Blog Archives

በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡ (ምንሊክ ሳልሳዊ) ውሸት ማራባት ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡የማታ ማታም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ሰዎችም በአንድ ውሸት ሲሳቡና ያንን ውሸት የራሳቸው ሲያደርጉ ከዚያ የሚለያቸው ኃይል አይኖርም፡፡ ኦርጅናሌ ዋሾውን እንደተአምረኛ ያዩታል፡፡ በዙሪያው ይከባሉ፡፡ እንደመንጋም ይነዳሉ፡፡ በየፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳያችን አንፃር የሌለንን አለን፣ ያለንን የለንም ብለን ከዋሸንና ካሳመንን፤ ተከታያችን ሊደሰትበት፣ አልፎም ሊኮራበት ይችላል፡፡ ይሄ እርግማን ነው፡፡ እርግማኑ በመንግሥትም፣ በተቃዋሚም፣ በሰባክያንም፣ በምዕመናንም አንፃር ብናሰላው ያው ነው፡፡ ህዝብን ማታለል ክፉ እርግማን ነው፡፡ የማታ ማታም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ያም ሆኖ እንደማናቸውም ነገር ውሸትም ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡ ያለአቅማችን ጉልበተኛ ነን ማለትም ሆነ ጉልበተኛ ሆነን ምስኪን ኮሳሳ ነን ማለትም ያው መዋሸት ነው፡፡ እያየን አላየንም፣ እየሰማን አልሰማንም፣ እያጠፋን አላጠፋንም ማለትም ያው መቅጠፍ ነው! ስለግልፅነት እያወራን የበለጠ ሚስጥራዊ የምንሆን ከሆነ ያው መዋሸት ነው፡፡ ዛሬ ያልነውን ነገ ካልደገምነው ያው መዋሸታችን ነው፡፡ ሰውን በሸራ ኳስ እያጫወትን እኛ በካፖርተኒ የምንጫወት ከሆነ ያው ማጭበርበራችን ነው፡፡ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክም ያው መዋሸት ነው!ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም ያው መዋሸት ነው! አስገድደን የምንፈፅመውም ሆነ ዋሽተን የምናሳምነው፣ አሊያም በገንዘብ የምንደልልው፤ የዘወትሩን ሰው ቢያስጨበጭብልንም የክቱን ሰው ያሳዝናል፡፡ በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡የሌለ ጀግና መፍጠርም ሆነ፤ ያለን ጀግና መካድ ሁለቱም ማታለል ነው፡፡በከፋ መልኩ ሲታይ ራስንም ማታለል ነው፡፡ የሰው ዓላማ የኔ ነው ማለትና የሌላውን ስም የራስ ማድረግ፤ ከኢኮኖሚ ዘረፋም የከፋ ዘረፋ ነው፡:ውሸት እንደማግኔት መግነጢሳዊ ኃይል አለው፡፡ ማግኔት፤
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለኢትዮጵያ የለውጥ ጅማሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና እየሰጠው ነው

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ሪፎርም ሂደት እውቅና እየሰጠው ነው- መንግስት በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን ሪፎርም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና እየሰጠው መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡፡ ጽ/ቤቱ ባወጣው ሳምንታዊ የመንግስት አቋም መግለጫው በነሃሴ ወር ብቻ የእንግሊዝ፤ የጀርመን፤ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች፤ የቪዬትናም፤ የሳኡዲ ዓረቢያ እና ሌሎች በርካታ ሃገራት ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል፡፡ ይህም ሃገሪቱ በኢኮኖሚውና በፖለቲካው ዘርፍ እያካሄደች ላለው ሪፎርም እውቅና እና ድጋፍ መስጠታቸውን የሚያሳይ ነው ብሏል ጽ/ቤቱ፡፡ በንግድ፤ ግብርና፤ ኢንቨስትመንት፤ አቅም ግንባታ፤ ትምህርት እና በሌሎች መስኮችም ከሃገራቱ ጋር ተባብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱ ለውጡ በዲፕሎማሲ በኩልም ከፍተኛ ውጤት እያስገኘ መምጣቱን እንደሚያሳይ ነው የገለጸው፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት መካከልም በተደረጉት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች የግጭት ስጋቱ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ መቀነሱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያስታወቀው፡፡ ይህ ሁሉ ድል ሊመዘገብ የቻለው በኢትዮጵያዊያን መካከል የነበረው የጥላቻ ግንብ በመፈራረሱና የአንድነት፤ የፍቅር እና የመተባበር ስሜት በህዝቡ ዘንድ በመስረጹ ነው ብሏል፡፡ በመሆኑም የተጀመረውን የይቅርታ፤ የፍቅር፤ የአንድነትና የመደመር ጉዞን አጠናክሮ ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡ ይህን ጉዞ ለማደናቀፍ በአንዳንድ አካባቢዎች እየተደረጉ ያሉ ድርጊቶችን ማስቆም ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ እንደሆነና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በሃላፊነት ሊከታተለው እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን መንግስት አሳወቀ ።

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን መንግስት አሳወቀ ። የቀድሞ የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኦማር መሐመድ ኢሌ አዲስ አበባ አትላስ ከሚገኛው መኖሪያ ቤታቸው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ $bp("Brid_47360_1", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-2118395115154726MP4.mp4", name: "አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን መንግስት አሳወቀ ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/FB_IMG_1535372913941.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); እንደ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጻ አቶ አብዲ በሕግ ጥላ ስር እንዲውሉ ካደረጋቸው የወንጀል ተግባራት መካከል የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የብሔር ግጭት፣ በሃይማኖት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ማድረግ የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡ፖሊስ እሳቸውን ጨምሮ በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ሌሎች አካላትን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑ ታውቋል። #MinilikSalsawi
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ ኃይሎች መሣሪያቸውን እየጣሉ ወደ አገር ቤት መግባት የፖለቲካ አስቂኙ ቀልድ ነው ።

ግዮን፡- በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ ኃይሎች በድርድር መሣሪያቸውን እየጣሉ ሠላማዊ ትግልን በመቀበል ደ አገር ቤት መግባት ጀምረዋል፤ ይህንንስ እንዴት አየኸው? ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፡- የፖለቲካ አስቂኙ ቀልድ ይሄ ነው፡፡ እየተደረገ ያለው ድርድር አይደለም፤ ለምሣሌ ግንቦት ሰባትን ብትወስደው ድርጅቱ ለአስር አመት ያህል በኤርትራ በርሃ ነበር፤ እዚህ በተለይ አዲስ አበባ ላይ ቁጥሩ የማይናቅ እጅግ በጣም በርካታ ደጋፊ አለው፡፡ ወያኔም በተደጋጋሚ ሣር ቅጠሉን ግንቦት ሰባት ነህ እያለ በማሰር ለግንቦት ሰባት በተዘዋዋሪ የሽያጭ ሠራተኛ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ግንቦት ሰባት የተሻለ ጠንካራ ድርጅት ነው ብለን እናምናለን፤ ስለዚህ ይሄ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለማረፍ በያዙት የውጭ ሀገር ሆቴል ውስጥ አይደለም ተነጋግሮ መምጣት ያለበት፡፡ በትክክል አደራዳሪ ተመድቦ መወያየት ነበረበት፡፡ ይብዛም ይነስም በረሃ ሰብስቦ ይዟቸው የገባው ልጆች ዕድሜ ቢያንስ በአስር ዓመት ተቃጥሏል፡፡ ክሬም የሆነውን የወጣትነት ዕድሜቸውን ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ነጻነት ሰውተዋል፡፡ የእነዚህ በበረሃ የቆዩት የድርጅቱ ታጋዮች ዕድሜ አልተቃጠለም የምንለው ግንቦት ሰባት እነሱን የሚመጥን ውይይት ሳይሆን ድርድር ከመንግስት ጋር ቢያደርግ ነበር፡፡ አሁን ግንቦት ሰባት ሌላ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ሌላ ግንባር ነው፡፡ ኦነግ ሌላ ድርጅት ነው ፤ ኦህዴድ ሌላ ድርጅት ነው፡፡ የምር እነ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ለውጥ ፈላጊ ከሆኑ ድርጅቶች መጥተው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ላይ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው አስበው ከሆነ ከእነሱ ጋር መነጋገር የፈለጉት፤ አደራዳሪ ተቀምጦ የሁሉም ድርጅት ተወካዮች ሃሳባቸውን በግልፅ አስቀምጠው ነበር የአውሮፕላን ትኬት መቁረጥ የነበረባቸው፡፡ አሁን ግን እየሆነ ያለው ያ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የብአዴን እግድ መሠረተቢስ እርምጃ ነው ሲሉ አቶ በረከት ስምኦን አማረሩ ።

ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር ያደረግኩት ቃለ መጠይቅ (ከእንግሊዘኛ የተተረጎመ): ጥያቄ: ፖለቲካ ይቀጥላሉ ወይስ በቃዎት? አቶ በረከት ስምኦን: አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከእኔ ግለ- አስተሳሰብ ጋር አብሮ ስላማይሄድ አልቀጥልም። I’m thinking of coping Lidetu’s way (የልደቱን መንገድ/መስመር ለመከተል እያሰብኩ ነው) ጥያቄ: በመጀመርያ ብአዴን ሰሞኑን እርስዎ ላይ ስለወሰደው እርምጃ እናውራ። እርምጃው የተወሰደበት አካሄድ ምን ይመስል ነበር? እርስዎስ እንዴት ያዩታል? ተቀብለውታል? አቶ በረከት: መሰረተቢስ እርምጃ ነው። እንዲታወቅ የምፈልገው እኔ ስብሰባው ላይ እንዳልነበርኩ እና ይህንንም ለእነርሱ ማሳወቄን ነው። ይህም የሆነው በአሁኑ ሰአት በክልሉ ላይ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው። በአሁን ሰአት ክልሉ ላይ የህግ የበላይነት የለም። እርግጥ እየሆነ ያለው የደቦ ፍርድ (mob justice) ነው። ይህንንም የክልሉ መንግስት መቆጣጠር የቻለበት ሁኔታ አይታይም። የተጠቀሰውን የንግድ ድርጅት በተመለከተ ስለተባለው ጉዳይ ያለኝ ሪከርድ ይመሰክራል። በእኔ አስተዳደር ምንም የጠፋ ነገር የለም። እንደ እኔ አስተሳሰብ ይሄ እርምጃ የመጣው አንደኛ ምክትል ጠ/ሚሩን በቅርቡ በተካሄደው የመተካካት ወቅት አለመደገፌ፣ በአቋሜ የማልደራደር ስለሆነ እና ፊት ለፊት ስለምናገር እንዲሁም የማጥራት አካሄድ (cleansing move) ነው። ምክንያቱም በረከት ከተለየ አካባቢ የመጣ ነው ስለሚባል ነው። እርግጥ ቤተሰቦቼ የኤርትራ ስር መሰረት ቢኖራቸውም እኔ ተወልጄ ያደግኩት ጎንደር ነው። የንግድ ድርጅቱን በተመለከተ አመታዊ የኦዲት ሪፖርት አለው። የእኛ ድርጅት ከኤፈርት ድርጅቶች አንደኛ ነው ታክስን በመክፈል ጨምሮ። በዚህ እኔ እርግጠኛ ነኝ። ጥያቄ: በብአዴን የተወሰደውን እርምጃ ሲሰሙ አዘኑ፣ ደነገጡ ወይስ ሌላ ስሜት አጫረቦት? አቶ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ማስጠንቀቂያ : ራኒ ጁስ ተመርዟል… ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ራኒ ጁስ ተመርዟል… ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። ለህመምተኞች ለወላድ ለአራሶች ለህፃናት እንዳይሰጥ ለወገንዎ ሼር በማድረግ ይድረሱለት:: ልጆች በፍቅር የሚወዱት ራኒ RANI ማንጎ ጁስ የጥራት ጉድለት እንዳለበት የጤና ክብካቤ አረጋግጦ ይሄንን ደብዳቤ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች መረጃውን በትኗል:: ራኒን ባለመጠቀም ከአደጋው ራሳችንንና ወገናችንን እንጠብቅ:: ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ከስር ያልለውን ደብዳቤ ያንብቡት::
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአለም ባንክ ከ13 አመት እግድ በኃላ ለኢትዮጵያ የበጀት ድጎማ 1 ቢሊዮን ዶላር ፈቀደ ።

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት የአንድ ቢሊዮን ዶላር የበጀት ድጎማ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል። ይሕ ካለፉት 13 አመታት በኃላ የመጀመሪያ ነው የተባለለት ድጋፍ በባንኩ ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቷል ። በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ የአለም ባንክ የበጀት እርዳታውን ድጋፉን አቁሞ ነበር። ሙሉ ዘገባውን እዚህ ላይ ያገኙታል።   
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ዛሬ በሰጡት የመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች ፤ • አሁን ላይ ለአዲስ አበባ ከንቲባ እንደተሾመ የሚወራው ስህተት ነው፡ ቀጣዩ ምርጫ እስኪደርስ ከተማዋ በባላደራ አስተዳደር ከምትመራ ሶስት ወጣት ፖለቲከኞች ተቀምጠዋል፡፡ ለጊዜው የተቆጠሩ የህዝብ ስራዎችን ይዘው ወደ ስራ ገብተው ውጤት እያሳዩ ነው፡፡ • በቀጣዩ ምርጫ የአዲስ አበባ ህዝብ የራሱን ከንቲባ ይሾማል፡፡ • በአለም ላይ ከአንድ በላይ ቋንቋዎች በአንድነት የብዙ አገራት የስራ ቋንቋ ሆነው ያገለግላሉ፡፡በኢትዮጵያም አፋን ኦሮሞ የስራ ቋንቋ ይሁን የሚል ጥያቄ አለ፤ሀሉም ወገን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማወቅ ቢጥር መልካም ነው፡፡ይሁን እንጂ አፋን ኦሮሞን የስራ ቋንቋ ለማድረግ የህገ መንግስት ማሻሻያ ስለሚፈልግ አሁኑኑ ይሁን የሚባለው ተገቢ አይደለም፡፡አማርኛን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአንድ ቋንቋ በላይ ለማወቅ መጣር አለበት፡፡ሁሉም ነገር ህግና አሰራርን ተከትሎ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ • የታጠቁ ኃይሎች ወደ አገር ቤት የተመለሱት ነፍጣቸውን ጥለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው፡፡እነሱን የሚደግፍ ተቋምም ይደራጃል፡፡ • ኢትዮጵያዊነት የአቃፊነት ባህል ነው ያለው እንጂ አግላይ አይደለም፡፡አልፎ አልፎ የታዩት ጥፋቶች መታረም ያለባቸው ናቸው፡፡የተፈናቀሉም ወደየቀያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው፡፡ • ወጣቶች ለስርዓት መታገል እንጂ ራሳቸው ፈራጅ መሆን የለባቸውም፡፡ • የኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ማንም ያሳካው ጅማሮውን እና የታየውን በጎ ፍላጎት ያማረ ፍፃሜ እንዲኖረው ማድረግ የሁሉም ድርሻ ነው፡፡ • ሀብት በማስመዝገብ ሌብነት አይጠፋም፣ ዋናው ጉዳይ ሌብነትን የሚጠየፍ አገልጋይ ትውልድ መፍጠር ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል፡፡ • ኢትዮጵያ ክብሯንና ትልቅነቷን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሙስሊም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት 60ሺህ ብር ድጋፍ ሰጡ፡፡

ሙስሊም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት 60ሺህ ብር ድጋፍ ሰጡ፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ለአረፋ በዓል ቅድመ ዝግጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ላሳዩት አብሮነት አመስግነዋል፡፡ በጎንደር ከተማ ዛሬ በተዘጋጀው የአብሮነት ፕሮግራም የሃይማኖቶቹ ተከታዮች ታድመዋል፡፡ለአረፋ በዓል ቅድመ ዝግጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ላሳዩት አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ኃይማኖታዊ አንድነትን ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት ሙስሊም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች 60ሺህ ብር አበርክተዋል፡፡ ነሀሴ 19/2010(አብመድ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ማብራሪያ ሊሰጡ ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሊሰጡ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ማብራሪያ ሊሰጡ ነው፡፡ ዛሬ ከ9:00 ሰዓት ጀምሮ ከሀገርና ከውጭ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ነሀሴ19፣2010
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አክሳሪ የቁጠባ መጣኝ (ጌታቸው አስፋው)

አክሳሪ የቁጠባ መጣኝ *** ጌታቸው አስፋው (የብሔራዊ ኢኮኖሚ ዕቅድ ባለሙያ) *** የገጠሬው ቁጠባ ያልደረሳቸው አንዳንድ የከተማ ነጋዴዎች በብድር ጥሬ ገንዘብ እጦት ሥራ ሊቆም ነው ይላሉ፤ ንግድ ባንኮች መንግሥት በምናበድረው ጥሬ ገንዘብ ሃያ ሰባት በመቶ ቦንድ እንድንገዛ ስለሚያስገድደን ለደንበኞቻችን የምናበድረው ጥሬ ገንዘብ አንሶናል ይላሉ፡፡ ብሔራዊ ባንክ በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሪፖርት ንግድ ባንኮች በሕግ ተደንግጎ በብሔራዊ ባንክ ማስቀመጥ ከሚገባቸው መጠባበቂያ ተቀማጭ በላይ እስከ ዐሥር ቢልዮን ትርፍ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ ወይም ብር በያመቱ እንደሚያስቀምጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የግልና የመንግሥት ንግድ ባንኮች የጥሬ ገንዘብ ችግር እንደሌለባቸው የባንክ ለባንክ መበዳደር እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆንም ማስረጃ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ውዥንብር ምንጩ ምንድነው? ሪፖርተር ጋዜጣ፣ እሑድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. “የፋይናንስ አቅርቦት አሁንም እያከራከረ ነው፤” በሚል ርዕስ ለንግዱ ማኅበረሰብ አንድ የብሔራዊ ባንክ ባለሥልጣን የአክስዮን ንግድ ሳይስፋፋ የመዋዕለንዋይ ባንክ ማቋቋም ዋጋ የለውም በማለት የሰጡትን መልስና የልማት ባንክ ባለሥልጣንም ልማት ባንክ ብሔራዊ ባንክ የፈቀደለትን ገንዘብ እንኳ አበድሮ አልጨረሰም በማለት የሰጡትን መከራከሪያ መልስ አውጥቶ ነበር፡፡ ስብሰባውን ያልተካፈለው የገንዘቡ ምንጭ የሆነው ቆጣቢው ድምጹን የማሰማት ዕድል አጥቶ እንጂ የርሱን ያህል የተጎዳ የለም፡፡ ከ2003 እስከ 2007 የነበሩት የዋጋ ንረት መረጃዎች አማካይ 16.3 ነው፡፡ በዚህ የዋጋ ንረት የገንዘብ ሸቀጦችን የመግዛት አቅም በዐሥራ ስድስት ነጥብ ሶስት በመቶ ስለሚወድቅ አምስት በመቶ የቁጠባ ወለድ እያገኘ ገንዘቡን ባንክ የሚያስቀምጥ ሰው ለተበዳሪው ዐሥራ አንድ ነጥብ ሦስት በመቶ ከፍሎ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‹‹አላውቅም›› ማለት ነውር የሆነበት አገር እየገነባን ነው ?? (አሌክስ አብርሃም)

‹‹አላውቅም›› ማለት ነውር የሆነበት አገር እየገነባን ነው ?? (አሌክስ አብርሃም) አገራችን ላይ ትልቁ ችግር የሚመስለኝ ….ታላላቆች በሁሉም ነገር ትልቅ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብና ‹ታናናሾች › በሁሉም ነገር ትንሽ እንደሆኑ አድርጎ ማናናቅ ነው … ለምሳሌ ሰፈራችን ውስጥ ያለን ታዋቂ አርቲስት …ህግም ፣ፍልስፍናም፣ መሃንዲስነትም ፣ የተበላሸ ቧንቧ ጥገናም ፣ ፖለቲካም ፣ስፖርትም ከሱ በላይ አዋቂ እንደሌለ አድርጎ መሃበረሰቡ ያስበዋል …ችግሩ ማህበረሰቡ ይሄን ማሰቡ አይደለም አርቲስቱም አሚን ብሎ መቀበሉ እንጅ ! በበርካታ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ላይ ለምሳሌ … የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች … ከሙያቸው ውጭ የስነልቦና ባለሙያዎች ሁነው ቁጭ ይላሉ …. እንደኔ እንደኔ በተለይ ውስብስቡን የሰው ልጅ ባህሪ ለባለሙያዎቹ መተው ተገቢ ይመስለኛል …ይሄ ብቻም ሳይሆን ሙያን ለባለሙያው መተው ጤናማ ነው …በፊልሞቻችን ብትሄዱ …በፖለቲካው ብትመለከቱ ሰዎች በሆነ ነገር ታዋቂ ከሆኑ የህዝብ አይን ካወቃቸው ስለሁሉም ነገር ያውቃሉ ተብሎ ይታመናል(በብዙሃኑ) በተቃራኒው የተማረ የመተቸትም ይሁን ይህን ነገር የማስተካከል አቅም አለው የምትሉት ማህበረሰብ ሰዎቹ የማያውቁትን እናውቃለን ሲሉ ብቻ ሳይሆን የሚያውቁትም በትክክል ሲናገሩ በደፈናው ማጥላላትና ማናናቅ ልምድ ስላደረገ ሌላው ማህበረሰብ ትክክለኛውንም ተቃውሞ ‹‹ምቀኝነት›› አድርጎ ይመለከተዋል!! አሁንማ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ባሰብንኮ …ልክፍት ነው ከምር ልክፍት ነው …. አንዳንዱ ኮስተር ብሎ ህመማችሁን ስታወሩ መድሃኒት ሁሉ ያዝላችኋል … ምናልባትም ሙያው የታክሲ ሹፍርና ይሆናል !አንድ ቢሮ ስትገቡ ከጥበቃው ጀምሮ እስከጸሃፊዋ የማይመለከታቸውን ጉዳይ የሚመለከተውን ባለሙያ ወክለን ካላስረዳን ሲሉ ታገኟቸዋላችሁ …ወደሚመለከተው ማለት ማንን ገደለ! ድሮ በሰገሌ ፍቅረኛዋ የካዳት ሴት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልፁ።

“በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን”- ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡ ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀው እስከ አሁን ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ አገራችን በልማት፣ በዴሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር መስራቷን እንደምትቀጠል ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ አሸባሪነትን በመዋጋት እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ እረገድ የአሜሪካ ጠንካራ አጋር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡ ይህም ወደፊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አገራችን በጋራ ትሰራለች ብለዋል ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ የመሆን ግዴታነትና የራሱ በሆነው በኢትዮጵያ ፊደል የመገልገል ተገቢነት

አብርሃም ቀጀላ Geezበተለምዶ ግዕዝ ፊደል ተብሎ የሚጠራው የሁሉም ኢትጵያያውያን ፊደል ከጥንት ጀምሮ አስቀድሞ በሀገረ ኢትጵያያ ላሉት የሕዝብ ቋንቋዎች ሁሉ በምልአት፣ በጥራትና በብቃት ሲያገለግል የነበረው፤ በተለምዶ ግዕዝ ፊደል ተብሎ የሚጠራው የሁሉም ኢትጵያያውያን ፊደል እ.ኤ.አ በ1983 ዓ.ም. በመንግሥት መለዋወጥ ተፈጥሮ በነበረው ክፍተት ጥቂት ግለሰቦች በፖለቲካ ስሜታዊነትና ግልፍተኝነት ወደፊት በቀጣዩ ሕዝቦች ላይ የሚያመጣውን ጣጣ፣ መዘዝ፣ ጉዳት እና ቀውስ ሳያጤኑ የቀድሞ ያለፈው ፖለቲካዊ ችግር በፈጠረው ቁጣና ትኩሳት ብቻ በመነዳት አፋን ኦሮሞ ግእዙን እንዲተው አድርገዋል። በዚህ በነባሩ የግዕዝ ፊደላችን አፋን ኦሮሞን በተመለከቱ 1ኛ. ከ16ተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ቅዱስ ቁርአን የተከተበበት ሰነድ በሀረር ይገኛል። 2ኛ. በ1845 ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን በፊት የመጽሐፍ ቅዱስ ወንጌላት በከፊል የተፃፋበት 3ኛ. ከ140 ዓመታት በፊት በኦሮሞው ሊቅ በቅዱስ አናሲሞስ ነሲብ (አባገመችስ) ሙሉው መፅሃፍ ቅዱስ በአፋን ኦሮሞ የተተረጎመበት 4ኛ. በ1967 ዓ.ም. ከ20 በላይ በሆኑ በተለያዩ ብሔርና ብሔረሰቦች ቋንቋ የመሬት አዋጅን ፈትፍቶና ቁልጭ አድርጎ የተገለፀበት 5ኛ. የኢትዮጵያ የመስረተ ትምህርት ከ30 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎች በብቃትና በጥራት ይሰጥበት የነበረ 6ኛ. የበሪሳ ታላቅ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጣ ለዘመናት በበርካት ቁጥሮች ሲሰራጭበት የነበረ 7ኛ. የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በበርካታ ባብዛኛው ከ 45 ብሔር ብሔረሰቦች በላይ ቋንቋዎች የተገለጡበት 8ኛ. በበርካታ የእስልምና ዝክሮች፣ መንዙማዎች የተፃፋበት የተዘከሩበት 9ኛ. በርካታ የክርስትያን መዝሙራት በኦሮምኛና በሌሎች ቋንቋዎች የተገለጡበት 10ኛ. በአፋን ኦሮሞና በሌሎችም ከረጅም ዘመናት በፊት የመዝገበ ቃላት የተደራጀበት ናቸው። ከእነዚህ ነገሮችም በላይ ብዙ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ስርዓት አልበኝነትን ተከትሎ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ በደቡብ ክልል እየተስፋፋ ነው፡፡

በደቡብ ክልል የመሬት ወረራ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑ ተገለፀ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ምክንያት በማድረግ የመሬት ወረራ እየተስፋፋ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር መነሻ በማድረግ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ በሚያካሄዱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብሏል ፖሊስ፡፡ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል እንደገለጹት ከሆነ በሀዋሳ ከተማና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች የመሬት ወረራና ህገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሳተፉ አካላትን በመለየት ህግ የማስከበር ተግባር ተጀምሯል፡፡ እንደ ኮሚሽነረየ ገለጻ በክልሉ ስርዓት አልበኝነት እንዳይስፋፋ መላው ህብረተሰብና የጸጥታ አካላት ተቀናጅተው እየሰሩ ነው፡፡ በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩ ቦታዎችን በመለየት ህግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተናጋሪ ያላቸውን ቋንቋዎች የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ፤ በክልሎች ያለውን የቋንቋ አፓርታይድ መስበር። (ኒሻን በላይ)

ከአንድ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተናጋሪ ያላቸውን ቋንቋዎች የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ፤ በክልሎች ያለውን የቋንቋ አፓርታይድ መስበር። *** ኒሻን በላይ *** የጽሑፌ ጭብጥ፡- በአገራችን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተናጋሪ ያላቸው ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ እና በክልሎች ሰፍኖ የሚገኘው የቋንቋ ምስቅልቅል እንዲሻሻል ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ስለቋንቋ ሕግና ፖሊሲ ስንነጋገር፣ የሕጉና ፖሊሲው ተቀዳሚ ዓላማ ዜጎች በራሳቸው ቋንቋ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብት ያላቸው መሆኑን ተቀብሎ ይህንን መብት ማስጠበቅ ነው፡፡ በሌላ በኩል፣ ቋንቋ በሚመለከት የሚወጡ ሕጎችና ፖሊሲዎች የብሔረ መንግሥት ግንባታውን (nation building) በሚያግዝ መልኩ የተቃኙ እንዲሆኑ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቋንቋን አስመልክተው የሚወጡ ሕጎችና ፖሊሲዎች ከጊዜያዊ የፖለቲካ ሆይሆይታ በፀዳ መልኩ በሰከነ፣ በተጠናና ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ ጥናት፣ ውይይት እና ክርክር ይቅደሙ፡፡ አርቆ-ማሰብ የሚጠይቅ ግዙፍ አጀንዳ ስለሆነ ሰከን ብለን እንያዘው፡፡ በእኔ አስተያየት፣ በአገራችን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተናጋሪ ያላቸውን ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ማድረግ ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው፡፡ ጉዳዩን ከብሔረ መንግሥት ግንባታ አንጻር ብንመለከተው፣ ለምሳሌ ሶማልኛ ቋንቋ የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ መሆኑ፣ የሶማሊ ብሔር አባላት በፌደራል ደረጃ በራሳቸው ቋንቋ የመጠቀም መብታቸውን ከመጨመሩም በላይ፣ በሶማሊ ብሔር አባላት ላይ የሚፈጥረው ስሜት በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ይህ ስሜት በትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ እና ሌሎች ብሔሮች ላይም እንደሚኖር መገንዘብ አይከብደም፡፡ ይህ ስሜት ነው ሁሉንም ባይባል ከፍ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች በተቀራራቢ ደረጃ ለአገሪቱ ህልውና መጠበቅና ሁለንተናዊ ልማት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወልቃይት የትግራይ ፖሊስና ሚሊሻ በነዋሪዎች ላይ የሚያደርሰው ግፍ ቀጥሏል።

ከስር የሚታየው ፎቶ ወጣቶች ከአራት ቀናት በፊት በወልቃይት ወደ አድረመጥ ፖሊስ ጣቢያ የኋሊት ታስረው ሲወሰዱ የሚያሳይ ነው! ወልቃይት ውስጥ ሲፈፀሙ የኖሩ የተወሰኑ ዘግናኝ ድርጊቶችን ከስር በሚታየው ፎቶ አስደግፌ ለመግለፅ እሞክራለሁ! እስከዛሬ ሲፈፀሙ የኖሩትን በደሎች የዛሬው ፎቶም በትንሹ ይገልፃቸዋልና! አፓርታይድ በወልቃይት! አታላይ ዘነበ፣ ባየው ቢያድግልኝ፣ አሻግር ዘውዴ፣ ማሙ ዘውዴ፣ ይርሳው ዘውዴ፣ ተበጀ በቀለ፣ ጎይቶም ሀድጎ፣ አያሌው ሰሙ፣ ገብረ መድህን ዘረፋ፣ ነጋ ተገኘ የማንነት ጥያቄ ያነሱ የነበሩ ናቸው። ከእነዚህ መካከል አብዘኛዎቹ የትህነግ/ህወሓት ሰዎች ሌሊት ቤታቸውን አፍነው አስረው ያጠፏቸው ናቸው። አስከሬናቸው የት እንዳለ አልታወቀም። አንድ የወልቃይት ኮሚቴ አባል ስለነዚህ ሰዎች አሟሟት እንዲህ አጫውቶኛል። “ጉድጓደረ ቆፍረው አሰረገቧቸው። አፉን ማገዶ ማገዱት። እሳት አቃጥለው። ጫምዳ የሚባል እንጨት ቅጠሉን ቆርጠው አፈኑት። ከቅጠሉ በላይ አፈር። በጢስ ነው የሞቱት። ይህ የተደረገው ሀለዋ ወያኔ የሚባል እስር ቤት አውጥተው ነው” ወልቃይት ላይ ይህን የመሰለ ጭካኔ ይፈፀማል! ( ይህን ፎቶ ወልቃይት ላይ የሰፈነው የአፓርታይድ አገዛዝ ዛሬም መቀጠሉን የሚያሳይ ነው። ፎቶው ዛሬም ወጣቶች በዚህ መልኩ ታስረው ወደ እስር ቤት እንደወሰዱ የሚያሳይ ነው) አበበ ይርጋ፣ አለበል ይርጋ፣ ገረማርያም አረፈ አይኔ፣ አንጋው እሱባለው፣ ጫኔ ይርጋ፣ በሪሁን ይርጋ፣ አላቸው አለማየሁ፣ መኮንን ለውጤ በማንነት ጠያቂነታቸው የተገደሉ ናቸው። አብዛኛዎቹ ተመሳሳይ ሰቆቃና ግፍ ተፈፅሞባቸዋል። በውጊያ ተገድለው አስከሬናቸው በመከከና የማይጎተቱት ጥቂቶች ናቸው። ተሰማ አውለው፣ ብርሃን በላይ፣ ሀየሎም ወንድማገኝ፣ አለም መብራት፣ ይልማ ገብረስላሴ፣ ደሞዝ ምትኬ ውጊያ፣ ፈጠነ ዘነበ ውጊያ ላይ የተገደሉ
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብሔረተኝነት – ግራዋ የሆነ መራራ ብሔርተኝነት ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ነኝ፡፡ (ግርማ ሰይፉ ማሩ)

ብሔረተኝነት – ግራዋ የሆነ መራራ ብሔርተኝነት ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ነኝ፡፡ (ግርማ ሰይፉ ማሩ) ይህ መብቴ እንዲከበር እፈልጋለሁ፣ ሰለዚህ ሌሎችም በፈለጉት ደረጃ ብሔረተኛ ቢሆኑ መብታቸው መሆኑን በማመን አከብራለሁ፡፡ አንድ አንድ ብሔረተኞች (በተለይ በኢህአዴግ ጥላ ሥር ያሉት) ለአማራ ብሔረተኝነት አንድ ሌላ ቅፅል ይሰጡት ነበር፡፡ ዴሞክራቲክ የአማራ ብሔረተኛ የሚል፡፡ ብአዴንም የአሁኑን አላውቅም “ዴሞክራቲክ የአማራ ብሔረተኝነት” የሚል ፈሊጥ ነበረው፡፡ በውስጠ ዘ “የአማራ ትምክተኝነት” የኢህአዴግ ብሔረተኝነት ዋልታና ማገር መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡ ብዙዎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችም ሆኖ አጋሮቹ በአማራ ጭቆና ምክንያት ብሔረተኛ እንደሆኑ ሰለሚተረክላቸው እና በዚሁ አውድ ሰለተቀረፁ ከትምክተኛ አማራ ብሔርተኝነት የፀዳ ዴሞክራቲክ የአማራ ብሔርተኝነት አሰፈልጓቸው ነው፡፡ በዚህ ሰንገረም መክረማችን ብቻ አልበቃንም፣ ሌላ ደግሞ ፅንፈኛ ብሔረተኛ ተነስቶልናል፡፡ መራራ የሆነው “ግራዋ የአማራ ብሔረተኝነት” በአብን ሹም ክርስቲያን ታደለ ተደርሶ ቀርቦልናል፡፡ መቼም ዴሞክራቲክ የሚባል ብሔረተኝነት የለም፡፡ ብሔርተኝነት ወገንተኝነት በመሆኑ፡፡ ይህ ቅጥ አንባሩ የጠፋ ነገር መስመር መያዝ አለበት ስንል፣ የባሰ አታምጣ ሆነና ግራዋ ብሔርተኝነት ሊግቱን የተነሱ ሀይሎች መኖራቸውን በይፋ አብስረውናል፡፡ ግራዋን በውድ ስትጠጣው መድሐኒት የመሆኑን ያህል ስትጋት ግን የሚግተው ላይ መትፋት እንደሚኖር ተዘንግቷቸዋል፡፡ ቀጥሎም ያዘጋጁትን ግራዋ መልሶ ሊግታቸው የሚችል ሀይል እንደሚፈጠር አልገመቱም፡፡ ኢትዮጵያ ብሔረተኝነት ጣፋጭ ነው፡፡ ለሁሉም ዜጎች እኩልነት የሚመኝ ነው- አድልኦን የሚጠየፍ ነው፡፡ ነገር ግን ለኢትዮጵያዊያን ወገንተኛ ነው፡፡ ለሱዳን፣ ለኬኒያ፣ ለጂቡቲ፣ ወዘተ … እኩል እድል አይሰጥም፡፡ በእነርሱ ቦታ ሆነን ስንመለከተው ዴሞክራቲክ ላይሆን ይችላል፡፡ ለእነርሱም ቢሆን ግን መራራ- ግራዋ እንዳይሆን መጣር
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ መከራን ተሻግራ ፈተናን ተቋቁማ ብቅ የማለት ታሪክ ያላት እፁብ አገር ናት ! (ቴዎድሮስ ፀጋዬ)

ኢትዮጵያዊነት አንዱ በተፈጥሮ የሚጎናፀፈው ሌላው ደግሞ በቸርነት የሚመፀወተው እርከን ወይም ደረጃ ያለው ማንነት ነው ብዬ በፍጹም አላምንም፣ ሁሉም ዜጎች አሁን በታሪክ ክፉ እድል ከኛ የተነጠሉትም ጭምር እኩል ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ተጠራጥሬ አላውቅም። እርግጥ ነው ከአንድ ወይም ከሌላ ብሄር ወገን ነን የሚሉ ባእድና የማይገጥም ጽንሰ ሀሳብ ከየትም ተበድረው አገርን በመስራት ሂደት ውስጥ የተፈጠሩን ቁስሎች ቦርቡረውና ታሪክ አዛብተው፣ እንደ ብሄር የመጠቃትን ስሜት የፈበረኩና ያግለበለቡ፣ በዚህም ፍብርክ ስሜት መሰላልነት ወደ ስልጣን የወጡና አሁንም አዲስ ሌላ ድንክ አገር መመስረትን የሚያልሙ ለአገራች ህልውና የሚያሰጉ ብዙዎች መኖራቸውን አውቃለው እቃወማቸውምአለው። በዚያውም ልክ ግን ራሳቸውን ከሌላው ይበልጥ ኢትዮጵያውያን አድርገው የሚሾሙ ዘረኝነታቸውን ኢትዮጵያ በሚል ውብ ስም የሸሸጉ በተግባር ግን ሁሉንም የዘረኝነት ብየና የሚያሟሉ፣ ከነርሱ የተለየ ሀሳብ የያዘን ሁሉ በራሳቸው የዘረኝነት ሚዛን ሰፍረው ስም የሚሰጡ፣ ኢትዮጵያውያ የሚለውን የተቀደሰ ስም በአፋቸው የመደጋገማቸውን ያህል በነውራቸው የሚያራክሱ ውድና ውብ ለሆነው ሁሉንም ለሚያስጠልለው ኢትዮጵያውያዊ ብሄርተኝነት እንደ ስድብ የሚቆጠሩ በርካቶችንም አስተውላለው። . ከልዩነቱ ገደል ወዲህና ወዲያ ያሉ ዘረኞች የቆሙበት አንፃር ይለያይ እንጂ አፈራረጃቸው አስተሳሰባቸውና አፈፃፀማቸው በእጅጉ ተመሳሳይ ነው። በነዚህ ሁለቱ ውዝግብና ፍጭት ሳቢያ የሚመጣው ዳፋ የሚወድቀውና እዳው የሚተርፈው፣ እርስ በእርስ ላይለያይ የተሳሰረው እየተጋባ እየተዋለደና እየተገበያየ ዘረኝነትን እንደማይሻ በተግባር ሲያሳይ የኖረውና አሁንም እያሳየ ያለው ህዝቡ መሆኑ ግን ልብ ይሰብራል። ኢትዮጵያ በዘውገኞች ቱማታ በውጭ ጠላቶች ጦር በተፈጥሮ አደጋም ሆነ በድህነት ህልውናዋ ይፈተናል ብዬ አላምንም። ኢትዮጵያ መከራን ተሻግራ ፈተናን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በስሜት መነዳትና የፖለቲካ ጥላቻ ወደ ገደል ሳይከተን መቆም አለበት ።

በስሜት መነዳትና የፖለቲካ ጥላቻ ወደ ገደል ሳይከተን መቆም አለበት ። ምንሊክ ሳልሳዊ ለተለያዩ ጊዜያት በፖለቲካ ጥላቻ የተሞላ መናቆርና መፈራረጅ እርስ በርስ መናከስ እንዲቆም ጮኸናል። ይህ የዘር ፖለቲካ ያመጣብንን ፍዳ ልንቋቋመው የምንችለው ተባብረን ተራርመን ተመካክረን ተከባብረን በኢትዮጵያዊነት ስንቆም ነው ካልሆነ የሚደርስብን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ኪሳራ ሰብዓዊ ቀውስ ያሸክመናል። ከፖለቲካው ጥላቻ በተጨማሪ በጭፍንና በስሜት መነዳት ሌላው ነገ ላይ አደጋን የደቀነ እኩይነት ነው። ካለፈ መማር ያልቻልን የራሳችም ጠላቶች መሆናችንን አቁመን የጋራ ሃገራዊ ራእይ መያዝ ይጠበቅብናል። በተደጋጋሚ እንደሚባለው በወሬና በጭብጨባ አገር አይመራም። ጭቆናን የተሸከመ ሕዝብ ነጻነት መሸከም እንዳይችል አድርገው ወደ ስርዓት አልበኝነት የሚወስዱ በስሜት የሚነዱ ፖለቲከኞች ሊቆነጠጡ ይገባል። ለለውጥ የሚደረገውን ትግል ማሳካት የምንችለው ይዘነው የመጣነውንን ትግል አጠናክረን ስንቀጥል ብቻና ብቻ ነው። ለውጡ አመጣጡና ምንጩ ከየትም ይሁን ለውጥ የምንፈልግ ሃይሎች ግን ያገኘነውን መስመርና እድል ተጠቅመን የሕዝብን ነጻነትና መብት በተግባር እንዲተረጎም የማድረግ ግዴታ አለብን። የማይሆኑ ፕሮፓጋንዳዎችን በመንዛት ሕዝብ ያገኘውን የነጻነት ተስፋ እንዲያጣ የምናደርገውን መታከክ ልናቆም ይገባል። #MinilikSalsawi
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብስለት የጎደለው ፖለቲካ ውድቀትን ያመጣል – የሰለጠነ ፖለቲካ ያስፈልገናል።

ምንሊክ ሳልሳዊ : ብስለት የጎደለው ፖለቲካ ውድቀትን ያመጣል። የፖለቲካ ድርጅቶች ካድሬዎቻቸውን አብስለው በሕዝብ ትግል የተገኘውን የለውጥ ሒደት ሊጠቀሙበት ይገባል። የሰለጠነ ፖለቲካ ያስፈልገናል። መልካም ጅማሮውን ለውጥ አድርገን ልንተረጉመው የምንችለው በወሬና በዜና መረጃ ቀውስ በመፍጠር ሳይሆን ፖለቲካ በመስራት ነው። ኢሕአዴግ የማይታመን ድርጅት ነው። ከዚያን ጎን ለጎን በጎጥና በዘር ላይ የተደራጁ ድርጅቶች ጠባብነታቸውን በሕዝብ ላይ ለመጫንና የመከነ ዘረኛ ትውልድ ለመፍጠር ዛሬም እየደከሙ ነው። ይህን ድካም ደግሞ ባለፉት ሀያ ሰባት አመታት ጎጥና ዘር አይተነው ምንም ለውጥ አላመጣም ፤ ሕዝብ የሚፈልገው ሰላም አንድነትና ሰርቶ መብላት መሆኑን ፖለቲከኞች ከተረዱትና ካድሬዎቻቸውን አብስለው ማውጣት ከቻሉ ዘረኞችን የማያደቁበት ምክንያት የለም። በኢሕአዴግ ውስጥ የተለወጠ ነገር ቢኖር ጥቂት የለውጥ ሃይሎች መፈጠር ብቻ ስለሆነ ኢሕአዴግን ከሚከተለው የፖለቲካ ባሕርይ አንጻር ልንመዝነው ልንገምተው ይገባል። የፖለቲካ ድርጅቶች በዲፕሬዥንና ስትረስ የሚሰቃዩ ቦዘኔዎችን ማስወገድ አለባቸው። የፖለቲካ እውቀት ያላቸውንና የተሻለ ሃገራዊ ራእይ የሰነቁ ካድሬዎችን ሊያፈሩ ይገባል። ካልሆነ እየተወዛወዙ ሽሙጥና ዘለፋ የኢሕ አዴግ ካድሬዎችንም ከጥቅም ውጪ አድርጓቸዋል። በሃገር ውስጥ ለሚዘረጉ ኔትወርኮች የተሻለ ስራ የሚሰሩ ካድሬዎችን መፍጠር ካልተቻለ ነባሩንም ኔትወርክ ለአደጋ ማጋለጥ ይሆናል። ፖለቲካ ሲደራጅ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ሊሰሩና ሊያሰሩ የጠላትን ወገን ሐሳብ አስቀይረው ወደ ትግሉ የሚቀላቅሉ የሰከኑ ካድሬዎች ያስፈልጋሉ። ብስለት የጎደለው ፖለቲካ ውድቀትን ያመጣል። ከተለያዩ ቦታዎች ተሁኖ በስድብ ማምታታት ስልጣኔ አይደለም። ፖለቲካ ስድብና ዘለፋ የተዋኻደው እለት እንደሰይጠነ ይቆጠራል። የሰለጠነ ፖለቲካ ለማራመድ የሚረዳው በጋራ ተመካክሮ ሃሳብን በማዳበር ብቻና ብቻ ነው። የሰለጠነ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቀድሞ “ተጨቋኞች” መካከል ያለው አጉል የፖለቲካ ሽኩቻ፣ብሽሽቅ አንድ ሊባል ይገባል።

በቀድሞ “ተጨቋኞች” መካከል ያለው አጉል የፖለቲካ ሽኩቻ፣ብሽሽቅ አንድ ሊባል ይገባል። ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የማየው ነገር ሁሉ ትንሽ ግራ እያጋባኝ ነው ። 27 ዓመት በሙሉ በወያኔ ጭፍንነትና ዘረኝነት በዘር የተበከለ ውሃ ጠጥተን ጤና እንዳልሰጠን ለሁላችንም ግልፅ ነው። ያ… ለኢትዮጵያ ህልውና እጅጉን አስከፊ ስርዓት ምንም እንኳን እንደጠበቅነው በሽግግር መንግስት ባይለወጥም ነባሩ ስርዓት “reform” ሆኖ እንዲቀጥልና ኢትዮጵያን ከተጋረጠባት የቁልቁለት መንገድ ማዳን በሚል ሁሉም አቅሙ በቻለው ተደምሯል። ነገር ግን አሁን ትንሽ ግራ እየገባኝ የመጣ በቀድሞ “ተጨቋኞች” መካከል ያለው አጉል የፖለቲካ ሽኩቻ፣ብሽሽቅ አንድ ሊባል ይገባል። የ እነ”ቶሎ ቶሎ ቤት…..” እንዳይሆን ነገሩን ቀስ ብለን የማንም ድርጅት ወይም የፖለቲካ ፓርቲ አምላኪ ሳንሆን አሁን ኢትዮጵያ ላለችበት ነባራዊ ሁኔታ የሚጠቅማት ትክክለኛ መንገድ የትኛው ነው? የሚለውን በሰከነ መንፈስ ልንይዝ ይገባል ባይ ነኝ። የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነት የህብረ ብሄር ጉዞ ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ይረዳል እንጅ አይጎዳም!!! አርበኞች ግንቦት 7ም ተደራጁ፣ተደራጁ፣ተደራጁ በማለት ህዝቡን አንቅቷል ያም ሲሆን ያየነው ኦሮሞው በኦሮሞነቱ ተደራጀ፣ ትግሬው በትግሬነቱ፣ አፋሩ በአፋርነቱ፣ ሶማሌው በሶማሌነቱ …. ወ.ዘ.ተ እያለ ይቀጥላል ። ታዲያ ይህ መደራጀት አማራው ላይ ሲደርስ ትንሽ የሚያበሳጨን ለምንድነው ? ጭቆናን ተዋግተን እኛስ ጨቋኝ መሆን እንችላለን? አንዳንድ በስሜትና ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ የሌላቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ማኒፌስቶ ያልገባቸው አክትቪስቶች ስመለከታቸው በሚያሳፍር እና በሚያስተዛዝብ ሁኔታ አጉል “የፕሮፖጋንዳ” ስራ በመስራት ድርጅቱንም ሆነ ከድርጅቱ “አንድነትና ህብረ ብሄር” አጀንዳ በተቃረነ በመጓዝ እንደ ጋዜጠኛ ጌታቸው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የት ላይ ነን? – ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር)

አምባገነናዊ ሥርዓትን ማስወገድ ከባድ ነው፤ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ደግሞ በጣም ከባድ ነው። እኛ የት ላይ ነን! የት ላይ ነን? *** ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር) *** የአፈና ሥርዓት ልዩ ባሕርይው ሕዝብን አቅመ-ቢስ ማድረጉ ነው፡፡ አገዛዙ ቀዳሚ የአገርና የሕዝብ ተቆርቋሪ፣ የአገዛዙ ተቀናቃኞች የሕዝብ ጠላቶች ሆነው የሚቀርቡበት፤ ይህን ትርክት ሕዝብ በውድም በግድም አሜን ብሎ እንዲቀበል የሚደረግበት፤ የማይቀበሉ አካላት የሚታሰሩበት፣ የሚገደሉበትና የሚሳደዱበት ሥርዓት ነው የአፈና ሥርዓት፡፡ ተቀናቃኝ ኀይሎች በልዩ ልዩ እመቃ ምክንያት ረብ-የለሽ ሆነው የሚታዩበት እና በሥልጣን ላይ ያለው የፖለቲካ ኀይል በምንም ዓይነት መንገድ ሊነቀነቅና ሊሸነፍ የማይችል (invincible) ሆኖ የሚታይበት ወይም እንዲታይ የሚደረግበት ሥርዓትም ነው፡፡ የለውጥ ኀይሎች ተቀዳሚ ተልዕኮ ይህንን የአፈና አገዛዙ ያሰፈነውን የ“አይነቀነቅም፤ አይሸነፍም” አስተሳሰብ በተግባር መናድ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 17 ቀን 2010 ሞሐመድ ቧዚዚ ራሱን አቃጥሎ ከገደለ በኋላ የቱኒዚያ ወጣቶች ገንፍለው ወደ አደባባይ በመውጣት ያደረጉት ይህንን ነበር፡፡ የቱኒዚያ ወጣቶች ትልቁ ድል የቤን አሊ አምባገነናዊ አገዛዝ የማይፈርና የማይገረሰስ በተግባር ማሳየት መቻላቸው ነው፡፡ አምባገነነናዊ አገዛዝ አንዴ ሊደፈርና ሊገረሰስ እንደሚችል በሕዝቡ ዘንድ ግንዛቤ ከተያዘ ሥርዓቱ (የፖለቲካ ማሻሻያ ካላደረገ በስተቀር) በነበረበት አካሄድ በሥልጣን ላይ የመቆየት ዕድሉ የመነመነ ነው፡፡ በአገራችን በአቶ መለስ ይመራ የነበረው ኢሕአዴግ ለ14 ዓመታት አስፍኖት የነበረው የ“አይነቀነቅም፤ አይሸነፍም” መንፈስ ከባድ ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተካሄደውን ብሔራዊ ምርጫ ታሪካዊ የሚያሰኘው፣ ያ ምርጫ የአቶ መለስ ኢሕአዴግ አስፍኖት የነበረውን የ“አይነቀነቅም፤ አይሸነፍም” መንፈስ በመስበሩ ነው፡፡ አቶ መለስ ሕዝቡ የአገዛዙን
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የህወሀትን ገበና እርቃኑን አስቀሩት

ሐይለማሪያም ደሳለኝ እውነቱን  አፍረጠረጠው። •ይህችን ሀገር አንድ ሰው ከመፍረስ እንዲያድናት ስፀልይ ነበር ። • የሚሰሩት ስራዎች የማፊያ ነበሩ ። • እስከ መጨረሻው እየገደሉ እየሰረቁ መቆየት ነበር ፍላጎታቸው ። “የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለዴይሊ ማቭሪክ የወሬ ምንጭ በሰጡት መረጃ የህወሀትን ገበና እርቃኑን አስቀርተውታል፡፡” • ህወሀቶች/ደደቢቶች እኔን ተጠቅመው የበላይነታቸውን ባሰፈነ አገዛዝ ለመቀጠል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ብለዋል፡፡ • በእኔ የስልጣን ዘመን ሀገሪቱም ሆነ ኢህአዲግ መለወጥ አለባቸው በሚሉ ሀይሎችና ዘላለማዊ የበላይነታቸውን አጽንተው ለመቀጠል በሚፈልጉ የህወሀትና አንዳንድ የበአዲን ሰዎች መካከል ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ ነበር፡፡ •በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኜ ነበር የምመራው ብለዋል ብለዋል ፡፡ • የለውጥ ሀሳብ ባቀረብኩ ቁጥር የህወሀትና አንዳንድ የበአዲን ጀሌዎቻቸው ሀሳቡን ውድቅ ሲያደርጉብኝ ነው የኖርኩት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም እንዴት ሳንዲዊች ሆነው ሀገር ለመምራት እንደተገደዱ ሁሉንም ጉድ ዘክዝከዋል፡፡ • በመለስ ዜናዊ የተቀመጠውን የአመራር መተካካት በሚመለከትም ሰፊ ልዩነት ነበረን ፡፡ በተዘዋዋሪ በህዉሓት የተቀባ መሪ ብቻ በቀጣይና በተከታታይ የመሾም ፍላጎት ነበራቸው ። • የሶማሊያ ክልል ጉዳይ የነበረኝ መረጃዎች እጅግ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ነበሩ የክልሉ የነዳጅ ዘይት ጉዳይ 80 ከመቶ ገቢው የቻይናዎቹ ሆኖ ቀሪውን የህዉሓት ኮንሰልታንሲ ድርጅቶች የሚወስዱትና መጠኑ ያልታወቀ ገቢ ደግሞ የክልሉ ፈላጭ ቆራጭ አብዲ ኢሌና የህዉሓት ጄኔራሎች የቻይና እና የሱዳን ኩባንያዎች ጋር ሕዝብ ሳያዉቅ በሚስጢር የተከወነ ነበር ። • ይህ እቅድ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ እኔን ጨምሮ በርካታ ወጣት አመራሮች አይምሮአቸው በኮሙኒስታዊ ፖለቲካ ከተጠመቀውና ከነባር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አፋኞቹ የፀረ ሽብር ፣ የበጎ አድራጎትና ማሕበራት ህጎች ሊሻሻሉ ነው።

በፀረ ሽብር፤ በበጎ አድራጎት እና ማሕበራት ጨምሮ በ5 ህጎች ላይ የማሻሻያ እየተከናወነ ነው $bp("Brid_45291_2", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-515927655534242.mp4", name: "አፋኞቹ የፀረ ሽብር ፣ የበጎ አድራጎትና ማሕበራት ህጎች ሊሻሻሉ ነው።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180819_164639.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዓቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጡ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዓቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ውስጥ በሁሉም መስኮች መሰረታዊና ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየተመዘገቡ ያሉበት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ብንገኝም በተጀመረው ስፋትና ጥልቀት ለውጡን ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት የሚያደነቅፉና የለውጡን አቅጣጫ የሚያስቱ ችግሮችም አብረው እየታዩ መምጣታቸውን በውል እንገነዘባለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚረዳው አገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየ ሥልጣኔ ባለቤት የሆነች፣ በዓመታት የጎለበተ የመንግሥት መዋቅርና ሥርዓት ያላት፣ የፍትህና ርትዕ ማህበረ ባህላዊ መረዳትም በህዝቦቿ ዘወትራዊ ህይወት ውስጥ የሰፈነባት እና ህዝቦቿም ለዘመናት ስለነጻነት ታሪካዊ ገድል የፈጸሙባት ታላቅ አገር ናት። በዘመናት ሂደት ውስጥ ከማዕከላዊው መንግስት በተጨማሪ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች ባሉ ማህበረሰቦች ተቀርፀው በቆዩ ልዩ ልዩ ባህላዊ ሥርዓተ-መንግሥታት መሰረት ህዝቦችም ሆኑ መሪዎች በሕግና ደንቦች ተገድበው ሲኖሩ ቆይተዋል። በመላው አገሪቱ የሚኖሩ ሕዝቦች በባህላዊ ትውፊታቸው እና በምሳሌያዊ አነጋገሮቻቸው ጭምር ለፍትህና ርትዕ የሚሰጡት ቦታ እጅጉን ትልቅ ነው። አብሮነትና መቻቻል በመልካምም ሆነ በፈታኝ የታሪክ አጋጣሚዎች ሁሉ የአገራችን ህዝቦች አይነተኛ ዕሴት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህች አገር ከትውልድ ትውልድ አንድነቷን ጠብቃ በሰላም የመቆየቷ ዋናው እና አይነተኛው ሚስጢርም ይሄው በመኖር የተፈተነ እና በአብሮነታችንም የገነነ ሀገራዊ ታሪካችን ነው፡፡ በህዝቦቿ መካከል ፀንቶ የኖረውና ከዘር ከሀይማኖት በላይ የቆመው የመተሳሰብ፤ የህብረት፣ የፍቅር እና የጽኑ አብሮነት ባህል ስር ሰዶ መቆየቱም በዘመናት የመውደቅ መነሳት ታሪካችን ውስጥ እንዳንለያይ አርጎ በፍቅር የገመደን የአብሮነት ማህተባችን ነው። በኢትዮጵያ ዘላቂ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ስሙኝማ…ዳያስፖራ ወዳጆቻችን አገሪቷን ሊያጥለቀልቋት አይደል! (ኤፍሬም እንዳለ) “የአገር ልጅ ዘው ዘው”

“–እናማ፣ ምን መሰላችሁ… እናንተ ዘንድ የፈለገ ሰው ‘የፓርኪንግ ሎት’ ኤክስፐርት እንደሚሆነው፣ እኛ ዘንድም የፈለገ ሰው ‘የፖለቲካ ተንታኝ’ መሆን ይችላል፡፡ እዚህ አገር “የት የሚያውቀውን!” የሚል ሀረግ አይሠራም፡፡ አንዲት እንጨት በመጋዝ ቆርጦ የማያውቀው ሁሉ የህንጻ ግንባታ ባለሙያ መሆን ይችላል፡፡–” እንዴት ሰነበታችሁሳ! ስሙኝማ…ዳያስፖራ ወዳጆቻችን አገሪቷን ሊያጥለቀልቋት አይደል! እንኳን ለአገራችሁ መሬት አበቃችሁ እንላለን፡፡ ቆይታቸው ደስተኛ እንዲሆንና መመለሻ አውሮፕላናቸውን በፈገግታ እንዲሳፈሩ የሚደረገው ዝግጅት አሪፍ ነው፡፡ ያው እንግዲህ ብዙዎቻችን ከስንት ጊዜ በኋላ ልንገናኝ አይደል! ዓይንም ፈጠጥ፣ ግንባርም ከስክስ ማለቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ‘ኮንፌሽን’ አለን… እስከ ዛሬ እንልክላችሁ የነበሩት ፎቶዎቻችን “እድሜ ለፎቶሾፕ፣” እያልን ያሳመርናቸው ናቸው። እንዲህ ተናግሮ እርፍ ማለቱ አይሻልም! ልክ ነዋ…ፎቶሾፕ ገላግሌ ጉንጮቻችንን የህጻን ልጅ ኳስ ያስመስላቸው እንጂ እንደ እውነቱ እኮ ቁፋሮው ያለቀለት የውሀ ጉድጓድ ነው የሚመስሉት፡፡ ያው ስትመጡ ታዩት የለ! እናማ… “አንተ ፎቶ ላይ እንደዛ ልትፈነዳ የደረስክ የምትመስለው ሰውዬ፤ ምንድነው በአንድ ጊዜ እንዲህ ያከሳህ? የእትዬ እንትና እንዝርት መስለሀል እኮ!” እንዳትሉን፡፡ (የ‘እንዝርት’ን ትርጉም ማወቁ ከጉብኝቱ ስኬቶች አንዱ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡) እንደዛ ስትሉን ሆድ ሊብሰን ይችላላ! አሀ…እናንተ በ‘ፋይቭ ናይንቲ ናይን’ ምናምን “ሀምበርገር፣ ቺዝ በርገር፣ ቺክን በርገር” እያላችሁ እንደምታማርጡት እንዳይመስላችሁ። እዚህ አንድ ቺዝ በርገር ከመግዛት ዶሮይቱን ከእነ ነፍሷና ከእነ አስራ ሁለት ቅመሞቿ መግዛቱ ሊረክስ ምንም አልቀረው፡፡ እናንተ “ጀንክ ፉድ” የምትሉት እዚህ “ቪ.አይ.ፒ. ፉድ” ነው፤ ቂ…ቂ…ቂ…! (እግረ መንገድ…“መግቢያ መደበኛ አራት መቶ ብር፣ ቪ.አይ.ፒ አንድ ሺህ ብር” ሲባል እንዳትደናገሩ፡፡ እዚህ ቪ.አይ.ፒ.
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወንጀልን ለማቆንጀት፣ ሰበብና ማመካኛ መደርደር ይብቃ! ( ዮሃንስ ሰ )

• አለዚያ፣ ህግና ስርዓት፣ ለጉልበት ወይ ለትርምስ ተሸንፎ ማጣፊያው ያጥረናል። • “የሕዝቡ ጥያቄ ስላልተደመጠ ነው” ብሎ ያሳብባል አንዱ ምሁር። (ጥፋትና ጭካኔን የሚያስውብተዓምረኛ እውቀት የያዘይመስል።) • “መንግስት ፈጣን ምላሽ ስላልሰጠ ነው” ይላል አንደኛው ፀሐፊ ። (ክፋትንና ምቀኝነትን የሚያቆነጅ ልዩ አስማት ያገኘ ይመስል።) • “የመወያየትና የመነጋገር እድል ስለሌለ ነው” ይላል አንደኛው ፖለቲከኛ (በዚህች ንግግሩ፣ ወንጀልን እንደፍትህ የሚቆጠርለት ይመስል።) በአሉባልታ ጭፍን ጥላቻንና ዛቻን የሚዘሩ፣… የሰውን ንብረት የሚዘርፉና የሚያቃጥሉ፣… ሰውን ከመኖሪያው የሚያሳድዱና የሚገድሉ ወንጀለኞችን ለማቆንጀት፣ እንደበቀቀን ነጋ ጠባ፣ ማሳበቢያ ቃላትን ማነብነብ፣ ማመካኛ አባባሎችን ሌት ተቀን መደጋገም ይብቃ! የስንቱ ሕይወት ጠፋ? የስንቱ አካል ጎደለ? ሚሊዮኖች ተፈናቅለው፣ ንብረታቸው ተዘርፎና ወድሞ፣ ኑሯቸው ሲናጋ፣ እለት በእለት እያየንም እንኳ፣ ትንሽ ሰከን ብለን ማሰብ አንጀምርም? አሁንም ሰበብ አስባብ መደርደር? መነሻው፣ ምንም ይሁን ምን፣ ጭፍን እምነትም ይሁን ሌጣ አላዋቂነት፣… ፖለቲካን እንደቁማር ጨዋታ የማየት ሞኝነትም ይሁን የአእምሮ ድንዛዜ፣ የዘረኝነት በሽታም ይሁን አልያም ሌላ መነሻም ይኑረው፣… የወንጀል ድርጊትንና ጥፋትን ለማቆንጀት፣ እንደ ልማዳዊ የእለት ስራ፣ ልማዳዊ ሰበቦችና ማመካኛዎች፣ በበቀቀን ደመነፍስ እየተነበነቡ፣ በሰላም መቀጠል አይቻልም – ወደባሰ ጥፋት ነው የሚያወርዱን። “ይሄኛው ጥያቄ ተገቢ ነው። ያኛው አቤቱታ ትክክለኛ ነው። ተሰሚነት ማግኘት አለባቸው። መንግስት ተገቢ ጥያቄዎችን ካላደመጠ፣ ባለስልጣን ትክክለኛ አቤቱታዎችን ካልሰማ፣ ትልቅ ጥፋት ነው። በዚያ ላይ፣ ለአጥፊ ወንጀለኞች መንገድ ይከፍታል” ብሎ ማብራራት አንድ ጉዳይ ነው። እንዲሁ የምበደፈናው፣ “የህዝብ ጥያቄ” እያሉ ማነብነብ ግን፣ ጤናማ አስተሳሰብ አይደለም። በዚያ ላይ፣
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የብሄር ብሄረሰብ ምሽግ ፈርሶ፣ ግልጽ አደባባይ ይገንባ!! በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)

ሀገራዊ የስነምግባር ዝቅጠት፣ ሥርዓተ አልበኝነት፣ የፍትህ ተቋማት አቅመ ቢስነት?? ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ፣ በምንኖርበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ የሚፃፍበት ገጽ ከማይገኝላቸው ጥቂት እንስሳዊ ተግባራት አንዱ ነው፡፡ በሊባኖስ ለስልጣንና ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት፣ እናቶችና ህፃናት ሳይቀሩ በህንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ከእነ ህይወታቸው ይቀበራሉ፡፡ በናይናማራ ሙስሊሞች እርቃናቸውን እንደ ድንጋይ ተነጥፈው ተሽከርካሪ ይነዳባቸዋል፤ አካላቸው ይቆራረጣል፤ በረሀብ ይቀጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ዜጎች ከመንገድ ተይዘው ይቃጠላሉ፤ ተዘቅዝቀው ይሰቀላሉ፤ ኮበሌዎች በቢላ ይቆራረጣሉ፤ ሚሊየኖች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ከኖሩበት አካባቢ፣ ንብረታቸው እየተዘረፈ፣ ቤታቸው እየተቃጠለ፣ አካላቸው እየጎደለ ይሰደዳሉ፡፡ የኢትዮጵያውያን ግፍና ኢ-ሰብአዊ ተግባር ከሌሎች በዓለማችን ከሚደረጉት ተመሳሳይ ድርጊቶች የሚለየው ሀገራቱ በአምባገነን መሪዎች የሚመሩና መሪዎቻቸው የድርጊቱ አስፈፃሚዎች ወይም ተባባሪዎች መሆናቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ስለ ፍቅርና መደመር የሚዘምር፣ ስለ ዲሞክራሲና ፍትህ መከበር ሙሉ ጊዜውን የሚሰራ፣ ሀገሪቱን ከተዘፈቀችበት የጥፋት መቀመቅ ለማውጣት ቆርጦ የተነሳ መሪ ያላት፣ ግን ደግሞ ያለ መሪ ብቻ ሳይሆን፣ ያለ ህሊና በደመነፍስ ብቻ በዱር የሚኖሩ እንስሶች በዝርያዎቻቸው ላይ የማይፈጽሙት በደል የሚፈጸምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡ ይህቺ በሁለት እግር የሚራመዱ ፍጡራን፣ ከእንስሳዊ ደመነፍስ ሚዛን የወረደ ግፍና ጭካኔ የሚፈጽሙባት ኢትዮጵያ፣ ያለፈው ግማሽ ምእተዓመት የደርግ አምባገነንነትና የኢህአዴግ የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ናት፡፡ እነዚህ ሁለት አምባገነን መንግስታት ገድለው ይጥሉ – አስረው ያሰቃዩ ነበር። ህዝቡ ደግሞ ሲደፍር ያምጻል፤ ሲፈራ ተደብቆ ያለቅሳል፡፡  በተለይ የሃያ ሰባት ዓመት የኢህአዴግ አምባገነን አገዛዝ፣ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ ሸንሽኖ ተፋቅረው እንዳይኖሩ፣ በጥላቻ የክልል ዋሻ ውስጥ ከትቷቸዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት ስርዓት አልበኝነትን አይታገስም። ጠ/ሚነስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ (ቪድዮ)

መንግስት ስርዓት አልበኝነትን አይታገስም። ጠ/ሚነስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ (ቪድዮ) ሕግና ሥርዓት የማህበረሰባችን መሰረት እና ያስተሳሰረን ነው። መንግሥት አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌና ሥርዓት አልበኝነትን አይታገስም።(ጠ/ሚነስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖችን ሲያስመርቅ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች:- • ነፃነትና ስርዓት አልበኝነት ባለመለየት መረን የወጣ ሕግና ስርዓትን የማያከብር የመንጋ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ መቆም ይኖርበታል፡፡ • ሕጋዊ ስርዓትን እያደከምን በመንጋ የሚሰጥ ፍትሕ ተከትለን በግል ስሜት መነዳት የለብንም፡፡ • ሕግ አልባና አመጽን የሚታገስ ስርዓት እንደ አገር መቆጠራችንን ከንቱ ስለሚያደርግ አገራዊ አንድነታችንን በሕግ አግባብ ማስጠበቅ የዘወትር ተልዕኮአችን ይሆናል፡፡ • ዘመናዊነት የሕግ የበላይነት ማክበር ነው፡፡ • እንደመር፣ በይቅርታ አንድ አገር እንገንባ ስንል ከመረን እንውጣ፣ ሕግ አናክብር በየከተማው ሽፍታ ይበራከት ማለት አለመሆኑን በአንክሮ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ • የይቅርታው ዓላማ ባለፍንበት መንገድ ያጣናውን ለማግኘት እንጂ የገነባነውን አገር ለማፍረስ ስላልሆነ እያንዳንዱ ዜጋ ይህ ከአብራኩ የወጣውንና በአነስተኛ ደሞዝ ሕይወቱን እየገበረ የአገር አንድነትን የሚያስጠብቀውን ኃይል የመውደድ፣ የማክበር፣ የሞራል ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡ • በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ያየነውን የመከላከያ አንድነት እና የለውጥ ኃይል መሆንን የማስቀጠል ፍላጎት በሁሉም ጄኔራል መኮንኖች እንዲደገም፣ በጡረታ የተገለሉ ጄኔራሎች ለወታደር ጡረታ ስለማይሰራ በየትኛውም ጊዜ ችግር ካጋጠመን እናት አገር ጥሪ ልታቀርብላቸው ስለምትችል ቀርባችሁ ሁኔታውን እያያችሁ በመምከር፣ በማገዝ፣ በመደገፍ፣ ወገናዊነታችሁን ማሳየት እንድትችሉ እንዳትበተኑ፣ አንድ ሆናችሁ አንዲት
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራን ትጥቅ የማስፈታት አዲሱ ስትራቴጂ! (ሙሉቀን ተስፋው )

አማራን ትጥቅ የማስፈታት አዲሱ ስትራቴጂ! (ሙሉቀን ተስፋው ) ባለፉት ዓመታት የወያኔ አገዛዝ የአማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ብዙ ጥሮ አልተሳካለትም ነበር፤ አሁን ያለው አደገኛ አካሔድ በጊዜ ካልተገታ ውጤቱ የከፋ ነው፡፡ ገበሬዎችን በገንዘብ በመደለል ትጥቃችሁን ፍቱ ማለት እጅግ ነውረኛ አካሔድ ነው፤ ሕወሓቶች መሣሪያ ከማስታጠቅም አልፈው ሁሉንም ትግሬ ወታደር ለማድረግ በሚነቀሳቀሱበት በዚህ ወቅት የአማራን ገበሬ በገንዘብ በመደለል ትጥቅ ለማስፈታት መሮጥ እጅግ እጅግ የከፋ መርዘኛ አካሔድ ነው፡፡ በበኩሌ ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት የአማራ ገበሬዎችን በየቦታው እየመዘገበ የእኔ ጦር የነበሩ ናቸው በማለት ሲያቀርብ አልተቃወምኩም ነበር፤ ምክንያቱ ደግሞ መንግሥት ለኦነግ ወታደሮች መቋቋሚያና ቤት ወዘተረፈ ለማቅረብ ስለተስማማ በዚህም የእኛ ገበሬዎች ተጠቃሚ ቢሆኑ ጉዳት የለውም ከሚል ነው፤ ይህም ብቻ ሳይሆን የአማራ ገበሬዎች አገዛዙ ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ የእነርሱንና የልጆቻቸውን ሕይወት ስለገበሩ መቋቋሚያ ማግኘት የግድ በመሆኑ በየትኛውም በኩል ይህን እገዛ ማግኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን አሁን አካሔዱ መስመር እየለቀቀ ነው፡፡ በዚህ ቀውጢ ጊዜ ነገሮችን ከመቼም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ሳይሆኑ የእኛን ገበሬዎች መቋቋሚያ ታገኛላችሁ በሚል መሣሪያና ትጥቅ ማስፈታት እጅግ አደገኛና ሁላችንም ልንቃወመው የሚገባ ነው፡፡ የግንቦት ሰባት አመራሮች ያሠማራችኃቸውን ወኪሎቻችሁን ይህን አደገኛ አካሔድ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ብታደረጉ መልካም ይመስለኛል፡፡ የአማራ ገበሬወችን ትጥቅ የማስፈታት ሒደት በእጅጉ እቃወማለሁ፡፡ ምስሉ የምዕራብ ጎጃም ገበሬዎች በግንቦት ሰባት የትጥቅ ማስፈታት ፕሮግራም ውስጥ እንዳሉ ነው የሚያሳየው፡፡
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አፋጣኝ መፍትሔና መሠረታዊ ለውጥ የሚሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች እና የመንገደኞች አቤቱታ

አፋጣኝ መፍትሔና መሠረታዊ ለውጥ የሚሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች እና የመንገደኞች አቤቱታ (ምንልክ ሳልሳዊ ) በብልሹ አሰራር የበሰበሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት ሀያ አመታት በሰራተኞቹ እና በመንገደኞች ላይ መንግስታዊ ወንጀል ሲፈፅም የኖረ ተቋም ነው ። በአቶ ተወልደ የሚመራው የተቋሙ ማኔጅመንት ከሕወሓት ኢሕአዴግ የደህንነት ተቋም ጋር ተቀናጅቶ በዜጎች ላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አድርሷል ። የሰራተኞችን መብት ማኔጅመንቱ እንዲያከብር መንግስት እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል ። ዘረፋንና ዘረኝነትን አጣምሮ የያዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ስር ነቀል የመዋቅር ለውጥ ሊደረግ ይገባል።ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ጀምሮ እስከ መንገደኞች ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከፍተኛ የሆነ ስሞታ ያቀርባሉ፤ በተለያየ መንገድ በድርጅቱ ላይ የገጽታ ግንባታ ፕሮፓጋንዳ ቢሰራም አየር መንገዱን ከዘረፋና ከዘረኝነት ሊታደግ ባለመቻሉ ዘረፋውና ዘረኝነቱ አይኑን አፍጥጦ እያየነው ነው። በተለያዩ የመስሪያ ቤቱ ቁልፍ መዋቅሮች ላይ የተመደቢ ዘራፊዎችና ዘረኞች አየር መንገዱን ለእዳና የዜጎችን መብት እንዲጣስ ከማድረጉም በላይ በከፍተኛ ደረጃ ሕገወጥ ስራዎች ይፈጸማሉ። የተለያዩ የሃገርን ኢኮኖሚ የሚጎዱ ኮንትሮባንዶች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ትእዛዝ ይሰራል ; ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡና ከሃገር የሚወጡ በርካታ ማቴሪያሎች የውጪ ምንዛሬዎች የተፈጥሮ ሃብቶች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሕገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ የሃገሪቷን ኢኮኖሚ ባዶ አስቀርተውታል። ዘረፋ ብቻ ሳይሆን አየር መንገዱ ዜጎችን ለማፈንና ሕጋዊ ተጓዦችን ለማስተጓጎል በሚደረገው ደሕንነታዊ ስራ ላይ ተባባሪ ነው፤ ዜጎች በነጻ እንዳይዘዋወሩ በሃገር ውስጥና በውጪ በረራዎች ላይ ሰላዮችን በመመደብ ወንጀል ላይ የ አየር መንገዱ ማኔጅመት ተሳታፊ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በስርአት አልበኞች ላይ እርምጃ አንዲወስድ ጠየቀች፡፡

መንግስት የሚያሳየው ትዕግስት ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ዕርምጃዎችን እንዲወስድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠየቀች፡፡ $bp("Brid_44804_4", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-529961874107237.mp4", name: "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በስርአት አልበኞች ላይ እርምጃ አንዲወስድ ጠየቀች፡፡", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180817_153914.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበር አካባቢዎች ላይ ጥምር ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበር አካባቢዎች ላይ ጥምር ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ላይ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ ጥምር ጦር ለማሰማራት ተስማምተዋል፡፡ የሁለቱ አገራት ጦር ኢታማዦር ሹሞች በትላንትናው ዕለት ካርቱም ላይ ተገናኝተው ከመከሩ በኃላ ነው ከስምምነት የደረሱት፡፡ የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ከማል አብዱል መዕሩፍ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በድንበር አካባቢ የሚሰፍረው የሁለቱ አገራት የጋራ ጥምር ጦር ሽብርን፣ ድንበር ዘለል የአማፂያን እንቅስቃሴን እና ህገ ወጥ ስደትን የመከላከል ተልዕኮ ይሰጠዋል፡፡ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን በበኩላቸው በሁለቱ አገራት አወሳኝ ድንበር ላይ የሚሰፍረው የጋራ ጥምር ጦር የቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ በማድረግ ሂደት አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ ምንጭ፡አናዱሉ የዜና ወኪል
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በመጭዎቹ ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ አረጋገጠ።

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በመጭዎቹ ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ አረጋገጠ። በብራዜል ሪዮ ዴጄኔሮ ውስጥ በተካሔደው የኦሎምፒክ ውዽር የብር ሜዳሊያ ለሃገሩ ያስገኘው እና በኢትዮጵያ የሚካሔደውን ግድያና እስር በመቃወም እጆቹን በማጣመር ለዓለም ጭቆናን ያጋለጠውና በአሜሪካ በጥገኝነት የሚኖረው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ አረጋገጠ። ባለቤቱንና ልጆቹን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ የተናገረው አትሌቱ በመጭዎቹ ሳምንታት አገር ቤት እንደሚገባ አረጋግጧል።   FILE - Ethiopian silver medalist Feyisa Lilesa crosses his arms on the podium after the men’s marathon at the 2016 Summer Olympics in Rio de Janeiro, Brazil, Aug. 21, 2016.FILE – Ethiopian silver medalist Feyisa Lilesa crosses his arms on the podium after the men’s marathon at the 2016 Summer Olympics in Rio de Janeiro, Brazil, Aug. 21, 2016. After winning the silver medal in the men’s marathon at the 2016 Olympic Games in Rio de Janeiro, Brazil, Feyisa Lilesa spent two years in self-imposed exile in the United States. Now, he’s returning home. Feyisa will return to Ethiopia in the coming weeks with his wife and children after two athletics groups notified him that he would receive a hero’s welcome upon arriving. Ashebir Woldegiorgis, the president of the Ethiopian Olympic Committee, told VOA Amharic that the call for Feyisa to return is meant to better the country. “He can teach his exemplary ways to other athletes and teach strength to our youngsters. That’s the main call, so he can come back to
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት

ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ተጠይቆ ለፋና ራዲዮ የሰጠው መልስ . ጥያቄ : ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን እንዴት ታየዋለህ? . መልስ : ኢትዮጵያ የቀለም ውህድ ስዕል ናት ለኔ። ኢትዮጵያን ስንስላት 80 ቀለሞችን ቀላቅለን ነው የምንስላት። እነዛ 80 ቀለሞች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ናቸው። ለኔ ኢትዮጵያዊነት የ 80 ብሄር ብሄረሰቦች ቅልቅል ውጤት ናት። በኢትዮጵያዊነቴ ማንም ሰው አንተ ‘ኢትዮጵያን አትወድም፤ አንተ ኢትዮጵያን ትወዳለህ’ ሊለኝ አይችልም። ምክንያቱም ቅድመ አያቴ ቦንሲቱቃበታ ከዚህ መቀሌን ነፃ ለማውጣት በእግሯ ስትጓዝ ኦሮሞ እዛ ስላለ አይደለም። እኔ የአያቴ አስክሬን ሲሸኝ አውቃለሁ በፈረስ ሲፎከርላት የነበረው “ቦንሲቱ ጋፋ መቀሌ ወይም ቦንሲቱ ያኔ በመቀሌ ጊዜ” እየተባለ ነበር አስከሬኗ ሲሸኝ የነበረው። በህይወት የሌሉ ቅድመአያቶቼ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር አጥንታቸውን ከስክሰዋል። ማንም ሰው ሀጫሉ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ እንደዚህ ያለ አቋም አለው የለውም የሚል መብት የለውም ምክንያቱም እኔ ስለማውቀው። ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው። ምክንያቱም 80 ቀለም ስላለው። . ነገርግን ስጋት አለኝ። ስጋቴ ምንድነው?! ድሮ መንግስት ሀላፊነቱን ይረሳና ጡንቻውን የሚያሳይበት ነበር። ያን ነገር ምስኪን ህዝብ ለመቀየር ይሄ ነው የማይባል መስዋትነት ከፍሏል። ከከፈለ በኋላ አሁን ይመስለኛል በተወሰነ መልኩ ባልተጠበቀ መንገድ ህዝባዊነት የሚታይበት ነገር አለ ስጋቴ ምንድነው ይሄን መንግስት መያዝ እንዳያቅተው ነው ስጋቴ። ጥንቃቄ እንደሚፈልግ እና በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት። . ጥያቄ : በቀጣይ ምን አይነት ስራዎችን ለመስራት አቅደሀል? . መልስ : አሁን መንግስትን ከመውቀስ ወጥቼ ልዩነት ማስፋት ሳይሆን ነገሮችን በማጥበብ ሀገርን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ ሰከን በል!

የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ ሰከን በል! ታዬ ደንዳዓ በተለያዩ ቦታዎች ህገ-ወጥነት ይታያል። አንዳንዴም ከባህላችን ያፈነገጠ አስነዋሪ ድርጊት ይፈፀማል። ይህ ወደነበርንበት እንዳይመልሰን ያሰጋል። ወጣቱ ብዙ ችግር እንዳለበት ይታወቃል። ችግራችን ከምናስበዉ በላይ ይከፋል። ሆኖም መረጋጋት ግድ ይሆናል። በስሜት እና በብሶት መንቀሳቀስ አቅጣጫ ያስታል። በዝህ ላይ የ1966ቱን አብዮት ማስታወስ ይጠቅማል። አብዮቱን ያመጣዉ የወጣቱ ትግልና መስዋዕትነት መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ከስሌት ይልቅ ስሜት ስለበዛ አብዮቱ ከሸፈ። አሁን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ወጣቱ ባደረገዉ ትግል መንግስትን አስገድዶ ወደ ተሀድሶ አስገብቷል። የዶር አብይ አስተዳደር ሊካዱ የማይችሉ ተጨባጭ ለዉጦችን አሳይቷል። ለዝህ ለዉጥ ኢትዮጵያዉያን በዉስጥም በዉጭም ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥቷል። ለዉጡን ለማስቀጠል ድጋፉን መሬት ማስነካት ይገባል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ስክነት ያስፈልጋል። ወጣቱ ሦስት ነገሮችን ማድረግ አለበት። አንደኛዉ ሰላም ማስፈን ነዉ። ያለሠላም የለዉጡ ባቡር ወደፊት ሊሄድ አይችልም። አመራሩ በእሳት ማጥፋት ስራ ይጠመዳል። ሁለተኛዉ የህግ የበላይነት ነዉ። ህግና ስርዓት ከሌሌ ምንም ሊኖር አይችልም። ወጣቱ ከምንም በላይ ለህግ የባላይነት ዘብ መቆም አለበት። ሦስተኛዉ ስራ ነዉ። ለዉጥ የአንድ ሰዉ ወይም የጥቂት ሰዎች ተአምራዊ ስራ አይደለም። የሁሉንም አስተዋፅኦ ይፈልጋል። ስለዝህ ሁሉም በተሰማራበት ስራ ዉጤት በማምጣት ለለዉጡ አስተዋፅኦ ማድረግ አለበት! ወጣት ሆይ፣ ተረጋጋ! የሚጠቅምህን እና የሚጎዳህን ለይ! ግርግር የሚበጀዉ ለሌባ ነዉ! ሰላም ዋሉ!
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአባይ ግድብ ጉዳይ ሳሊን ኩባንያ የኢትዮጵያን መንግስት ከ350 ሚለየን ዩሮ በላይ ካሳ ጠየቀ ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሜካንካል ስራውን ሜቴክ በጊዜ እና በትክክል ሰርቶ ማስረከብ ስላልቻል ሳሊን ሌሎች ስራዎችን መቀጠል አልቻለም። በዚህም ምክንያት ሳሊን ኩባንያ የኢትዮጵያን መንግስት ከ350 ሚለየን ዩሮ በላይ ካሳ እንደጠየቀ ለፕሮጀክቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልፀዋል ። ግድቡ በጠቅላላው ስራ ይጀምራል በተበለበት ጊዜ ላይ በሜካንካል (ሜቴክ የያዘው ክፍል) ስራው ችግር ምክንያት 16ቱም ታርባይኖች መስራት አለመቻላቸው በጣም አስደንጋጭ እንደሆነ ምንጮቼ አክለው ገልፀውታል ።
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጎጃም ሸበል በረንታ ውስጥ በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመ ት/ቤት ስያሜው ተቀየረ።

በአማራ ልጆች ትግል ለመለስ ዜናዊ መታሰቢያነት የተሰየመው ትምህርት ቤቶች ስም ወደነበረበት እየተቀየረ ነው! ( አቻምየለህ ታምሩ ) መለስ ዜናዊ ያለውን አቅምና ጉልበት ሁሉ ሳይቆጥብ ለክፉ ተግባር ያዋለ፤ በእምነትና በቅን መንፈስ ተገፋፍቶ ያለፋቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙበት፤ በትምህርት ተወልደው መልካም የሚሰሩና ለወገናቸው የሚያስቡ ሰዎችን በማጥፋት ክብረወሰን የተቀዳጀው፤ ድሀ ዘራፊና ገፋፊ፤ ተራ ወንጀለኛና ጨካኝ አረመኔ ነበር። እኛ የምናውቀው መለስ ዜናዊ በካድሬዎቹ እንደሚወራለት ማለፉ ዓለምን ያጎደለ፣ አፍሪካንም ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ ያሳጣና ሞቱ አህጉሩንም የጎዳ ሳይሆን ተሰርቶ ያላለቀና ከፈረንጅ አፍ ሰምቶ በማስታወሻ ደብተሩ የያዘውን ሁሉ በአንድ አዳር የአገር ፖሊሲ በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ብክነት ማዕከልነት ሲቀይር የኖረ በጥላቻ የናወዙ የትግራይ አረመኔያዊ ሽፍቶች አለቃ ነበር። የገነባው የአፓርታይድ አገዛዝ እስኪያንገሸግሸን ድረስ የመተረን ተጠቃን ብለን የማንጮህ፤ ተዘረፍን ብለን የማንቆጣ፤ ሕጋዊ ስርዓት ተፋለሰ ብለን የማንበሳጭ፤ የድሃውና የስራ አጡ ለቅሶ ሰሚ ሳይኖረው የጭቆና አስተዳደር ተከናንበን የምንኖር ህዝቦች በመሆናችን፤ ኩራትና ክብራችን ዋጋ አጥቶ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ታፍኖ እያየን በልቶ በማደር የኑሮ ግዴታ ብቻ ስለተጠመድን ብቻ ነው። በጭካኔ ክብረ ወሰን የሰበረው መለስ ዜናዊ ምልክቶች ከኢትዮጵያ ምድር ተነቅለው መወገድ ይኖርባቸዋል። ለሱ ሐውልት ማቆም የሚሻ ቢኖር ከመለስ ዜናዊ ጋር በጭካኔ የሚመትሩት አገር ለመመስረት ጫካ የገቡት እነ ኦነግ፣ ኢሕአፓ፣ ሻዕብያ፣ ጀብሃ፣ መኢሶን፣ ወዘተ ጋር ተባብሮ ቢፈልግ ደደቢት በረሀ፣ አሊያም አሲምባ ተራራ፣ ቢያሻቸው ሞቃዲሾ ዚያድ ባሬ ቤተ መንግሥት ወይንም ናቅፋ ተራራ ላይ በእጁ መዶሻና አካፋ፤
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ማፍያዎች ድብቅ ሴራ

Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ትግራይ ውስጥ ታፍነው የታሰሩትን የስቃይ ሰለባዎች የሚያስፈታቸው አካል አልተገኘም።

ሊቁ እንደስራቸው አግማሴን ጨምሮ ከ2000 በላይ እስረኞች ትግራይ ውስጥ ታፍነው ይገኛሉ። እነዚህን የስቃይ ሰለባዎች የሚያስፈታቸው አካል አልተገኘም። ስቃያቸው ተለመደና ዝም ዝም ሆኗል። ያላቸው አማራጭ ሕዝብ ብቻ ነው! መምህር እንደስራቸውን ጨምሮ ትግራይ ውስጥ የታፈኑት ሆን ተብሎ፣ በእቅድ ነው። ይህን ዝም እያሉ፣ ሕዝብ በግብታዊነት እህል አወረደ ብሎ ግን የሚዘልፍ ሞልቷል። የምንጠይቀውን ኃላፊነት ያለበት አካል እንጠይቅን። የምናስረዳውን ሕዝብ እናስረዳ! የታፈኑት ንፁሃን ይፈቱ! ንፁሃንን አጉሮ ሕዝብ እህል እንዳያልፍ አገደ ብሎ ማማረር ትክክል አይመስለኝም! ነፍስ አግቶ፣ ስለ ጥራጥሬ ማውራት ተገቢ አይደለም! የሚቀድመው ይቅደም!
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዴሞክራሲ ብቻ! — ብርሃኑ አበጋዝ

ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ – አዲስ አበባ *** በኢትዮጵያችን ዴሞክራሲን የግድ የሚያደርገውም የዴሞክራሲ (የዴሞክራሲ ሽግግር) አንቅፋቱም ዘውጌ ብሔርተኝነት ነው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ መድኀን ዴሞክራሲ ነውና መንገዱ አስቸጋሪም ቢሆን በዚኸው አቅጣጫ ከመግፋት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ሁሉም እንደሚያውቀው በአገራችን ላለፉት ከአርባ በላይ ዓመታት ሲቀነቀን የኖረው የዘውግ ፖለቲካ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ማዕከላዊ ቦታ ከመያዙም በላይ፣ ሌላ የፖለቲካ ትርክት የጠፋ ይመስል ሁሉም ነገር ዘውግ ተኮር ሊሆን በቅቷል፡፡ ዘውገኝነት በፖለቲካው አካባቢ ሳይወሰን የግል ዘርፉንም በክሎታል፡፡ የሠራተኛ ቅጥሩ፣ የሸር ካምፓኒ ምሥረታው፣ የኢንቨስትመንት ቦታ መረጣው ወዘተ. ሁሉ ዘውግ ተኮር ሆኗል፡፡ ይህን ነባራዊ ሐቅ ሊያስተናግድና በሒደት መልክ እንዲይዝ ሊያደርግ የሚችለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ብቻ ነው፡፡ የኢዴሞክራሲ አማራጭ (አማራጭ ከተባለ) ወደ ምስቀልቅል ብቻ ነው ሊወስደን የሚችለው፡፡ ከዚህ በኋላ በልማታዊ መንግሥት ወይም በሌላ ‹ኢ-ሊብራል› አማራጭ እያሳበቡ የኢኮኖሚ ልማት እስኪረጋገጥ ድረስ በኢዴሞክራሲያዊ መንገድ ማዝገም ይቻላል ማለት ፈጽሞ ጊዜው አልፎበታል፡፡ “መደመር” የሚለው የነ ዶ/ር ዐቢይ መርህ ከዚህ የተለየ ስለመሆን አለመሆኑ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያዊያን እየወደቅንም እየተነሳንም፣ እያጠፋንም እያለማንም ቢሆን ዴሞክራሲን ብቻ ነው መለማመድ ያለብን፡፡ ወጣቱ፣ ዘውጌ ብሔርተኝነትና ዴሞክራሲ *** በግልጽ እንደሚታየው የለውጡ እንቅስቃሴ ሞተሩ ወጣቱ ነው፡፡ ይኽ በገጠርም በከተማም የሚኖር ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ 70 ከመቶ የኅብረተሰብ ክፍል ድርሻ አለው፡፡ ወጣቱ ነገሮች ቢመቻቹለት በአጭር ጊዜ ወደ መካከለኛ መደብ ሊደርስ የሚችል ኀይል ነው፡፡ ነገሮች ቢመቻቹለት፣ ትክክለኛ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ቢቀየስለት፣ ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቢዘረጋለት በአጭር
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“መደመር” እና የምርኮው ፖለቲካ (ጌታቸው ሺፈራው)

“መደመር” እና የምርኮው ፖለቲካ (ጌታቸው ሺፈራው) ባለፉት 27 አመታት ከአገዛዙ በተቃራኒ የቆሙ በርካታ የፖለቲካ ቡድኖች ነበሩ። በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያሉ/የነበሩ፣ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል የሚታገሉ ቡድኖች ከአገዛዙ ጋር የነበራቸው ልዩነት ሰፊ ነው። ይሁንና ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ከኦነግ ውጭ ያሉት የፖለቲካ ቡድኖች ምንም አይነት ድርድር ሳያደርጉ “ተደምረናል” ብለዋል። ተደምረዋል ሲባል አንድ ከገዥዎቹ ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ቡድን የሚያደርገውን ድርድር ሳያደርጉ ነው። ድርድር በአንድ ወቅት የሚታየው ክስተት፣ መልካም ሁኔታ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም። ቀጣይነቱም ላይ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። የዶክተር አብይ አህመድ መንግስት በውጭም በሀገር ውስጥም ለነበሩት ቡድኖች የሰጠው ተስፋና፣ “ተደምረናል” ያሉበት የመጀመርያው ነገር “ስለ አንድነት፣ ስለ ነፃነት” መሰል ነገሮች መስበክ ነው። በተጨማሪም የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት መጀመራቸው የፖለቲካ ቡድኖቹ ያለ መሰረታዊ ድርድር “ተደምረናል” እንዲሉ ያደረጓቸው ምክንያቶች ናቸው። አብዛኞቹ የፖለቲካ ድርጅቶች በቀናነት የተመለከቱት የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች መፈታት ጉዳይ በሕዝብ ትግል እና በእነ ዶክተር አብይ እንጅ ድርጅቶቹ ተደራድረው የተወሰነ ባለመሆኑ አሁንም ለሁሉም ተፈፃሚ አልሆነም። የፖለቲካ ድርጅቶች ለረዥም ጊዜ በመደራደሪያነት ያቀርቡት የነበረው “ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ” የሚል ጥያቄ እውን አልሆነም። እነ ዶክተር አብይ እንፈታለን ሲሉ “ካላችሁ መልካም ነው” ብሎ ማጨብጨብን የመረጠው፣ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብሎ መክሮ አስገዳጅነት ያላስቀመጠቅ የፖለቲካ ሀይል አሁንም “ለምን ሁሉም አይፈቱም?” የማለት የሞራል የበላይነት አላገኘም። አሁንም እስረኞች እየማቀቁ ከገዥዎቹ ጋር እየተጨባበጠ ከመቀጠል ውጭ አማራጭ አልፈለገም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀይሎች
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል

በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል ቢቢሲ አማርኛ ባለፉት ሁለት ሦስት ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም የመንጋ ፍትህ ከህግ የበላይነት አንፃር ምን አይነት አደጋዎች እንደተጋረጡ አመላካች ነው። በምስራቅ ወለጋ ወሊጋልቴ ገጠር ቀበሌም ቅዳሜ እለት ማምሻውን ሁለት ግለሰቦች በቡድን በድንጋይ ተደብድበው መሞታቸው ተሰምቷል። እሁድ ደግሞ በሻሸመኔ ቦምብ ይዟል በሚል አንድ ሰውን ወጣቶች የስልክ እንጨት ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለዋል። ትላንት ጀዋር መሀመድን ለመቀበል በርካቶች በሻሸመኔ ከተማ ስታዲየም ተገኝተው ነበር። በህዝብ መጨናነቅ ሳቢያ በተከሰተው መገፋፋት ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉም አሉ። የብዙሀኑ መነጋገሪያ የነበረው ግን ተደብዶቦ ህይወቱ ያለፈና ልብሱ ተገፎ፣ ተዘቅዝቆ የተሰቀለው ሰው ነው። ግለሰቡ ማንም ቢሆን፣ ምንም አይነት ተግባር ቢፈጽምም የደረሰበት አሰቃቂ ጥቃት ኢ-ፍትሀዊ ነው የሚሉ አስተያየቶች ተደምጠዋል። አንድን ሰው በአንድ ወንጀል ከሶ፣ ራስ ምስክር፣ ራስ ፈራጅ፣ ቀጪም ራስ የሆነበት የደቦ ፍትህ በሻሸመኔ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም እየተስተዋለ ነው። በሻሸመኔ ከተማ ጀዋርን ለመቀበል ወደ ስታዲየሙ አቅንተው ከነበሩ መካከል ስሜ አይጠቀስ ብሎ አስተያየቱን የሰጠን ግለሰብ ግርግር ካየ በኃላ ነበር ስለ ክስተቱ የሰማው። “ቦንብ ይዟል” የተባለው ሰው ተሰቅሎ የተመለከተ ሲሆን ተግባሩን “ትልቅ ስህተት” ይለዋል። ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ማሰብና ከመሰል እርምጃ መቆጠብ እንዳለበትም ይናገራል። ሰው ተሰቅሎ ማየቱ እጅግ የዘገነነው ግለሰብ “አስጸያፊ ነው። በሀገራችን በባህላችንም የለም። ፍትሀዊም አይደደለም” ብሏል። የሻሸመኔ ከተማ የፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአፋር ሱልጣን ሐንፍሬ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ።

ለአመታት በውጭ አገር በስደት የቆዩ የአፋር ሱልጣን ሐንፈሬ አሊሚራህ በታዋቂ የአፋር ፖለቲካ አመራሮች ታጅበው ዛሬ ማክስኞ ጠዋት  ወደአገር ቤት ገብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ፣ የአፋር ክልል አመራሮች ፣ የአፋር የለውጥ ሐይል ወጣቶች ለአፋር ሱልጣንና ለፖለቲካ ድርጅቶች በቦሌ ኤርፖርት ላይ ደማቅ አቀባባል አድርገውላቸዋል ።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መቻቻልን እንቻልበት እንጅ ! (አሌክስ አብርሃም)

መቻቻልን እንቻልበት እንጅ ! (አሌክስ አብርሃም) በቋንቋ ህግ እንኳን ስም አይተረጎምም !! ከበደ ከሆንክ በጀርመንኛም ተጠራ በፈረንሳይኛ ያው ከበደ ነህ !! የቋንቋ ምሁራን ካላችሁ ያው ታውቁታላችሁ ! አሁን ይህን ምን ይሉታል ?አንድ ታዋቂ የህዝብ ሚዲያ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ፊንፊኔ ዩኒቨርስቲ ብሎ መተርጎም እንደው ፖለቲካውን ትተነው የቋንቋ መርሁን የተከተለ ነገር ነው? ስር የሰደደ የስም ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር እዚህ ግባ የሚባል ጥቅም ያለው ጉዳይ አይደለም ! እዚህ ድረስማ አናክር ጓዶች ! ለአብሮነትም ምንም የማይፈይድ ተግባር ነው !! ለምሳሌ <<አዲስ አበባ ታደሰ>> የምትባል አማተር ተዋናይ አውቃለሁ ፣ ይች ልጅ ነገ ታዋቂ ብትሆንና ይሄው የህዝብ ሚዲያ ቢያቀርባት <<ታዋቂዋ ፊንፊኔ ታደሰ>> ሊላት ነው? ሳር ቅጠሉን የኛ ብለንማ ትሻልን ሰድጀ ትብስን አመጣሁ በራሳችን ላይ አናስተርት!
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኦህዴድና ትህነግ(ሕወሓት) በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው)

ኦህዴድና ትህነግ በማን ላይ ተስማሙ? (ጌታቸው ሺፈራው) ~በእነ አብይ መንግስት ላይ ግንባር ቀደሙ አማፂ ትህነግ/ህወሓት ነው። ለዚህ ስራው የቀን ጅብ የሚል ስም ተሰጥቶታል። ከወንጀሉ ሁሉ በስተጀርባ አለበት እየተባለ ነው። ዶክተር አብይ አህመድ በሚኒሶታ ለተነሳለት ጥያቄ ከአንዲት ከሁለት የትግራይ ተወላጆች የተነሳለትን ጥያቄ ከትህነግ/ህወሓት የመጣ እንደሆነ አድርጎ መልሷል። ዶክተር አብይ አህመድ በሰጠው መልስ ከትህነግ ጋር እልህ ውስጥ እንደገባ በግልፅ ያሳየ ነበር። ~ዶክተር አብይ ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ በሶማሊ ክልል ለተፈፀመው ጭፍጨፋም የጅቦቹ እጅ እንዳለበት ከመገመቱ ባለፈ ፌደራል መንግስቱ በገዳዮቹ ላይ እርምጃ እንዳይወስድ በግልፅ መግለጫ የሰጠው ትህነግ ብቻ ነው። ትህነግ እንደፈለገ በሚጋልበው በሶማሊ ክልል ፕሬዝደንት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ፌደራል ስርዓቱን እንደሚያፈርስ አድርጎ ሲያስፈራራ ቆይቷል። ~ዶክተር አብይ አህመድ እና መንግስቱ በሶማሊ ክልል ለተፈፀመው ጭካኔ የሚገባውን ሳያደርግ አልፎታል። ጭራሹን በዚህ ወቅት ዶክተር አብይ በህይወት የመኖሩ ጉዳይ ሲያጠራጥር ቆይቷል። ታፍኗል፣ ታግቷል ከማለት አልፎ በሕይወት አለ ወይ ሲባል ሰንብቶ በይፋ የታየው ደብረፅዮን ጋር ነው። ~ የግል ፀብ ያላቸው ያህል ማዶና ማዶ ሆነው አብይና ደብረፅዮን ከአብይ መጥፋት በኋላ አብረው መታየታቸው እንዲሁ የሚታይ አይደለም። በእርግጥ ዶክተር አብይ አህመድ “አንተም ተው፣ አንተ እረፍ” ብትል ከምትሰማው አሜሪካ ከርሞ ነው የመጣው። እነ ደብረፅዮን ወደ ኤርትራ ቢያንጋጥጡም ኢሳያስ “ከዛው እርጉ” ብሏቸዋል። የትህነግ እና ኦህዴድ ግብግብ የዝሆኖች ግጥሚያ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ደብረፅዮን ከዶክተር አብይ ጋር ብቅ ብሏል ~ዶክተር አብይ አህመድ እና ደብረፅዮን አንድ ላይ የታዩት
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦችን ማንገላታቱን ቀጥሎበታል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦችን ማንገላታቱን ቀጥሎበታል ዛሬም እንደ ተለመደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦችን ባልተገለፀ ምክኒያት የኢትዮጵያ-ሳውዲ አረቢያ በረራውን መሰረዙን በመግለፁ ምክንያት በአሁን ወቅት በኤርፓርት ውስጥ የሐጅ ተጓዦች እየተንገላቱ ይገኛሉ። ይህ አየር መንገድ በኢትዮጵያ ሓጃጆች ላይ የሚፈፅመው በደል ከልክ አልፏል። በአሁኗ ሰዓት እንኳ መንገደኞችን በረራ ሰርዞባቸው ውጭ ላይ እየተንገላቱ መሆናቸውን ከስር የተያየዘውን ፎቶ ተመልከቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየአመቱ ከሚያቅዳቸው ዕቅዶች ውስጥ “ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦችን ማንገላታት” የሚል ያለበት ይመስል ካቻምና፣ አምናም ዘንድሮም ኢትዮጵያውያን የሐጅ ተጓዦችን ማንገላታቱን ቀጥሎበታል
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አጉል ጀብደኝነት ዋጋ ያስከፍላል። (ምንሊክ ሳልሳዊ )

አጉል ጀብደኝነት ዋጋ ያስከፍላል። (ምንሊክ ሳልሳዊ ) ከፊታችን የተደቀነውን ከባድ አደጋ ለማክሸፍ መንግስት ጥብቅ እርምጃ በመላው ኢትዮጵያ ሊወስድ ይገባል። አካባቢያችንን በቅጡ ካላየንና በሚገባ ካልመረመርን፣ እያሰብን ሳይሆን እየተኛን ነው፦ ከተኛን ደግሞ የተመኘነው ለውጥ አይመጣም፡፡ በሀገራችን የምንናገረውን የሚያዳምጥ፣ ያዳመጠውንም የሚያውጠነጥን ዜጋ ከሌለ የለውጥና የተሀድሶ ተስፋ ይጨልማል፡፡ ፍቅርን አንድነትን መደመርን ሰላምን ለማግጨት የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ በጥሩ መንገድ ተጉዘው ስኬትን ቢያስመዘግቡም አንዳንድ አከባቢዎች ላይ ግን ቅጣትን የሚሹ ልክ መግባት ያለባቸው ስርዓት አልበኞች ተፈጥረዋል። መንግስት ጉልበት እንዲጠቀም የሚጋብዙ ሰዎች እኩይ ተልእኳቸውም ማቆም አለመቻላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ባለፈው የሕወሃት አገዛዝ አግዓዚ ሕዝብን ሲገድል እያዩ አጠገባቸው ወገናቸው እየተገደለ እያዩ ካለፈው አሰቃቂ ሂደት መማር ያልቻሉ ሰዎች ለውጥ ለማምጣት የሚካሄደውን መልካም ጅማሮ ለማደናቀፍ ይሁን በእኛነት ጀብድ ከፍ ብሎ ለመታየት በሆነ መንገድ ማሰቢያቸውን አረመኔያዊ አድርገው የአደባባይ ሽብር እየፈጸሙ ይገኛሉ። ካሁን ቀደም ሲደረጉ የነበሩ ተቃውሞዎችንም ሆነ ክፋቶች አሁን ላይ እንዲደገሙ በፍጹም አንፈልግም። ካሁን ቀደም ያደረግናቸው ከባርነት ነጻ ለመውጣት የሔድንባቸው መንገዶች ለነጻነት መንገድ ያበኩን በመሆኑ ነጻነታችንን በእጃችን አጥብቀን ለመያዝ አገርና ሕዝብ ላይ አደጋ ከመፍጠርና አደጋ የሚፈጥሩትን ከማበረታታት ልንቆጠብ ይገባል። የተለያዩ የትግል ስልቶችን እየቀያየሩ ከመተቀም ይልቅ ሽብርና ጥላቻን መዝራት አደጋው የከፋ ነው። አጉል ጀብደኝነት ዋጋ ያስከፍላል። (ምንሊክ ሳልሳዊ ) መግደል መሸነፍ ነው ፤ መዝረፍ መሸነፍ ነው ፤ መንገኝነት መሸነፍ ነው ፤ ማፈናቀል መሸነፍ ነው። አንድነት ከሌለ መቻቻል ከሌለ ፣ ፍቅር ከሌለ ሰላም አይኖርም ፤
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በስደት የቆዩት የአፋር ሱልጣን ሐንፈሬ አሊሚራህ አዲስ አበባ በነገው እለት ይገባሉ።

ለአመታት በውጭ አገር የቆዩ የአፋር ሱልጣን ሐንፈሬ አሊሚራህ በታዋቂ የአፋር ፖለቲካ አመራሮች ታጅቦ ነገ ማክስኞ ጧዋት ላይ ከውጭ ወደአገር ቤት ይገባሉ፡፡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች ለአፋር ሱልጣንና ለፖለቲካ ድርጅቶች በቦሌ ኤርፖርት ላይ ደማቅ አቀባባል ያደርጋሉ፡፡ እርሶም በዚህ ታሪካዊ አቀባበል ላይ በመሳተፍ የታሪክ አካል እንዲሆኑም ተጋብዘዋል፡፡ኑ! አብረን እንደሰት፡፡ ነገ የአዲስ አበባ ሰማይ በተለያዩ የአፋር ባህላዊ ጨወታ ይደምቃል፡፡ እግረ መንገዶዎ በአዲስ አበባ አየርማረፊያ ትንሿ አፋርን በአንድ ጀንበር ይመልከቱ፡፡ Nek maraqina ” እንዳትቀሩብን ይላሉ የአፋር ወዳጆቻችሁ፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሊብራል ገበያ የንግድ ሥነ-ምግባር ( ጌታቸው አስፋው )

በሊብራል ገበያ የንግድ ሥነ-ምግባር *** ጌታቸው አስፋው *** በዓለም ዐቀፍ ኢኮኖሚ ጥናት ከምርትም በላይ ትኩረት ስቦ ብዙ የተባለለት ንግድ ነው፡፡ በተግባር ቅደም ተከተል ማምረት ከመነገድ ይቀድማል፡፡ ሆኖም ግን ሰዎች ከራሳቸው የግል ፍጆታ አልፈው በግብይይት መልክ ያመረቱትን ሽጠው ከገበያ የሚፈልጉትን ለመግዛት ያደረጉት እንቅስቃሴ በኢኮኖሚ ጥናት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የዚህ ምክንያቱም ማምረት ግላዊ ብቻ ሊሆንም ሲችል፣ ንግድ ግን ማኅበራዊ ስለሆነ ነው፣ የሰፊ ሕዝብ እንቅስቃሴ ስለሆነ ነው፡፡ ተጨማሪ እሴት የሚፈጠረው በምርት ሂደት ቢሆንም ዋጋ ግን የሚወሰነው በንግድ ሂደት ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ ኢኮኖሚክስ እንደ የማኅበራዊ ኑሮ ዘዴ የጥናት መስክ ሆኖ ሲጀምር የሞራልና የሥነ-ምግባር ጥበብ ነበር፡፡ ጥንት ከከፕሌቶና አሪስቶትል ጀምሮ ስለ ሀብት ይዞታና አጠቃቀም በሥነ-ምግባር ደንብ ተጠንቷል፡፡ ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለይ ንግድ ለብዙ ዘመናት ማጭበርበርና ማታለል ያለበት የማኅበረሰብ ጠንቅና የተወገዘ ነገር ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ ሮማውያንም የግሪኮችን ወርሰው ለንግድ በጎ አመለካከት አልነበራቸውም፡፡ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከጥሬ ገንዘብ ንግድ (ብድር) ወለድ መውሰድን እንደነውር ቆጥራ አውግዛለች፡፡ ዛሬም በእስልምና ሃይማኖት ባንክ ከሚቀመጥ ጥሬ ገንዘብ ወለድ መቀበል ሀጢዓት ተደርጎ ወለድ አይቀበሉበትም፡፡ አቅመቢሱን በንግድ ግንኙነት በዝብዞ፣ ሌላውን አደህይቶ ራስ መክበር ዛሬም ቢሆን የግለሰቦችና የአገራት የብልጽግና መንገድ ነው፡፡ ሆኖም ንግድ በሁለት ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው አካላት ስምምነት የሚፈጸም ስለሆነ ሕጋዊ ነው፡፡ በሕግ ከተደነገጉት የሰው አካልን ወይም እጾችን ከመነገድ ሸቀጦችን ደብቆ አላግባብ እጥረት ፈጥሮ ከማትረፍ በቀር በስምምነት መነገድ ማትረፍ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሻሸመኔ ከተማ ከፍተኛ አመፅ ተከስቷል።

በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ ጃዋር መሀመድን ለመቀበል የወጣው ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት እና በአንዳንድ አለመግባባት በጠፈጠረ ትርምስ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ የቦንብ ጥቃት ለመሰንዘር የመጣ መኪና ተብሎ የተጠረጠረ ተሽከርካሪ ላይ ህዝቡ እርምጃ ወስዷል። ከተማዋ ውስጥ ባሁን ሰአት ከፍተኛ አመፅ ተነስቷል። ሊወገዝ የሚገባው ሕገወጥ ነውረኛ ተግባርና ስርዓት አልበኝነት በሰለጠነ ዘመን ለመስማትም ይሁን ለማየት የሚቀፍ አሳፋሪ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በቄሮዎች ተፈፅሟል ሻሸመኔ ላይ የተደረገው አሰቃቂ ግድያ በጣም ያሳዝናል የጁሀር አቀባበበል ላይ ቦንብ ሊያፈነዳ ነው የሚል መረጃ የደረሳቸው የሻሸመኔ ቄሮዎች ይህን ወጣት በዚህ መልኩ ዘቅዝቀው ሰቅለውታል ። የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ከመታገል ይልቅ አጉል ጀብደኝነትን ማሳየት የወረደ ስራ ነው። መግደል መሸነፍ ነው። አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ ገጠር ፓለቲካ ሀላፊው በኦሮምኛ እንደገለፁት በሻሸመኔ የተቃጠለው መኪና የከተማው አስተዳደር እንደሆነ ገልፀዋል ። ስለሚባለው ቦንብም ፓሊስ ያገኘው መረጃ የለም እያጣራ ነው ብለዋል ። እንዲሁም የሻሸመኔን ወጣት ተረጋጉ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ። #MinilikSalsawi
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፓርቲ ለመመሥረትና አፍርሶ ለመስራት የጠቅላላ ጉባዬ ወጪ የሚሸፈነው በወያኔ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ዋና መምሪያ መሆኑን የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ ይፋ ሆነ።

የነውረኛው አየለ ጫሚሶ ጉድ. . . በአቻምየለህ ታምሩ ነውረኛው አየነ ጫሚሶ ለፋሽስት ወያኔ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ዋና መምሪያ በ2004 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ወጪ በመዘርዘር የደኅንነት መስሪያ ቤቱ የጠየቀውን ገንዘብ እንዲለቅለት በእጁ ጽፎ በፈረመው ደብዳቤ ጠይቋል! ነውረኛው አየለ «የደኅንነት መስሪያ ቤቱ አብሬው እንድሰራ ባያስገድደኝ ኖሮ ከኢሕአዴግ ጋር አብሬ መስራት አልፈልግም ነበር» ብሏልም!
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጅቡቲያውያን ኢትዮጵያውያን የግድያና ከሃገር የማባረር ዘመቻ ጀምረዋል ፤ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል።

ጅቡቲያውያን ኢትዮጵያውያን የግድያና ከሃገር የማባረር ዘመቻ ጀምረዋል ፤ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። የኢትዮ ኤርትራን ስምምነት ተከትሎ ጥቅማችን ቀረ ብለው የተበሳጩት ጅቡቲያውያን በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የተነሳውን ቀውስ በድሬዳዋ የተገደሉትን ጅቡታውያን ተንተርሰው ኢትዮጵያውያን ላይ የግድያና ከሃገር የማባረር ዘመቻ ባለፉት ሶስት ቀናት ጀምረዋል። የዓይን እማኞች እንደሚናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ የበቀል እርምጃ ወስደዋል። ምሽትን ተገን በማድረግ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማቁሰላቸውና ስድስቱን መግደላቸው የታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያውያን ንብረት የሆኑ ሱቆችን ማውደማቸው ሲታወቅ ፖሊስ እያየ ዝም ማለቱን እማኞቹ ይናገራሉ።   በድሬዳዋ ነዋሪ የሆኑ ጅቡቲያውያን ሲገደሉ እንደፈነዳ የሚነገርለት ይህ ዓመጽ መነሳቱን ተከትሎ በርካቶች በተለይ የኦሮሞ ተወላጆች ኢትዮጵያውን መፈናቀላቸው ንብረታቸው መዘረፉና መቃጠሉ ሲታወቅ ተጎድተዋል ተገድለዋል። ጅቡቲ ወደ ሁለት ሺህ ዜጎቿን ከድሬዳዋ አስወጥታለች። በሶማሌ ክልል የርእሰመስተዳደሩን ከስልጣን መባረር ተከትሎ በድሬዳዋ የሚኖሩ ደጋፊዎቻቸው መጤ ባሏቸው ሕዝቦች ላይ ግድያ ፈጽመዋል። #Miniliksalsawi
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰላም አስተማማኝ እየሆነ ነው ሲሉ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰላም አስተማማኝ እየሆነ ነው ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰላምን አስተማማኝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አመራሮችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰላሙን ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ ሰፊ ምክክር ማድረጋቸውንና ከመግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም የክልሉ ሰላም ወደ ቀድሞው ይዞታ መመለሱን ተናግረዋል፡፡ የሰው ህይወትና ንብረት መጥፋቱ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የሶማሌ ክልል የመገንጠል ጥያቄ አንስቷል ተብለው ለቀረበላው ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ እንደ ዛፍ ፍሬ የሚገነጠል አይደለም፣ ግለሰቦች የፈጠሩትን ችግር መስመር ለማስያዝ እየተሰራ መሆኑን ለመገናኛ ብዙኃን ዛሬ ተናግረዋል፡፡ ebc
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ወሎ ወልዲያ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ ( የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ )

በሰሜን ወሎ ወልዲያ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል። የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በ145ኛ ልዩ መግለጫ የተመለከተው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የተፈጸሙትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ሲሆን የመብት ጥሰቱ የተፈጸመው ከሕዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 04 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ነው። ሰመጉ ባለሙያዎቹን ወደ አካባቢው ልኮ የማጣራት ሥራውን የሰራው ከየካቲት 05 እስከ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወልደያ ከተማ፣ ወልደያ ዙሪያ ወረዳ፣ ቆቦ፣ ሮቢት፣ መርሳ፣ ውርጌሳ እንዲሆም በደቡብ ወሎ ደሴ የተፈጠሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርምሮ በዚህ መግለጫ አካቷል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተሰነዘሩ17 ዜጎች እንደጠፋ እና የአካል ጉዳት እንደደረሰ ሪፖርቱ በምስል አስደግፎ አቅርቧል። 1. ሟች መምህር ታምሩ በሪሁን፡- ዕድሜ 42፣ በፌደራል ፖሊስ በጥይት የተገደለ። 2. ሟች ተማሪ ዮሴፍ እሸቱ፡- ዕድሜ 15፣ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች በጥይት የተገደለ። 3. ሟች ገብረመስቀል ጌታቸው፡- ዕድሜ 35፣ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች በጥይት የተገደለ። 4. ሟች ወ/ሮ ዝይን ንጋቴ፡- ዕድሜ 60፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭንቅላታቸውን በጥይት ተመተው የተገደሉ። 5. ሟች ንጉሴ አበበ፡- ዕድሜ 18፣ በታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ግራ ጎኑ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ። 6. ሟች ህጻን ዳንኤል ካሳ፡- ዕድሜ 9፣ ታጠቁ የመንግስት ኃይሎች ጀርባው ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ። 7. ሟች ሰይድ ፍሬው ፡- ዕድሜ 31፣ በታጠቁ የመንግስት
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሶማሌ ክልል በሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም የሚመራ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ ።

ከኢፌዴሪ መከላከያ ሃይል ከፌደራል ፖሊስ እና ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ በዛሬው እለት የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እና ሌሎች የፀጥታ ሃይል አዛዦች በተገኙበት በጂግጂጋ ከተማ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ለክልል ሰላም በትብብር እና በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል። ዋና አዛዡ እንደተናገሩት የፀጥታ ሃይሎቹ ክልሉን ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ በመከላከያ ሰራዊት ዕዝ ስር ሆነው እንዲሰሩ ተወስኗል። የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ለክልሉ ሰላምና ደህንነት በጋራ የሚሰራ መሆኑንም ዋና አዛዡ ተናግረዋል። FBC  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዱከም በዜታ ኮንስትራክሽን ስም በተመዘገቡ 20 ኮንቴይነሮች ውስጥ የተከማቹ ፈንጂዎች ተያዙ ።

ከዚህ በታች በፎቶ ላይ የሚትመለከቷቸው ቤቶች የመኖሪያ ቤቶች እንዳይመስላችሁ የእቃ ማከማቻ ኮንቲኔሮች ናቸው ። ብዛታቸው 20 ንብረትነቱ ደሞ የአቶ ማርቆስ ሀዱሽ ገዛ የተባለ ሰውዬ “ዜታ ኮንስትራክሽን” በተባለው ድርጅታቸው ስም ተመዝግቦ ዱካም ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ፤ ዛሬ በኮንቲኔሮቹ ላይ በተካሄደው “ድንገተኛ ፍተሻ” ሙሉ ፈንጂ ተከማችቶበት በመገኘቱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። (Esmael DawedEnderis)
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከባህር ማዶ የተመለሱ የተቃዋሚ መሪዎችና ግለሰቦች የሆቴልና የመጓጓዣ ወጪ መንግስትን እየፈተነ ነው

ዋዜማ ራዲዮ- ቀደም ሲል ወደ ሀገር ቤት የገቡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጉዳይ አስፈፃሚዎችን በዓየር ለማጓጓዝ ለሆቴልና ትራንስፖርት መንግስት ዳጎስ ያለ ወጪ ማውጣቱ ተሰምቷል። ለግለሰቦቹ የየዕለት የሆቴል መስተንግዶና ሌሎች ወጪዎች ከዕለት ዕለት እየናረ መምጣቱን የሚናገሩት የመንግስት የሰራ ሀላፊዎች ወጪው ለሀገር ሰላምና ዕርቅ ሲባል የሚከፈል በመሆኑ ጉዳዩን መንግስት በሆደ ሰፊነት ሲመለከተው ቆይቷል። አሁን ግን የወጪው መናር ያሳሰባቸው ሆቴሎች መንግስት ክፍያ እንዲፈፅም መጠየቃቸውንና እየቀረበ ያለው የገንዘብ መጠን አነጋጋሪ መሆኑን ለዋዜማ ቅርብ የሆኑ የአዲስ አበባ ምንጮች ነግረውናል። የገንዘብ ወጪውንና ምን ያህን እንግዶች በመንግስት መስተንግዶ እየተደረገላቸው እንደሆነ የጠየቅናቸው ምንጫችን ሆቴሎች ሀገራዊ ፋይዳውን በመረዳት ቅናሽ ቢሰጡንም ተሰተናጋቾቹ በርካታ እንግዶች የሚጎበኟቸው በመሆኑና የቢሮ አገልግሎት የሚጠቀሙም ስላሉ ወጪውን ከፍ ማድረጉን ያስረዳሉ። የገንዘቡን መጠን መናገር ግን እንደማይደፍሩ ነግረውናል። አሁን ቢያንስ ሀምሳ ሁለት ያህል እንግዶች በመንግስት እየተሰተናገዱ ሲሆን ከሶስት ወር እስከ አንድ ሳምንት የቆይታ ዕድሜ አላቸው። አንዳንዶቹ ለጊዜው ከሆቴል ውጪ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ይቆዩና ተመልሰው እንደሚመጡ አንዳንዶቹ ደግሞ አዲስ አበባ ቤተሰብ ስለሌላቸው በቋሚነት የሆቴሉ እንግዶች ሆነው ቀጥለዋል። የፀጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውም ሆቴል መሆኑን እንደሚመርጡ ተሰምቷል። በተያያዘ ዜና ከሰሞኑ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች መንግስት ለጉዞና ለሆቴል ወጪያቸውን ለመሸፈን ያቀረበላቸውን ግብዣ ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ስምተናል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በአሜሪካ በነበረው ውይይት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በአንድ አውሮፕላን መመለስ እንደሚችሉ የተነገራቸው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሶማሌ ክልል ጥቅማቸው የቀርባቸው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች በተለይም ካቢኔው በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ ነው።

ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አሳሳቢ መረጃ (ዮናታን ተስፋዬ) በአሁኑ ሰዓት መከላከያ አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ከሀገር ሽማግሌዎች እና ተቆርቋሪ ዜጓች ጋር እየሰራ ቢሆንም – ጥቅማቸው የቀርባቸው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች በተለይም ካቢኔው በህዝቡ ላይ (መጤ ወይም ደገኛ በተባለው ህዝብ ላይ) ሽብር እየነዙ ነው። በሶማሊኛ ቋንቋ የሚተላለፈው ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እስካሁን በአብዲ ኢሌ ካቢኔ እና ዘመዶች ቁጥጥር ውስጥ በመሆኑ በህዝብ ላይ ከፍተኛ የሽብር ፕሮፖጋንዳ ከፍተው እያወኩ ነው። ከዚሀም የተነሳ ከ10 ሺህ በላይ ‘ደገኞች’ ክልሉን ለቀው በመውጣት ላይ ሲሆኑ – በአንዳንድ ቦታ በቴሌቪዥን ጣቢያው በሚተላለፈው ፕሮፖጋንዳ የተነሳ የተደራጀ ማፈናቀል እየተካሄደ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች የፌደራል መንግስት ሚዲያውን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ኃላፊነት በሚሰማው ሰው እንዲሰራ ጥሪ እያቀረቡ ነው።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የምሁራን ሚና ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኀረ ምረቃ ክፍል ዳይሬክተር ከሆኑት ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጋር ያደረገው ቆይታ

የምሁራን ሚና *** (በሪሁን አዳነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኀረ ምረቃ ክፍል ዳይሬክተር ከሆኑት ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጋር ያደረገው ቆይታ) ………………………… ከምሁራን የሚጠበቀው ኀላፊነት ምንድነው? ……………………………… ፕ/ር በቀለ፡- ትምህርት መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ ትምህርት ደግሞ ሰውን እንዲጠይቅና እንዲመረምር ማስቻል አለበት፡፡ “ያለንበት ሁኔታ ምክንያታዊ ነው ወይ? ያለንበት ሁኔታ ተቀባይነት አለው ወይ? ወዘተ. የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተሳሰቦችን የማመንጨት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ኅብረተሰቡን ለማገልገል ተቋማት የተቋቋሙለትን ዓላማ እየፈጸሙና እያስፈጸሙ ነው ወይ? አኗኗራችን ለእኛ ተቀባይነት ያለው ነው ወይስ ከላይ ነው የተጫነበን?” የሚሉትን ጥያቄዎች የመጠየቅ ጉዳይ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ጉዳይ እኛ ብዙ ጊዜ የምንወቀስበት ነገር ነው፡፡ በእኔ ግምት ወቀሳውም አግባብነት አለው፡፡ በዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያለነውም ሆነ ሌላው የኅብረተሰብ ክፍል ዝምታን ነው የምንመርጠው፡፡ ዝምታው ደግሞ ከፍራቻ የተወለደ ነው፡፡ መንግሥት ዜጎች በነጻነት የሚሠሩበትን ሁኔታ ስለማይፈጥር ኅብረተሰባችን በፍራቻ የታጠረ ነው፡፡ ዝምታውና ፍራቻው ግን ተገቢ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን ከምሁራን የማይጠበቅም ነው፡፡ በእርግጥ በምሁራኑ ላይ መፍረድ ትንሽ ያስቸግራል፡፡ በአንድ በኩል የመኖርና የመሥራት ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን አካሄዱ ማንኛውንም ዓይነት ችግር ተቀብሎ የመኖርን ሁኔታ ስለሚፈጥር በጣም አደገኛ ነው፡፡ በመሠረቱ ዝምታ ብልህነትም አይደለም፤ ደፋርነትም አይደለም፡፡ ለአገርም ሆነ ለራሱ ለምሁሩ የሚበጀው አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ በአፍሪካም ደረጃ ያየን እንደሆነ ብዙ ለውጦች ታይተዋል፡፡ ከቅኝ አገዛዝ ማብቃት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተስፋና መነቃቃት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በብዙ የአፍሪካ አገራት የተከሰተው መንሸራተት በምሁራኑ ላይ ከፍተኛ በትር ነው ያሳረፈው፡፡ በአገራችንም ብናይ ለምሳሌ ይህን ዩኒቨርሲቲ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአፋር ሁለት ሐይሎች ጎራ ፈጥረው ተፋጠዋል፡፡

ለ27 አመታት ተዳፍኖ የቆየ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ህዝቡ ይጠይቃል ነገር ግን ምላሽ ሠጭ አካል የለም፡፡ ህዝቡ ለመሆን ይጥራል ነገር ግን እንዳይሆን የሚፈልግ አካል ከአናቱ ተቀምጧል፡፡ አናቱ በማይድን በሽታ ተለክፈዋል፡፡ ግን ላይዲን ግማቱ ገምተዋል፡፡ የዘመናት ጥያቄ እንዳይመለስ የበላዮቹ ተፅዕኖያቸውን የቀጠሉ ሲሆን ጠያቂዎች ግን ከመጠየቅ ሳይታክቱ የወጣቱ ክፍል እየጠየቀ ነው፡፡ አሁን በአፋር ሁለት ሐይሎች ጎራ ፈጥረው ተፋጠዋል፡፡አንዱ የ27 አመት አሮጌ ስርዓት ይዞ ለመቀጥል፡፡ ሁለተኛው ግን አዲስ ትውልድ በመሆኑ አዲስ ነገር ማየት ፈልጎ ራሱን መሆን ይፈልጋል፡፡ማንነት ደግሞ ከሁሉም ቀዳሚ ነው፡፡ አሁን በነጋዴው በለውጥ ፈላጊ መካከል ቀዝቃዛ ጦርነት ተከፍቷል፡፡ እሳቱ ላይጠፋ ተያይዞ መንዳድ ግን አልቻለም፡፡ መንስኤው ደግሞ አለቃ ተብየው እጃዙር መአቀብ በማድረግ የወጣቱን ጥያቄ ለማክሸፍ እየሞከረ በመሆኑ፡፡ ብዙዎቹ የወጣቱ ክፍል የመንግሥት ደሙዝ ጥገኛ በመሆኑን የእለት እንጄራውን ላለማጣት መብቱን ማስከበር ተስኖት አጎብዳጅ ሁኖዋል፡፡ ጥቂት ቁራጦች ግን ለመቀቡ እጅ ላይሰጡ ፡ ለርካሽ ጥቅም ላያጎበድዱ ቃል ተገባብተው የትግሉ ፊታውራሬ ሁናዋል፡፡ ለማንኛውም አሁን ሜዳው ከሁለት ጎራ ሁነዋል፡፡ አንዱ ክንፍ ምንም አይነት ለውጥ አያስፈልግም በዚህ እንቀጥል የሚለው አብዴፓ እና አይሆንም ልክ እንደጎራቤቶቻችን ለውጥ ያስፈልገናል አዲስ ፊት እንፈልጋለን ማንም ይምራን አዲስ አመራር እንፈልጋለን የሚለው ወጣቱ ዱኮሂና ሌላኛው የለውጥ ናፋቂ ቡዱን ነው፡፡ ይህ ክፍል ለአገር ተስፋ፡ የነገ ጉልበት የሆነው አገር ተረካቢ የተማረ ወጣት ክፍል የያዘ ሐይል ነው፡፡ አሁን ፍጥጫው ተጧጡፏል፡፡ አብዴፓ ውድቀቱን ላለማያት ምሎ ተነስተዋል፡፡ አዲስ የካቢኔ ድልድል አድርገዋል፡፡ጥያቄው ግን አዲሱ ለውጥ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የደገሃቡር ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት እንዲሰማራላቸው ጠየቁ

የደገሃቡር ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት እንዲሰማራላቸው ጠየቁ $bp("Brid_41909_5", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-2063657920332740.mp4", name: "የደገሃቡር ከተማ ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት እንዲሰማራላቸው ጠየቁ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/FB_IMG_1533376507858.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዴሞክራሲ፤ እንዴት? ( አሸናፊ ሞላ )

ዴሞክራሲ፤ እንዴት? *** አሸናፊ ሞላ *** በአገራችን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ተፈቅዷል ከተባለበት ከ1984 ዓ.ም. ጊዜ ጀምሮ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች ተቋቁመዋል፤ ከተቋቋሙት ድርጅቶች መካከል በርካቶች ይህ ነው የሚባል ተግባር ሳይፈፅሙ፣ ሕዝብም ከነመኖራቸው ሳያውቃቸው ሞተዋል፤ የቀሩት በየጊዜው እየተሰነጣጠቁ በከፍተኛ ደረጃ ተዳክመዋል፡፡ ይኹን እንጂ አሁንም አዳዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች እየተቋቋሙ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ አሁን ከምንገኝበት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ እንድንወጣ እና የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል እንድንገነባ ካስፈለገ በተለመደውና በኖርንበት መንገድ መቀጠል እንደማንችል፤ የሚያስፈልገን ከላይ ከማዕከል ወደታች የሚንቆረቆር ሳይሆን ከታች ወደላይ እየተገነባ የሚሄድ የፖለቲካ ዘይቤ እንደሆነ፣ ይህን ለማድረግ የሚያስችለን አደረጃጀት ደግሞ ፓርቲ ሳይሆን ንቅናቄ ስለመሆኑ ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡ በጽሑፉ የመጀመሪያ ክፍል የፖለቲካ ፓርቲና የንቅናቄን ምንነት በአጭሩ ካስታወስኩ በኋላ፣ ለጠቅ አድርጌ ለምን ንቅናቄ እንደሚያስፈልገን እና ንቅናቄዎቹ በምን መልኩ ሊደራጁ እንደሚችሉ (እንደሚገባ) የተወሰኑ ነጥቦችን እሰነዝራለሁ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲንና የንቅናቄን ልዩነትና ተመሳሳይነት በሚመለከት አንድ ሁሉን የሚስማማ ብያኔ መስጠት ባይቻልም፣ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል “የፖለቲካ ፓርቲ ለፖለቲካ ሥልጣን የሚታገል፣ በሕግ የተመዘገበ እና ከሞላ ጎደል ተቀራራቢ የፖለቲካ አስተሳሰብና ዓላማ ያላቸው ዜጎች ስብስብ ነው፤” የሚለውን ብያኔ እንደመነሻ እንጠቀም፡፡ ማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ለፖለቲካ ሥልጣን ከመወዳደሩ በፊት ይብዛም ይነስም የራሱ የሆነ፣ ብመረጥ አስፈጽመዋለሁ የሚለው ፕሮግራም ይኖረዋል፡፡ ፓርቲው ይህን የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለሕዝብ በማስተዋወቅና ሕዝብ እንዲቀበለው በማድረግ፣ ይልቁንም ከሌሎች ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ሲወዳደር የእሱ ፕሮግራም የተሻለ እንደሆነ በማሳመን ለፖለቲካ ሥልጣን ይታገላል፡፡ አብላጫ ድምጽ አግኝቶ የመንግሥት ሥልጣን ከተረከበም ያቀረባቸውን የፖሊሲ አጀንዳዎች
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግራ አጋቢ ምክር በውጭ ጣልቃ ገቦች ( ጌታቸው አስፋው)

ግራ አጋቢ ምክር በውጭ ጣልቃ ገቦች ጌታቸው አስፋው (የብሔራዊ ኢኮኖሚ ዕቅድ ባለሙያ) *** ታዳጊ አገራት በቀጥታ ወደ ገበያ ኢኮኖሚ ሊገቡ ስለማይችሉ በቅድሚያ በኢኮኖሚ ልማት ራሳቸውን ማሳደግ አለባቸው ብለው ያማከሩት በገበያ ኢኮኖሚ ፍልስፍና ያደጉ ምዕራባውያን ናቸው፣ ከጊዜ በኋላ ሐሳባቸውን ቀይረው የመዋቅር ማሻሻያ ፕሮግራም ነድፈው ወደ ገበያ ኢኮኖሚ ግቡ ያሉትም እነሱው ናቸው፡፡ ከቅኝ ግዛት ማብቃት ጀምሮ እስከ ግሎባላይዜሽን በነበረው ጊዜ የእያንዳንዱ አገር ኢኮኖሚ ግንኙነት የተመሠረተው በኹለትዮሽ የአገራት ንግድ ስምምነት ላይ ስለነበረ፣ ታዳጊ አገራት ራሳቸውን ችለው በኢኮኖሚ ልማት ፍልስፍና ለአገራቸው የሚበጅ የውስጥና የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነት ቢያድጉ ምዕራባውያንን የሚጎዳቸው ነገር ስለሌለ አልተቃወሟቸውም፡፡ በግሎባላይዜሽን ዘመን ግን በሌላ አገር ጥሬ የተፈጥሮ ሀብት ለማደግ የንግድ ትስስር መፍጠርና በሌላ አገር ርካሽ ጉልበት ለመጠቀም በውጭ አገር መዋዕለንዋይ ማፍሰስ ተፈልጎ ምዕራባውያን መንግሥታት በዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ተጽዕኖ ታዳጊ አገራት የገበያ ኢኮኖሚን እንዲከተሉ ግፊት አደረጉ፡፡ የውስጥና የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነት ፖሊሲያቸው የዓለም ዐቀፍ ንግድን እንዳያደናቅፍ ብለው ከለከሏቸው፡፡ ለአገራቸው ከማሰብ ይልቅ ለዓለም እንዲያስቡ መከሯቸው፡፡ የመዋቅር ማሻሻያ ፕሮግራም ወይም አንዳንዴ እንደሚጠራው የዋሽንግተን መግባቢያ ስምምነት ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ለታዳጊ አገራት በሚሰጡት ብድርና እርዳታ ወደ ገበያ ኢኮኖሚ ለማስገባት በቅድመ ሁኔታነት እንዲያሟሉ የነደፉት ፕሮግራም ነው፡፡ ይህን ፕሮግራም ብዙ ታዳጊ አገራት አልጠቀመንም ብለው ሲተውት፣ ዓለም ዐቀፍ ተቋማቱ ያልጠቀማቸው ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ስላላደረጉት ነው ይላሉ፡፡ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ብሔራዊ ኢኮኖሚውን ማረጋጋት እና ከግሎባላይዜሽን ጋር አብሮ ለመራመድ ለንግድና ለውጭ ኢንቨስትመንት በርን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮ ሶማሌ ክልል አስተዳደር የሕዝብ ተቋም ሳይሆን የማፊያ ድርጅት እንደሆነ ተገለጸ።

መታየት ያለበት ቃለ-መጠይቅ! ኢቲቪ ዛሬም እንደትላንቱ ሁለት የክልሉ ምሁራን ጀባ ብሎናል-አደም ፋራህና መስጠፋ ኡመር! ሙስጠፋ ኡመር ከዓመት በፊት ለምን ስለኔና ስለክልሉ ትፅፋለህ በማለት አራጁ አብዲ ኢሌ ታናሽ ወንድሙን ኢንጂኔር ፌይሰልን ከመኪና ላይ በመወርወር ገድሎበታል፡፡ ሙስጠፋም በአብዲ ኢሌ ካገራቸው ካሰደዳቸው ምሁራን መካከል ይገኝበታል፡፡አደም ፋራህም የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከአብዲ ኢሌ ጋር ባለመስማማታቸው ስልጣናቸውን ሊለቁ በቅተዋል፡፡ $bp("Brid_41805_6", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-525105341275616.mp4", name: "የኢትዮ ሶማሌ ክልል አስተዳደር የሕዝብ ተቋም ሳይሆን የማፊያ ድርጅት እንደሆነ ተገለጸ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Ethiopia-somali-region.png"}, "width":"550","height":"309"}); እነዝህ ሁለት ምሁራን የክልሉ ችግር አስተዳደራዊ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡ ሰብአዊ መብት ጥሰት፣ አምባገነናዊነት በክልሉ ተባብሶ ይታይ እንደነበረ ይገልፃሉ፡፡ መግደል፣ ማፈናቀል፣ ግጭት መፍጠር ከሌላው በተለየ ሁኔታ የክልሉ አይነተኛ መለያ ባህሪ እንደነበረም አውስተዋል፡፡ ምን መደረግ አለበት? ለሚለው ሁለቱ ምሁራን የሚከተለውን ሀሳብ አቅርበዋል:: • ሕግና ሥርዓት ማስከበር፤ • የተዘረፉ ንብረቶች ማስመለስ • ወንጀል የፈፀሙትን ተጠያቂ ማድረግና ለህግ ማቅረብ፡፡ ለተጎጂዎች የፍትህ ሥራ መስራት! • የልማትና የዲሞክራሲ ችግሮችን መቅረፍ ይጠቀሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት እነዝህን የክልሉን ምሁራን በማማከር ክልሉ ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት የሱማሌን ሕዝብ መካስ ይኖርበታል፡፡ እስከአሁን ድረስ አብዲ ኢሌን የመሰለ አራጅና መሀይም ሕዝቡ ላይ በመጫን ለመናገር የሚከብድ በደል በሕዝብ ላይ ተፈፅሟል፡፡ ካለፈው ትምህርት ወስደን ለሚመሰረተው መንግስት የሱማሌ ሕዝብ ምርጫ እንድከበር እንጠይቃለን!
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤሌክትሪክ ታሪፍ በአራት እጥፍ ለመጨመር ማሰብ በበደል ላይ በደል ደሃውን መግደል ነው ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው።

 ምንሊክ ሳልሳዊ – የኤሌክትሪክ ታሪፍ በአራት እጥፍ ለመጨመር ማሰብ በበደል ላይ በደል ደሃውን መግደል ነው። ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው። ከካርታው የፖለቲካ ቁማር ይልቅ በደሀው ሕዝብ ላይ የሚጨመር የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ አሳሳቢ ነው። ለራሳችን ሳናውቅ ለጎረቤቶቻችን የምንሸተው የኤሌክትሪክ ፍጆታ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል። ይህ ችግር ፋብሪካዎችና ተቋማት ስራ ከማቆም ጀምሮ ሰራተኞችን አስከመበተን ዘልቋል። የተበተነው ሰራተኛ ቤቱም ሔዶ ኤሌክትሪክ የለውም ፤ በወር የኤሌክትሪክ ፍጆታውን እንደተጠቀመ ሰው ግን የደሃ ገንዘቡን በመንግስት ይነጠቃል። ይህ አደገኛ አካሔድ መንግስትን ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም። የኤሌክትሪክ ፍጆታን በአራት እጥፍ መጨመር ማለት አብዛኛው ደሃ በሆነባት ሃገር ውስጥ በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል ይሆናል። ኢትዮጵያ ከጎረቤትም ሆነ ከሌሎች ሀገራት ለኤሌክትሪክ ኃይል የምታስከፍለው ታሪፍ አነስተኛ ስለሆነ ይህንን ደሃ ሕዝብ መብራት በማሳጣት ብቻ ሳይሆን ታሪፍም በመጨመር ማማረር ያስፈልጋል የሚል አቋም የያዘው መንግስት ለጎረቤት ሃገራት በርካሽ እየሸጡ ለዜጎች ሲሆን ሀገሪቱ አሁን እያስከፈለችው ባለው ታሪፍ ጥራቱን የጠበቀ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ የማይቻል ነው በማለት አቅርበው የማያውቁትን ጥራት ሰበብ በማድረግ በፖለቲካና በኢኮኖሚ የደቀቀውን ሕዝብ ሊያሰልሉት እያሟሟቁ ነው። ዜጎችን በጨለማ እያሳደሩ ለጎረቤት አገሮች ኤሌክትሪክ በመሸጥ ገንዘቡን በሙስና የሚቀራመቱ መሆኑን በተደጋጋቢ ተሰምቷል ፤ ካሁን ቀደም የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመብራት ሃይል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ አስናቀ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ጀርመን አገር በሚገኝ ባንክ ማስቀመጣቸው የሲአይኤ ሰነድ ዋቢ አድርገው አምባሳደር ያማማቶ ለዶክተር አብይ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፔይኒ ሞርዳንት ጋር ተወያዩ

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፔይኒ ሞርዳንት ጋር ተወያዩ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክብር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የእንግሊዝ ዓለምአቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዲ.ኤፍ.አይ.ዲ) ሃላፊ የሆኑት ፔይኒ ሞርዳንትን ዛሬ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ የውይይቱ ማጠንጠኛ በኢኮኖሚ እና በድህነት ቅነሳ ዙርያ ላይ ያደረገ ነው፡፡ ፔይኒ ሞርዳንት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ለውጥን አድንቀው የሚመሩት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክር ገልፀዋል፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ኢትዮጵያዊ”፤ “ኢትዮጵያዊት” የሚል ዲጅታል መታወቂያ ሊሰጥ ነው

ብሔር ከመታወቂያ ላይ ሊነሳ ነው በቀበሌ መታወቂያ ላይ ብሔር እንዲጠቀስ ለምን ተፈለገ? የህጋዊነቱስ ጉዳይ? Aerial view of the Addis Ababa መስከረም 15/2010 ዓ.ም የእንግሊዙ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (BBC) በአማርኛ ዜና ትንታኔው ላይ እንዳቀረበው የምስል መግለጫ መታወቂያ ላይ” ብሔር” የሚለውን ለማስተካከል ረጅም ጉዞ የተጓዘው ያሬድ ሹመቴ በሚል ርዕስ ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሞያ ያሬድ ሹመቴ ያደረገውን ጥረት በሰፊው አትቷል፡፡ እንደ BBC ዘገባ ከሆነ ያሬድ ሹመቴ ይህንን ጥረቱን ከስምንት ወራት በፊት የጀመረው ቢሆንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ አቋርጦት ከቆየ በኋላ አሁን ግን አቤቱታውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ገልጧል፡፡ ይህም ከአንድ ያገባኛል ከሚል ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ያሬድ ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ማበረታታት ይገባናል፡፡ የብሔር ጉዳይ በመታወቂያ ላይ መኖር አለመኖር ጋር ተያይዞ እኔም በውስጤ ይብላላ የነበረ ሀሳብን ያሬድ ሹመቴ በግልጽና በድፍረት አንስቶ ለመገናኛ ብዙሀን እንዲደርስ ማድረጉ በእጅጉ ደስ ስላሰኘኝ የእሱንም ሆነ የእኔን አተያይ ለፌስቡክ ወዳጅ ዘመዶቼ በማጋራት ይዞት የተነሳው ሀሳብ የውይይት ርዕሰ ጉዳይ እንዲሆን ፈለግሁና ቀጥሎ በሚገኙት አንቀፆች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ በ BBC ድረ ገጽ ላይ የሰፈረውን የያሬድ ሹመቴን አስተያየት በማጣቀስ ጭምር ትንሽ ነገር ማለትን ፈለግሁ፡ እርግጥ ነው ባለፉት 26 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ከቀድሞው በተለየ ሁኔታ በጥቅሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለው አባባል ቀርቶ ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ ብሎ መጥራት በእጅጉ እየተለመደ መጥቷል፣ በሽግግር ወቅት ቻርተር እና በአዋጅ ቁጥር 7/1984 ላይ የተጀመረው የብሔር-ብሔረሰብ ጽንሰ ሀሳብ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአብዲ ኢሌ ቀኝ እጆች ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ ፤ ለቀማው ቀጥሏል።

የአብዲ ኢሌ ቀኝ እጆች ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ ፤ ለቀማው ቀጥሏል። የአብዲ ኢሌ የሚዲያ አማካሪና የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ። ከስልጣን አልወርድም በማለት ከፍተኛ የሃገር ክሕደት የፈጸመው አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ የሚዲያ አማካሪው የነበረው መሃመድ ቢሌ ድሬዳዋ ውስጥ ከተሸሸገበት በቁጥጥር ስር ውሏል።ግለሰቡ በተጨማሪ የሙያና ቴክኒክ ስልጣና ኃላፊ ሆኑ ክልሉን ያገለግላል። በተጨማሪም የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊና በድሬዳዋ የአብዲ ኢሌ ወኪል ሞሃመድ አሕመድ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል። ግለሰቦቹ የሶማሌን የሃገር ሽማግሌዎች በመግደልና በማሰር የሚታወቁ ሲሆን የውጪ ምንዛሬም በኮንትሮባንድ በማመላለስ የ አብዲ ኢሌን ትእዛዝ የሚያስፈጽሙ ቀንደኛ ወንጀለኞች መሆናቸው ታውቋል። ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸው አፈናንና ግድያን በድሬዳዋና በ አከባቢው ማስፈጸማቸው ማስረጃ መንግስት ስላገኘባቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተጨማሪም የቀድሞ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የ አሁኑ የልማት ፕሮጄክት Pastoral Community Development Project (PCDP) ኃላፊ አብዲሃኪን ኤግል ቤቱ የተበረበረ ሲሆን እስካሁን የተሸሸገበት ባለመገኘቱ የደሕንነትች እያሰሱት ይገኛል። RAJO NEWS Arrests and house searches made in Dire-Dawa – We are getting reports from reliable sources that Mohamed Bille “Miig”, head of Technical and Vocational Training (TVeT) and Media Advisor to former regional president Abdi Iley is arrested today in Dire-Dawa. – The house of Abdihakin Egal was searched. Mr. Abdihakin was former VP and now the current head Pastoral Community Development Project (PCDP). – Mohamed Ahmed, Diredhaba Security
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት የደሕንነት ሹም የነበረው የጌታቸው አሰፋ የተደበቁ ጉዶች ሲጋለጡ

የጌታቸው አሰፋ የተደበቁ ጉዶች ሲጋለጡ የቀድሞው የብሔራዊ የደህንነት መስሪያቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ በስልጣን ዘመኑ እጅግ አስቸጋሪና እጅግ ክፉ ሰው እንደነበረ ሁሉም ሰው ይገልፀዋል። ስልጣኑን እና የተሰጠውን ሀገራዊ ሀላፊነት ከልክ እና ከአግብ በላይ የሚጠቀም ዘረኛና ሸረኛ ሰው ነበር። ለዚህም የሚከተሉትን በማሳያነት መጥቀስ ተገቢ ይሆናል። <1> የፌዴራል መንግስት የሀገሪትዋን የጦር መሳርያ ለማዘመን የተለያዩ ዘመናዊና ውድ የሆኑ መሳርያዎችን ከውጭ በማስመጣት በየካምፑና በየመጋዘኑ እንዲቀመጥ ያደርጋል። ይህን ያየው የደህንነት ሀላፊ የነበረው አቶ ጌታቸው ከስነ-ምግባርና ከህግ ውጪ የሚበቃውን ያህል በማውጣት ለትግራይ ክልል ፓሊስ ለመስጠት ወደ ትግራይ ክልል ይዞ ይሄዳል። ሆኖም በሚያስደንቅና እጅግ ሊያስመሰግን በሚችል ሁኔታ የትግራይ ክልል የፀጥታ ቢሮ ግን ከሌሎች ክልል ፖሊሶች ተለይተን እኛ ብቻ እጅግ የዘመነ መሳርያ መያዝ የለብንም ብለው አንቀበልም በማለታቸው ይህ ዘመናዊ መሳርያ በቅርቡ ወደ የጋዘን እንዲገባ ተደርጉዋል። እዚህ ጋር የትግራይ ክልል ፖሊስን ሀቀኝነት እና ሀገር ወዳድነት ሳያደንቁ ማለፍ ነውር ነው። የጌታቸው አሰፋን ርካሽ ዘረኝነት እና ሀላፊነት የጎደለው ሶራ በማኮላሸታቸው ክብር ይገባቸዋል። <2> በቅርቡ የተዘጋው ENN ቴሌቪዥን እና Zami FM በዚሁ በደህንነት ቢሮ ሀላፊው በአቶ ጌታቸው አሰፋ እጅግ የተጋነነ እና ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ ሲደረግላቸው እንደነበር ተደርሶበታል። አዎ ብታምኑም ባታምኑም ለENN ቴሌቪዥን ብቻ በወር 1ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲሆንለት ያደርግ እንደነበር ተጨባጭ ከባንክ የተገኙ ሰነዶች ያስረዳሉ። Zami FM’ም እንዲሁ ለግዜው መጠኑ ያልታወቀ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲገባላቸው ሲያደርግ የነበረ መሰሪ ሰው ነው። እግዜር ያሳያችሁ፣ ENN
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዐቃቤ ሕግ “ክሳቸው ተቋርጦ ይፈታሉ” ያላቸውን የፖለቲካ እስረኞች ሊያስፈርድባቸው ነው!

ዐቃቤ ሕግ “ይፈታሉ” ያላቸውን የፖለቲካ እስረኞች ሊያስፈርድባቸው ነው! የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፖርላማው በወሰነው መሰረት በሽብር የተከሰሱትን ክስ እንደሚያቋርጥ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል። የተፈረደባቸው ደግሞ በምህረት አዋጁ መሰረት ይፈታሉ ተብሎ ነበር። ሁሉም ግን አልተፈቱም። ከ80 በላይ በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱ፣ እንዲሁም በኦነግ የተከሰሱ፣ በአጠቃላይ ከመቶ በላይ በአርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ የተከሰሱ በእስር ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ ተከሳሾች ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ነው። በእስር ላይ ይገኛሉ። እነ ገብሬ ንጉሴ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። በእነ ገብሬ ንጉሴ ክስ መዝገብ 14 ሰዎች ተከስሰው ነበር። 9ኙ “በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ፈፅመናል” ብለው ስላመኑ እስከ 16 አመት ተፈረደባቸዋል። የተፈረደባቸው ከወር በፊት ሲፈቱ ገብሬ ንጉሴ፣ ጌትነት ዘሌ፣ ሻንቆ ብርሃኑ፣ ተሻገር መስፍን እና ሰጠኝ ጎባለ አሁንም በእስር ላይ ናቸው። ያልተፈቱት “የአርበኞች ግንቦት 7 አባል ነን፣ ነገር ግን በክሱ ላይ ተፈፀመ የተባለውን አልሰራንም” ብለው በመከራከራቸው መከላከያ ምስክር እንዲያመጡ ተቀጥሮባቸው ቂሊንጦ ቆይተዋል። የተፈረደባቸው ሲፈቱ በአንድ መዝገብ ተከሰው ያልተፈረደባቸው ግን “የሰው ህይወት አጥፍታችኋል አትፈቱም” ተብለዋል። ዛሬ! በተደረገው ጦርነት የሰው ህይወት መጥፋቱን አምነው “አድርገነዋል” ያሉት ተፈርዶባቸው ተፈትተዋል። በአንድ ክስ መዝገብ ተከሰው “አላደረግነውም” ያሉት ግን በእስር ላይ ይገኛሉ። ለነሃሴ 15/2010 ለውሳኔ ተቀጥረዋል። በተመሳሳይ በማዕከላዊ ብዙ ስቃይ የተፈፀመበት አስቻለው ደሴም “የምህረት አዋጁ አይመለከትህም” ተብሎ ሌላ ለውሳኔ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል። ክሱም አይነሳልህም ተብሏል። ዐቃቤ ሕግ ክሳቸው ተነስቶ እንዲሁም በምህረት አዋጁ ይፈታሉ ቢልም ይህን መግለጫ የሰጠው
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅጅጋ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በጅጅጋ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ ከሐያ ሰባት ሴቶች አንዷ በወሊድ ምክንያት ትሞታለች።

1 in 27 women die while giving birth in Ethiopia. pic.twitter.com/AIrSrmWW0E — Al Jazeera English (@AJEnglish) August 5, 2018 በኢትዮጵያ ከሐያ ሰባት ሴቶች አንዷ በወሊድ ምክንያት ትሞታለች። 1 in 27 women die while giving birth in Ethiopia.  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የጅግጅጋ ልጆች ኢቲቪ በር ላይ ተቃውሞ አድርገዋል

ኢቲቪ የጅግጅጋውን ጉዳይ እየዘገበ አይደለም። የጅግጅጋ ልጆች ኢቲቪ በር ላይ ተቃውሞ አድርገዋል ተብሏል!  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ሕወሓቶች ስለሕገመንግስት የማውራት ሞራል የላቸውም ፤ ሕወሓትን በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም እንቀጣዋለን።

ሕገመንግሥት ይከበር ያሉ ዜጎችን በአሸባሪነት ሲያስሩና ሲያሳድዱ የነበሩ ሰወች ስለሕገመንግስት የማውራት ሞራል የላቸውም ። ሕወሓትን በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም እንቀጣዋለን።(ምንሊክ ሳልሳዊ) ትላንት በተለያየ መንገድ ሕገመንግስቱ እንዲከበር የጠየቁ ዜጎች ላይ አረመኔያዊ ተግባር የፈጸሙ ያስፈፀሙና የደገፋ ዛሬ የመርሕ ሰው ሆነው ስለሕገመንግስት አፋቸውን ሞልተው መናገር ይፈልጋሉ። ዛሬ ሕገ መንግስት ይከበር የማለት ሞራሉን ከየት አመጡት ? ከ25 አመት በላይ ሐገሪቷ ፍትሕ አልባ ስትሆን የሚሰቀጥጡ ወንጀሎች እና መንግስታዊ ሽብሮች ሲፈፀሙ እዚሁ አብረውን ነበሩ ፤ እኛ ስንጮህ ራሳቸው ያወጡትን ሕግ እንዲያከብሩ ስንጠይቅ አሸባሪ ብለው ሲፈርጁን ነበር። አንድም ቀን ስለሕገመንግስትና ስለመንግስታዊ ሽብር ተንፍሰው አያውቁም ። ከባባድና አደገኛ የሕግ ጥሰቶችን ዝም ብለው እያየዩ ጥቅማቸው ሲነካ ስለሕገመንግስት ቢያወሩ የሚሰማቸው የለም። ከአደባባይ ግድያ እስከ ኢሰብአዊ ስቃይ ሲፈፀም ፣ በክልሎች ጣልቃ ገብነት ጀምሮ እስከ አደገኛ አፈናዎች ሲፈፀሙ ፣ የሕግ የበላይነት ሲደፈጠጥ ወዘተ ዛሬ ላይ ሕገ መንግስት ይከበር የሚሉ ሰወች ሕገመንግስቱን ሲጥሱ ሲያስጥሱና ገዳዮችን ሲደግፉ የነበሩ ጥቅመኞች ናቸው ።ትላንት ስላልቆሙለት ሕገመንግሥት ዛሬ ላይ ለማውራት ምንም ሞራል የላቸውም። ዜጎች በተለይ በአገር ውስጥ ያሉ ከሰላማዊ ሰልፍ ጀምረው እስከበይነ መረብ ዘመቻ ለሕገመንግስቱ ክብር እንዲሠጥ ጮኸዋል ። በምላሹ ከመንግስት የተሰጣቸው ዱላ እስር እና ስደት ነበር ፤ ዛሬ ላይ አሳሪዎች ገዳዮች ገራፊዎች ዘራፊዎችና ወዳጆቻቸው ለእኩይ አላማቸው ስለ ሕገ መንግስቱ ጠበቃ ሆነው ቆመዋል። እፍረት ያልፈጠረባቸው እነዚህ ድኩማኖችና የቀን ጅቦች በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም እንቀጣቸዋለን ። #MinilikSalsawi
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለውጥ ያስፈልጋል ካልን፣ የተለሳለሰ ለውጥ የሚባል ነገር የለም – የትግራይ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል – ሜ/ጀ አበበ ተ/ሃይማኖት

– ለውጥ ያስፈልጋል ካልን፣ የተለሳለሰ ለውጥ የሚባል ነገር የለም – ህዝቡ ከእንግዲህ በፀረ-ዲሞክራሲያዊ መንገድ አልገዛም ብሏል – የመንግስት ሚዲያዎች ትልቅ ስካር ውስጥ ነው ያሉት – ለውጥ አንፈልግም የሚሉትም ቢሆኑ ሃሳባቸው መሰማት አለበት – በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እንደ ዶ/ር ዐቢይ የገለፀ መሪ አላውቅም – የትግራይ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል አዲስ አድማስ የህወኃት አንጋፋ ታጋይና የቀድሞው የአየር ሃይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት፤ የኢትዮጵያን ህዝብ የትግል እንቅስቃሴ በመደገፍ ይታወቃሉ፡፡ ኢህአዴግ ራሱ ያፀደቀውን ህገ መንግስት እየጣሰ መሆኑን በመግለፅም ህገመንግስቱ እንዲከበር አበክረው ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡ ትክክለኛው ለውጥ የሚመጣው በወጣቱ ሃይል ነው የሚል ፅኑ አቋምና እምነት ያላቸው የፖለቲካ ምሁርና ተንታኝም ናቸው፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በታዩ የለውጥ ጅማሬዎችና በአጠቃላይ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታው ላይ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር ተከታዩን ጥልቅ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ እነሆ፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ እየታዩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን እንዴት ይመለከቷቸዋል? የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ይፈልግ ነበር። ኢትዮጵያ ውስጥ ፀረ- ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሁኔታ በጣም ነበር የሠፋው፤ ፍትህ የታጣበት፣ ሙስና የሰፋበት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ መብት የታፈነበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ ስለዚህ ለውጥ ያስፈልግ ነበር፡፡ ለውጥ ሁልጊዜ በተለያዩ ሃገሮች በተለያየ መንገድ ነው የሚመጣው፡፡ በሃገራችን በተለይ በእነዚህ 3 አመታት የነበረውን ሁኔታ ስናየው፣ ከሞላ ጎደል በህዝቡ ተነሣሽነት የመጣ ለውጥ ነው። እንዲህ ያለውን ለውጥ መሪ አልባ ለውጥ ወይም ማህበረሠብ- መር ለውጥ ልንለው እንችላለን።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓቱ ጄነራል አብረሃ አብዲ ኢሌ ያደራጃቸውን ልዩ ሀይል ለተደራጀ ዐመፅ እየመራ ይገኛል።

ሜጀር ጄነራል አብረሃ ወ/ማሪያም አብዲ ኢሌ ያደራጃቸውን ልዩ ፖሊስ/ሀይል ለተደራጀ ዐመፅ እየመራ ይገኛል በጅግጅጋ እና ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸው የሶማሌ ክልል ከተሞች ዘረፋ፣ ግድያ… ቤተ ክርስቲያን፣ ባንክ እና ሱቆችን ማቃጠል እየፈፀሙ የሚገኙት እና የሚመሩት ልዩ ሀይሎች/ፖሊሶች ኳርተር የተባለው ሜ/ጄ አብርሃ እንደሚታዘዙ ታውቋል። ከዚሁ ጄነራል ጋርም ኮለኔል ገብሬ ጨምሮ አምስት የሚደርሱ ኮለኔሎች ልዩ ፖሊስ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት እንዲገጥም እየገፋፉ እና እያመቻቹ ይገኛሉ። ሜ/ጄ አብርሃ ቴክኒካል እና ሎጀስቲክ ድጋፍ እያደረገ የሚመራው የአብዲ ኢሌ ልዩ ሀይል መከላከያ ላይ ተኩስ ከፍቷል ከከተማው ዳር በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ከአንድ ሬጅመንት የሚያንስ ወታደር በልዩ ሀይሉ ተከቦ ተኩስ ተከፍቶበት አካባቢውን እንዲለቅ እየተገደደ ነው። ልዩ ሀይሉ ከጄነራሉ በሚያገኘው ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቀ ነው። ጅግጅጋ አሁንም በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ጭስ ጭጋግ እንደተሸፈነች ሲሆን – ከከተማው ዳር የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ (ከድምፃቸው ሳይቀር) መገንዘብ ችያለሁ።  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ አዲስ አበባ በይፋ በረራውን ጀምሯል።

የኤርትራ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ በይፋ በረራውን ጀመረ የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ አዲስ አበባ በይፋ በረራውን ጀምሯል። በዚህ የመጀመሪያ በረራ የኤርትራ የትራንስፖርት እና የቱሪዝም ሚኒስትሮችን ጨምሮ የኤርትራ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ እና ሌሎች ባለስልጣናት አዲስ አበባ ገብተዋል። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ እና ሌሎች ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት ከኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 465 ሰዎችን የያዘ የህዝብ ለህዝብ ቡድን ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ አስመራ መሄዱ ይታወሳል፡፡ ምንጭ:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመንግስት ስር ያሉትን ትልቅ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፋ ለማዘዋወር የሚያደርገውን ሂደት ግልፅ እና ተጠያቂነት ባለበት መንገድ የሚከታተል ኮሚቴ ተዋቀረ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በመንግስት ስር ያሉትን ትልቅ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፋ ለማዘዋወር የሚያደርገውን ሂደት ግልፅ እና ተጠያቂነት ባለበት መንገድ የሚከታተል 21 አባላት ያሉት የአማካሪ ኮሚቴ እንዳዋቀሩ ከጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሀላፊው አቶ ፍፁም አረጋ ሰምተናል። የኮሚቴ አባላቱም ዝርዝር በምስል የተለጠፋት ናቸው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሶማሌ ልዩ ሃይል የሚፈጸመውን ጥቃት በመሸሽ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ መሰደዳቸው ታወቀ።

በሶማሌ ክልል ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ ተሰደዱ (ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 27/2010) በሶማሌ ልዩ ሃይል የሚፈጸመውን ጥቃት በመሸሽ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጅቡቲ መሰደዳቸው ታወቀ። ከትላንት ጀምሮ በደወሌ፣ አይሻና ሽንሌ ዞን የተሰማራውና በአብዲ ዒሌ የሚታዘዘው ልዩ ሃይል ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ህዝቡ በመሰደድ መጀመሩ ነው የተገለጸው። በጥቃቱም የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። የፌደራል ፖሊስ ህዝቡን ከልዩ ሃይሉ ጥቃት ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በድሬዳዋ በሶማሌ ክልል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የተዘጋጀውንና ከ1500 በላይ ሰዎች እየተሳተፉ ያሉበትን የሰላም ኮንፍረንስ ለማወክ የተደረገው ሙከራም መጨናገፉ ታውቋል። የሶማሌ ክልል ቀውስ ዳግም አገርሽቷል። ላለፉት ሶስት ወራት ያዝ ለቀቅ እያደረገ የዘለቀው ተቃውሞ ከትላት ጀምሮ በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች ተቀስቅሶ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ለማወቅ ተችሏል። ከትላንት ጀምሮ እየተካሄደው ያለው ተቃውሞ በተለይ አይሻ በተባለች ከተማ ላይ ጠንከር ያለ መሆኑ ተገልጿል። የከተማዋን ከንቲባ የአብዲ ዒሌ ታጣቂዎች ለመግደል ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን ተከትሎም ተቃውሞ መባባሱን የኢሳት ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ዘግይቶ በደረሰን ዜናም የአብዲ ዒሌ ሚሊሺያ ሀይል በህዝቡ በደረሰበት ተቃውሞ ከተማዋን ለቆ መጣቱ ታውቋል። አይሻ ላይ ባለው ውጥረት የተነሳም ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚኣገናኘው ዋናው መስመር ተዝግቶ ውሏል። በሽንሌ፣ በፍዴር፣ በሊበን፣ በሸበሌና በኤረር ዞኖች የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ ከስልጣን እንዲወርዱ በምጠየቅ ህዝቡ ዳግም የጀመረው ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። ከትላንት ምሽት ጀምሮም አቶ አብዲ ዒሌ የልዩ ሃይልና የሚሊሺያ ሰራዊታቸውን የተቃውሞ ማዕከል ወደ ሆነችው የሽንሌ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለሕወሓት ድህረገፆች ኢትዮቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት 1 ሚሊየን ብር ስፖንሰርሺፕ ተቋረጠ

ለዳንኤል ብርሃኔ ‘ሆርን አፊርስ’ ኢትዮቴሌኮም፤ ለዳዊት ከበደ ‘አውራምባ ታይምስ’ -የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት 1 ሚሊየን ብር ስፖንሰር ያደርጉ ነበር። አሁን ላይ ይህ እንደተቋረጠ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፣ የመንግሥት ኮሚኒኬሽንስ ሚኒስትር ዲኤታ ተናግረዋል Source: ODN
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በተሳሳተ መረጃ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነት እንደማይበላሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነት እንደማይበላሽ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነት እንደማይበላሽ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “የመደመር ጉዞ” የአሜሪካ ቆይታ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ቆይታቸው በዚያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች “እስልምናን ጥላለች” ብለዋል በሚል የወጡት ዘገባዎች ፍፁም ከእውነት የራቁ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ ያልተናገሩት መሆኑን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በመንግስትም ሆነ በመሪዎች ደረጃ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸውም አቶ መለስ አስታውቀዋል። በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የሚበላሽ አይደለም፤ ምንም የተለወጠ ነገር የለምም ነው ያሉት።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደንቢዶሎ በምጥ የተያዘችውን የገደሉት ለፍርድ አልቀረቡም።

በምጥ የተያዘችውን የገደሉት ለፍርድ አልቀረቡም ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ‘በምጥ ለተያዘች ነፍስ ጥይት?!’ በሚል ርዕስ በዚሁ ማሕበራዊ ገጽ ያጋራሁዋችሁ መረጃ ነበር። ጉዳዩ በአጭሩ በተጠቀሰው ዕለት ምጥ የጠናባት ወ/ሮ ብርሃኔ ማሞ ከሜጢ ከተማ ወደደምቢ ዶሎ ሆስፒታል ሪፈር ተብላ ደምቢዶሎ ከተማ ከምሽቱ 5:30 ላይ ስትደርስ በክልሉ ፖሊስ ልዩ ሃይል በጥይት ተገድላለች። አብረዋት የነበሩ የቤተሰቦቿ አባላት የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህ ግፍ ጋር በተያያዘ በቀጣዩ ቀን ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ በከተማዋ ተቀስቅሶ የነበረ ሲሆን በግድያው ተሳትፈዋል የተባሉ ሶስት የፖሊስ አባላት ማለትም 1ኛ ኮንስታብል አብርሃም ስዩም፣ 2ኛ ኮንስታብል በቀለ በዳዳ(Badhaadhaa)፣ 3ኛ ኮንስታብል መልካሙ ነጋሳ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንደተጀመረ ጠቁሜ ነበር። እውነታው ግን ከዚያ የተለየና አስደንጋጭ የማናለብኝ የፍትሕ ጥሰት እየተፈፀመ መሆኑን ዛሬ ያነበብኩት የረዥም እስር አጋሬና ጓደኛዬ የ Lammii Beenyaa መረጃ አረጋግጦልኛል። ተጠርጣሪዎቹ እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረቡም! ያሳዝናል፤ ልብ ይሰብራል! በደምቢዶሎ ከሚገኙ ጓደኞቼ ደውዬ እንዳረጋገጥኩትም ሁኔታው ሆን ተብሎ ሕዝቡን ወደቁጣ ለመምራት በሚመስል መንገድ የፍትሕ መበየንን ወደጎን በማድረግ ጉዳዩን ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ በመስጠት ለመሸፋፈን እየተሞከረ ነው ብለውኛል። በቁጥጥር ስር ዋሉ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ያሉበት ወታደራዊ ካምፕም በቀላሉ ለማምለጥ አመቺ መሆኑ ሕዝቡን ቁጭት ውስጥ እንደከተተው ነግረውኛል። በምጥ ስትቃትት በጥይት ናዳ ያለፈችው የወ/ሮ ብርሃኔ ደምና ይህችን ምድር እንዳይቀላቀል በግፍ የተቀጨው ህፃን ነፍስ ይጮሃሉ። ይህን ግፍ አቅልሎ ማለፍ የህሊናም፣ የመንፈስም፣ የነፍስም፣ በአጠቃላይም የሰው መሆን ዕዳችን ነው። ደጋግመን እንላለን፤
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወደ ሚኒሶታ ስንሔድ ህዝቡ በ11 ስታዲየሞች ተሰብስቦ ጠበቀን፣ ከዚያ በስንት ድርድር ወደ አንድ መጣ ፦ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ከመድረክ ጀርባ ስንት ጉድ እንዳለ ተመልከቱ! .ይድነቃቸው ከበደ “ወደ ሚኒሶታ ስንሔድ ህዝቡ በ11 ስታዲየሞች ተሰብስቦ ጠበቀን፣ ከዚያ በስንት ድርድር ወደ አንድ መጣ” . ዲያቆን ዳንኤል ክብረት . ” የኢሳቱ ብሩክ ይባስና አበበ ገላው ወዲያና ወዲህ የቆሙ ኃይሎች ለአንድ ዓላማ እንዲሰለፉ ሌት ተቀን የደከማችሁትን ድካም መቼም አልዘነጋውም ” . የሦስት ወሩን አድካሚና አስደሳች ሩጫ አገባደድነው፡፡ አሁን የቀረን ዝርዝር ሪፖርቱን ተረጋግቶ መጻፍ ነው፡፡ ብዙ አስገራሚ፣ አሳዛኝ፣ አስደሳች፣ አስቂኝ ገጠመኞችን በቀጣዮቹ ቀናት አወጋችኋለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በአሜሪካ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለማነጋገር ወደ አሜሪካ እንደሚሄዱ የታቀደው ግንቦት ወር ላይ ነው፡፡ የዳላሱ የኢትዮጵያውያን ስፖርት በዓል ግብዣ ሲመጣ ነገሩ ሌላ መልክ ይዞ ነበር፡፡ ጋባዡ ማን ነበር? ክልከላውስ ከየት መጣ? በብዕር ወደፊት እንራመድበታለን፡፡ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የርእሳነ መንግሥታት ታሪክ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎች በዋናነት ከአሜሪካ መንግሥት፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከሌሎች ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ የዲያስፖራው ጉዳይ በጎንዮሽ የሚያዝ ነው፡፡ የዚህኛው ጉዞ ዋናው ልዩነቱ በዋናነት ኢትዮጵያውያንን ለማግኘት የተዘጋጀ መሆኑ ነው፡፡ ለአዲስ ሐሳብ አዲስ አካሄድ በሚል ጉዞውን የሚያስተባብረው ኮሚቴ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከባለ በጎ ፈቃድ ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡ የዳሰሳ ጥናት ተዘጋጀ፡፡ ዝርዝር ዕቅድ ወጣ፡፡ መጀመሪያ በዋሽንግተን ዲሲ በመቀጠል በሎስ አንጀለስ በመጨረሻም በሚነሶታ ኮሚቴዎች ተቋቋሙ፡፡ እንግዳው ነገር ተጀመረ፡፡ የኢሕአፓ፣ የመኢሶን፣ የቅንጅት፣ የኢሕአዴግ፣ የሰማያዊ፣ የግንቦት ሰባትና የሌሎቹም ፓርቲዎች አባላት በአንድ ኮሚቴ ውስጥ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ቀረበ፡፡ አባሎቻቸውና
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው በሰኔ 16ቱ ህዝባዊ መድረክ ላይ የቦንብ ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው በሚል በተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው። ተጠርጣሪዎቹ አብዲሳ ቀነዒ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ከሆነ አንደኛ ተጠርጣሪ አብዲሳ ቀነዒ በዕለቱ በወንጀሉ ተጠርጥረው የህክምና ዕርዳታ እየተሰጣቸው የነበሩትን ሰዎች ለማስመለጥ ሙከራ ያረገ ሲሆን ሶስተኛው ተጠርጣሪ ጌቱ ግርማ ደግሞ የቦንብ ጥቃቱን በማስተባበር ወንጀል ነው የተጠረጠረው። ተጠርጣሪው ከዚህ በፊት በወንጀል ተጠርጥሮ ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በምህረት የተለቀቀ መሆኑን የፖሊስ ማስረጃ ያስረዳል። አራተኛዋ ተጠርጣሪ ህይወት ገዳ በዕለቱ የአእምሮ ህመምተኛ በመምሰል በወንጀሉ የሳተፈች ስትሆን አሁንም በአማኑኤል ሆስፒታል ህክምናዋን እየተከታተለች መሆኗን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል። የምርመራ ቡድኑ የምርመራ ስራውን አጠናቆ መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ አስረክቧል። ዓቃቢ ህግም በህጉ መሰረት ክሱን አደራጅቶ ለመመስረት ችሎቱን የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቅዶለታል። ተጠርጣሪዎች ጨለማ ቤት ውሰጥ ተቆልፎብናል፣ ህገመንግስታዊ መብታችንም ተጥሷል በሚል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል ። መርማሪ ቡድኑ ግን የአያያዝ ችግር እንደሌለ እና ይህንንም በቪዲዮ አስደግፎ ለፍርድቤቱ ማቅረብ እንደሚችል ገልጿል። ፍርድ ቤቱ ከፈለገም ገለልተኛ አጣሪ ቡድን በመመደብ ሊያጣራ እንደሚችልም አስታውቋል። ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ከአያያዝ ጋር በደል እንዳይደርስባቸው፣ ክትትል እንዲደረግላቸውና በቀጣዩ የቀጠሮ ቀን ነሐሴ 12፣ 2010 በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተጠርጣሪዎች ማረፊያ የስራ ኃላፊ ቀርበው ስለ አያያዛቸው ማብራሪያ እንዲሰጡም አዟል።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ በጅቡቲ እና ኤርትራ መካከል ያለውን አለመግባባት ልትሸመግል ነው

በጅቡቲ እና ኤርትራ መካከል ያለውን አለመግባባት ኢትዮጵያ ልትሸመግል ነው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንደተናገሩት ሁለቱ አገራት የኢትዮጵያ ወዳጆች በመሆናቸው ለመሸምገል ፍላጎቱ እንዳላት አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የሽምግልና ጥያቄ ለጅቡቲ አቅርባ ተቀባይነት ማግኘቱንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡ ኤርትራና ኢትዮጵያ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት ከፈቱ በኋላ በምስራቅ አፍሪካ ያለው የሰላም ፍላጎት እያደገ መጥቷል ተብሏል፡፡ በሌላ ዜና በውጭ አገራት ኢትዮጵያን ወክለው እንዲሰሩ የተሾሙ አምባሳደሮች በነገው ዕለት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙም አቶ መለስ አለም ቃለ መሃላ ተናግረዋል፡፡ በነገው ዕለት ቃለ መሃላ የሚፈፅሙትና የሙሉ አምባሳደነት ሹመት ያገኙት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ አቶ እሸቱ ደሴ፣ አቶ አዛናው ታደሰ፣ አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣ አቶ ድሪባ ኩማ፣ አቶ ያለው አባተ እና አቶ አብዱልፈታ አብዱላሂ ናቸው።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ግፍ ተፈፅሞብኛል ፤ ግፍ አልፈፀምኩም ይላሉ። (ቃለመጠይቁን ያዳምጡት )

$bp("Brid_39721_7", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-10213039583729012.mp4", name: "የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ግፍ ተፈፅሞብኛል ፤ ግፍ አልፈፀምኩም ይላሉ። (ቃለመጠይቁን ያዳምጡት )", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180803_085659.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ግፍ ተፈፅሞብኛል ፤ ግፍ አልፈፀምኩም ይላሉ። (ቃለመጠይቁን ያዳምጡት )
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Poem

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት በአርበኞች ግንቦት 7 ስም አዲስ የሽብር ክስ እየተመሰረተ ነው።

ብአዴን እንዴት ነው የሚያስበው? ዛሬም አዲስ የሽብርተኝነት ክስ? (ጌታቸው ሺፈራው) የተወካዮች ምክር ቤት አርበኞች ግንቦት 7ን ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ እንዲነሳ ሰኔ 28/2010 ዓም አፅድቋል። ከመፅደቁ በፊት መንግስት የወሰነው ቀደም ብሎ ነው። ነገር ግን አሁንም አዲስ የሽብር ክስ እየተመሰረተ ነው። አሁንም “ግንቦት 7 የሚባል አሸባሪ ቡድን እየተባለ ክስ እየቀረበ ነው። ሚኪያስ ተስፋ የንግስት ይርጋ የእናቷ ልጅ ነው። እሷ ከታሰረች በኋላ ማዕከላዊ ገብቶ ተሰቃይቷል። “ከእኛ ጋር ትሰራለህ” ብለው ከእስር ከፈቱት በኋላ እንደገና አስረውታል። በተደረጋጋሚ በፍርድ ቤት ዋስ መብቱ ተጠብቆለት ሳይፈቱት ቆይተዋል። በጊዜያዊ አዋጁ ነው የታሰረው ብለው አዋጁ ከተሻረ በኋላም እስር ላይ አቆይተውታል። በዋስ ከእስር ከተፈታ በኋላ ሀምሌ 13/2010 ዓም አዲስ ክስ ተፅፎለታል። የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ አዟል። ክሱ የሽብር ክስ ሲሆን የተከሰሰው በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ከፀረ ሽብር አዋጁ ስም የተነሳለት ሰኔ 28/2010 ዓም ነው። የአርበኞች ግንቦት 7 ክስ ከፀረ ሽብር አዋጁ እንዲነሳ የተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቀ ከ15 ቀን በኋላ ግን የሽብር ክስ እንደአዲስ ተመስርቷል። ሀምሌ 13/2010 ዓም! የአርበኞች ግንቦት 7 ስም በፓርላማ ከፀረ ሽብር አዋጁ ከተነሳ በኋላ በሚኪያስ ላይ የተመሰረተው ክስ የአማራ ክልል ብሔራዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በሆኑት ጥጋቡ ተገኘ ፊርማና በክልሉ ፍርድ ቤት ማህተም ያረፈበት ነው። የፌደራል መንግስቱ በሽብር የተፈረጁ ድርጅቶችን ከፍረጃው ሲያነሳ የአማራ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጣና በለስ ፕሮጀክት በተቀሰቀሰ ግጭት ሶስት ሰዎች ሞተዋል ፣ የተባለው ወሬ ውሸት ነው ተባለ።

የስኳር ኮርፖሬሽን ፣ በጣና በለስ ፕሮጀክት በተቀሰቀሰ ግጭት ሶስት ሰዎች ሞተዋል ፣ የተባለው ወሬ ውሸት መሆኑን ዕወቁልኝ አለ፡፡ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ በነበሩት የአቶ ስመኘው በቀለ ፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተፈፀመበት ቀን መብራት በመጥፋቱ በፈንደቃ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር፡፡ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ ፈንደቃ ከተማ ፣ በቀብሩ እለት መብራት የጠፋው ሆን ተብሎ ነው በሚል መነሻ በተቀሰቀሰው ረብሻ 3 ሰዎች መሞታቸው የስኳር ኮርፖሬሽን ይናገራል፡፡ ይሁንና ፣ግጭቱ የተነሳውና የሞቱትም ሰዎች የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ናቸው ተብሎ መነገሩ ሀሰት ነው ብሏል፡፡ ግጭቱ የተነሳበት ፈንደቃ ከተማ ከፕሮጀክቱ በሶስት ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝና የሞቱትም የፕሮጀክቱ ሰራተኞች አለመሆናቸውን የተናገረው ስኳር ኮርፖሬሽን ሰራተኞቼ ፣ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጡና ተቻችለው ተዋደውና ተከባብረው የሚኖሩ ናቸው ብሏል፡፡ Sheger fm
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የክልሉፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል የስራ ሂደት መሪ ኢንስፔክተር መሃመድ አህመድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት ሁለት ቀን በፊት ከጉባ ወደ አሶሳ በሚመጣ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ዉስጥ በሁለት የልብስ ሻንጣ የተሞላ 5 መቶ የክላሽንኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ህብረተሰቡ በሰጠዉ ጥቆማ በሆሞሻ የፍተሻ ኬላ ላይ ጥይቶቹ ከአዘዋዋሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከባለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ከ37 በላይ የሚሆኑ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ መሃመድ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለዉ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ ሪፖርተር፡ ያለለት ወንድዬ (አሶሳ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት እንዴት? ( ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር))

ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት እንዴት? *** ዳንኤል ኪባሞ (ዶ/ር) *** ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊት (multinational) አገር ብትሆንም፣ ይህንን ኅብረ ብሔራዊነቷን የሚያስተናገድ ሥርዓት መገንባት አልቻለችም፡፡ በአገራችን ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት እስካልተገነባ ድረስ ግን ዕድገት ብሎ ነገር የሚታሰብ አይሆንም፤ ይልቁንም ግጭቱና የሕዝብ መፈናቀሉ ሥር እየሰደደ ይቀጥላል፡፡ ሄዶ ሄዶም የዘር ፍጀት የሚከሰትበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ ይህ እንዳይሆን፣ ሳይረፍድ ከአሁኑ መላ ልንፈልግ ይገባናል፡፡ የኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት መሠረቱ ዴሞክራሲ ነው፡፡ ያለ ዴሞክራሲ ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓትን ማሰብ አይቻልም፡፡ አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት ከፀደቀ ወዲህ ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት ወይም በተለመደው አማርኛ “ዴሞክራሲያዊ አንድነት” ተገንብቷል ይላሉ፡፡ ይህ አስተያየት ግን ፈጽሞ ውኃ የሚቋጥር አይደለም፡፡ ኅብረ ብሔራዊ ሥርዓት ያለ ዴሞክራሲ አይታሰብም፡፡ ኢትዮጵያም ደግሞ ዴሞክራሲያዊት አገር አይደለችም፡፡ ስለሆነም በአገራችን ዴሞክራሲያዊ አንድነት ብሎ ነገር የለም፡፡ አሁን በሥራ ላይ ያለው ፌደራላዊ ሥርዓት ብዙ ጠቃሚ ጎኖች ቢኖሩትም ያሉበት እንከኖችም በጣም በርካታ ናቸው፡፡ አንደኛውና መሠረታዊው ችግሩ፣ በብሔረሰቦች መሀከል ያለው መስተጋብር በጎና ሰላማዊ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ፣ እያንዳንዱ ብሔረሰብ የራሴ የሚለውን ክልል ወይም ዞን ወይም ልዩ ወረዳ “የእኔ ብቻ ነው፤ ማንም ሊደርስብኝ አይችልም፤ አይገባምም፤” ብሎ “ሌሎችን” ማኅብረሰቦች ከአካባቢው ሲያባርር፣ የሥራ ዕድል ሲከለክልና ሲገድል ነው የሚታየው፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ማንኛውም ዜጋ፣ በራሱ ቋንቋ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ ተዘዋውሮ የመሥራትና የመኖር መብቱን የሚያስከብርበት፣ ይህ መብቱ ሳያከበር የቀረ እንደሆነ ወደ ፍርድ ቤት አቤት ብሎ መብቱን የሚያስከብርበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስላልተመሠረተ ነው፡፡ የዜግነት መብትን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ ፖለቲካ እንደምን ወደዳር አገር ፖለቲካ ተገፋ? (በፍቃዱ ኃይሉ)

የትግራይ ፖለቲካ እንደምን ወደዳር አገር ፖለቲካ ተገፋ? የኢትዮጵያ ሥርወ መንግሥት መነሻ ማዕከሉ (core state የሚሉት) ሰሜን ላይ ነበር – አክሱም። ቀስ በቀስ ወደ ደቡብ እያፈገፈገ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ ላይ ሸዋ ላይ ከትሞ እስከ ዛሬ ዘልቋል። ‘የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ’ በአሁኑ ቅርፅዋ የተሠራችው በ19ኛው ክፍለዘመን ማገባደጃ ነው። ከዛሬዪቱ ኢትዮጵያ በፊት የነበረችው ‘ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ’ ነች። ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ እንደሌሎቹ የዓለማችን ጥንታዊ አገራት ሁሉ፣ ድንበር አልነበራትም – የተፅዕኖ አድማስ እንጂ። የተፅዕኖ አድማሷ ደግሞ እንደ ጊዜው እና እንደ ነጋሹ አቅም ሲሰፋና ሲጠብ ነው የከረመው። ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ የአማርኛ ተናጋሪዎች እና የትግርኛ ተናጋሪዎች በዋነኝነት የሚዘውሯት ነበረች። በተለይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ወዲህ ያለችው ኢትዮጵያ በሁለቱ ፉክክር እና ማመቻመች (compromise) ነበር የቆመችው። ዳግማዊ ምኒልክ ደቡቡን እና ምሥራቁን የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ አካል ባደረጉበት ወቅት ግን በቁጥር ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ እና ከአማርኛ ተናጋሪዎቹ የሚበልጡ ኦሮሞዎች የአገረ መንግሥቱ አካል በመሆናቸው፥ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች በፊት ከነበራቸው ተቀናቃኝነት የበለጠ ኃይል አግኝተዋል። ይህ ክስተት ኢትዮጵያን ሦስተኛ የሥልጣን ተፎካካሪ እንድታገኝ አድርጓታል። (ይህ ማለት ግን ከዚያ በፊት ኦሮሞዎች የአገረ መንግሥቱ አካል አልነበሩም ማለት አይደለም፤ ሸዋ ቀድሞውንም ቅይጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ‘ታላቁ የኦሮሞ ፍልሰት’ የኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ተቀላቅለዋል። ይህም የወሎና የጁ ኦሮሞ ፖለቲከኞችን አፍርቷል። በዘመን ወደኋላ በነጎድን ቁጥር ታሪኩ ይለዋወጣል፤ ስለዚህ ርቀን ባንሔድ ጥሩ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማም ዛሬን በሚጫኑ የቅርብ ጊዜ ታሪካዊ መቀናቀኖች ላይ ማተኮር ብቻ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከኮሎኔል መንግስቱ ጋር (መንግስቱ ሙሴ)

ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከኮሎኔል መንግስቱ ጋር (መንግስቱ ሙሴ) በለውጥ መአበል መሀል ስለሆንን ብዙ አዳዲስ ነገር እያየን ነው። ከሁሉም የዛሬዋ ደግሞ ለየት ያለች ድራማ ሆና አገኘኋት። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን እርቅ ይፈልጋሉ። ከራስ መታረቅ። ከራስ እርቅ ስንል ስንቶች ተረት ተረት እንዳሉን ግልጽ ነው። ስንቶች ተነጥፋችሁ ካልተገዛችሁ እንካችሁ ጥይት እንካችሁ ዱላ እና እስር ብለው እንደተሰቃየን ይቅር ምንተግዚያብሄር ይገባል። እየተካሄደ ያለው ትግል ደግሞ ቡድን መቧደን። ወይንም እነእከሌ በነ ወዲ —ተወደዋል እና እነሱን ብናቀርብ የሚያሰኝ አይደለም። መሆንም የለበትም። ብዙ ታጋዮች አያሌ መስዋእትነት ከፍለዋል። ለምሳሌ አቶ ኃይለማሪያም በቀጭን ትእዛዝ ሰራዊታችንን እና የጸጥታ ኀይሎችን አዝዘናል።   ጸጥታውን ማስከበር ሀላፊነት አለብን። ትእዛዝም አስተላልፌአለሁ በሚል ለግዜው ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ የወጣት ህይወት ተቀስፏል። በተመሳሳይ እንዴው የእስታሊንን በትር (ቀይ ሽብርን) ትተን ኮሎኔሉ 60 የቀድሞ ባለስልጣናትን በአንድ ሌሊት ሲረሽኑም ሆነ አገሪቱ በወግ እና በማእረግ አስተምራ ያሳደገቻቸው የጦር፣ የፖሊስ፣ የባህር ኃይል ጀኔራሎችን ከአጠፉ እና ሰራዊቱን ያለመሪ ከለቀቁት በኋላ በአንድ አመት ግዜ የሆነው የህወሓት ነፍሰገዳይ ቡድን አምልጠው ሐራሪ መግባታቸው እሙን ነበር። አንዳንዴ ይገርመኛል እና ዝምታንም ስንመርጥ ደግሞ ለሰው ብለን ከሆነ ያሳዝናል። በላይ ዘለቀን በስሙኒ ገመድ ሲያንጠለጥሉት እረጎበዝ አይሆንም አልተባለም ያኔ። አንድ ትውልድ ተመትሮ አንዳንዶች ሲያሾፉም ቅሬታ አይሰማንም። በበኩሌ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ለከት ቢኖረው እና ወንጀለኛን የትናንቱ ወንጀለኛ ከታች አምናው ተቃቅፎ ማህበራዊ ገጽን ሲሞላው ሞራል የምትባለዋ የት ገባች እንድንል ሆእነናል። ለዘመናት የታገሉ። የዘረኛ ጉግማንጉግን ሁሉ በግንባር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወታደራዊ ስነምግባር ጥሰትና በኩብለላ ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ተደረገ

በወታደራዊ ስነ ምግባር ጥሰትና ኩብለላ ወንጀሎች ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ አለሙ፥ ለኢዜአ እንደገለጹት መንግስት በሃገር አቀፍ ደረጃ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለማስቀጠል መከላከያ ሰራዊት ለውጡን በመደገፍ እየሰራ ነው። በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውን የምህረት አዋጅ መሰረት በወታደራዊ የስነ ምግባር ጥሰት ተከሰው በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቀደም ሲል ከሃገር የኮበለሉ የሰራዊት አባላት ምህረት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። የምህረት አዋጁ የሚመለከታቸው የሰራዊት አባላት ተቋሙ ባዘጋጃቸው አካባቢዎች ባሉ ጽህፈት ቤቶች በአካልም ሆነ በተዘጋጀ ፎርም ማመልከት እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። በዚህም በተቋሙ አዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ ታራሚዎች ቤላ አካባቢ በሚገኘው የፍትህ ዳይሬክቶሬት ጽህፈት ቤት ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ታራሚዎች ባሉበት ክልል በተጠባባቂ የፍትህ ዳይሬክቶሬት ጽህፈት ቤት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ በወረዳና በዞን ላሉ ደግሞ በዞኑ በሚገኘው ጽህፈት ቤት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። በዚህም ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤቱ ፎርሙን ማስሞላት እንደተጀመረ ጠቅሰው፥ በክልሎች ደግሞ ከነሃሴ አንድ ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሪፖርት አድርገው ያላጠናቀቁ ታራሚዎች የጊዜ ገደቡ ሲጠናቀቅ ሪፖርታቸው ተቀባይነት እንደማይኖረውም አሳስበዋል። (ኤፍ ቢ ሲ)
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ሲገቡ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

$bp("Brid_39205_8", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-2048275005204365.mp4", name: "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ሲገቡ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/FB_IMG_1533131232996.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ሲገቡ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ሀሳቦች፤ •የማንፈልገውና የእኛ ያልሆነ አንድም ዜጋ የለም • ግንቡ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ፈርሷል፣ ፍርስራሹን የመጠራረግ ስራ በሚኒሶታ እውን ሆኗል፡፡ • አቡነ መርቆሪዮስ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ሲገቡ የመጀመሪያውን የግንባታ ጡብ አስቀምጠዋል፡፡ • በአሜሪካ የሚኖሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውንና ወገናቸውን ናፍቀዋል፡፡የተሳካለቸው በአዲስ አመት እንዲመጡ ጋብዣቸዋለሁ፡፡ • ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገንዘባቸውን ሳይሆን ፍቅርና እንክብካቤ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡ • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አባቶች አንድነት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ደስታ ነው፡፡ • የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ እህት ቤተክርስቲያን ጋር በቅርቡ እንደምትደመር እንጠብቃለን፡፡ • ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት አገራቸው ገብተው ለማገልገል አረጋግጠውልናል፡፡ • ጀዋር ሙሀመድና ታማኝ በየነም በቅርቡ ወደ አገራቸው ገብተው በድልድይ ግንባታ ውስጥ እንደሚሳተፉ አረጋግጠውልኛል፡፡ • በዘርና በሀይማኖት ሳንከፋፈል ኢትዮጵያዊ ወገንተኝነትን በማሳየት ወደ እኛ የሚመጡ ወገኖቻችንን ልንቀበል ይገባል፡፡ • አንዱ ብሄር ሌላውን ብሄር፣ አንዱ ሀይማኖት ሌላውን ሀይማኖት ሳያጠቃ በአንድነት ወደፊት መገስገስ ይጠበቅብናል፡፡ • በአሜሪካ ለተደረገልን መስተንግዶ ለዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ምስጋና ክብር አቀርባለሁ፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

አማራን የሚያገልና የሚጨቁን የፌዴራሊዝም አተገባበር ነው የነበረው!!

በኩር፤ ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓም አማራን የሚያገልና የሚጨቁን የፌዴራሊዝም አተገባበር ነው የነበረው!!   ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግና አስተዳደር መምህር ናቸው:: በሰብዓዊ መብት ዙሪያም የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አላቸው:: ዶክተር ሲሳይ በአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ በምክትል ሀላፊነት ያገለገሉ ሲሆን በቀድሞ ስሙ የኢህዴን (ብአዴን) ታጋይም ነበሩ:: ዶክተሩ የዚህ እትም እንግዳችን ናቸው:: መልካም ንባብ! ስምዎ በተለየ ሁኔታ ከራያ ህዝብ ጋር ብዙ ጊዜ ይነሳል:: ምክንያቱ ምንድን ነው? ተወልጀ ያደግሁ ራያ ውስጥ ነው:: በራያ ስማር በነበረው የፖለቲካ ትኩሳት ወደ ኢህዴን ገብቸም ታግያለሁ:: ኢህዴን /ብአዴን/ በነበርኩበት ጊዜ የራያን ህዝብ መብትና ጥቅም እንዲጠበቅ እታገል ነበር:: የራያ ህዝብ ፍላጐት ሳይጠየቅ በሁለት ክልሎች እንዲተዳደር ተደርጓል:: በ2005 ዓ.ም የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና የማዕከላዊ መንግሥታት ምላሽ ከአፄ ዮሐንስ እስከ ኢህአዴግ የሚል መጽሀፍ ከጓደኛዬ ጋር ሆነን አዘጋጅተናል:: የራያን ህዝብ ታሪክ እና ተጋድሎም እያሳወቅሁ ነው:: የራያን ህዝብ ተጋድሎ ትግራዮች ደግሞ ቀዳማዊ ህዝብ ወያኔ ትግል የሚሉትን ታሪክ በተመለከተ በማስረጃ ሞግተናል:: ቀዳማዊ ህዝብ ወያኔ የራያ ህዝብ ታሪክ ነው:: በዚህ ጉዳይ ጽፌያለሁ፤ሞግቻለሁ:: ለዚህ ይመስለኛል ስሜ ከራያ ህዝብ ጋር ጐልቶ የሚነሳው:: የራያ ህዝብ ስነ ልቦናዊና ባህላዊ ቅርበቱ ከየትኛው ማህበረሰብ ጋር ነው? የራያን ህዝብ ሠዎች በተለያየ መንገድ ይገልፁታል:: የራያ ህዝብ ስንል በድሮው የራያ ቆቦና አዘቦ አውራጃ የሚኖር ህዝብ ድምር ነው:: የራያነት ስነ ልቦና አለው:: ራያ የነ ጥላሁን ግዛው ሀገር ነው:: አማርኛ ይነገራል:: ትግረኛ የሚመስል
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሴኪዩላሪዝም ሽፋን በሂጃባቸው ምክንያት ከስራቸው የተፈናቀሉ ሙተነቂብ እህቶቻችን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ተወሰነ።

በሂጃባችሁ ምክንያት ከስራ ገበታችሁ ለተፈናቀላችሁ ሙተነቂብ እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ! ሙተነቂብ በመሆናቸው ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉት እህቶቻችን ወደ ስራቸው በክብር እንዲመለሱ ተወሰነ! አቡ ዳውድ ኡስማን ላለፉት አመታት በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን መንግስት አክራሪነትን እዋጋለው በሚል ዘመቻ ሽፋን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ድንጋጌዎቻቸውን እንዲጥሱና የሃይማኖት ነፃነታቸው ተገፎ እምነታቸውን የሚያዛቸውን ትዕዛዛት እንዳይፈፅሙ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ከሌሎች የሃገራችንን ዞኖች በተለየ የስልጤ ዞን ሙሉ በሙሉ ሙስሊም እንደመሆኑ መጠን በቀድሞ በፌደራል ጉዳዬች ሚኒስትር በኩል ከፍተኛ ጫና ይደረግብት የነበረ ዞን ነው፡፡ የዞኑ አመራሮች ሁሉም ሙስሊሞች ቢሆኑም ወይ ስልጣናቸውን አልያ ደግሞ እምነታቸውን እንዲመርጡ ሲገደዱ ነበር፡፡ በስልጤ ዞን በፀረ አክራሪነት ዘመቻ ስም ከተደረጉ ፀረ ህገ መንግስት ተግባራት መካከል ሙስሊም ሴት እህቶች ኒቃብ እንዳይለብሱ የሚከለክል ተግባር ነበር፡፡ ተወላጆቹ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም በሆኑባት የስልጤ ዞን ከበላይ የመንግስት አካል በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት አክራሪነትን እንዲዋጉ አልያ ከስልጣናቸው እንደሚነሱ ተዝቶባቸው ቆይቷል፡፡ ይደረግባቸው ከነበሩት ጫናዎች መካከል በዞኑ ኒቃብ የሚለብሱ ሙስሊም ሴቶች በአክራሪነት የተፈረጁ በመሆናቸው ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ ማስገደድ እንዲሁም የዞኑ የመንግስት አመራሮችም የገዛ የትዳር አጋራቸውንም ቢሆን ኒቃቧን በማሶለቅ በዞኑ ኒቃብ የማሶለቅ ዘመቻውን በተግባር እንዲያሳዩ ሲገደዱ ነበር፡፡ በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ኒቃብ የሚለብሱ ሴቶች ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ አልያ ደግሞ ከስራቸው እንዲሰናበቱ ተወሰነ፡፡ በዚህም በርካታ ሙተነቂብ እህቶች ከመንግስት መስሪያ ቤት እና ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡ ለሚሰሩበት የመንግስት መስሪያ ቤት ለቦታው የሚመጥን እውቀት፣ችሎታ እና ብቃት ቢኖራቸውም ሃይማኖታቸው ያዘዛቸውን ኒቃብ በመልበሳቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መቀሌ ተያዙ ።

መረጃዎች እንዳመለከቱት ቡድኑ የተጓዘው መቀሌ የተሸሸጉትን በሙስና እና በሽብር ተግባር የተሰማሩ የሕወሃት ቱባ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከትግራይ መስተዳደርና ከፖሊስ ኮሚሽኑ እንዲሁም ከትግራይ ጸረ ሽብር ግብረ ኃይል ጋር ተነጋግሮ የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዞ ወደ መቀሌ እንደበረረ ሲያወቅ በጉዳዩ ጣልቃ የገቡት የመከላከያ ሹማምንት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ጨምሮ ባደረጉት ተልእኮውን የማክሸፍ ስራ ከመሃል ሃገር የሔዱት ፖሊሶች ታስረው አንቶኖቩ ባዶውን እንዲመለስ ተደርጓል። ተልእኮውን ካከሸፉ በኋላ የተሳሳተ መረጃ በማዘጋጀት በጀርመን ድምጽ ራዲኦ እንዲተላለፍ ያደረጉ ሲሆን የጀርመን ድምጽ ራዲኦ ጽፈው የሰጡትን ሳያጣራ ሳይመረምር በማስተላለፍ ሕዝብን አደናግሯል። ከዚህ በታች ያለው የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ ነው። የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል የሚል መለዮ እና አርማ ያደረጉ ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መቀሌ፤ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣቢያ ተያዙ። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ምንጮች ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ታጣቂዎቹን ያሳፈረዉ አንቶኖቭ አዉሮፕላን መቀሌ ያረፈዉ ዛሬ ጠዋት ነዉ። መትረየስ ጭምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያ የታጠቁት ሰዎች ከሱዳን አዲስ አበባ ለመጓዝ አልመዉ በስሕተት መቀሌ ማረፋቸዉን ተናግረዋል ተብሏል።ዉስጥ አዋቂ ምንጮቻችን እንደሚሉት የትግራይ መስተዳድር ልዩ ኃይል ታጣቂዎቹን ክብቦ ጉዳዩ እየተጣራ ነዉ። DW amharic
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ቡራኬ ሰጡ።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ልዩ ጽ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ። በሲያትል የመጨረሻ ቡራኬያቸውን ያደረጉት አባታችን  አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook