2.4 ሚሊየን በላይ ዜጎች በኢትዮጵያ መፈናቀላቸውን አንድ ሪፖርት አመለከተ

በ2024 ምን ያህል ሰዎች ተፈናቀሉ ?

ዓለም አቀፉ የተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል (IDMC) ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2024 በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች (IDP) ቁጥር የተመዘገበበት ሆኗል ሲል በዓመቱ 83.4 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጿል  ።

በተለያዩ አከባቢዎች የተነሱ ግጭቶችና አመጾች መበራከት የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ለማሳየቱ ምክንያት ነው ሲባል በዚህ ብቻ ለ73.5 ሚሊዮን ሰዎችን ተፈናቅለዋል።

በዓመቱ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በአንጻሩ ለ 9.8 ሚሊዮን ሰዎች በምክንያትነት ተቀምጧል።

ሱዳን በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛውን ድርሻ በዓመቱ የያዘች ሲሆን 11.6 ሚሊየን ሱዳናዊያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ሶሪያ፣ ጋዛ እና ዩክሬን በከፍተኛ ሁኔታ ዜጎቻቸው የተፈናቀሉባቸው ሀገራት ናቸው።

29 ሃገራት በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ዜጎቻቸው እንደተፈናቀሉ መግለፃቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ በ2024 የተመዘገበው የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥርም ከፍተኛው እንደሆነ አንስቷል

ድርጅቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሪፖርቱ  ውስጥ ያካተተ ሲሆን በ 2024 2.4 ሚሊየን በላይ ዜጎች በሀገር ውስጥ መፈናቀላቸውን ሲገልጽ ከ80 በመቶ በላዩ የተፈናቀሉት ከግጭት ጋር በተያያዘ መሆኑን አስታውቋል።

በ2023 በአለም አቀፍ ደረጃ የውስጥ ተፈናቃይ የነበሩ ሰዎች ቁጥር 75.9 ሚሊየን ነበር።   https://www.internal-displacement.org/countries/ethiopia/