የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው አዋጅ “ጊዜውን የጠበቀ አይደለም” በሚል ተተቸ
የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቅስ ንብረት ባለቤት እና ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው አዋጅ “ጊዜውን የጠበቀ አይደለም” በሚል በፓርላማ አባላት ተተቸ። ትችቱ የቀረበው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 12፤ 2017 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
በአራት ክፍሎች እና በ20 አንቀጾች የተከፋፈለው የአዋጅ ረቂቅ፤ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ ለመሆን ማሟላት ስለሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፣ የፈቃድ አሰራሮች፣ ገደቦች፣ መብቶች እና ግዴታዎች አካትቶ ይዟል። የህግ ረቂቁ በዝርዝር እንዲታይ ለተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከመመራቱ አስቀድሞ በተደረገ ውይይት ላይ፤ ሁለት የፓርላማ አባላት ትችት አዘል ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል።
የአዋጁ ዋና ዓላማ “የውጭ ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ ማምጫ” እና “የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንደሆነ” መገንዘባቸውን የገለጹት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ ተወካዩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ በህግ ረቂቁ ላይ ያላቸውን ስጋቶች እና አስተያየቶች በዝርዝር አቅርበዋል። የፓርላማ አባሉ ለስጋታቸው በምክንያትነት ካስቀመጧቸው ጉዳዮች አንዱ የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ እና ደመወዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ሲነጻጸር ያለውን ልዩነት ነው።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15990/
🔴 የፓርላማ አባላቱን አስተያየት ለማድመጥ ➡️ https://youtu.be/0WW5cfnTOJc