Blog Archives

የሊቅ ዐቢይ አስቸጋሪ ምርጫ። የግል አስተያየት (ከኀይሌ ላሬቦ)

የሊቅ ዐቢይና የነለማ ቡድን ተብሎ የሚጠራውን አንጃ ደጋፊዎች፣ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ የአንድነት ጐራ ናቸው ብል ስሕተት አይመስለኝም። የነለማ ቡድን ግን ሁሉም የኢሕአዴግ አባላት ናቸው። የዚህ ቡድን ደጋፊዎች ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢሕአዴግ በመልካም እንተርጉም ካልን ሆድና ጀርባ፣ በመጥፎ እናስመስል ከተባለ ደግሞ እባብና ርግብ መሆናቸውን ነው። ምንም ብንመኝ፣ ሁለቱ በፍጹም አብረው ሊኖሩም ሊደመሩም አይችሉም። “መደመር” የሚለው የሊቅ ዐቢይ ፈሊጥ ለነዚህ ሁለቱ በፍጹም አይሠራም። ባንድ አልጋ እንኳን ቢተኙ፣ ሕልማቸው ተጻራሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዘመን ተሻጋሪና ለማንም የማይበገር፣ ሌላውን ጐረቤቱንም ሆነ አካባቢውን እያሰፋና እያቀፈ የሚሄድ፣ እንከን የለሽ ስብጥርና ጒንጒን ማንነት ነው። ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት የሚታወቁት በተፈጥሯቸው ማንንም አስተናጋጅና ዐቃፊ በመሆናቸው ነው። የኢትዮጵያዊነት ዐቃፊነት፣ ኢትዮጵያ ከተባለው ግዙፍ ምድር መጥቆ ወሰኑንና ድንበሩን ዐልፎ፣ ለሌላውም ዓለምና ሕዝብ ተትረፍርፏል። የዓለም፣ በተለይም ጭቁንና ጥቊር፣ ሕዝብ በምዕራባውያን መብቱ ተጨፍልቆ ይኖር በነበረበት ወቅት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግሉን ድምፅ፣ በያለበት ሲያክላላው፣ ሲያስተጋባው፣ ሲያክለውና ሲያንረው ቈይቶ፤ የኋላ ኋላ ግቡን ለመምታት የበቃው በኢትዮጵያዊነት ዙርያ በመሰለፍና በመሰባሰብ ነው። ኢሕአዴግ በተቃራኒ በባሕርዩ ከፋፋይ፣ በልዩነት ላይ ያተኰረ፣ በጥላቻ መሠረት ላይ የተካበ፣ የጐጠኞችና የአገር ከሓጂዎች ጥርቅማጥርቅም ነው ማለት ይቻላል። ብዙዎች የሚሳሳቱት ኢሕአዴግን እንደፖለቲካ ድርጅት እያዩ ነው። ኢሕአዴግ የተፈጠረው የኢትዮጵያን ጥፋት ከኋላ ሁነው ይሸርቡ በነበሩት በውጭ ኀይሎች ሤራና ምክር ሲሆን፣ በእጁ ጠፍጥፎት ህልውና የሰጠው ግን፣ የታላቂቷ ትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ (ሕወአት) ነው። ሕወአት በኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት አያምንም።
Tagged with: , , , , , , , , , , , , ,
Posted in Ethiopian News

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ስለአሜሪካ ቆይታቸው ሀገር ቤት ሲገቡ የሰጡት መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ስለአሜሪካ ቆይታቸው ሀገር ቤት ሲገቡ የሰጡት መግለጫ   $bp("Brid_39362_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-undefined_1.mp4", name: "የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ስለአሜሪካ ቆይታቸው ሀገር ቤት ሲገቡ የሰጡት መግለጫ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180802_055541.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

አቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ከጅማ ዩንቨርስቲ ተሰጣቸው።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት (Peace and Security) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አገኙ የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት እና በ አሁኑ ስዓት ላለው ለወጥ ትልቁን ሚና በመጨወታቸው ከፍተኛ አድናቆትን እየተቸሩ ያሉት አቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ከጅማ ዩንቨርስቲ መቀበላቸው ተረጋግጧል ::
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ንፁሐን ዜጎች ላይ የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት የሚወገዝና የሀገሪቱን ህዝቦች ለበለጠ አንድነት የሚያነሳሳ እንደሆነ አቶ ለማ መገርሳ ገለፁ፡፡ (ቪድዮ)

