቀስ ሰው ነህ:: እባክህ የትግራይ ወገኖቻችንን በራሳችን ችግር እና ጩኽት ውስጥ የምናይበት ድልድይ አታሳጣን፤ምክንያታዊ ሁን፣ ለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ፣ህወሃትን የሚያስመስሉ ነገሮች እያየሁብህ ነው፡፡ ትግሬ ሁሉ አንድ ነው የሚያስብለው እንዲህ ያለው የእናንተ ወንክርክር ንትርክ ነው” ብየ ልመና አይሉት ምክር ይሁን ማስጠንቀቂያ ላኩለት፡፡ መልሱ ምን ቢሆን ጥሩ ነው “ስድስት ነው አምስት ሚሊዮኑን ትግሬ የማይወድ እኔን ይወደኛል ብየ አላስብም” ብሎኝ ቁጭ አለ፡፡ የኔ ሃሳብ ለእሱ ያለንን ፍቅር አስመልክቶ አልነበረም፡፡ አልተግባባንም! ከዛ በሁዋላ ከእኔው ጋር ቅልጥ ያለ ንትርክ ውስጥ ገብተን አረፍነው፡፡ ለወትሮው ብንከራከርም ነገራችንን በቀልድ አሳርገን፤ የምናነባቸውን ነገሮች
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News

የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮችና የጦር ጄኔራሎች የታሰሩ የደሕንነትና የፖሊስ ባለስልጣናት እንዲፈቱ ጫና መፍጠር መጀመራቸው ታወቀ

* በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ቁጥር 30 ደረሰ፡፡ * የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮችና የጦር ጄኔራሎች የታሰሩ የደሕንነትና የፖሊስ ባለስልጣናት እንዲፈቱ ጫና መፍጠር መጀመራቸው ታወቀ * ለዶክተር አብይ አሕመድ እየተደረገለት ያለው ጥበቃ አሳሳቢ ነው ። ይህ ደግሞ እንደሃገር አስጊ ነውና ጥንቃቄ ያሻዋል ። ( ምንሊክ ሳልሳዊ  ) በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ ከፈነዳው ቦንብ ጀርባ እጃቸው አለበት ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ቁጥር 30 ደረሰ፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል እንዳስታወቁት ፖሊስ ከአደጋው ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ለመለየት የሚያደረገው ክትትል እንደቀጠለ ነው፡፡ ፖሊስ  6 ጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልፆ ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው አደጋ ክፍተት አሳይተዋል የተባሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ ዘጠኝ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 21 ዶክተር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆኑ ጀምሮ የሰሩትን የለውጥ ስራ ለማበረታታትና ለማመስገን በተጠራ ሰልፍ ላይ ሚሊዮኖች በተገኙበት የፈነዳውን ቦምብ ተከትሎ በፖሊሶችና በደሕንነቶች ሴራና ንዥላልነት የሆነ ነው በሚል ጥርጣሬ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣናትና የደሕንነት ሓላፊዎች ለምርመራ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል። ከፍተኛ የፖሊስና የደሕንነት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ምርመራው ላይ ተፅእኖ ከመፍጠር ጀምሮ የታሰሩት እንዲፈቱ ጫና እስከማድረግ ድረስ ሕገወጥ ተግባር መጀመሩን ለጉዳዩ ቅርብ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቦምብ በሻንጣ የጫነችው የፖሊስ መኪና (ፖሊስ ኢት 0384 ET) ሆን ተብሎ እንድትቃጠል ተደርጋለች።

መኪናዋ… ይህች ላንድክሩዘር መኪና (ፖሊስ ኢት 0384 ET) ከመቃጠሏ በፊት የፖሊስ ደንብ ለብስ የለበሱ ሰዎችን ጭና መስቀል አደባባይ ነበረች። ኋላ ላይ…ቦንብ ከፈነዳ በኋላ በውስጧ ቦንብ የያዘ ሻንጣ መገኘቱን ሰምቻለሁ። መኪናዋ ከመቃጠሏ በፊት መለያ ታርጋዋን ወጣቶች ገንጥለው ይዘውታል። ታርጋውን ከነገጠሉት ልጆች መካከል አንደኛው ልጅ ላንድክሩዘሯ የፖሊስ መኪና ውስጥ ቦንቦችና ሌሎችም ተቀጣጣይ ነግሮች እንደነበሩ ገልጾልኛል። መኪናዋን ማን እንዳቃጠላት አላወኩም። ባትቃጠል ኖሮ ተጨማሪ ማስረጃዎች በውስጧ ሊገኙ ይችል ነበር። የዛሬውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ያበቃለት ቡድን መሆኑን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

  የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሕወሓት ከእንግዲህ የማያንሰራራ ያበቃለት ቡድን ነው ሲሉ ተናገሩ። የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት ከእንግዲህ በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ያበቃለት ቡድን መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ  በኤርትራ ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል። “ አዲስአበባ ድረስ ታንክና መድፍ ይዘን የገባነው ለሁለቱ ህዝቦች ዘላቂ ጥቅም ስንል ነበር” ሲሉም ተደምጠዋል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት በኤርትራ ቴሌቪዥን በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በህወሃት አደፍራሽነት 25 አመታት የገጠማቸውን ኪሳራ የሚያስመልሱበት ግዜ ሩቅ እንዳልሆነም ነው የተናገሩት።
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ሊያደርጉት ያቀዱት ሰልፍ መሰረዙ ተሰማ።

  በሕወሓት ጥያቄ መሰረት የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ጉዳይ ላይ የወሰነውን ውሳኔ ለመቃወም የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ሊያደርጉት ያቀዱት ሰልፍ መሰረዙ ተሰማ። የተሰረዘው በደሕንነት ስጋት ነው ብለዋል። የሕዝብን ደሕንነትና ሰላም ሲገፉ ኖረው ዛሬ ተገልብጦ ለነሱ ስጋት መሆኑ አስገራሚ የፖለቲካ ሂደት ነው። የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች የኢሕአዴግ ምክር ቤት በባድመና በድንበር ከተሞች ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃውም በመስቀል አደባባይ ሊያደርጉት ያቀዱትን ሰልፍ መሰረዙን የሕወሓት አፈቀላጤ የሆነው ሆርን አፍየርስ በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል። በሕወሓት ጥያቄ መሰረት የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ በትግራይ ክልል የሚገኙ የድንበር ከተሞችን ለኤርትራ በ አልጀርሱ ስምምነት መሰረት አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን ለኤርትራ ይሰጣሉ የተባሉትም ባድመ ኢሮብ ፆረና ዛላንበሳን ጨርሞ አስራ ሰባት ወረዳዎች ሲሆኑ ይህንን በመቃወም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ ቄሮዎች ለሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች ማስጠንቀቂያ ሰጡ

ውድ የፊንፊኔ ከተማና በዙሪያዋ የሚገኙ ቄሮዎች =============================== የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች በአሁን ሰዓት በሀገራችን እየታየ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ለማደፍረስና የለውጥ ሂደቱን ለማደናቀፍ የተለመደ ሴራቸውን በመሸረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህ መሠረት በነገው ዕለት (ሰኔ 10/ 2010) የዶ/ር አብይን አመራር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ የህወሓት ደጋፊዎች እና ተላላኪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ያቀዱት ህዝባዊ ድጋፍና መሠረት ኖሯቸው ሳይሆን በዚህ አጋጣሚ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳትና የሀገር ውስጥና የውጪ ሚዲያ ሽፋን ለማግኘት፣ በዚህም የዶ/ር አብይን አመራርና የቄሮዎችን ስም ጥላሸት ለመቀባት ነው፡፡ በመሆኑም በነገው ዕለት የሚያደርጉትን የተቃውሞ ሰልፍ በማንኛውም መልኩ ማደናቀፍ አያስፈልግም፡፡ ከዚያ ይልቅ ሊደረግ የታቀደው የተቃውሞ ሰልፍ ያለ ምንም ችግር እንዲካሄድ በመፍቀድ፣ 1ኛ) በህገ-መንግስቱ የተደነገጉ ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ፣ 2ኛ) ህዝባዊ መሠረት እንደሌላቸውና ፋይዳ-ቢስ መሆናቸውን በአደባባይ እንዲያጋልጡ ማድረግ የሸረቡትን ሴራ ውድቅ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ በመቀጠል በቀጣይ ሳምንት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ታላቅ የሆነ የደጋፍ ሰልፍ በማካሄድ ለዶ/ር አብይ ያለንን ድጋፍ፣ “ለቀን ጅቦች” ያለንን ተቃውሞ መግለፅ ይቻላል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሃት መራሹ የትግራይ መስተዳደር የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ወነጀለው

