የጤና ሚንስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ፣ የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ የጤና ባለሙያዎች ባስቸኳይ ወደ ሥራቸው ካልተመለሱ የሙያ ፍቃዳቸውን ሊነጠቁ እንደሚችሉ ለመንግሥታዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል አስጠንቅቀዋል። በአድማው ሳቢያ የተወሰነ የሆስፒታሎች አገልግሎት መስተጓጎል መኖሩን ያመኑት ሚንስትር ደኤታው፣ ከድንገተኛ እና ከእናቶችና ሕጻናት ሕክምና ክፍሎች ጥለው የወጡ የሕክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን እናውቃለን ብለዋል። የአድማው ዋነኛ ተሳታፊዎች፣ ሬዚደንት ሐኪሞች እንደኾኑም ዶ/ር ደረጀ ጠቅሰዋል። የጤና ባለሙያዎች ሙሉ የሥራ ማቆም አድማ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል።