በኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ላይ ስለሚፈጸመው ተደጋጋሚ እስር ሲፒጄ ምን አለ?
በኢትዮጵያ ከመጋቢት ወር አጋማሽ እስከ ሚያዝያ ወር አጋማሽ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ 14 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሰራተኞች ለእስር ተዳርገው እንደነበር ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) አስታወቀ። ከታሰሩት ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች ውስጥ ሁለቱ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ሲፒጄ ገልጿል።
ሲፔጄ ይህን የገለጸው፤ በየሀገራቱ ያሉ ጋዜጠኞችን የተመለከቱ ሰሞነኛ ጉዳዮችን አጠናቅሮ ይፋ በሚያደርግበት ዘገባ ላይ ነው። ድርጅቱ ትላንት አርብ ግንቦት 8፤ 2017 ባወጣው ዘገባ፤ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠች አስታውሷል።
በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችን በተመለከተ ድርጅቱ በየዓመቱ በሚያወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፤ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ከኢትዮጵያ በላቀ ጋዜጠኞች የታሰሩባት ሀገር ኤርትራ መሆኗ ተመልክቷል። ዓመታዊ ሪፖርቱ እስከተጠናቀረበት እስካለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ድረስ በኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞች ስድስት እንደነበሩ ሲፒጄ በትላንቱ ሪፖርቱ ጠቅሷል።
ይህ ቁጥር ባለፈው መጋቢት እና ሚያዝያ ወር በተፈጸሙ እስራቶች በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቦ ነበር። በመጋቢት ወር ከተፈጸሙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እስሮች ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች ላይ ነው።
ለዝርዝሩ
https://ethiopiainsider.com/2025/15939/