ሕወሃት መራሹ የትግራይ መስተዳደር የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ወነጀለው ፤ አስፈራራው። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያስተላልፈው ጥላቻ መንግስቱ ሃይለማርያም በስልጣን ዘመናቸው መጨረሻ ከሚያስተላልፉት ፕሮፓጋንዳ ጋር አንድ አይነት ነው ሲል ሕወሓት ሚዲያውን ወንጅሎታል።እጅግ አደገኛ የሆኑ ጥላቻዎችንና ክፋቶችን ሕወሓት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲረጭ ኖሯል። ከዚህ በላይ ውሸቶችንና መንግስታዊ ሽብሮችን ሲነዛበት ኖሯል።ሕወሓት በተቆጣጠረው የትግራይ ክልል መስተዳደር ስም ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለቅሶ አዘል ማስፈራሪያ ደብዳቤ ጽፏል።Minilik Salsawi Image may contain: text No automatic alt text available.
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የስዩም መስፍን/መለስ ዜናዊ እና የህወሓታውያኑ ክህደት (መንግስቱ ሙሴ)

የስዩም መስፍን/መለስ ዜናዊ እና የህወሓታውያኑ ክህደት (መንግስቱ ሙሴ) ማሕሉን ዳር የማድረግ የወያኔ እስትራቴጅክ ሴራ (ጎንደርን ለሱዳን/ትግራይን ለኢሳያስ) የትግራይ ትግሪኝ አዲስ ሀገር የመመስረቱ የመጨረሻ ==================================== የህወሓትን ዘመነ ስልጣን አየን። ገና ከጅምሩ በሸፍጠት እና ጥላቻ የተወለደችው ህወሓት በለስ ቀንቷት እና አለማቀፍ እና የጎረቤት ሀገራትን ትብብር ተችራ ስልጣን ለመቆናጠጥ እና በሀገሪቱ አራጊ እና ፈጣሪ ለመሆን በቃች።፡ከ 1991 ጀምሮ አንድ በጎ ነገር ሰራች ብሎ ለመናገር በሚቸግር ህዝብን እና ሀገርን በመግደል ግዛተ ዘመኗን ጨርሳለች። የኢትዮጵያን ባህር ኃይል አፍርሳ የባሕር በራችንን ያለአንድም ቅድመሁኔታ ሰጥታለች። አሰብ ዛሬ ዳዋ ለብሷል። ግራቀኙ ገንጣይ እና አስገንጣዮች ቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚጠቀም ዳዋ ይልበስ፣ ወና ሆኖ የአይጥ እና ፈልፈላ ሀገር ይሁን በሚል እሳቤ ነው መቶ ሚሊዮን ሕዝብን የጥቃቅን ጎረቤት ሀገራት የትርፍ ሲሳይ ያደረጉት። የወልደአብ ልጆች፣ የሞሶሎኒ ድቃዮች፣ የሹምባሹ እድሪስ አወቴ የመንፈስ ተከታዮች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻ ገደብ የለሽነቱን በ27 አመታት የግዛት ዘመናቸው አየነው። የመጨረሻው መጨረሻ ግን ያው የፈረደበት በድንበር የሚኖረው የሳሆ አዲ ኢሮብ ጾረና፣ ዛል አንበሳ፣ ባድሜ ነዋሪ ነው። በአዲ ኢሮብ ሕዝብ ላይ ህወሓት ሁልግዜም ቂም እንደቋጠረች ነው። የነ ተስፋየ ደበሳይ ሀገር። የነገብረ እግዚያብሔር (ጋይም) ትውልድ ህወሓት ስትመሰረትም ኢሕአፓን እንጅ አናውቅሽም ብሎ የወጋት እና ለአረንዷዴው ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ከፍተኛ ክብር ያለው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ዜጋ ሰልፍ ወጧል። ኤርትራ እንኳን በቅኝ ግዛት በነበረችበት ዘመን ከቀሪው ወገኑ ያልተለየውን ሕዝብ ነው ወያኔ የእኛ አይደላችሁም ይሂዱ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት መግለጫ አንድምታዎች፤ (ዳንኤል ኪባሞ)

የሕወሓት መግለጫ አንድምታዎች፤ (ዳንኤል ኪባሞ) ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ትናንትና ያወጣው መግለጫ በርካታ አጀንዳዎችን የሚዳስስ ነው፡፡ ከመግለጫው በግልጽ መረዳት የሚቻለው የሕወሓት አመራር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የለውጥ ጎዳና ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው፤ ይልቁንም ሕወሓት ለውጡ ደረሰበትን ደረጃ መረዳት ተስኖት ቆሞ መቅረቱን ነው፡፡ ኢሕአዴግ የሚመራበት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መስመር አደጋ ላይ እንደወደቀ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ውሳኔ ተቀብሎ ባድመን ለመመለስ መስማማቱ ለሕዝብ የተገለፀበት መንገድ ትክክል አለመሆኑ፣ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የሚሾሙበት መንገድ ከተለመደው አሠራር ያፈነገጠ መሆኑ እና የቀድሞ የድርጅቱ መሪዎች ሊከበሩ እንደሚገባ ወዘተ. ተመልክቷል፤ በመግለጫው፡፡ መግለጫውን ከለውጡና ከአገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ አንጻር ካየነው ዕድልም አደጋም ያዘለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሕወሓት በበላይነት ሲመራው የቆየው ሥርዓት በአገርና በሕዝብ ላይ ምን ያህል መከራ እንዳመጣ መግልጽ አያስፈልግም፤ በግልጽ ስለሚታወቅና እየኖርነው ስለሆነ፡፡ ስለሆነም “አገራችን ከዚህ አስከፊ የብሉይ ዘመን ጭቆና እየተላቀቀች ነው፤ ለዚህም ዶ/ር ዐቢይና ጓዶቻቸው ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው፤” ብሎ የሚያምነው ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የተጀመረው በጎ ጅምር በሕወሓት መሪዎች እንዳይቀለበስ በዶ/ር ዐቢይ ከሚመራው አዲሱ የለውጥ ኀይል ጎን ይሰለፋል፡፡ በዚህ ምክንያት አዲሱ የለውጥ ኀይል በሕዝብ ሲደገፍና አቅሙ ሲፈረጥም፣ ከዚህ በተቃራኒው ለውጥን ተጻርሮ የቆመው ሕወሓት ይነጠልና ይዳከማል፤ እንቅፋትነቱ ያቆማል፡፡ ይህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ እሳቸው ለጀመሩት የለውጥ ሒደት ትልቅ ዕድል ነው፡፡ መግለጫው አደጋም ያዘለ ነው ሊባል የሚችለው ደግሞ፣ ሕወሓት ለውጡ የደረሰበትን ደረጃና የብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ ፍላጎትና ቁርጠኝነት መረዳት አቅቶት፣ በለውጥ እንቅፋትነቱ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት የስልጣን ሕልውናዬ በውስጥና በውጪ ኃይሎች ተነጥቋል ሲል መግለጫ አወጣ።

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ I. መግብያ፡- II. ውሳነዎች ሀ. የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ግንቦት 28/2010 ዓ.ም ባካሄደዉ አስቸኳይ ሰብሰባ የኢትዮ-ኤርትራን ግጭት በሰለማዊ መንገድ ለመፍታትና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አስመልክቶ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ የቀረበለት ሪፖርት በዝርዝር በማየት የሚቀጥሉትን ውሳኔዎች አሰልፏል። 1. ከምንም ነገር አስቀድሞ የኢህአዴግ ስራ ኣስፈፃሚ ሊያየው ይገባ የነበረዉ ጉዳይ የኢህአዴግ ምክርቤት በመጋቢት /2010 ዓ.ም ያስቀመጠዉን ወሳኔና ግምገማ መሰረት በማድረግ በድርጅታችን በግልጥ እየታየ የመጠዉን መሰረታዊ የአመራር ብልሽትና ያስከተለዉን ጉዳት፣ እንዲሁም ባለፈዉ የተጀመረዉ የጥልቀት መታደስ የደረሰበት ደረጃን በጥልቀት በመገምገም በሃገራችን ዋነኛ ችግር ላይ ትኩረት ኣድርጎ ማየት አለመቻሉ አንድ መሰረታዊ ጉድለት ነው። 2. የኢህኣዴግ ስራ አስፈፃሚ ማየት የነበረበት ሌላ መሰረታዊ ጉዳይ አሁን ገጥሞን ላለው መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ ላይ ትኩረት ኣድርጎ መውያየት መሆን ሲገባዉ የችግሩ ባስከተላቸው ውጤቶችና ለጊዚያዊ መፍትሔዎች ቅድሚያ መስጠቱ አንድ ሌላ ጉድለት እንደ ሆነና፣ ዘለቂው መፍትሔ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን በግልፅ የለያቸውን የልማት አቅምቻችን ማለትም መላው ህዝባችን፣ መንግስትና የግል ባለሃብቱን በማደራጀት ርብርብ እንዲያደርጉ መቻል ላይ ያለብን ችግር ላይ ትኩረት ስጥቶ መውያየት ኣልቻለም። 3. እነዚህ እላይ የጠቀስናቸው ጉድላቶች እንደ ተጠበቁ ሆነው ስራ ኣስፈፃሚው የኢትዮዽያና የኤርትራን ጉዳይ ኣስመልክቶ የወሰነው ውሳኔ በመሰረቱ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ በኢህአዴግ የሚመራዉ መንግስት ለኣፍሪካ ቀንድ ሰላም በጠቃላይ ለሁለቱ ሃገራት ወንድማሞች ህዝቦች በተለይ ሲባል ስምምነቱን ያለቅድመ ሁኔታ በመቀበል ህዝባችንና መላዉ ኣበላችንን በማወያየትና በማሳመን እንድሁም ዓለም ኣቀፉን
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው

የሕወሓት ሳቦታጅ አንዱ ክፍል የመረጃ ቀውስ መፍጠር ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ውጥረት ከኢሕአዴግ የፖለቲካ ባሕሪይ አንጻር መለካት መጭውን ጊዜ ለማወቅ ይረዳል። ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው ፤ ለሕዝቡ የድንበር ውሳኔውን አጀንዳ ስለሰጠው ይህን ያሕል አይሰጋም ፤ አጃቢው አረና አጀንዳውን በሰላማዊ ሰልፍ ያደምቅለታል። በሰበር ዜናና በተባራሪ ዘገባዎች የመረጃ ቀውስ ተፈጥሮ የተቃዋሚዎች ትግል የእንቅልፍ ላይ የቅዠት መወራጨት አድርጎታል ። ለኤርትራ ይሰጣሉ የተባሉት መሬቶች ሕጋዊ የውሳኔና የማስረከብ ፕሮሰሳቸው መስመሩን የተከተሉ አይደሉም ፤ ስለዚሕም ኤርትራ የሚፈለገውን ከመናገር ተቆጥባለች ፤ ሕጋዊ መስመሩ ኢሕአደግ ውሳኔው ለተመድ ቀጥታ ማሳወቅ ነበረበት ፤ ተመድም ለኤርትራ መንግስት ያስተላልፍና የኤርትራን መልስና መግለጫ ተከትሎ ሕጋዊ አግባቡ ይተረጎማል ። ወያኔ ግን ይህንን ሕጋዊ መስመር ካለመከተሉም በላይ የወሰነው ውሳኔ የሐገር ውስጡን ትኩሳት ለማብረድና በሰበር ዜናና በሰልፎች ሐገሩን ማመስ ይዟል። ወያኔ ኢሕአደግ በተከታይነት ሕዝቤ በውሳኔው ስላልተስማማ ተመልሼ ላጢነው የሚል ተመሳሳይ መግለጫዎችን ይለቃል ። #MinilikSalsawi
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የትግራይ ህዝብን ለምን ትጠላለህ?”፤ “‘ተሳስተሃል’ እያለ ‘ትጠላለህ’ ጋር ምን ወሰደህ?” ( ስዩም ተሾመ )

( ስዩም ተሾመ ) – ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ ጥቅም የቆመ በማስመሰል ብዙሃኑን መጠቀሚያ በማድረግ ጥቂቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የፖለቲካ ቡድን ነው። እነዚህ ጥቂቶች ደግሞ ህወሓት ለብዙሃኑ ሕዝብ ጥቅም እንደቆመ አድረገው በማቅረብ የራሳቸውን ጥቅምና ተጠቃሚነት ለማስቀጠል ዘወትር ይታገላሉ። እነዚህ የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ከሌሎች የሀገራችን የፖለቲካ ልሂቃን ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር እንወክለዋለን ለሚሉት የትግራይ ሕዝብ ፍፁም ደንታ የሌላቸው መሆናቸው ነው። ለእነሱ “የትግራይ ሕዝብ” ማለት በራሳቸው ዙሪያ (ሰርክል) ያሉት የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ናቸው። ሀገርም ሆነ መንግስታቸው ህወሓትና ህወሓት ብቻ ነው። ፓርቲው ትክክል ያለውን ነገር ይደግፋሉ፣ የተቃወመውን ነገር ይቃወማሉ። የህወሓትን ሥራና ተግባር ስትተች “የትግራይ ሕዝብን ይጠላል” ይሉሃል። በሃሳብ ስለሞገትካቸው ብቻ በድብደባ ብዛት ቆዳህ እንዲላጥ ሌት ከቀን ይወተዉታሉ። የሚያመልኩት ድርጅት ሆነ የሚመሩበት አመለካከት ፍፁም ዘረኛ እንደሆነ ስትናገር እንድትታሰር፥ እንድትሰደድ ወይም እንድትገደል የስም ማጥፋት ዘመቻ ይከፍቱብሃል። እንዲህ ያለ ስርዓት በሀሰት መረጃ ማንነትህን (ስምና ክብርህን) ካጠፋ በኋላ (Character assassination) ከዚያ ቀጥሎ ወይ አድራሻህን ወይም ነፍስህን ሊያጠፋ ይመጣል። ያኔ ከወዳጅ ዘመዶችህ በስተቀር “አይዞህ፥ አለሁልህ” የሚል ሰው ይጠፋል። ምክንያቱም ስምና ክብርህ ከተገፈፈ በኋላ የራስህ የሆነ ማንነት የለህም። ስምህን አጥፍቶ ስጋህን ቢገድል ከአንድ ሰሞን እዬዬ ባለፈ ማንም ዞር ብሎ ስለ አንተ አይጠይቅም። የቀድሞ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የፕሮቶኮል ሹም የነበሩትን ግለሰብ እስኪ እንመልከት። መቼም ይህ ግለሰብ የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች እንዳሉት “ሻይ አፍዪ”፣ “ስጋ ቆራጭ” ወይም “አትክልተኛ” እንዳልሆነ ታውቃለህ። ምክንያቱም ጠ/ሚኒስትሩ አሜሪካ ኒውዮርክ ድረስ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር ደብረጽዮን ምነው ያልጠበቅነው በጠራራ ጸሀይ ሀቅን መካድ ( ከአስገደ ገብረስላሴ )

ዶክተር ደብረጽዮን ምነው ያልጠበቅነው በጠራራ ጸሀይ ሀቅን መካድ??????????????????????????? —————————————————– ዶክተር ደብረጽዮን በትላንትና ጉንበት 20/09 / 2010 ዓ ም ማታ ከምሽቱ 1 .30 በጋዜጠኛ ታጋይ ብርሀኑ አባዲ ጥየቄ ሲያቀርብልህ ሰማሁ ። ጥያቄው ምንም እንኳን አድር ባይነት ያዘለና ፈሪ ቢሆንም ብርያኑ የጠየቀው ነጥብ እናንተ ለነባር ታጋዮች ምንም እንኳን ልዩነት ቢኖራቸው ያሳለፉት መራራ የትግል ጊዜ ፣የጓደኝነት ፍቅር አስታውሳችሁ የእግዚአቢሄር ሰላምታ እንኳን እንደመስጠት በቂም በቀልና በጥላቻ ነው የምታዩዋቸው ለምን እንዲህ ይሆናል? የኦሮሞ ኦሆዴድ አማራር ለእንደ ዶክተር ኖጋሶ ጊዳዳ እንክብካቤ ከማድረግ አልፎ የክብር ሽለማትም ሰጥቶዋቸዋል እንዳው ህወሓት ኢህአደግ ህገመንግሰት መብታቸው ነጥቆ ደሞዛቸው ፣ቤታቸው፡፡መኪናቸው ቀምቶ የሰደዳቸው። ታድያ እንደዚህ አይነት በጎ ምግባር የህወሓት መሪዎች ለምን አይከተሉትም ?? የሚል የአብዛኛው የትግራይ ህዝብ ነው ? ጥያቄ ነው ብሎ ሲጠይቅ ጠያቂው ፣ ደጉተር ደብረጽዮን የሰጠው መልስ ይላል ፣እኔ እንደዚህ አይነት የህዝብ ጥያቄ አላውቅም አሁን የቀረበ ጥያቄ ለእኔ አዲስ ስለሆነ በፍጥነት አጥንቸ በአጭር ጊዜ መልስ እሰጥበት አለሁ ብለዋል ። አሳዛኝ ነገር ፣ዶክቶር ደብረጽዮን አንተ የማትረሳው ነገር ላስታውስህ ? 1ኛ — በ1984 እና 1985 ዓ /ም 32 000 ታጋዮች አንዳ አንዶቹ በውሀ ቀጠነ የታሰሩ ፣ አብዛኞቹ ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ የአገርና የዜጎች ሉአሏውነት አነስተው የታሰሩ በድምር 32000 ታጋዮች በመላው የሀገራችን ወታደራዊና ማረምያ ቤት ታስረው ጥቂቶቹ ከ 1 አመት እስከ 3 አመት በላይ ታስረው አብዛኞቹ ተባርረው ጠቂቶቹ ተመልሰው ታስረውበት የነበረ ወህንቤትና በድህንነት መስራቤት ኮኖሌኔል
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሃት-ወያኔ ታድሶ ብቅ ብሏል! (ሀይሉ አባይ ተ.)

