የአሜሪካ አምባሳደር ከሕወሓት መሪዎች ጋር በመቀሌ ተገናኙ

የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ ዛሬ ወደ ትግራይ አቅንተው ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አማኑኤል አሠፋና ከጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ አዛዦች ጋር በጸጥታ፣ ፖለቲካዊ፣ በሰብዓዊ ጉዳዮች፣ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበርና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። አምባሳደሩ የሽሬውን የተፈናቃዮች መጠለያ የጎበኙ ሲኾን፣ ለተፈናቃዮች ዕርዳታ መስጠት ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችልና መፍትሄው ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደኾነ መናገራቸውን የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። አምባሳደሩ፣ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ከተፈናቃዮቹ ጋር ካደረጉት ውይይት ተረድቻለሁ ተብሏል።