  ሰኔ 16/2ዐ1ዐ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ንፁሐን ዜጎች ላይ የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት የሚወገዝና የሀገሪቱን ህዝቦች ለበለጠ አንድነት የሚያነሳሳ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ገለፁ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ጎብኝተዋል፡፡ $bp("Brid_28361_2", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/Facebook-1988774737821059.mp4", name: "ንፁሐን ዜጎች ላይ የተፈፀመው የቦንብ ጥቃት የሚወገዝና የሀገሪቱን ህዝቦች ለበለጠ አንድነት የሚያነሳሳ እንደሆነ አቶ ለማ መገርሳ ገለፁ፡፡ (ቪድዮ)", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/IMG_20180630_041147.jpg"}, "width":"550","height":"309"});  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንመልሳለን – አቶ ለማ መገርሳ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ክልል ያለአግባብ የተፈናቀሉ በክልሉ ሲኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰሩ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ለማ ተፈናቃዮቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ቦታ ላይ ሰላም ቢሰፍንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉ ገልጸው፥ ህዝቡ ከመንግስት ጋር በመተባበር ሰላሙን እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በሌሎች ሶስተኛ አካላት የሚሰጡ አጀንዳዎችን በመለየት ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ሊታገላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ተመሳሳይ ችግሮችን ሲፈጥሩ የነበሩ ኪራይ ሰብሳቢዎች የመልካም አስተዳደር ችግር የታየባቸው ጎሰኝነት እና አድሎ የሚያራምዱ አመራርና ሰራተኞች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት እና ህዝብ ባህል ሆኖ የቆየውን የብሄር ብረሰቦች አብሮነት ለማስቀጠልም ይሰራል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በኢንቨስትመንት ተቋማት አካባቢ በሰራተኛ እና አሰሪ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን በመነጋገር መፍታት ሲገባ ወደ አልተገባ ግጭት መሄድ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ ምንጭ  ፋና ብሮድካስት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይም ፕረዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በኦህዴድ አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ አስደናቂ ውሳኔ ማሳለፉን OBN ዘገበ።አማራዎችን ከኦሮሚያ ክልል ያፈናቀሉ ባለስልጣናት መባረራቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ድርጅት ጠቁሟል። በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅላችኋል፣ ወይም ለማፈናቀል ሞክራችኋል፣ ጥላቻን ዘርታችኋል፣ ወይም ህዝብ ለህዝብ እንዲጣላ ምክንያት ሆናችኋል የተባሉ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ ና የልዩ ልዩ ቀበሌዎች አመራሮችን አሰናብተዋል፣ የአንዳንዶቹም በህግ እንዲታይ አድርገዋል ብሏል የክልሉ ቴሌቪዥን። <<..የአማራ ህዝቦች ወንድሞቻችን ናቸው፣ ያለ እነሱ እነሱም ያለኛ..ወይም አንዳችን ያለ አንዳችን መኖር አንችልም..በቅርቡ የመጣውን ለውጥ እንኳን ተመልከቱ፣ የሁሉቱ ክልል ህዝቦች ትግል ነው..አሁን የምታዩት ለውጥ ያመጣው… የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች በአማራ ክልል ያለምንም ችግር እየኖሩ ነው፣ ስለሆነም ወንድሞቻችን በኦሮሚያ ክልል ያለምንም ስጋት ሰርተው እራሳቸውን መለወጥ፣ ሀብት ማከማቸት ይችላሉ፣ አንዳንዶች በኦሮሚያ ና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ አለመተማመንን ለመፍጠር እየተሯሯጡ እንደሆነ በዚህ ሳምንት የታየ ድርጊት መሆኑን አረጋግጫለሁ፣ ስለዚህ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ይንን ሴራ መመከት ያስፈልጋል.. >>..ሲሉ ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትም ተናግረዋል ሲል ነው የዘገበው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው)

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው) በኦሮሚያ ክልል በብዙ ዞኖች አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ለምሳሌ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌና ሌሎችም የአዲስ አበባ ዙሪያ ዞንን ጨምሮ አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ አንዱ ሲያቆም ሌላው እየተከተለ ሁሉም ቦታ ተፈናቃይ ብቻ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ የሚፈናቀሉት በሕወሓት ትእዛዝ ነው ማለት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡ ሁሉም አማሮች እየተፈናቀሉ ያሉት ለአማራ ተወላጆች ከ2 ሔክታር መሬት በላይ አይገባቸውም በሚል ከኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በወረደ ትእዛዝ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባና እንግልት ያደርሳሉ፡፡ ለምን ብለው የሚጠይቁ በወንጀለኛነት ይታሠራሉ፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው ከአመያና ኖኖ ወረዳ ቤት ንብረታቸው ወድሞ እንደገና 14 ዓመት በላይ እስር ተፈርዶባቸው በአምቦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አማሮች አሉ፡፡ የሚፈጠሩ አጋጣሚዎችን ሁሉ ወደብሔር ግጭት ለመውሰድ የሚጥሩ አካላት በሁለቱም በኩል እንዳሉ እሙን ነው፡፡ ይህ ችግር የኦሮሞ ሕዝብ ችግር እንዳልሆነ እናምናለን፡፡ ችግሩ የሚያስፈልገው ፖለቲካዊ መፍትሔ ነው፡፡ አቶ ለማና ዶክተር ዓቢይ ለአገር አንድነት እንሠራለን እንደሚሉት የዚህን ጉዳይ በአፋጣኝ መልስ ሊሰጡት ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን የሚከተለውን ቀውስ ለመተንበይ የግድ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡ ስለሆነም በሰከነ አእምሮ የሚያስብ ማንኛውም ፍጡር ሁሉ ይህን ኢሰብአዊ ድርጊት እያወገዘ ውስብስብ ችግር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ልንጠይቅ ይገባል፡፡
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ ለማ መገርሳ ኦሕዴድን ይንቁና ይጠየፉ የነበሩ ሰዎችን በትግላችን ለሐገራቸው አብቅተናቸዋል ሲሉ ተናገሩ።

አቶ ለማ መገርሳ ኦሕዴድን ይንቁና ይጠየፉ የነበሩ ሰዎችን በትግላችን ለሐገራቸው አብቅተናቸዋል ሲሉ ተናገሩ። “ኦፒዲዮ ስለሆን ለዘመናት ይጠየፍን እና ይንቁን የነበሩትን ነፃ አውጥተን ለሀገራቸው አብቅተናቸዋል” ፕ/ት ለማ መገርሳ ላለፉት አመታቶች ኦሕዴድ የሕወሃት አሽከርና የትሮይ ፈረስ ተብሎ በተቃዋሚዎች ሲተች የነበረ ሲሆን በተለይ እንደ ኦነግ ያሉ በሌንጮ ለታ የሚመሩ ቡድኖች ኦሕዴድን እንደ ጋርቤጅ ይጠየፉትና ይንቁት ነበር። ቢሆንም በስተመጨረሻ በቄሮ ትግል በኦሕዴድ አስተባባሪነት በተገኘ ሕዝባዊ ድል እነ ሌንጮ ለታ ኦሕዴድን እንደ ንጉስ እንዲቀበሉ አድርጎ ወደ ሐገር ቤት ገብተዋል። 1/ዲሞክራሲ በወሬ ብቻ አይመጣም፡፡ የሚሰባበረውን መሰባበር የሚነቀለውን መንቀል ያስፈልጋል፡፡ 2/ባህላችንም ዲሞክራሲን እንዲሰፋ የሚያግዝ ሳይሆን በተቃራኒው እንዲቀጭጭ የሚያደረግ ስለሆነ እሱ ላይም መስራት አለብን፡፡ 3/እስረኛውን እንደወራጅ ወንዝ እየለቀቅን ያለነው እስርቤት ለመዝጋት እቅድ ስላለን ሳይሆን አዲስ የፓለቲካ አየር ለመፍጠር ስለምንፈልግ ነው፡፡ 4/..በኦሮሚያ በአንድ አመት ውስጥ 40ሺ እስረኛ በላይ የለቀቅነው ግለሰብን ብቻ ነፃ ለማውጣት ስለምንፈልግ እንዲሁም ለመወደድ ወይም እንዲጨበጨብልን ስለፈለግን ሳይሆን የመጠላለፍ እና የመጠፋፋት ባህላችንን ለመቀየር ነው ፡፡ 5/ሰዎችን ከእስርቤት አይደለም ነጻ ያወጣነው..ተሰደው የዜግነት መብታቸውንም ካጡት የስደት ኑሮ ነው..ከባዕድ ሀገር እስር ቤት ጭምርም ነው ፡፡ 6/ታሪክ እየቀየርን ነው.. ሁሉንም የፓለቲካ ፓርቲ ከያሉበት ግቡና አብረን እንስራ የምንለው የፓለቲካ ገበያ ለመክፈት ሳይሆን በእውነት እና በሀቅ የሀገሪቱን ታሪክ ለመቀየር ስለምንፈልግ ነው፡፡ 7/ ኦፒዲዬ ስለሆን ለዘመናት ይጠየፍን እና ይንቁን የነበሩትን እና ከእናንተ በላይ ነን የሚሉትንም ነፃ አውጥተን ለሀገራቸው አብቅተናቸዋል፡፡ 8/ እኔ ምኞቴን ነግራችሁለው..እዚህ ወንበር
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል ኣማርኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን፣ ኦሮምኛም በግዕዝ ፊደል ትምህርት እንዲሰጥ ምሁራን ለ አቶ ለማ መገርሳ ደብዳቤ ፃፉ።