ህወሃት-ወያኔ ታድሶ ብቅ ብሏል! (ሀይሉ አባይ ተ.) ዛሬ ግንቦት 19/2010 ዓ.ም በመቀሌ ስብሰባ ላይ የህወሃት እውነተኛው መንግስት ባለሟሎች ይህንን ብለዋል:: “መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ ጠላት የሚነዛው ህዝብን ከህዝብ ጋር የማቃቃር ተግባር በዝቶ ይታያል እንጂ የትግራይ ህዝብ በተለየ ሁኔታ እጅግ የከረረ የጥላቻ ኢላማ አልሆነም።” (አቶ ጌታቸው ረዳ) ==== “ጠላት መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ የከፈተብንን የአዕምሮ ጦርነት ከሕዝቡ ጋር በመሆን መዋጋት አለብን” (አቶ ሥዩም መስፍን) === “የኛ ባልሆኑ የተሸነፉ አስተሳሰቦች በኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ ሰርገው ስለግቡ የተበላሹ አሠራሮች ተበራክተዋል” (አቶ ኅላዌ ዮሴፍ) ==== ‘አሯሯጮች ዙሩንና የሩጫውን ፍጥነት ይጨምራሉ እንጂ የድሉ ባለቤት ሌላው ሯጭ ነው:: ውሻ በቀደደው የሚገባው ጅብ ነው::’ ይህ ሁሉ ድጋፍ በጭብጨባ ያገኙት አቢይ አህመድ “የለውጥ” ፕሮግራሞች ያለ ህወሃት ፍቃድ የሚከውኑ ከሆነ “ህወሃት ዴሞክራቲክ እንጂ አምባገነን አልነበረም” ብለን ነበር:: “ወታደራዊና የሴኩሪቲ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ስር እስካሉ ድረስ የህወሃት የበላይነትን መተካት አይቻልም” አልን:: ሰሚ የለም:: ህወሃት ‘በመንግስት ውስጥ ያለ ጥልቅ መንግስት’ ነው ስንል በጨበጣ ሳይሆን መረጃና ማስረጃ ይዘን ነበር:: “ህወሃት ዋነኛው ሯጭ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ አሯሯጭ (pacemaker) ናቸው” ስንልም አሾፉብን:: እኛ ግን አሯሯጭ ለሌሎች ድልና ሠዐት ማሻሻል ይርዳ እንጂ በራሱ ድል እንደማያደርግ እንረዳለን:: በጠ/ሚ አቢይ ጣፋጭ ንግግሮች የተማረኩ ሃይሎች “ፋታና ጊዜ” ሲጠይቁ ሰማንና ‘አረ ተዉ ህወሃትን ለመጠናከር ይጠቀምበታል’ አልን:: ጨለምተኛም ተባልን:: ህወሃት አልበረደውም:: አልሞቀውም:: ቢላውን ስሎ ቀርቧል:: ህዝባዊ የሆኑትን የነፃነት፣ የዲሞክራሲና የፍትህ ጥያቄዎችን በመተው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሃቶች አብዲ ኢሌ በስልጣን ላይ እንዲቆይላቸው የፈለጉበት ምክንያት ሲጋለጥ

ህወሃቶች አብዲ ኢሌ በስልጣን ላይ እንዲቆይላቸው የፈለጉበት ምክንያት ምን ይመስላችኋል? ለአብዛኞቻችን በጣም እንቆቅልሽ የሆነብን ጥያቄ ለምንድነው አብዲ ኢሌ ሁል ጊዜ አምባገነንና ሰብዓዊ መብት ረጋጭ ከሆኑት ህወኃት ዘንድ ድጋፍ የተቸራቸው? ህወሃቶች በሶማሌ ክልል ላይ እየፈጸሙት ካሉት ችግሮችና ህገ-መንግሥታዊ ጥሰቶች በተጨማሪ በክልሉ ላይ እጅግ በጣም መጠነ ሠፊ የሆነ ኢኮኖሚያዊ በደሎችን እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ረገድ ከክልሉ ህዝብ በኩል እምብዛም ተቃውሞ ባለመኖሩ (አብዲ ኢሌን ስለሚፈሩ)፤ህወሃቶቹ የክልሉን ኢኮኖሚ ግልጽ በሆነ መልኩ እየዘረፉ ይገኛሉ፡፡ህወሃቶቹ በክልሉ ላይ እየፈጸሙት ካሉት ግልጽ ዘረፋዎች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ለአብነት ያህል እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡ 1. የእርሻ መሬት፡- በክልሉ ለጎዴ መስኖ እርሻ ልማት የታቀደውን ሰፊ የእርሻ መሬት ሙሉ በሙሉ ለአንድ የትግራይ ተወላጅ ለሆነ ግለሰብ እንዲተላለፍ የተደረገ መሆኑ፡፡ ይሄው ግለሰብ በዚህ ሠፊ የእርሻ መሬት ሳቢያ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል በኢንቨስትመንት ስም ከፍተኛ ብድር ወስዶበታል፡፡ 2. የእርሻ መሬት፡- በድርቅ ሳቢያ ከሺኒሌ/ሲቲ ዞን የተፈናቀሉትን አርብቶ አደሮች መልሶ ለማስፈር እንዲሆን የታቀደው የእርሻ መሬት ደግሞ ከጀርመን አገር ለመጣ አንድ የትግራይ ተወላጅ የተላለፈ ሲሆን ይሄው ግለሰብ በዚህ ሠፊ የእርሻ መሬት ሳቢያ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል በኢንቨስትመንት ስም ከፍተኛ ብድር ወስዶበታል፡፡ 3. ሆቴሎች፡- በጅግጅጋ ከክልሉ የስብሰባ አዳራሽ ፊትለፊት ባሉት መደዳዎች ወደ ጎማጣ ሰፈር መነሻ ወደ ምሥራቅ እስከ የድሮው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ድረስ ያሉት ቦታዎች በመገንባት ላይ ያሉት ሆቴሎች የጄኔራል ሳሞራ ሚስትና የወ/ሮ ኤደን መስፍን (የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የነበሩት ልጅና ወንድም)
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከፍተን ብናየው? ሻእቢያና ኦነግ – መስተፋቅር ( አሰፋ ጫቦ)

ከፍተን ብናየው? ሻእቢያና ኦነግ – መስተፋቅር! ( አሰፋ ጫቦ ) እንደመግቢያ ዛሬ ትንሽ መጻፍ የፈለኩት በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና በኢሳያስ አፈወርቂ መካከል ያለውን የቆየ ጥብቅ ትስስር በመጠኑ ለመፈተሽ ነው። መነሻ የሆነኝ እንግሊዝ አገር ሎንዶንና አሜሪካ፤ አትላንታ፣ ጆርጂያ የኦሮሞ “ምሁራንና ብሔርተኞች” ያደረጉት ስብሰባና የሰጡት መግለጫ ነው። ያ ራሱን ችሎ መነገር ያለበት ስለሚመስለኝ እመለስበታለሁ። የዚህኛው አላማ እዚያ ስብሰባ ላይ ተካፋይ ከነበሩት “ነፃ አውጭዎች” አንዱን፣ ኦነግን በጨረፍታ ለመታዘብ ነው። እዚያ ከመዝለቄ በፊት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመግባቢያ ያክል በመጠኑ መዳሰስ፤ ማየትና ማሳየት እሞክራለሁ:: ብዙ የአፍሪቃ መሪዎች (ፕሬዝዳንቶች) “የእድሜ ልክ ፕሬዚዳንት” (President for Life) የሚል ማእረግ ነበራቸው። እኔ ወድጅዋለሁ! በየአራት ወይ ስድስት ዓመቱ ምርጫ እየተባለ ጊዜም ገንዘብም ከሚባክን “ወደዳችሁ ጠላችሁ የራሳችሁ ጉዳይ” ብሎ እቅጩን መናገርን የመሰለ ነገር የለም። ከዚያ ውስጥ አንዱ፤ ጂን ቤዴል ቦካሳ (Jean-Bédel Bokassa)፤ የመካከለኛ አፍሪቃ ሬፐብሊክ “ንጉሠ ነገሥት!” (Emperor) ሆኖ አረፈው። እሱም እውነቱን መናገሩ ነበር። አንድምታውን ወዲያ ትተን፣ “የእድሜ ልክ ፕሬዚዳንትም ማለት ያው ንጉሠ ነገሥት ማለት አይደል!?” ማለቱ መሰለኝ። ይህ ነገር የኛው የነበረውን፣ አሁን የጎረቤት “አገር” “ፕሬዚዳንት” የሆነውን ኢሳያስ አፈወርቂን አስታወሰኝ። “የኛው የነበረውን” ያሰኘኝ የደሴ ልጅ መሆኑ፤ የቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረ መሆኑ፤ ከሁሉም በላይ ጣሊያን ኤርትራ ብሎ የሰየማት የባህረ ነጋሽ ልጅ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ተረት፣ ትንግርት (Mythology) ተብሎ የሚነገረው አብዛኛው የተሸመነው ባሕረ ነጋሽ ነውና። የዚህ፣ ጣሊያን ኢትዮጵያን የወረራት ዘመን፣
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት በመከላከያ ስም የእህል ክምችቶችን እየዘረፈ ነው ፡፡

ሕወሓት በመከላከያ ስም የእህል ክምችቶችን እየዘረፈ ነው ፡፡ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም በደረሰን መረጃ ወረታ ከሚገኘው የእህል መጋዝን ከግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ በመከላከያ ተሽከርካሪዎች እየተጫኑ ወደ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የድቄት ፋብሪካ በማስፈጨት ትግራይ ለሚገኘው የመከላከያ ኃይል ነው በሚል ሽፋን ድቄቱ እየተጫነ በመጓጓዝ ላይ ነው ። ከሽፊሮቹ ውስጥ አንዱ የወሰድነውን ድቄት መቀሌ ከአንድ ማህበር ትልቅ መጋዝን ነው ያራገፍነው እንጅ ከመከላከያ ካምፕ አልወሰድነውም በማለት መረጃ በመስጠቱ ከእህል መጋዝን ኃላፊዎች ውስጥ አንዳንድ ለሕዝብ ተቆርቋሪዎች ከህወሓት የመከላከያ አመራሮች ጋር ወደ ግጭት አምርተዋል ። መጀመሪያም በአገሪቱ ብሎም በባህርዳር ; ጎንደር; ደሴና በተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የዳቦ እጥረት በተከሰተበት ወቅት በመከላከያ ስም ወደ አንድ ክልል ብቻ እየተወሰደ ድቄቱን ማከማቸት ለሕግም ለሞራልም ተገቢ አይደለም ሲሉ ተቃውመዋል ። የመከላከያ አመራሮች ግን ክፍያውን የፈፀመውም ድቄቱኑም እየተጠቀምንበት ያለነው ለእኛ ለመከላከያ አባላት እንጅ ለሊላ አይደለም የሚል ተልካሻ መልሶችን እየሰጡና እያስፈራሩ ይገኛል ። በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የዳቦ አቅርቦት እጥረት በገጠመበት እና ስንዴ ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ ችግር እንደገጠመው በሚናገርበት ወቅት በመጠባበቂያ ስም የተከማቸን እህል በአድሎ መመንዘር ተገቢ አይደለም። ይህን ጉዳይ እንዲነጋገሩበት ለአማራ ክልል አመራሮች መረጃው ቢሰጣቸውም ፡ መልሳቸው ይህን የእህል ክምችት የሚቆጣጠረው የፌደራል መንግስት ስለሆነ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም የሚል ምላሽ ልክ እንደ ኤሌትሪክ አቅርቦት አይነት ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡ በመሆኑም ሕዝባችን ይህን አውቆ ከአቅራቢያው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት ወ አረና ካድሬዎች ጩኸት የበታችነት የወለደው ነው (ምንሊክ ሳልሳዊ)

አብዛኛውን ጊዜ የሕወሃት ወ አረና ካድሬዎች የራሳቸውን የዘረኝነት ካባ ሌላው ላይ ለመደረብ ይራወጣሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚባለው የመንግስት ተቀጽላ ተቋም በወልዋሎ ስፖርት ክለብ ብልግና ላይ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ የሕወሃት ወ አረና ካድሬዎች ከ አመራሮች ጀምሮ የበታችነት ችግራቸውን ላንቃቸው እስኪበጠስ በመጮኽ በዘረኝነት ፍትሕ የሚገኝ መስሏቸው እየተንጫጩ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ የስፖርታዊ ጨዋነትን ብክለት የፈጠረው ሕወሃት መራሹ የዘረ ፖለቲካ ፖሊሲ ነው። ይህ የዘር ፖለቲካ ፖሊሲ ወደ ስታዲዮሞች እንዲገባ ያደረገውም የሕወሃት የፖለቲካ ሲስተም እንጂ ሕዝቡ አይደለም። በተለያዩ ስታዲዮሞች ቡድኖችን ለረብሻ የሚያደራጁት እነዚሁ በበታችነት የሚሰቃዩ የሕወሓት ሰዎች ናቸው። ይህንን በማጀብ ደረጃ በኢትዮጵያ ስም ተሸሽጎ ሲቀባጥር የነበረና ዘረኝነቱ ገንፍሎ የወጣበት አረና የተሰኘው ፓርቲ ሌላኛው የበታችነት መገለጫ ነው። በተለይ አረና በ አመራር ደረጃ ያሉ ሳይቀሩ የተነከሩበት የዘረኝነት አባዜ ፍትሕን በጠባበኝነት ለማግኘት የተጠለሉበት መስመር ውርደት ሆኖባቸዋል። በኢትዮጵያ ስም ተከልለው ከሕወሃት የዘረኝነት ታክቲክ በባሰ መንገድ ከፍተኛ የዘረኝነት መርዛቸውን የሚረጩት አረናዎች ስፖርቱን የፖለቲካ መድረክ ለማድረግ እየተጉ ነው። ስፖርቱን ለስፖርት ትተው የፖለቲካ ድርጅታቸውን አላማ ማራመድ ሲገባቸው የደም መፋሰሻ የሆነውን የዘር ፖለቲካ ወደ ስፖርቱ ሜዳ ይዘው መዝለቃቸው ራሳቸውን እርቃን አስቀርተዋል። የወልዋሎ ደጋፊዎችና ክለቡ በበቂ ሁኔታ መከራከር እየቻሉ የክለቡ ደጋፊዎች ሰልፍ መውጣትም ሌላኛው በስፖርቱ ላይ የተደነቀረ የዘረኝነት አደጋ ነው። ክለቡ ራሱን ወክሎ በደጋፊዎቹ እየታገዘ ለመከራከር በቂ አቅም አለው። የፖለቲከኞችንና የደም ጥማት ያለባቸውን ካድሬዎች እርዳታ ክለቡ አይፈልግም። ወልዋሎ ፍትሕ ተነፍጓል ከተባለ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ መኳንንት አደብ ግዙ (መስከረም አበራ)

መለስ ዜናዊን የመሰለ ዘረኝነት ናላውን ያዞረው ግለሰብ የፈጠረው ስርአት ወገኖቻችንን ለስደት ለእንግልት መዳረጉን የዚህ እርጉም ፍጡር ሰፈር ሰዎች ስላድበሰበሱት የሚጥፋፋ ወንጀል አይደለም፨ እሱን በሞት ከመገላገላችን በፊት መፈናቀሉ በባለቤት አልቦው አማራ ላይ ብቻ የወረደ መአት ነበር፨ የዚህ ህዝብ እንግልት የመለስ ዜናዊን እና የመንፈስ ልጆቹን አፍ በሳቅ የሚሞላ ትርኢት ነበረ፨ እንደ ግመል የሚነዳቸውን አሽከሮቹን ልኮ ለፍቶ አዳሪ ህዝብ ካፈናቀለ በሁዋላ ይህን ማድረጉ ልክ እንደሆነ ሊነግረን በፖርላማ ይሰየም ነበር፨ ይሄ ደግሞ ዘረኝነት ለሚጫወትባቸው የሰፈሩ ሰዎች ጀግንነት ይመስላቸው ነበር- አማራን ማጥቃትን የመሰለ ጀግንነት ከየት ይመጣል¡¡¡ ሞቶም መዘዙ አይለቀንምና እነሆ ዘር ተቆጥሮ ማፈናቀሉ እድገት አምጥቶ በአራቱም ማዕዘን እየተጧጧፈ ይገኛል ¡ አሁን አንድ ሚሊዮን ህዝብ ሜዳ ላይ እንደተዘረጋ ክረምት እየመጣ ነው ፨ ፀሃይ ሲወቅረው የኖረ ህዝብ ዝናብና ውሽንፍሩም እንዳያልፈው ዝም ተብሏል! ጭራሽ አዲስ ተፈናቃይ እየታከለ ነው፨ አማራ፣ ኦሮሞ ፣ጌዲኦ የተባሉ የሰው ዘሮች እንደ ብቅል ሜዳ ላይ ተሰጥተዋል፨ የትግሬ አክቲቪስቶችም በአስር ሽህ የሚቆጠር ዘመዳችን ከአማራ ክልል ተፈናቅሏል፣ በመቶዎች የሚቆጠር ሞቶብናል እያሉ ነው፨ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ሁሉ እናዝናለን ፨ የአማራው ፣ኦሮሞው ፣ ጌዲኦው ተፈናቃዮች አንድ ቦታ ሰፍረው ሲቆዝሙ የሚያሳይ የፎቶ እናያለን፤የሞቱ ሰዎች ፎቶ ተለጥፎ ነፍስ ይማር ብለናል፨ ምነው ታዲያ የትግሬ ተፈፈናቃይ ወገኖቻችን ያረፉበት አድራሻ አይታወቅ ? ምነው ተፈናቅለው ከሰፈሩበት ስፍራ የተወሰደ ፎቶ አላየን ? ነው “ወርቅ ስለሆኑ” ለካሜራ ያንፀባርቃሉና ፎቶ መውሰድ አልተቻለም?! የሞቱትንስ ነፍስ ይማር ለማለት ምነው ፎቷቸው አልተለጠፈ?
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሀት ከአማራው ህዝብ ከፍተኛ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደሚችል በስጋት እየገለጸች ነው። (መሳይ መኮንን)

ትኩረት ወደ አማራው (መሳይ መኮንን) ህወሀት በቅርቡ በትግራይ ውስጥ አንድ ሚስጢራዊ ስብሰባ አድርጋ ነበር። በስብሰባው ላይ የህወሀት የጦር መኮንኖች ብቻ የተገኙ ሲሆን መድረኩን የሚመሩት አባይ ጸሀዬ፡ በረከት ስምዖንና የህወሀት ጄነራሎች ነበሩ። ዓላማው የዶ/ር አብይ አህመድን ስልጣንና አካሄድ ከህወሀት ጥቅምና ፍላጎት አንጻር መፈተሽ ነበር። የትግራይ ተወላጆች ከፌደራል መንግስቱ ቁልፍ ቦታዎች ተገፍትረው ወጥተዋል የሚል የከረረ ቅሬታ ከህወሀት የጦር ሹማምንቶች የተሰማ ሲሆን እነአባይ ጸሀዬ ”አሁንም ቁልፍ ቦታዎች በእጃችን ናቸው። መከላከያውን ከህወሀት መዳፍ ፈልቅቆ የሚነጥቅ በተአምር አይኖርም። ዋናዋናዎቹ የመከላከያ ክፍሎች ትግራይ ገብተዋል። የሚያሰጋን ነገር የለም” በሚል ለማረጋጋት መሞከራቸው ተሰምቷል። የሚስጢራዊው ስብሰባ ዋና ዓላማ ከአማራው ህዝብ የሚመጣውን ቀጣይ አመጽ እንዴት እንመክተዋለን የሚል ነበር። ህወሀት ከአማራው ህዝብ ከፍተኛ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደሚችል በስጋት እየገለጸች ነው። እነበረከትም በሚስጢራዊው ስብሰባው ላይ እንዲታደሙ የተደረገው ይህን አይቀሬ አመጽ እንዴት መመከት ይቻላል የሚለውን ለመምከር ነው። በረከት ስለህወሀት ጥቅም በአማራው ላይ የተጣበቀ አልቅት መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሯል። ህወሀት አደጋ ውስጥ ስትገባ ከእነስብሃት ነጋ ጎን ተሰልፎ ምሽግ የሚይዝ መሆኑም ይታወቃል። አሁንም ይህን ‘ከህወሀቶች በላይ ህወህት’ መሆኑን እያሳየ ነው። ሰሞኑን ብአዴን ቁርጡ ይለይለታል የተባለ ስብሰባ ተቀምጦ ከርሟል። እነበረከት የመስመር ክህደት ተፈጽሟል የሚል አጀንዳ ቀርጸው ህወሀት ላይ ያመጹ የድርጅቱን አመራሮች ለማሸማቀቅና ከተቻለ ለማሰር የጠሩት ስብሰባ መፈንቅለ አጀንዳ ተፈጽሞበታል። ለዓመታት የህወሀት ተላላኪ፡ አሽከር፡ ባሪያ እየተባለ ሲረገም የነበረው ብአዴን በተለይም መካከለኛና የታች አመራሩ ”ይለያል ዘንድሮ” ብሎ ተነስቷል። የለማ መገርሳን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሃት ሙሉ ስልጣኑን መልሶ የሚቆጣጠርበትን ስልት ለመንደፍ ጥናት እያደረገ ነው

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ተከታታይ የሆኑ ህዝባዊ ተቃውሞዎች የበዙበት ህወሃት፣ ሙሉ ስልጣኑን መልሶ የሚቆጣጠርበትን ስልት ለመንደፍ መቀሌ ላይ ከትሞ ጥናት እያደረገ ነው ። ህዋሃት እራሱን ከአንዳንድ የፌደራል መንግስት የስልጣን ቦታዎች በማራቅና ህወሃት የሌለበት በማስመሰል እንዲሁም የፌደራል መንግስትን የማስፈጸም አቅም በተለያዩ እንቅፋቶች በመክበብ እና በማደነቃቀፍ ህወሃት የሌለበት ነገር ውጤታማ አይሆንም ወደ ሚያስብል አስተሳሰብ ህዝቡንና የድርጅቱን አባላት ለመክተት እቅድ በመንደፍላይ ነው። በተለይ ሙሉ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በሚገኘው የደህንትና የመከላከያ ተቋማት አማካኝነት የተለያዩ ግጭቶችን በመቀስቀስና አለመረጋጋት በመፍጠር ተቀባይነቱን ለማጉላት በስልትነት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል ። ህወሃት ባደለባቸውና በሚተማመንባቸው ባለሃብቶች እንዲሁም በፓርቲው የንግድ ተቋማት አማካኝነት አገራዊ ኢኮኖሚውን ችግር ውስጥ በመክተትና መንግስታዊ አገልግሎት አሰጣጡን ቀርፋፋ በማድረግ ህዝቡ “የድሮው ይሻለናል” ብሎ ተመራጭ ለመሆን ማቀዱንም ምንጮች ገልጸዋል። እንዲሁም ታዳጊ ክልሎችን ወይም ኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች የሚላቸውን በድምጽ ወደ ሚሳተፉበት አሰራር በማምጣት ዋናዎቹን የኦህዴድና የብአዴን ለውጥ ፈላጊዎች አስተሳሰብ አናሳ ወይም በጠባብ አመለካከት አራማጆች አስተሳሰብ የመተብተብና እርምጃዎችን የማንገራገጭ የሴራ ፖለቲካን ለመከተል እቅዶችን እየነደፈ ነው ። ህወሃት ኦህአዴድ እና ብአዴን የራሳቸውን የውስጥ ድክመት በህወሃት በማሳበብ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንዲጠላ እንዳደረጉት ያምናል። ከእነዚህ ሃይሎች ጋር የሚኖረውን የወደፊት ግንኙነት ለመወሰን የተለያዩ አማራጮችን በማጥናት ላይመሆኑንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኮማንድ ፖስት ሽፋን ዝርፊያ የሚፈፅሙ የሕወሓት ወታደሮች በቄሮ ትግል በቁጥጥር ስር ዋሉ ።

ሌባን ምንጠራ ተጀምሯል ። ይህ ምታዩት የትግሬ አፓርታይድ ስርዓት ጀሌ በአስቸኳይ ገዳይ ኮማንድ ፖስት ስም የተለመደውን የደደቢት ማፊያ ስራ ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ ሲል <በምእራብ ሸዋ ቶኬ ኩታዬ ወረዳ> ላይ በቁጥጥር ስር ዉለዋል ።   እነዚህ ሌቦች ህዝብን ለማገልገል በቆረጡና.የደሀዉ ሕዝብ ወገን በሆኑ የሰራዊት “ስምና መለዮ” ኮቾሮ እያረረበት በየቤቱ እየዞሩ ሕዝብን በቁም የሚግጡ, በተቋማዊ መዋቅር ስም የተሰገሰጉና, ሲዘርፉ የነበሩ ነጭ ሌቦች በሕዝብና በወጣቱ እርብርቦሽ እጅከፍንጅ የተያዙ ናቸዉ ። አሁን እዛ ሰፈር ተጋሩ በአገሩ መቀመጫ አጣ. የሚል ሲንግል. ይጠበቃል ። VIVA ቄሮ ትግሉ ይቀጥላል ይቀጣጠላል ። Esmael Dawed Endris
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዲሌና ህወሓት (ብርሐኑ ተክለያሬድ )

አብዲሌና ህወሓት (ብርሐኑ ተክለያሬድ ) ይህን ሰው በዚህ ትምህርት ቤት ተማረ እዚህ ሲማር አውቀዋለሁ የሚል አንድም ሰው አይገኝም እርግጥ ነው ብዙዎች መብራት ሰራተኛ ሆኖ ሽርፍራፊ ሳንቲም ካልሰጣችሁኝ በማለት ገመድ እየቆረጠ ደባ ሲሰራባቸውና በአካባቢው ባህልና በእስልምና ሀይማኖት ያልተፈቀደ ነውረኛ ተግባር ሲፈፅም አስካሪ መጠጥ ጠጥቶ ሴቶችን ሲጎነትልና ሽማግሌዎችን ሲያንጓጥጥ ያስታውሱታል ። እድሜ ለወሮበላው ህወሓትና ለጎሳ ፌዴራሊዝሙ ይሁንና ይህ ሰው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ህወሓት ከወለዳቸው የዛር ውላጅ ድርጅቶች የአንዱ አጋር ድርጅት አባል ሆነ የህወሓት የስልጣን መውጫ መስፈርቶች የሆኑትን የተበላሸ ስብዕና ባለቤትነትንና ጥልቅ አድር ባይነትን አጣምሮ የያዘ ሰው ነበርና በአጭር ጊዜ ውስጥ የክልል ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ተገኘ ። መለስ መራሹ ህወሓት ከክልሉ መሪዎች ጋር በየጊዜው በሚፈጠረው አለመግባባት የክልሉን መሪዎች ገሚሱን ለእስር ገሚሱን ለስደት ሲዳርግ የህን ሰው ኳርተር የሚል ቅፅል ስም በተሰጠው የወያኔ ጄነራል ሞግዚትነት የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ የዚህ ሰውና የህወሓት የግል ይዞታ የክልሉ ነዋሪዎችም የክፉው እሳት ማገዶ ሆነዋል ሰውየው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ ነው ።ይህ ግለሰብ በስልጣን ዘመኑ በዜጎች ለይ የፈፀማቸው ግፎች ተሰፍረው የማያልቁ ቢሆኑም እነሱን ለታሪክ ትተን በእስር ቤት የሚገኙ የግፉ ሰለባዎች ካጫወቱኝና እኔም ከተመለከትኩት አሰቃቂና አስገራሚ ድርጊቶቹ ጥቂት እንጨልፍ አሀዱ በአብዲ ክልል ዳኛ ፍርድ ቤት ህግ ወዘተ የሚባል ነገር የለም ህግም ፍርድ ቤትም ዳኛም ራሱ ብቻ ነው ኦብነግ ገባ ብሎ አንድ መንደር አሰከብቦ ያቃጥላል ሲመሽ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በ”ቅማንት ጥያቄ” ስም የሚነግደው የሕወሓት ሴራ ሲጋለጥ

(መነበብ ያለበት የትህነግ/ህወሓት ሴራ! የትህነግ/ህወሓት ተከፋይ ፌስቡከኞች በቅማንት ስም እንዴት እየነገዱ እንደሚገኙ የሚያሳይ ጥናት ነው! ይህን መረጃ አንብባችሁ፣ ለሌላው አድርሱ! ቢቻል ለገበሬውም ፕሪንት ተደርጎ መድረስ ነበረበት! ……ይህ ጥናት ከደረሰን መረጃ ትንሹ ሲሆን በቀጣይም በተከታታይ እናደርሳለን) በ”ቅማንት ጥያቄ” ስም የሚነግደው የሕወሓት ሴራ ሲጋለጥ ዶ/ር አብይ አህመድ መቀሌ ላይ ስለ ወልቃይት ካደረገው ንግግር በኋላ የወልቃይት ጉዳይ እንደገና መነጋገሪያ ሆኗል። በአማራ ሕዝብ ላይ በሚፈፀመው በደል ጩኸቱ ገዥዎችንም እስከ ማስደንገጥ ደርሷል። ከመጀመርያውም የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ የተነሳው ህወሓት የአማራን ሕዝብ እርስ በእርሱና ከሌላ ሕዝብ ጋር በማጋጨት የስልጣን ጊዜውን ሲያራዝም ኖሯል። ሰሞኑን የወልቃይት ጥያቄ እንደገና በአዲስ መልክ መነሳቱ ያሰጋው ህወሓት የተለመደ ሴራውን ጀምሯል። ዶ/ር አብይ ጎንደር በሄደበት ወቅት የቅማንት ጥያቄን የሚያነሱ ሰዎች ባነር አስልፈው እስከመግባት ደርሰዋል። ምን ምን ጥያቄ ማንሳት እንዳለባቸው ጎንደር ላይ በገዥዎቹ ድጋፍ መወያየታቸውም ተሰምቷል። ከትናንት ጀምሮ ደግሞ በቅማንት ጥያቄ ሰበብ የአማራን ሕዝብ ለማጫረስ ወደ ተግባር መገባቱ ታውቋል። በቅርብ አመታት በደሉ የወልቃይት ጥያቄ፣ እንዲሁም የአማራ አርሶ አደሮችን እያፈናቀለ ለሱዳን የሰጠው መሬት ላይ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማዳፈን የአማራን ሕዝብ እርስ በእርስ ለማጋጨት ያስችለኛል ያለውን የቅማንትን ጥያቄ አንስቷል። የቅማንት ጥያቄ እንዲነሳ የተደረገው የወልቃይትና የሱዳን መሬት የተሰጠባቸው አካባቢዎች ድንበር ላይ መሆኑ ጥያቄ የሚያነሳውን ሕዝብ በመከፋፈልና በመወጠር ላይ የተሰመረተ ፖሊሲ ስለመሆኑ በግልፅ የሚያስረዳ ነው። የአማራን ሕዝብ እርስ በእርስ በማፋጀት የወልቃይትና ለሱዳን የተሰጠውን መሬት ጉዳይ ለማዳፈን የቅማንትን ጉዳይ በደህንነት
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በስልጣን መከታ በዘረፋ የተገነባው ኤፈርት ይወረስ !!! ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ አቋም ነው።

በስልጣን መከታ በዘረፋ የተገነባው ኤፈርት ይወረስ !!! ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ አቋም ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ)   ሕወሓት ከመላው ኢትዮጵያ በዘረፈው ገንዘብና ንብረት የተገነባው ኤፈርት የትግራይ ሕዝብ ንብረት አይደለም። የኢፈርት ገንዘብና ንብረት ሕወሓት ስልጣኑን መከታ አድርጎ ያከማቸው ስለሆነ በመንግስት ይወረሳል ። ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ሽፋን ከባድ የሆኑ በርካታ የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በኢትዮጵያ ላይ ሰርቷል። እንዲሁም በጎጥ ያደራጃቸው የኢፈርት ቅርንጫፍ የሆኑት ጥረትና ዲንሾ የተሰኙ ድርጅቶች መወረስ አለባቸው። የፖለቲካ ድርጅቶች በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተው ሌላውን ነጋዴ ከገበያ ውጪ ከማድረጋቸውም በላይ የሃገርን ኢኮኖሚ አድቅቀውታል።   ኤፈርት በዝርፊያ የከበረ ድርጅት እኮ ነው ፤ ሕወሓት ያሰማራቹ የትግራይ አክቲቭስቶች ዘላችሁ ምስኪኑ የትግራይ ሕዝብ ላይ ትንጠለጠላላቹ ፤ ነገ ተነገወዲያ የሕወሓት ጄኔራሎችና ባለስልጣናትም የዘረፉት ንብረት የትግራይ ሕዝብ ነው ከማለት አትመለሱም ፤ የኢፈርት ገንዘብና ንብረት ሕወሓት ስልጣኑን መከታ አድርጎ ያከማቸው ስለሆነ በመንግስት ይወረሳል ። የበይ ተመልካች መሆን እያበቃ ነው ሕዝቡ ጠላቱ ሕወሓት እንደሆነ አውቋል። የትግራይ ሕዝብን ሽፋን እያደረጉ መነገድ ይቁም።   ከሞራልም ይሁን የወደቀውን ኢኮኖሚ ከማንሳት አንጻር የግዴታ የፖለቲካ ድርጅቶች ስልጣንን መከታ በማድረግ በዝርፊያ የገነቡት ኤፈርት የተባለ የኢኮኖሚ አውራ እና እንደ ዲንሾና ጥረት ያሉ መነገጃ ድርጅቶች ሊወረሱ ይገባል። ድርጅቶቹ በሕገወጥ መንገድ ከፍተኛ የሆነ መዋእለ ንዋይ በሃገር ውስጥና በውጪ ሃገር አከማችተዋል። ይህ የሕዝቦች ንብረትና ሃብት በመንግስት ቁጥጥር ስር ከዋለ ከፊሉን ወደ ግል ባለሃብቶች ከፊሉን ወደ ንግድ ማህበራት በማዘዋወር ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ለውጥ እድገትና ታላቅ ስኬት
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ትግራይ የኢትዮጵያ ሞተር ነች! ዶ/ር አብይም ትክክል ነው! ቅኔውን ይዘርፈዋል!

