የአማራ ክልል ዳኞች በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ “ሃሳብ እንዳይሰጡ” የሚከለክል ደንብ ወጣ   

የአማራ ክልል ዳኞች በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ “ሃሳብ እንዳይሰጡ” የሚከለክል ደንብ ወጣ

በአማራ ክልል የሚገኙ ዳኞች፤ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት ወይም “አወዛጋቢ በሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ “በየትኛውም” ማህበራዊ ሚዲያ “ሃሳብ እንዳይሰጡ” የሚከለክል ደንብ ጸደቀ። ደንቡ በክልሉ የሚገኙ ዳኞች “ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን “እንዳይጠቀሙ”፣ “እንዳይከተሉ” እና “አባል እንዳይሆኑ” ይከለክላል።

የዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎችን የስነ-ምግባር እና የዲሲፕሊን የሚመለከተው ይህ ደንብ የጸደቀው ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ግንቦት 5፤ 2017 ነው። ደንቡን ያጸደቀው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች አስተዳደር አብይ ጉባኤ፤ ደንቡ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፏል።

የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ለማሻሻል በ2014 የወጣው አዋጅ፤ ለዳኞች እና ለጉባኤ ተሿሚዎች የስነ ምግባር እና የዲሲፒሊን ደንብ የማውጣት ስልጣን የሰጠው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ላለው አብይ ጉባኤ ነው። እስካሁን በስራ ላይ የቆየው የስነ ምግባር እና የዲሲፒሊን ደንብ የወጣው በ2007 ዓ.ም ነበር።

ይህ ደንብ “በርካታ ጉዳዮችን ያካተተ ቢሆንም ግልጽነት የጎደላቸው ጉዳዮችን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ” በአዲስ መልክ እንዲዘጋጅ መደረጉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። አዲሱ ደንብ እንዲዘጋጅ ከተደረገባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ በቀድሞው ደንብ ያልነበረ “የዳኞች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን” ማካተት በማስፈለጉ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

🔴 ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15924/