በኦሮሞ ክልል ኦሮምኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው ዞኖችና ወረዳዎች፣ እንዲሁም በክልሉ ኣማርኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን፣ ኦሮምኛም በግዕዝ ፊደል ትምህርት እንዲሰጥና የሌሎች ማህበረሰባትን መብታቸው ተረግጦ፣ ደህንነታቸው አደጋ ላይ ወድቆ፣ ከኦሮሞው ማህበረሰብ እኩል እንዳያታዩ ያደረጉ  የክልል መንግስቱ አሰራሮች፣ ፖሊሶዎችና ሕጎች እንዲሻሻሉ ጥሪ አቅርበዋል። ቋንቋ የመግባቢያ መሳሪያ እንደሆነ የገለጹት ምሁራኑ፣ ኦሮምኛ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በሌላው ህየአገሪቷ ክፍል እንዲነገርና እንዲስፋፋ፣ በአማራ ክልል በትምሀት ቤቶች፣ በግ እዝ እንዲጻፍ ለአቶ ገዱ አንዳራጋቸው መጻፋቸው ይታወቃል። ለአቶ ለማ በጻፊትም ደብዳቤ አፋን ኦሮሞ በላቲን መጻል ትክክል እንዳልነበረና አሁንም እንዳልሆነ በድጋሚ አስምረዉበት፣ ኦሮምኛ እንዲያድግ፣ ሌሎች ማህበረሰባትም የኛ ነው ብለው እንዲቀበሉት፣ እንዲማራትና እንዲያውቁት ለማበረታታ የአገር ቅርስ የሆነው፣ በሙሉም መስፈርት ለኦሮሞኛ ብቃት ያለውን የግእዝ ፊደል መጠቀመ እንዲጀመር አሳስበዋል። መምህራኑና አክቲቪስቶቹ መምህር ልዑለቃል አካሉ፣  ዶ/ር ኣበራ ሞላ ፣ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፣  ፕ/ር ማሞ ሙጬ፣  ፕ/ር ባዬ ይማም ፣ ፕ/ር ኀይሌ ላሬቦ፣ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣  ዶ/ር አበባ ደግፌ፣ የተከበሩ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ያሬድ ጥበቡ፣ አቶ ሰይፉ አዳነች ብሻው፣  አቶ ተፈራ ድንበሩ፣ አቶ ብርሃኑ ገመቹ፣  አቶ አብርሃም ቀጄላ፣ አቶ ታደሰ ከበደ፣ ወ/ሮ እስከዳር አውላቸው፣  አቶ ተመስገን መኩሪያ  እና አቶ ግርማ ካሳ  ሲሆኑ ጽሁፋቸውን እንደሚከተለው ከዞኢህ በታች አቅርበናል።   ደብዳቤዉ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ===== ጉዳዩ – በክልሉና ኦሮምኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው ዞኖችና ወረዳዎች ኣማርኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን፣ ኦሮምኛም
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብይ ተመርጧል፣  ለማ አሸንፏል! (ስዩም ተሾመ)

አብይ ተመርጧል፣  ለማ አሸንፏል! (ስዩም ተሾመ) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሲሆን ያሸነፈው ለማ መገርሳ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የህዝባዊ ንቅናቄው ባለቤት የኦሮሚያ ቄሮዎች ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ በኢህአዴግ መንግስት ውስጥ የለውጥ ንቅናቄ የተጀመረው በለማ ቡድን (Team lemma) አማካኝነት ነው፡፡ ስለዚህ በፖለቲካና ኢኮኖሚው ረገድ ስር-ነቀል ለውጥ እንዲመጣ እየጠየቀ ያለ ማህብረሰብ እና ይህን ጥያቄ ተቀብሎ ለማስተናገድ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ያለው አመራር አለ፡፡ ነገር ግን የለማ አመራር የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ሁለት መዋቅራዊ ችግሮች ነበሩበት፡፡ አንደኛ፦ በማንኛውም አግባብ የለውጡን ንቅናቄ ለመቀልበስ ጥረት የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ የሆነ የፖለቲካ ቡድን (ህወሓት) የለማን እጅ ጠምዝዞ ይዞት ነበር፡፡ ሁለተኛ፦ በአገልጋይነት እና ኪራይ ሰብሳቢነት መስፈርት ተመርጠው በክልሉ የሲቪል ሰርቪስ መዋቅር እና በድርጅቱ ኦህዴድ ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የሚፈለገው ለውጥ የሞት ያህል ያስፈራቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ በክልሉ ውስጥ ካሉት 500ሺህ ሲቪል ሰርቫንቶች 100ሺህ (20%ቱ) በተጭበረበረ የትምህርት ዶክመንት ተቀጥረው የሚሰሩ ናቸው፡፡ አንደኛ ላይ የተጠቀሰው እንቅፋት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የለማን ቡድን ለማስወገድ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል የለማ አመራር ሁለተኛውን እንቅፋት ለመፈንቀል ሙከራ ሲያደርግ ካድሬዎቹ ከወላጃቸው ህወሓት/ኢህአዴግ ጋር በመመሳጠር ለማን እጁን ጠምዝዘው ለመጣል ይሞክራሉ፡፡ የዶ/ር አብይ መመረጥ ከማንም በላይ የለማን አመራር ጠቅሞታል፡፡ ምክንያቱም የለማ ቡድን እጁን ከፀረ-ለውጥ ቡድኑ አስለቅቋል፡፡ በመሆኑም አሁን በነፃነት መወሰን፣ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በአገልጋይነት እና ኪራይ ሰብሳቢነት መስፈርት ተመርጠው በክልሉ መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉትን ሆድ-አደሮች መንጥሮ ማስወገድ ይችላል፡፡ በዚህ መሠረት፣ በክልሉ ህዝብና መንግስት መካከል
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እርሙ እና የአንድ ሰሞኑ የቲም ለማ ትያትር ማብቂያው ሰአት (መንግስቱ ሙሴ)

እንደሚመስለኝ አሁንም ቲም ለማ የተባለውን የኦሕዴድ አመራር ቡድን እንደየለውጡ አካል አርገው የሚያዩ ተራ ዜጎች ብቻ አይደለም የሚዲያም ሰወችም እንዳሉ ለመረዳት ችያለሁ። ከዚህ በፊት ጄኔራል ጻድቃን ወ/ተንሳይ በጻፉት ላይ አስተያየት እና ነቀፋም አቅርቤ ስለነበር “የቲም ለማ” ተብየው የመድረክ ቅንብርን ገና ከመጀመሪያው የጻድቃን ወ/ተንሳይን ውትወታ የተከተለ ለመሆኑ ብዙ አመላካች ነበርቱ እና የቲሙ የቶሎ ቶ ሎ ኢትዮጵያዊነት ያልጣመኝን ያክል። ከመሀላቸው አንደኛው ሰው ለጠቅላይሚኒስቴርነት ሲመረጥም የነበረኝን አቋም ባለመቀየሬ እና አስተያየቴን በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ ገጼ በማንጸባረቄ የአካባቢው የዳላስ ሬዲዮ ከአንድ ወዳጀ ጋር በጉዳዩ እንድከራከርበት ጋብዞኝ እንደነበር ወዳጀም ሀሳቤን አክብሮ መለያየታችንን አስታወሰኝ። በኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት እየሞቱ እየታሰሩ መጠነሰፊ ችግርም በስርአቱ እየደረሰባቸው ታግለዋል። የዜጎች ደም በየጎዳና ፈሷል። በባህርዳር የ70 ወጣቶች ደም የፈሰሰ ቀንን ያህል ከባድ ወንጀል አላየሁም። በጎንደር በሰላም በወጡ ዜጎች ላይ የበአዴኑ የባንዳ ቡድን ከህወሓት አጋዚ ጋር ተደምሮ ያደረሰው እስራት፣ ግድያ እና ሽብር የሚረሳ አይደለም። በአንቦ ወጣቶች ላይ ድፍን ሁለት አመታት መብትን በሰላም ወጠው በመጠየቃቸው የተፈጸመባቸው መንግስታዊ ወንጀል ለአፍታ የምንረሳው ጉዳይ አይደለም። በአለማያ፣ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲወች የተፈጸመው በደል እና ወንጀል አሁንም ፍርድ ይፈልጋል። በአጭሩ በኦሮሞ እና አማራ ሕዝባችን ላይ የወረደውን መከራ የሚስተካከል የታሪክ ገጠመኝ ከዘመነ ህወሓት ውጭ የለም አይኖርምም። እናም የ OPDO ቲም በድንገት ብቅ ማለት ብዙ አነጋጋሪ ቢሆንም ዜጎች እየታደኑ ባለበት ወቅት የታየ phenomena በመሆኑ እየተጠራጠሩም ቢሆን ግዜ እንስትጥ ወደማለት የዞሩ መባዛታቸው ለትያትሩ የሚያስገርም አይደለም።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News