Blog Archives

በደቡብ ክልል በተከሰተ አለመግባባት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በደቡብ ክልል በተከሰተ አለመግባባት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ $bp("Brid_39500_1", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-2049970615034804.mp4", name: "በደቡብ ክልል በተከሰተ አለመግባባት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180802_173815.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ የሰጡትን የዲሞክራሲ ተስፋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችል የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ገለጸ።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የትጥቅ ትግሌን ላቆም እችላለሁ አለ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ የሰጡትን የዲሞክራሲ ተስፋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ። ንቅናቄው የሰለጠነ ፖለቲካ የምንመርጠው ፣ የምናውቀውና የምመኘው የትግል ስልት ነው በሚል ባወጣው መግለጫ እንዳለው አርበኞች ግንቦት ሰባት የመሳሪያ ትግልን ዋነኛ የትግል ስትራቴጂው በማድረግ የፖለቲካ ስልጣን የመያዝ አላማ ኖሮት አያውቅም። ሆኖም ግን አገዛዙ ይከተለው በነበረው ኋላ ቀር ፖለቲካ ምክንያት ዜጎች ከመንግስት ሽብር ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሲያበረታታና እራሱንም ከጥቃት ሲከላከል ቆይቷል ብሏል በመግለጫው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሰሞኑን ለፓርላማ ያደረጉት ገለጻ የሚያበረታታና የሚደነቅ ሲል አወድሶታል። መንግስት የሽብር ተግባር ይፈጽም እንደነበር ዶክተር አብይ በይፋ መናገራቸውና የፍትህ ስርአቱ ችግር ያለበት መሆኑን ማመናቸው ሃቅን ለመናገር የሚደፍሩ መሪ መሆናቸውን ይሳያል ሲል ንቅናቄው ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ይህ ብቻ አይደለም እሳቸው የሚመሩት ቡድንም ለሃገራዊ መግባባት ያለውን ዝግጁነትም ያሳያል ብሏል አርበኞች ግንቦት ሰባት። ዶክተር አብይ በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን ክልል የሚያጠና ኮሚሽን ይቋቋማል ማለታቸውንም አዎንታዊ ነው ሲል በመግለጫው አመልክቷል። ሕወሃትንና የትግራይን ሕዝብ ለይቶ ስለመመልከት ዶክተር አብይ አህመድ የተናገሩትም አርበኞች ግንቦት ሰባት ከልብ የሚያምንበትና በጽናት ሲያራምደው የቆየ እምነት መሆኑንም ገልጿል። እንደ አርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ ከሆነ በሕወሃት ውስጥ የለውጥ ሃይሎች መኖራቸው እሙን ነው። እናም የኢትዮጵያን ሰቆቃ በመቀነስ ረገድ ሕወሃት ውስጥ ያሉ የለውጥ አራማጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን እናምናለን ብሏል አርበኞች ግንቦት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሰሞኑ ግጭትና አለመረጋጋት በስተጀርባ የህወሓት እጅ አለበት! (ስዩም ተሾመ)

