የፋኖ ኃይሎች የሰሩት ኦፕሬሽን ጠላት ኪሳራውን ተከናንቧል

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሃይል ጎጃም ቀጣና ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር መተከል ጣና በለስ ብርጌድ እና መብረቁ ብርጌድ በጥምረት በሰሩት አስደናቂ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረስ ችለዋል። በቀን 08/09/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:30 ሰዓት ወደ ፓዊ ወረዳ መንደር 26 ቀበሌ ሰርገዉ በመግባት በመከላከያ ካምፕ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 10 የጠላት ሀይል ሲደመሰስ 15 ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።

ሌላዉ 2 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸዉ የመተከል ጣና በለስ ብርጌድን ተቀላቅለዋል። “ድል ለተገፋዉ ለሰፊው የአማራ ህዝብ” !!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ጎጃም ቀጠና ጃዊ መተከል 4ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን