Blog Archives

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ሲገቡ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

$bp("Brid_39205_1", {"id":"12272", "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-2048275005204365.mp4", name: "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ሲገቡ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/FB_IMG_1533131232996.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአሜሪካ ጉዟቸውን አጠናቀው ሲገቡ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ሀሳቦች፤ •የማንፈልገውና የእኛ ያልሆነ አንድም ዜጋ የለም • ግንቡ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ፈርሷል፣ ፍርስራሹን የመጠራረግ ስራ በሚኒሶታ እውን ሆኗል፡፡ • አቡነ መርቆሪዮስ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ሲገቡ የመጀመሪያውን የግንባታ ጡብ አስቀምጠዋል፡፡ • በአሜሪካ የሚኖሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውንና ወገናቸውን ናፍቀዋል፡፡የተሳካለቸው በአዲስ አመት እንዲመጡ ጋብዣቸዋለሁ፡፡ • ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገንዘባቸውን ሳይሆን ፍቅርና እንክብካቤ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡ • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አባቶች አንድነት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ደስታ ነው፡፡ • የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ እህት ቤተክርስቲያን ጋር በቅርቡ እንደምትደመር እንጠብቃለን፡፡ • ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት አገራቸው ገብተው ለማገልገል አረጋግጠውልናል፡፡ • ጀዋር ሙሀመድና ታማኝ በየነም በቅርቡ ወደ አገራቸው ገብተው በድልድይ ግንባታ ውስጥ እንደሚሳተፉ አረጋግጠውልኛል፡፡ • በዘርና በሀይማኖት ሳንከፋፈል ኢትዮጵያዊ ወገንተኝነትን በማሳየት ወደ እኛ የሚመጡ ወገኖቻችንን ልንቀበል ይገባል፡፡ • አንዱ ብሄር ሌላውን ብሄር፣ አንዱ ሀይማኖት ሌላውን ሀይማኖት ሳያጠቃ በአንድነት ወደፊት መገስገስ ይጠበቅብናል፡፡ • በአሜሪካ ለተደረገልን መስተንግዶ ለዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ምስጋና ክብር አቀርባለሁ፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በዋሽንግተን ዲሲና ሎስ አንጀለስ ድልድዩ ፈርሷል፤ በሚኒሶታ ፍርስራሹ ተጠርጓል¬- ጠ/ሚ ዶክተር አብይ

በዋሽንግተን ዲሲና ሎስ አንጀለስ ድልድዩ ፈርሷል፤ በሚኒሶታ ፍርስራሹ ተጠርጓል¬- ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በአካባቢው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የባሰባሰብ በዚህ መድረክ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳና የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተገኝተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለህዝቡ ባስተላለፉትም መልዕክት የተበተነው ህዝብ ተደምሮ በሀገሩ ላይ እንዳይሳተፉ የተጋረጡበትን ግንብ መደርመስ ያስፈልጋል ሲሉ ንግግራቸውን ጀምረዋል። የተገነባው ግንብ ብዙ ቋንቋ በመናገራችን፣ ከተለያየ ዘር መምጣታችን እና ኃይማኖት መከተላችን አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እነዚህ ሁሉ ውበታችን ናቸው ብለዋል። እኛን የለያየን የጥላቻ ፣ የመናናቅ ፣ የራስ ወዳድነት ፣ የቂም በቀል ግንብ ነው፤ በኛ ዘመን ይህ የተከለከለ ነው ልንል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በአሜሪካ የመደመር ጉዞ በዋሽንግተን ዲሲና ሎስ አንጀለስ ድልድዮ እንደፈረሰና በሚኒሶታ ደግሞ ፍርስራሹ መጠረጉን በመድረኩ ላይ ጃዋር መሀመድን በማቀፍ ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ አብስረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አማራ ለኦሮሞ፣ ኦሮሞ ለሶማሌ፣ ሶማሌው ለሌላው ስጋት ሳይሆን ጉልበት መሆኑን ገልፀዋል። ልጆቻችን ተነጋግረው መወያየት እንዳይችሉ፤ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርገናልና ያንን ለማካካስ ተደምረን ቀን ከሌት መስራት አለብን ሲሉ ነው ያሳሰቡት። ሀገር ስትፈርስ የሚጠቀመው ማን ነው? ከሌሎችና ከታሪክ ተምረን በፍቅር አንዲት ታላቅ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ትሩፋት የምትሆን ሀገር መገንባት ይኖርብናልም ብለዋል። የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው፥ ዘር፣ ሀይማኖት ሳይገድበን እንዲህ ባማረ ሁኔታ መገናኘታችን ያስደስታል ሲሉ የተሰማቸውን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook