­

አብይብ አሕመድ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ጥሷል ሲል ሕወሓት ከሰሰ

ሕወሓት፣ ፌደራል መንግሥቱ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት በመጣስ በትግራይ ሕዝብ፣ በፖለቲካ ድርጅቱ፣ በባለሥልጣናቱ፣ በጸጥታ ኃይል አዛዦቹና በተቋማቱ ላይ “ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል” በማለት ዛሬ ባስተላለፈው አጭር መልዕክት ከሷል። ሕወሓት፣ መንግሥት በተለይ በቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አማካኝነት የከፈተው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በትግራይ ሕዝብና በዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ላይ “ከፍተኛ ስጋት” ፈጥሯል ብሏል። የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አንቀጽ 3 ሕወሓትና የፌደራል መንግሥቱ ከማናቸውም የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እንዲቆጠቡ ይደነግጋል ያለው ሕወሓት፣ ፌደራል መንግሥቱ ከፕሮፓጋንዳ ድርጊቶቹ ይቆጠብ ሲል ጠይቋል።