የሕክምና ማስተማሪያ ሆስፒታሎች ያሏቸው በርካታ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የጤና ባለሙያዎችን ለመቅጠር ማስታወቂያ በማውጣት ላይ እንደኾኑ የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎች ገልጸዋል። አለርት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ 50 ጠቅላላ ሐኪሞችን፣ 120 ነርሶችንና 100 ሚድዋይፈሮችን ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱን አስተባባሪዎቹ ያጋሩት መረጃ ያሳያል። የካቲት 12 ሆስፒታል ሬዚደንት ሐኪሞች እስከ ዓርብ ግንቦት 15 ወደ ሥራና የትምህርት ገበታቸው ካልተመለሱ አካዳሚያዊ ርምጃ እንደሚወስድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሲያወጣ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በበኩሉ እስከ ነገ እኩለ ቀን ወደ ሥራቸውና ትምህርታቸው ያልተመለሱ ረዚደንት ሐኪሞች ጥቁር ከዩኒቨርስቲው እንዲለቁ አሳስቧል።