ትክክል ነው! ትግራይ የኢትዮጵያ ሞተር ነች! ሞተርም አይጠፋትም! ዶ/ር አብይም ቅኔውን ይዘርፈዋል! ከስር ዝርዝሩ ላይ ያሉት ፋብሪካዎች ያላቸውን ሞተር እንኳ ብናሰላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት መካከል ከ80 በመቶ በላይ ነው። የቀሩት፣ በሌላ ቦታ ያሉትን፣ የመከላከያ ሰራዊቱ ጀኔራሎች የሚቆጣጠሩት የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ሞተሮች ሲጨመሩ የዶ/ር አብይን አባባል እውነት ያደርገዋል!
Tagged with: , , ,
Posted in Ethiopian News

“አብይን ያስቀመጥነው በአሜሪካ ግፊትና ብአዴንን ፍራቻ ነው ።” ሕወሓት

ዶ/ር አብይ የኢህአደግ ሊቀመንበር ከሆነ ጀምሮ በህወህት ቤት መረጋጋት ጠፍቷል:: ሰሞኑን ለኮንፍረንሱ ከሸገር መቀሌ የከተሙት የህወሃት ጋዜጠኛና ብሎገር ከህወሀት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተገናኝተው ነበር::ጋዜጠኞቹና ብሎገሮቹ “እንደት ብታስቡ ነው አብይን ጠ/ሚ/ር ያደረጋችሁት?ኦህዴድን ፈርታችሁ ?ወይስ መንገድ የሚዘጋውን ወሮ በላ ፈርቲችሁ ነው የተሸነፋችሁት? የሚሉ ተጨማሪ ግን መልስ የሌላቸውን ጥያቄዎች ንደት በተሞላበት ሁኔታ ቢጠይቁም ከባለ ስልጣኖቹ ያገኙት መልስ አጭርና ግልፅ ነበር:” አሳልፈን የሰጠነው አይደለም ኦህዴድን ልንፈራ ብአዴንንም አልፈራንም ተኮራርፈው ነው በየፊናቸው የበረሩት ፤ ሼባዎቹ ጎረምሶቹን በጠረባ ይጥሏቸዋል ፤ ብአዴን ደሕንነት ቢሮውን ይቆጣጠራል የሚል ስጋት አለባቸው ። ነገር ግን ሁሉም ነገር የተከናወነው በአሜሪካ መንግስት አስገዳጅነት ነው :ምንም ማድረግ እልቻልንም ::”የሚል መልስ ነው የሰጧቸው ሲሆን :አንድ ታዋቂ ብሎገር ግን “እንደት ለነጭ ትንበረከካላችሁ?መለስ በህይወት ቢኖር ያፍርባችሁ ነበር “ሲላቸው አንዱ ባለ ስልጣን “ዝም በል ባክህ ስቴት ድፓርትመን ለሳሊኒ ያከራየሁን መኪና ከምንም ስለማይቆጥረው አንተን ምንም አያሳስብህም :እኛ ግን ብዙ የሚያስጨንቅ ነገር አለብን”ሲል መለሶለታል::ብአዴን ግን ለምን እንደሆን ባይታወቅም ከኦህዴድ በላይ በደስታ ስክራ ትገኛለች::
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News

Rearrest of journalist outrageous attack on right of free expression – Pen America (ESAT)

The re-arrest of Eskinder Nega is inhumane and an outrageous attack on the right of free expression in Ethiopia, Pen America, a press watchdog said in a statement. The statement by the Pen America came after authorities in Ethiopia rearrested journalists and bloggers last Sunday for what the authorities allege was holding an “unauthorized” meeting and displaying an Ethiopian flag. The journalists and bloggers, some of whom released not a month ago were at a private get together at the residence of journalist Temesgen Desalegn, who was also arrested, when security forces detained them. Leaders of opposition parties, including Andualem Arage were also jailed with the journalists and bloggers. Eskinder, a 2012 Freedom to Write Award honoree, who also got several other international recognitions from press freedom watchdogs, was released in February after almost seven years of imprisonment on trumped up charges. “The arrest of Eskinder Nega and other previously imprisoned bloggers, journalists, and activists demonstrates that despite their recent overtures toward credible reform efforts, the Ethiopian government has no intention of softening their brutal suppression of free speech,” said Karin Deutsch Karlekar, Director of Free Expression at Risk Programs at PEN America. “For ​Eskinder, his freedom was an opportunity
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ይድረስ ለቀድሞ የህወሃት ታጋዮች ( ከአርቲስት አስቴር በዳኔ )

ይድረስ ለቀድሞ የህወሃት ታጋዮች ( ከአርቲስት አስቴር በዳኔ ) ያኔ የዛሬ 43 ወይም 44 ዓመት ወጣትነታችሁንና ልጅነታችሁን ለመሰዋት ወደ ትግል የገባችሁበትን ዘመን መለስ ብላችሁ አስቡት እስኪ። ትግራይን ነፃ ለማውጣት(ከኢትዮጵያ ለመገንጠል)አልነበር? ዛሬም ስማችሁን አልቀየራችሁም አላማችሁን ግን እንጃ፣ ህዝባችን ተበድሏል ብላችሁ ያሰባችሁለትን የትግራይ ህዝብ ፍትህና እኩልነት ለማጎናፀፍ እና በሌሎች በርካታ ብሶቶች እንደሆነ ብዙ ግዜ ነግራችሁን ነበር። በሂደት መንግስት ለመመስረት የኢትዮጵያ ህዝብን ነው የምንወክለው ብላችሁ 3 ደርጅቶችን ፈጠራችሁ። ብዙውን ታሪክ ልዝለለውና ልነግራችሁ ወዳሰብኩት ነጥብ ላተኩር ። አዲስ አበባን ስትቆጣጠሩ የተናገራችሁትን በወቅቱ ትንሽ ልጅ ብሆንም ፈፅሞ አልረሳውም የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊትደርግ ሲጠቀምበት የኖረውን የአዲስ አበባውን ሬዲዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ተቊጣጥሮታል። ጉምቦት 20 ሺዘጠኝ ሞቶ 83 ዓ.ም. ይህን መልዕክት ከጠዋት ጀምሮ እስከማታ ስለሰማሁት የድምፁ ቅላፄ ሳይቀር ዛሬም ድረስ ይሰማኛል። የዘመናት ብሶት ያላችሁን የ17 ዓመቱን የደርግ አገዛዝ ዘመን ነበር። እናንተ ስልጣን ላይ ከወጣችሁ 27 አመት ሊሆናችሁ ነው። ደርግ አትናገሩ አትተቹ እርምጃ እወስዳለሁ ስላለ ደፍሮ የሚናገር አልነበረም። እናንተ ደሞ ዴሞክራሲያዊ መብታችሁ ነው እንደልባችሁ ተናገሩ ብላችሁ ነፃነትን አስለመዳችሁን። ይኸው ዛሬ ዝም በሉ ብትሉንም ዝም ማለት አልቻልንም። መንግስት የሚቀያየረው በምርጫ ነው ብላችሁ ምርጫ አሳጥታችሁን ብቻችሁን 27 ዓመት መራችሁን ( ገዛችሁን) እናም ዛሬ ብዙ እጥፍ ብሶት የወለደው ትውልድ አፈራችሁ። በፈጣሪ አስቡት እስኪ “ብሶት የወለደው “ብሎ ስልጣን ላይ የወጣ ሌላ “ብሶት የወለደው” እስኪጥለው ይጠብቃል??? ዛሬ በዚህ እድሜያችሁ እየተዋጋችሁ
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News