  አንዳንድ ግዜ በጣም ግራ የሚያጋቡ ፖለቲካዊ ክስተቶች ይከሰታሉ። ፍፁም ያልተጠበቁ በመሆናቸው የተከሰቱበትን ምክንያትና የሚያስከትሉትን አሉታዊና አዎንታዊ ተፅዕኖ በቀላሉ መገመት አስቸጋሪ ይሆናል። እንዲህ ያሉ ፖለቲካዊ ክስተቶችን መንስዔና ውጤት ለመረዳት ዝርዝር መረጃዎችን ከማሰባሰብና በተጨማሪ ከመሰረታዊ የፖለቲካ መርህ አንፃር መመልከት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ባለፉት ጥቂት ቀናት በደቡብ ክልል ዲላ፣ ሐዋሳ፥ ወልቂጤ፥… ወዘተ በመሳሰሉ ከተሞች ያልተጠበቀ ግጭትና አለመረጋጋት ተከስቷል። አብዛኞቻችን ከእነዚህ ግጭቶች በስተጀርባ የማን እጅ እንዳለና ዓላማው ምን እንደሆነ ከግምትና ጥርጣሬ በዘለለ ተጨባጭ ማስረጃ የለንም። ምክንያቱም በዚህ መልኩ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርስ አካል ሥራና ዓላማውን በግልፅ አስቀምጦ አይንቀሳቀስም። በመሆኑም ግጭትና አለመረጋጋት እንዲቀሰቀስ የሚያደርግበት ሂደትና ዓላማ በግልፅ ለመረዳት ዝርዝር መረጃዎችን ከማሰባሰብ በተጨማሪ በመሰረታዊ የፖለቲካ መርህ ላይ የተመሰረተ ትንታኔ ያስፈልጋል። በዚህ መሰረት ሰሞኑን በዲላ፥ ሐዋሳ፥ ወልቂጤና በመሳሰሉት የደቡብ ክልል ከተሞች ግጭትና አለመረጋጋት የተቀሰቀሰበት መሰረታዊ ምክንያት መረዳት ይቻላል። በመጀመሪያ ደረጃ በተጠቀሱት ከተሞች ግጭትና አለመረጋጋት የተቀሰቀሰው በዋናነት ቦምብ በማፈንዳት እና የብሔር ግጭት በመቀስቀስ ነው። ስለዚህ የግጭቱ መንስዔ ብቻ ሳይሆን ዓላማውም በዜጎች ላይ ሽብርና ፍርሃት መፍጠር ነው። ታዲያ በዜጎች ላይ ሽብርና ፍርሃት የሚፈጥረው ምን ዓይነት የፖለቲካ ቡድን ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ በፖለቲካ ሳይንስ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሆነውን “Politics” የሚለውን የአርስቶትል መፅሃፍ ዋቢ እናድርግ። እንደ አርስቶትል አገላለፅ፣ የሽብርና ፍርሃትን መጀመር የሚወስነው ተራ ዜጋ (ordinary man) ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣን ነው። በዜጎች ላይ ሽብርና ፍርሃት በመፍጠር ፖለቲካዊ ትርፍ የሚያገኙ በምን ዓይነት
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግብፅ ያሰረቻቸውን ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ፈታች ።

ግብፅ በሀገሪቱ ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ለቀቀች።ከአመታት በፊት በሊቢያ በአሸባሪዎች የተገደሉ ዜጎች አፅም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በክብር እንዲያርፍ ግብጽ እገዛ እንደምታደርግም መግባባት ላይ ተደርሷል። ሀገሪቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግብፅ ጉብኝታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤልሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው ኢትዮጵያውያኑን የፈታችው። ኢትዮያውያኑ ወደሀገራቸውም እንደሚመለሱም በውይይት ላይ የተሳተፉት የጠቅላይ ሚኒስቴር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግረዋል።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ያለመታከት ለዘጠኝ አመት የአገር ሀብት እየተዘረፈ ነው ሲሉ የሚጮኹት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ሰሚ አላገኙም ።

በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ …………….. ሰሚ ሳይኖር ተስፋ ሳይቆርጥ ዝም ብሎ የሚጮህ ሰው ታውቃላችሁ ? እኚህ ሰው እንዲህ ናቸው ። አቶ ገመቹ ዱቢሶ ይባላሉ ። እናም እኚህ ሰው ላለፉት ሁለት አመታት አይደለም ፡ ሶስት አራት አመታትም አይደለም ። ስድስት ሰባት አመታትም አይደለም ። ይኸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሆነው ከተሾሙ ከዛሬ ዘጠኝ አመት ጀምሮ አንድ ቀን ጩኸቴ ይሰማ ይሆናል እያሉ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ ሲያሰሙ ፡ ኸረ የህዝብ ገንዘብ እየጠፋ ነው ፡ ኸረ የመንግስት ሃብት እየተመዘበረ ነው እያሉ በተለያዩ ተቋማት ላይ በሚደረግ ምርመራ ላይ የሚገኘውን ጉድለት አቅርበው እርምጃ እንዲወሰድ አቤት ! እያሉ ይኸው አሉ ። ስለ እኚህ ሰው ሳስብ ጽናታቸው ይገርመኛል ። ሪፖርት ባቀረቡባቸው ተቋማት ላይ ከአመት አመት እርምጃ እንዳልተወሰደ እያወቁ ተስፋ ባለመቁረጥ ሁሌ እንደተናገሩ ነው ። አሁን አሁን ግን እኚህ ሰው ተስፋ ወደ መቁረጥ ተቃርበዋል ። ላለፉት ዘጠኝ አመታት እጮሃለሁ ነገር ግን ጩኸቴ ፍሬ አላፈራም እያሉ ነው ። በምድረ በዳ እንደሚጮህ ሰው ድምጽ ጩኸታቸው ሰሚ አላገኘም ። አቶ ገመቹ እንግዲህ ምን እንላለን ጽናቱን ይስጦት
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook