ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ።
በፓርላማ ውድቅ የተደረገው ነገር ግን ህወሃት በጉልበት ያጸደቀው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገበት የካቲት 9/2010 ዓ.ም ጀምሮ አገራችን ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቃ እየማቀቀች እንደሚገኝ ይታወቃል። በመሆኑም ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በበላይነት የሚያስፈጽሙትና የሚቆጣጠሩት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣የመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ፣ የመከላከያ ሚኒስተሩ፣ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም እንዲሁም የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነር ናቸው።
በዚህም መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተገኙ ውጤቶች፣ የጠፉ ጥፋቶች፣በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም እንዲገመገሙ በየቀጠናው የተሰበሰቡ መረጃዎች ተጠቃለው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ዝርዝር ሪፖርት እንዲደረግ ያዛል።
ይሁን እንጂ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት የሚቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዦች የሆኑት የህወሃት ወታደራዊ አዛዦች ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር መረጃ እንዲሁም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በመላ አገሪቱ ስለታሰሩት ዜጎች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ለዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲሁም ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አናደርግም ማለታቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
የመረጃ ምንጮቻችን አክለው የህወሃት ሰዎች ለዶክተር አቢይ ሪፖርት ብናቀርብ ነገሮችን ያበላሽብናል ብለው መስጋታቸውን አብራርተዋል። በተለይ ጄነራል ሳሞራ የኑስ <<ትላንት ለእኔ በተጠንቀቅ ሰላምታ ይሰጠኝ ለነበረ ለአንድ ተራ ወታደር ዛሬ ገና ለገና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ ብየ ሪፖርት አላቀርብም >> ሲል መናገሩ ተከትሎ ሁኔታው ዶ/ር አቢይ አህመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ያበላሽብናል ከሚል የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነሳሞራ አንሸነፍም ባይነት እንዲሁም የመታብይና የበታችነት ስሜት የተቀዳ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል። በዚህም ምክንያት በእነሳሞራ በአጠቃላይ በህወሃት ሰዎች ጥርስ ውስጥ