Blog Archives

በአብይ ሿሚነት የሚፈራረቁት ባለስልጣናት የአማራን ሕዝብ የግፈኞች ሰለባ አድርገውታል።

በአብይ ሿሚነት የሚፈራረቁት ባለስልጣናት የአማራን ሕዝብ የግፈኞች ሰለባ አድርገውታል። አሁንም ተዘጋጅተዋል። አዳዲስ ተመዳቢዎች አሉ ስንል እነ አብይ ሐሳባቸውን ሊቀይሩ ይችላሉ የሚሉ አስተያየቶች ቢኖሩም ያም ሔደ ያም መጣ አማራ ከጀመረው ትግል አያፈገፍግም። ለአማራ ክልል አዲስ ሹመኞች ከኦሕዴድ ሰፈር ሊመደቡለት መሆኑ ታውቋል። እነዚህ ተመዳቢ ሹማምንት ጨፌ ኦሮሚያ ኦረንቴሽን የተሰጣቸው ሲሆን ከአራት ኪሎ የሚወርድ ትእዛዝ አስፈፃሚዎች ናቸው። የአማራ ክልል ምክር ቤት የነዚህን ሰወች ሹመት አፀደቀ ማለት የአማራ ሕዝብን ጥያቄ እንዳይመለስ ተባባሪ እንደሆነ ይቆጠራል። በድሮን የደበደበውን ሕዝብ ሳያፍር አስተዳዳሪ ልሹምልህ ማለት ይሉኝታቢስነት ነው። የአማራ ሕዝብ ጥያቄው ካልተመለሰ ትግሉ አያቆምም። የአማራ ሕዝብ ላይ ዝመቱ ብሎ ለኦሕዴድ መሪዎች ደብዳቤ የላከው ይልቃል ከፋለና ጀሌዎቹ አዲስ አበባ አንዴ ገስት ሐውስ አንዴ ሆቴል በቁም እስር እየተንከራተቱ ጥቃቅን ሹመቶችን አንጋጠው እየጠበቁ ነው። ከዚህ በላይ ውርደት ይጠብቃቸዋል። በክልሉ በአብይ ሿሚነት የሚፈራረቁት ባለስልጣናት የአማራን ሕዝብ የግፈኞች ሰለባ አድርገውታል። ከሕዝብም ከግፈኞችም ሳይሆኑ እንደ ሸንኮራ እየተመጠጡ ተተፍተዋል። በቀጣይነት የሚመጡ የኦሕዴድን ተልእኮ ከማስፈፀም የዘለለ አንዳችም ነገር ለአማራ ሕዝብ የሚፈይዱት ስለሌለ ልንታገላቸው ይገባል። የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች እስኪመለሱ ትግሉ ይቀጥላል። በመላው ኢትዮጵያም ይዳረሳል። የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች ነው። የሕልውና ትግል ነው። አያቆምም። ፋኖም ስራውን እየሰራ ነው። #MinilikSalsawi ባለስልጣናቱ በወጡበት እንዲቀሩ ተወሰነባቸው። ባይጸናላቸውም አዳዲስ አንዳውላዎች ሊሾሙ ነው። 1. ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ተሹመዋል። የኢንተርፕራይዞች ሃላፊ የነበሩ ሲሆን የርዐሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለን ቦታ ተረክበዋል።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሊቅ ዐቢይ አስቸጋሪ ምርጫ። የግል አስተያየት (ከኀይሌ ላሬቦ)

የሊቅ ዐቢይና የነለማ ቡድን ተብሎ የሚጠራውን አንጃ ደጋፊዎች፣ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ የአንድነት ጐራ ናቸው ብል ስሕተት አይመስለኝም። የነለማ ቡድን ግን ሁሉም የኢሕአዴግ አባላት ናቸው። የዚህ ቡድን ደጋፊዎች ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢሕአዴግ በመልካም እንተርጉም ካልን ሆድና ጀርባ፣ በመጥፎ እናስመስል ከተባለ ደግሞ እባብና ርግብ መሆናቸውን ነው። ምንም ብንመኝ፣ ሁለቱ በፍጹም አብረው ሊኖሩም ሊደመሩም አይችሉም። “መደመር” የሚለው የሊቅ ዐቢይ ፈሊጥ ለነዚህ ሁለቱ በፍጹም አይሠራም። ባንድ አልጋ እንኳን ቢተኙ፣ ሕልማቸው ተጻራሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዘመን ተሻጋሪና ለማንም የማይበገር፣ ሌላውን ጐረቤቱንም ሆነ አካባቢውን እያሰፋና እያቀፈ የሚሄድ፣ እንከን የለሽ ስብጥርና ጒንጒን ማንነት ነው። ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት የሚታወቁት በተፈጥሯቸው ማንንም አስተናጋጅና ዐቃፊ በመሆናቸው ነው። የኢትዮጵያዊነት ዐቃፊነት፣ ኢትዮጵያ ከተባለው ግዙፍ ምድር መጥቆ ወሰኑንና ድንበሩን ዐልፎ፣ ለሌላውም ዓለምና ሕዝብ ተትረፍርፏል። የዓለም፣ በተለይም ጭቁንና ጥቊር፣ ሕዝብ በምዕራባውያን መብቱ ተጨፍልቆ ይኖር በነበረበት ወቅት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግሉን ድምፅ፣ በያለበት ሲያክላላው፣ ሲያስተጋባው፣ ሲያክለውና ሲያንረው ቈይቶ፤ የኋላ ኋላ ግቡን ለመምታት የበቃው በኢትዮጵያዊነት ዙርያ በመሰለፍና በመሰባሰብ ነው። ኢሕአዴግ በተቃራኒ በባሕርዩ ከፋፋይ፣ በልዩነት ላይ ያተኰረ፣ በጥላቻ መሠረት ላይ የተካበ፣ የጐጠኞችና የአገር ከሓጂዎች ጥርቅማጥርቅም ነው ማለት ይቻላል። ብዙዎች የሚሳሳቱት ኢሕአዴግን እንደፖለቲካ ድርጅት እያዩ ነው። ኢሕአዴግ የተፈጠረው የኢትዮጵያን ጥፋት ከኋላ ሁነው ይሸርቡ በነበሩት በውጭ ኀይሎች ሤራና ምክር ሲሆን፣ በእጁ ጠፍጥፎት ህልውና የሰጠው ግን፣ የታላቂቷ ትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ (ሕወአት) ነው። ሕወአት በኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት አያምንም።
Tagged with: , , , , , , , , , , , , ,
Posted in Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሰብ እና ምጽዋ ወደቦች ጉብኝት በኋላ አስመራ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሰብ እና ምጽዋ ወደቦች ጉብኝት በኋላ አስመራ ገቡ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአለም ባንክ ከ13 አመት እግድ በኃላ ለኢትዮጵያ የበጀት ድጎማ 1 ቢሊዮን ዶላር ፈቀደ ።

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት የአንድ ቢሊዮን ዶላር የበጀት ድጎማ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱ ታውቋል። ይሕ ካለፉት 13 አመታት በኃላ የመጀመሪያ ነው የተባለለት ድጋፍ በባንኩ ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቷል ። በ1997 የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ የአለም ባንክ የበጀት እርዳታውን ድጋፉን አቁሞ ነበር። ሙሉ ዘገባውን እዚህ ላይ ያገኙታል።   
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ዛሬ በሰጡት የመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች ፤ • አሁን ላይ ለአዲስ አበባ ከንቲባ እንደተሾመ የሚወራው ስህተት ነው፡ ቀጣዩ ምርጫ እስኪደርስ ከተማዋ በባላደራ አስተዳደር ከምትመራ ሶስት ወጣት ፖለቲከኞች ተቀምጠዋል፡፡ ለጊዜው የተቆጠሩ የህዝብ ስራዎችን ይዘው ወደ ስራ ገብተው ውጤት እያሳዩ ነው፡፡ • በቀጣዩ ምርጫ የአዲስ አበባ ህዝብ የራሱን ከንቲባ ይሾማል፡፡ • በአለም ላይ ከአንድ በላይ ቋንቋዎች በአንድነት የብዙ አገራት የስራ ቋንቋ ሆነው ያገለግላሉ፡፡በኢትዮጵያም አፋን ኦሮሞ የስራ ቋንቋ ይሁን የሚል ጥያቄ አለ፤ሀሉም ወገን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማወቅ ቢጥር መልካም ነው፡፡ይሁን እንጂ አፋን ኦሮሞን የስራ ቋንቋ ለማድረግ የህገ መንግስት ማሻሻያ ስለሚፈልግ አሁኑኑ ይሁን የሚባለው ተገቢ አይደለም፡፡አማርኛን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአንድ ቋንቋ በላይ ለማወቅ መጣር አለበት፡፡ሁሉም ነገር ህግና አሰራርን ተከትሎ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ • የታጠቁ ኃይሎች ወደ አገር ቤት የተመለሱት ነፍጣቸውን ጥለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው፡፡እነሱን የሚደግፍ ተቋምም ይደራጃል፡፡ • ኢትዮጵያዊነት የአቃፊነት ባህል ነው ያለው እንጂ አግላይ አይደለም፡፡አልፎ አልፎ የታዩት ጥፋቶች መታረም ያለባቸው ናቸው፡፡የተፈናቀሉም ወደየቀያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው፡፡ • ወጣቶች ለስርዓት መታገል እንጂ ራሳቸው ፈራጅ መሆን የለባቸውም፡፡ • የኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ማንም ያሳካው ጅማሮውን እና የታየውን በጎ ፍላጎት ያማረ ፍፃሜ እንዲኖረው ማድረግ የሁሉም ድርሻ ነው፡፡ • ሀብት በማስመዝገብ ሌብነት አይጠፋም፣ ዋናው ጉዳይ ሌብነትን የሚጠየፍ አገልጋይ ትውልድ መፍጠር ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል፡፡ • ኢትዮጵያ ክብሯንና ትልቅነቷን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ማብራሪያ ሊሰጡ ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሊሰጡ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ማብራሪያ ሊሰጡ ነው፡፡ ዛሬ ከ9:00 ሰዓት ጀምሮ ከሀገርና ከውጭ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ነሀሴ19፣2010
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ ይጠናቀቃል ሲሉ ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

‹‹ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ ይጠናቀቃል፡፡››ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ግንባታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ የነበሩ የስኳር ፕሮጀክቶች አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ዶክተር ዐብይ ይህንን ያሉት በባህርዳር ከተማ ከብአዴን አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር ላይ ነው፡፡ ባለፉት 9 ወራት የተሻለ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማምጣት ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውንም ነው የጠናገሩት፡፡ በሀገሪቱ የተሻለ መግባባት ለመፍጠርም ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የነበረውን ግንኙነት የማስተካከልና በሀይማኖቶች ውስጥ የነበረውን መከፋፈል የማጥፋት ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በኢኮኖሚ ረገድም የውጭ ምንዛሬ በቤታቸው ያከማቹ ዜጐች ወደ ባንክ እንዲያስገቡ በተጠየቀው መሠረት በሁለት ሳምንታት ብቻ እስከ 130 ሚሊየን ዶላር በባንኮች ተመንዝሯል ብለዋል፡፡ ግንባታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ የነበሩ የስኳር ፕሮጀክቶችም አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራ እየተሰራ መሆኑንና ከስድስት ወራት በኋላ ሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች እንደሚጠናቀቁም ገልፀዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጡት መልካም ለውጦች የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ትክክለኛ የአመራር ስልትን ለመተግበር አመራሮች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በባሕር ዳር በብአዴን የውይይት መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

በብአዴን የውይይት መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች • ለዘመናት በመልካምም ሆነ በፈታኝ የታሪክ አጋጣሚዎች ሁሉ አብሮነት እና መቻቻል የሀገራችን ህዝቦች አይነተኛ እሴት ነው፡፡ • ከትውልድ ትውልድ ይህች ሀገር አንድነቷን ጠብቃ የመቆየቷ ዋናው ሚስጥር በህዝቦቿ መካከል ጸንቶ የኖረው ከዘር እና ከሃይማኖት በላይ የቆመው የመተሳሰብ ተግባር ስር ሰዶ መቆየቱ ነው፡፡ • በኢትዮጵያ ዘላቂ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት እንዲፋጠን በህግ የበላይነት እና በህዝቡ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት ያስፈልጋል፡፡ ይህን ለማሳካት የግለሰብ እና የቡድን መሰረታዊ መብቶች ያላንዳች ልዩነት እንዲከበሩ ህገመንግስቱ መሰረት ማደራጀት ያስፈልጋል፡፡ • ባለፉት አራት ወራት የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች የህዝቡን ጥያቄ በተወሰነ ደረጃ በመመለስ ፋታ ያስገኙ ቢሆንም መሰረታዊ የሆኑት የፍትህ ፣የዲሞክራሲ እና የህግ የበላይነት ጥያቄዎች በመመለስ ረገድ ገና ብዙ ይቀረናል፡፡ • ቀደም ባሉት አመታት በህግ ስም የመግዛት አካሄድ ያመጣቸውን መዘዞች ለማረም ከተወሰዱት ርምጃዎች መካከል አንዱ ያላግባብ ይወነጀሉ የነበሩ ዜጎችን እና የፖለቲካ ቡድኖችን ጉዳይ በይቅርታ እና በምህረት እልባት እንዲያገኝ ማድረግ ነው፡፡ • ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዱ የተጋረጠብን ፈተና ነጻነትን እና ስርዓት አልበኝነትን ባለመለየት መረን የለቀቀ ህግ እና ስርዓትን የማያከብር እንቅስቃሴዎች እና ድርጊቶች መስፋፋት ነው፡፡ • አሁን በሃገራችን እየታየ ያለው እና ለህግ የበላይነት ትልቁ ፈተና ለህግ ተገዥነትን ወደጎን የማድረግ ትልቅ ዝንባሌ ነው፡፡ • በስሜትና በጥላቻ የሚወሰዱ እርምጃዎች ህግን ወደራስ እጅ በመውሰድ በመንጋ የሚሰጥ የወሮበሎች
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከብአዴን አመራሮች ጋር እየመከሩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከብአዴን አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አመራሮች ጋር በባህር ዳር ከተማ እየመከሩ ነው፡፡ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች መድረክ ትናንት የተጀመረው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም የመድረኩ ተሳታፊ ናቸው ተብሏል፡፡ በመድረኩም የክልሉ እና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ የአማራ ብዙሃን መገናኛ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዓቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጡ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዓቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ውስጥ በሁሉም መስኮች መሰረታዊና ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየተመዘገቡ ያሉበት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ብንገኝም በተጀመረው ስፋትና ጥልቀት ለውጡን ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት የሚያደነቅፉና የለውጡን አቅጣጫ የሚያስቱ ችግሮችም አብረው እየታዩ መምጣታቸውን በውል እንገነዘባለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚረዳው አገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየ ሥልጣኔ ባለቤት የሆነች፣ በዓመታት የጎለበተ የመንግሥት መዋቅርና ሥርዓት ያላት፣ የፍትህና ርትዕ ማህበረ ባህላዊ መረዳትም በህዝቦቿ ዘወትራዊ ህይወት ውስጥ የሰፈነባት እና ህዝቦቿም ለዘመናት ስለነጻነት ታሪካዊ ገድል የፈጸሙባት ታላቅ አገር ናት። በዘመናት ሂደት ውስጥ ከማዕከላዊው መንግስት በተጨማሪ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎች ባሉ ማህበረሰቦች ተቀርፀው በቆዩ ልዩ ልዩ ባህላዊ ሥርዓተ-መንግሥታት መሰረት ህዝቦችም ሆኑ መሪዎች በሕግና ደንቦች ተገድበው ሲኖሩ ቆይተዋል። በመላው አገሪቱ የሚኖሩ ሕዝቦች በባህላዊ ትውፊታቸው እና በምሳሌያዊ አነጋገሮቻቸው ጭምር ለፍትህና ርትዕ የሚሰጡት ቦታ እጅጉን ትልቅ ነው። አብሮነትና መቻቻል በመልካምም ሆነ በፈታኝ የታሪክ አጋጣሚዎች ሁሉ የአገራችን ህዝቦች አይነተኛ ዕሴት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህች አገር ከትውልድ ትውልድ አንድነቷን ጠብቃ በሰላም የመቆየቷ ዋናው እና አይነተኛው ሚስጢርም ይሄው በመኖር የተፈተነ እና በአብሮነታችንም የገነነ ሀገራዊ ታሪካችን ነው፡፡ በህዝቦቿ መካከል ፀንቶ የኖረውና ከዘር ከሀይማኖት በላይ የቆመው የመተሳሰብ፤ የህብረት፣ የፍቅር እና የጽኑ አብሮነት ባህል ስር ሰዶ መቆየቱም በዘመናት የመውደቅ መነሳት ታሪካችን ውስጥ እንዳንለያይ አርጎ በፍቅር የገመደን የአብሮነት ማህተባችን ነው። በኢትዮጵያ ዘላቂ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት ስርዓት አልበኝነትን አይታገስም። ጠ/ሚነስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ (ቪድዮ)

መንግስት ስርዓት አልበኝነትን አይታገስም። ጠ/ሚነስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ (ቪድዮ) ሕግና ሥርዓት የማህበረሰባችን መሰረት እና ያስተሳሰረን ነው። መንግሥት አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌና ሥርዓት አልበኝነትን አይታገስም።(ጠ/ሚነስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖችን ሲያስመርቅ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች:- • ነፃነትና ስርዓት አልበኝነት ባለመለየት መረን የወጣ ሕግና ስርዓትን የማያከብር የመንጋ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ መቆም ይኖርበታል፡፡ • ሕጋዊ ስርዓትን እያደከምን በመንጋ የሚሰጥ ፍትሕ ተከትለን በግል ስሜት መነዳት የለብንም፡፡ • ሕግ አልባና አመጽን የሚታገስ ስርዓት እንደ አገር መቆጠራችንን ከንቱ ስለሚያደርግ አገራዊ አንድነታችንን በሕግ አግባብ ማስጠበቅ የዘወትር ተልዕኮአችን ይሆናል፡፡ • ዘመናዊነት የሕግ የበላይነት ማክበር ነው፡፡ • እንደመር፣ በይቅርታ አንድ አገር እንገንባ ስንል ከመረን እንውጣ፣ ሕግ አናክብር በየከተማው ሽፍታ ይበራከት ማለት አለመሆኑን በአንክሮ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ • የይቅርታው ዓላማ ባለፍንበት መንገድ ያጣናውን ለማግኘት እንጂ የገነባነውን አገር ለማፍረስ ስላልሆነ እያንዳንዱ ዜጋ ይህ ከአብራኩ የወጣውንና በአነስተኛ ደሞዝ ሕይወቱን እየገበረ የአገር አንድነትን የሚያስጠብቀውን ኃይል የመውደድ፣ የማክበር፣ የሞራል ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡ • በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ያየነውን የመከላከያ አንድነት እና የለውጥ ኃይል መሆንን የማስቀጠል ፍላጎት በሁሉም ጄኔራል መኮንኖች እንዲደገም፣ በጡረታ የተገለሉ ጄኔራሎች ለወታደር ጡረታ ስለማይሰራ በየትኛውም ጊዜ ችግር ካጋጠመን እናት አገር ጥሪ ልታቀርብላቸው ስለምትችል ቀርባችሁ ሁኔታውን እያያችሁ በመምከር፣ በማገዝ፣ በመደገፍ፣ ወገናዊነታችሁን ማሳየት እንድትችሉ እንዳትበተኑ፣ አንድ ሆናችሁ አንዲት
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕዝባቸው ጋር ሊገናኙ ይገባል! የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አስቸኳይ መግለጫ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕዝባቸው ጋር ሊገናኙ ይገባል! የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አስቸኳይ መግለጫ ቀን፤ ነሐሴ 11፤ 2010ዓም ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ በተደጋጋሚ ከሕዝብ ጋር ቀጥተኛ ሲያደርጉ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝባቸው ጋር ግንኙነት ሳያደርጉ ሁለት ሳምንታት አልፈዋል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተለው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የጠ/ሚ/ሩ ደጋፊዎችና መላው ሕዝባችን ሁኔታውን እንዲያውቅና አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲወስድ ይፋ ለማድረግ ተገድዷል። በእርግጥ ዶ/ር ዐቢይ በተቀነባበረ በሚመስል ስልት ሁለት ሦስት ጊዜ ያህል ለሕዝብ ዕይታ ቀርበዋል። ሆኖም ከወትሮው በተለየ መልኩ ለውጡን አጥብቀው የሚቃወሙና ለማክሸፍ የሚፈልጉ ኃይሎች ያቀነባበሩት በሚመስል የተከናወነው ከሚዲያ ፍጆታ የማያልፍና በጥያቄ ውስጥ ያለውን ሕዝብ ለማርገብ የተሰራ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ሆኖ ነው ያገኘነው። ስለዚህ ሕዝባችን መሪውን የማግኘትና የማነጋገር መብቱ ሊነፈግ አይገባም፤ ይህም ባጭር ጊዜ ውስጥ በጋዜጣዊ መግለጫም ሆነ በፊት ሲደረግ እንደነበረው ዓይነት የውይይት መድረክ መገለጽ ይገባዋል በማለት አኢጋን አቋሙን በግልጽ ያስታውቃል። ከዚህ በፊት “የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ በየሰዓቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መገለጽ አለበት፤ ከእንግዲህ በኋላ በኢትዮጵያ የድብቅ ፖለቲካ አበቃ፤ …. የእኔ ሥራ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት … ማስፈጸም ብቻ ነው” የሚል ቃል የገቡልን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም የመደበቅ እና የመሸረብ ፖለቲካ ማብቃቱን ያበሰሩልን መሪያችን ሕዝብ እንዲህ ተጨንቆና ባገሩ ላይ የመኖር ኅልውናው አደጋ ላይ ወድቆ ባለበት ወቅት ከሕዝባቸው ጋር እንደበፊቱ እንዳይነጋገሩ የገደባቸው ኃይል ምንድነው? የጉራጌና የቀቤና ሕዝብ በተጋጨበት ወቅት በፍቅር ተግሳጽ ታረቁ ብለው መክረው ወዲያው ያስማሙ ብልሃተኛ ከሕዝባቸው ጋር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በስርአት አልበኞች ላይ እርምጃ አንዲወስድ ጠየቀች፡፡

መንግስት የሚያሳየው ትዕግስት ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ዕርምጃዎችን እንዲወስድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠየቀች፡፡ $bp("Brid_44804_2", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-529961874107237.mp4", name: "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት በስርአት አልበኞች ላይ እርምጃ አንዲወስድ ጠየቀች፡፡", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180817_153914.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“መደመር” እና የምርኮው ፖለቲካ (ጌታቸው ሺፈራው)

“መደመር” እና የምርኮው ፖለቲካ (ጌታቸው ሺፈራው) ባለፉት 27 አመታት ከአገዛዙ በተቃራኒ የቆሙ በርካታ የፖለቲካ ቡድኖች ነበሩ። በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያሉ/የነበሩ፣ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል የሚታገሉ ቡድኖች ከአገዛዙ ጋር የነበራቸው ልዩነት ሰፊ ነው። ይሁንና ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ከኦነግ ውጭ ያሉት የፖለቲካ ቡድኖች ምንም አይነት ድርድር ሳያደርጉ “ተደምረናል” ብለዋል። ተደምረዋል ሲባል አንድ ከገዥዎቹ ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ቡድን የሚያደርገውን ድርድር ሳያደርጉ ነው። ድርድር በአንድ ወቅት የሚታየው ክስተት፣ መልካም ሁኔታ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም። ቀጣይነቱም ላይ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። የዶክተር አብይ አህመድ መንግስት በውጭም በሀገር ውስጥም ለነበሩት ቡድኖች የሰጠው ተስፋና፣ “ተደምረናል” ያሉበት የመጀመርያው ነገር “ስለ አንድነት፣ ስለ ነፃነት” መሰል ነገሮች መስበክ ነው። በተጨማሪም የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት መጀመራቸው የፖለቲካ ቡድኖቹ ያለ መሰረታዊ ድርድር “ተደምረናል” እንዲሉ ያደረጓቸው ምክንያቶች ናቸው። አብዛኞቹ የፖለቲካ ድርጅቶች በቀናነት የተመለከቱት የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች መፈታት ጉዳይ በሕዝብ ትግል እና በእነ ዶክተር አብይ እንጅ ድርጅቶቹ ተደራድረው የተወሰነ ባለመሆኑ አሁንም ለሁሉም ተፈፃሚ አልሆነም። የፖለቲካ ድርጅቶች ለረዥም ጊዜ በመደራደሪያነት ያቀርቡት የነበረው “ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ” የሚል ጥያቄ እውን አልሆነም። እነ ዶክተር አብይ እንፈታለን ሲሉ “ካላችሁ መልካም ነው” ብሎ ማጨብጨብን የመረጠው፣ ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብሎ መክሮ አስገዳጅነት ያላስቀመጠቅ የፖለቲካ ሀይል አሁንም “ለምን ሁሉም አይፈቱም?” የማለት የሞራል የበላይነት አላገኘም። አሁንም እስረኞች እየማቀቁ ከገዥዎቹ ጋር እየተጨባበጠ ከመቀጠል ውጭ አማራጭ አልፈለገም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀይሎች
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከኤምሬቶች ባለሀብቶች ጋር የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክን ጎበኙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢንደስትሪ ፓርኩን የጎበኙት ከተባባሩት ዓረብ ኤምሬቶች ከመጡ ባለሀብቶች ጋር በመሆን ነው፡፡ የባለሀብቶቹ ልዑካን ቡድን ጉብኝት በኢንደስትሪ ፓርኩ ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ከኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ዱከም ኢንዱስትሪያል ፓርክ፣ በጅማና በቦንጋ የሚገኙ የጫካ ቡናዎችንም ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬት ባለሀብቶች ጋር በመሆን ነው የጎበኙት፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም ባለሀብቶቹ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸው ተገልጿል። በ61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጅማ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምእራፍ ግንባታ ከ93 በመቶ በላይ መከናወኑም ታውቋል። የፓርኩ የመጀመሪያ ምእራፍ ግንታባ ዘጠኝ ሼዶችን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጽዋል፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰላም አስተማማኝ እየሆነ ነው ሲሉ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰላም አስተማማኝ እየሆነ ነው ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰላምን አስተማማኝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አመራሮችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰላሙን ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ ሰፊ ምክክር ማድረጋቸውንና ከመግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም የክልሉ ሰላም ወደ ቀድሞው ይዞታ መመለሱን ተናግረዋል፡፡ የሰው ህይወትና ንብረት መጥፋቱ አሳዛኝ ድርጊት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የሶማሌ ክልል የመገንጠል ጥያቄ አንስቷል ተብለው ለቀረበላው ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ እንደ ዛፍ ፍሬ የሚገነጠል አይደለም፣ ግለሰቦች የፈጠሩትን ችግር መስመር ለማስያዝ እየተሰራ መሆኑን ለመገናኛ ብዙኃን ዛሬ ተናግረዋል፡፡ ebc
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኢምሬት የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አነጋገሩ።

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ጠዋት የተባበሩት አረብ ኢምሬት የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑትን ክብርት ሪም አል ሃሺሚን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ሁለቱ አገራት በኢንቨስትመንት እና የሁለትዮሽ ትብብር የሚጠናከሩባቸውን እና የሁለቱ አገራት ግንኙነት ጠንካራ መሰረት እንዲኖረው የሚችልባቸውን አጀንዳዎች ተነስተው በስፋት ተወያይተውበታል፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በጋሞ ጎፋ ዞን ምእራብ አባያ ወረዳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን አመራር የሚደግፉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው።

በጋሞ ጎፋ ዞን ምእራብ አባያ ወረዳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን አመራር የሚደግፉ ወጣቶች እየታሰሩ ነው። የደረሰኝ ሙሉ መረጃ ይኸው 👉 ማሕሌት ፋንታሁን “ምዕራብ ዓባያ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መስተዳድር፥ በጋሞ ጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች አንዷ ናት። በወረዳዋ ውስጥ የሚገኙ የዶ/ር አብይ አህመድ ደጋፊዎች “ለውጥን እንደግፍ፥ ዴሞክራሲን እናበርታ” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ለማካሄድ ኮሚቴ አዋቅረው በህጋዊ ደብዳቤ (የኮሚቴዎችን ስም ዝርዝርና ኋላፊነት እንድሁም በዕለቱ ስለምከናወኑ ተግባራት ዝርዝር የያዘ) የወረዳውን አስተ/ር በመጠየቅ የወረዳው አስተ/ርም አዎንታዊ ነልስ ለኮሚቴው በመስጠት የድጋፍ ሰልፉ በቀን 24-11-2010 ዓም (ማክሰኞ ዕለት) እንደሚካሄድ ከተስማሙና ለዝግጅቱም አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅቶች (ባንድራዎችን መስፋት፥ ለህብረተሰቡ የቅስቀሳ ሥራ፥ ወዘተ) እየተደረጉ ባሉበት ወቅት ከቀናት ልዩነት በኋላ የወረዳው አስተ/ር የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪ ክኮሚቴዎችን ዳግም በማስጠራትና በመሰብሰብ የድጋፍ ሰልፉን እንደከለከሉ አስታወቃቸው። ለዝህም እንደምክንያት የተጠቀሰው ወረዳዋ የድጋፍ ሰልፉ ከተፈቀደ በኋላ የስጋት ቀጠና ሆናለች በሚል ከዞን የመጡ አመራሮች የጋሞ ጎፋ ዞን አስተ/ር አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ እንድሁም የፀጥታ መምሪያ ኋላፊው አቶ ቤታ አንጁሎ ወደ ወረዳዋ ድረስ በመምጣት የድጋፍ ሰልፉን ከልክሉ ብለውናል የሚል ነው (የወረዳዋን ወቅታዊ ሁኔታ ከዞን አመራሮች በላይ እንደሚያውቅ እየታወቀና ችግሮች ብኖሩም እንኳን እችላለሁ ብሎ የወረዳው አስተ/ር ከፈቀደ በኋላ ለዞን አመራሮች ቅድሚያ በመስጠት ከሕዝቡ ተቀንሷል)። ስለሆነም በነዝህ ቀናቶች ውስጥ ስለድጋፍ ሰልፉ ቅስቀሳ በፌስቡክ ቀስቅሳቿል፥ በፌስቡክ አመራሮችንና ባለሀብቶችን ሰድባችኋል፥ የቀን ጅብ ብላችኋል ተብለው እንድሁም ኮከብ የሌለውን ህገ-ወጥ ባንድራ ሰፍታችሁ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወደ ሚኒሶታ ስንሔድ ህዝቡ በ11 ስታዲየሞች ተሰብስቦ ጠበቀን፣ ከዚያ በስንት ድርድር ወደ አንድ መጣ ፦ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ከመድረክ ጀርባ ስንት ጉድ እንዳለ ተመልከቱ! .ይድነቃቸው ከበደ “ወደ ሚኒሶታ ስንሔድ ህዝቡ በ11 ስታዲየሞች ተሰብስቦ ጠበቀን፣ ከዚያ በስንት ድርድር ወደ አንድ መጣ” . ዲያቆን ዳንኤል ክብረት . ” የኢሳቱ ብሩክ ይባስና አበበ ገላው ወዲያና ወዲህ የቆሙ ኃይሎች ለአንድ ዓላማ እንዲሰለፉ ሌት ተቀን የደከማችሁትን ድካም መቼም አልዘነጋውም ” . የሦስት ወሩን አድካሚና አስደሳች ሩጫ አገባደድነው፡፡ አሁን የቀረን ዝርዝር ሪፖርቱን ተረጋግቶ መጻፍ ነው፡፡ ብዙ አስገራሚ፣ አሳዛኝ፣ አስደሳች፣ አስቂኝ ገጠመኞችን በቀጣዮቹ ቀናት አወጋችኋለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በአሜሪካ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለማነጋገር ወደ አሜሪካ እንደሚሄዱ የታቀደው ግንቦት ወር ላይ ነው፡፡ የዳላሱ የኢትዮጵያውያን ስፖርት በዓል ግብዣ ሲመጣ ነገሩ ሌላ መልክ ይዞ ነበር፡፡ ጋባዡ ማን ነበር? ክልከላውስ ከየት መጣ? በብዕር ወደፊት እንራመድበታለን፡፡ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የርእሳነ መንግሥታት ታሪክ ወደ አሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎች በዋናነት ከአሜሪካ መንግሥት፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከሌሎች ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ የዲያስፖራው ጉዳይ በጎንዮሽ የሚያዝ ነው፡፡ የዚህኛው ጉዞ ዋናው ልዩነቱ በዋናነት ኢትዮጵያውያንን ለማግኘት የተዘጋጀ መሆኑ ነው፡፡ ለአዲስ ሐሳብ አዲስ አካሄድ በሚል ጉዞውን የሚያስተባብረው ኮሚቴ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከባለ በጎ ፈቃድ ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡ የዳሰሳ ጥናት ተዘጋጀ፡፡ ዝርዝር ዕቅድ ወጣ፡፡ መጀመሪያ በዋሽንግተን ዲሲ በመቀጠል በሎስ አንጀለስ በመጨረሻም በሚነሶታ ኮሚቴዎች ተቋቋሙ፡፡ እንግዳው ነገር ተጀመረ፡፡ የኢሕአፓ፣ የመኢሶን፣ የቅንጅት፣ የኢሕአዴግ፣ የሰማያዊ፣ የግንቦት ሰባትና የሌሎቹም ፓርቲዎች አባላት በአንድ ኮሚቴ ውስጥ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ቀረበ፡፡ አባሎቻቸውና
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዋሽንግተን ዲሲና ሎስ አንጀለስ ድልድዩ ፈርሷል፤ በሚኒሶታ ፍርስራሹ ተጠርጓል¬- ጠ/ሚ ዶክተር አብይ

በዋሽንግተን ዲሲና ሎስ አንጀለስ ድልድዩ ፈርሷል፤ በሚኒሶታ ፍርስራሹ ተጠርጓል¬- ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በአካባቢው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የባሰባሰብ በዚህ መድረክ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳና የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተገኝተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለህዝቡ ባስተላለፉትም መልዕክት የተበተነው ህዝብ ተደምሮ በሀገሩ ላይ እንዳይሳተፉ የተጋረጡበትን ግንብ መደርመስ ያስፈልጋል ሲሉ ንግግራቸውን ጀምረዋል። የተገነባው ግንብ ብዙ ቋንቋ በመናገራችን፣ ከተለያየ ዘር መምጣታችን እና ኃይማኖት መከተላችን አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እነዚህ ሁሉ ውበታችን ናቸው ብለዋል። እኛን የለያየን የጥላቻ ፣ የመናናቅ ፣ የራስ ወዳድነት ፣ የቂም በቀል ግንብ ነው፤ በኛ ዘመን ይህ የተከለከለ ነው ልንል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። በአሜሪካ የመደመር ጉዞ በዋሽንግተን ዲሲና ሎስ አንጀለስ ድልድዮ እንደፈረሰና በሚኒሶታ ደግሞ ፍርስራሹ መጠረጉን በመድረኩ ላይ ጃዋር መሀመድን በማቀፍ ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ አብስረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አማራ ለኦሮሞ፣ ኦሮሞ ለሶማሌ፣ ሶማሌው ለሌላው ስጋት ሳይሆን ጉልበት መሆኑን ገልፀዋል። ልጆቻችን ተነጋግረው መወያየት እንዳይችሉ፤ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርገናልና ያንን ለማካካስ ተደምረን ቀን ከሌት መስራት አለብን ሲሉ ነው ያሳሰቡት። ሀገር ስትፈርስ የሚጠቀመው ማን ነው? ከሌሎችና ከታሪክ ተምረን በፍቅር አንዲት ታላቅ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ትሩፋት የምትሆን ሀገር መገንባት ይኖርብናልም ብለዋል። የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው፥ ዘር፣ ሀይማኖት ሳይገድበን እንዲህ ባማረ ሁኔታ መገናኘታችን ያስደስታል ሲሉ የተሰማቸውን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአንድነት ኃይሉ ዕጣ (ሚኪ አምሐራ )

የአንድነት ኃይሉ ዕጣ (ሚኪ አምሐራ ) ዶ/ር አብይ እና ዲያስፖራዉ ጥሩ የሚባል ግንኙነት እያካሄዱ ነዉ፡፡ እነ ታማኝንና ሌሎች አክቲቪሰቶችን ማግኘቱ ለጠሚዉ የወደፊት ስራዉ ቀና ያደርግለታል፡፡እነ ታማኝ ትልቅ ቡድን የሚመሩ እና ሚዲያ ጨምሮ ትልቅ ተጽእኖ ያለዉ ሰዉ ነዉ፡፡ ኢሳትንና ኢሳት ዉስጥ የሚሰሩ ሰዎችንም ጠሚዉ ማሞጋገሱ በእርግጠኝነት የወደፊት ስራዉን እጅግ አቅልሎለታል፡፡ አሁን ባጠቃላይ የአንድነት ካምፑን በእጁ አስገብቷል፡፡ዲያስፖራዉ በጠሚዉ እጅግ ደስተኛ ነዉ፡፡ የፓርቲ አባላት እንኳን ጠሚዉን ላለማስቀየም በሚመስል ሁኔታ የሚጠይቁት የፖለቲካ ጥያቄ አስቂኝ ነበር፡፡ በዚህ መሃል ያሳዘነኝ አምባሳደር ተክለብርሃን ነዉ፡፡ ዝግጅቱን በተቻለ መጠን ለማጥበብ እና አንዳንድ ሰወች ከጠሚዉ ጋር እንዳይገናኙ የማድረግ ስራ ሰርቷል እየተባለ ሲወቀስ ሰንብቶ ነበር፡፡ ከዛም በላይ ግን ዶ/ር አብይ እነ ተስፋየን፤ እነ ገዱን እና አምባቸዉን ሲያመሰግን ፊቱ ይቀላ ነበር፡፡ ስለ ሌብነት እና አጎብዳጅነት ሲያወራም እንዲሁ፡፡ የተከለከለዉ ታማኝ መድረክ ላይ ሲወጣም እንዲሁ፡፡ የዶ/ር አብይ የአንድነት ሃይሉን በእጁ ማስገባቱ ግን የብሄር ፖለቲካዉን በደንብ ማጦዙ አይቀርም፡፡ በ 2012 ምርጫ ከኢህአዴግም ከሌሎች የአንድነት ፓርቲም በተሻለ የብሄር ፓርቲ እና ፖለቲካ የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ለምን? 1.የአንድነቱ ቡድን ከዚህ በኋላ ከኢህአዴግ የተለየ የፖለቲካ አማራጭ የማምጣት አድሉ ጠባብ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ኢህአዴግ እዉነተኛ ዲሞክራሲ ማራመድ ከጀመረ ለምሳሌ ነጻ ሚዲያ፤ ፍርድ ቤት፤ የምርጫ ሁኔታ፤ ወታደሩን ደህንነቱን እና የመሳሰሉትን ሪፎርም አድረጎ ሌሎች ተቋማትንም በሁለት አመት ዉስጥ ከፖለቲካ ነጻ አድርጎ ከመሰረተ የአንድነቱ ቡድን ከዚህ የተለየ የፖለቲካ ርዮተ አለም ወይም አጀንዳ አይኖረዉም፡፡ምናልባት ኢህአዴግ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በዋሽንግተን ዲሲ ለኢትዮጵያው ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ነጥቦች

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በዋሽንግተን ዲሲ ለኢትዮጵያው ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ነጥቦች •የኢትዮጵያዊነትን ህብር ቀለም ስላሳያችሁን አመሰግናለሁ • የጋራ ዕራይ መሰነቅ ለዛም መሰለፍ ለዓለም ያስመሰከራችሁ በመሆናችሁ ግርምት ፈጥራችኋል • ኢትዮጵያዊነት ከደማችን ጋር የተዋሀደ መሆኑን ዋሽንግተን ምስክር ናት • ለ40 ዓመታት የገነባነው ከፋፋይና የጥላቻ ግንብ ለማፍረስ ዛሬ ቃል እንግባ • ስንደመር የኢትዮጵያን ቀን የምናውጅ መሆናችንን ዛሬ አይተናል • ግንቡን ማፍረስ ብቻ በቂ አይደለም ስለዚህ ግንቡን እዳፈረስን ድልድዩን እንገንባ • የሚገነባው ድልድይ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ለትውልድም ጭምር ሊሆን ይገባል • እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ አደዋ ዛሬም ታሪክ እንሰራለን • ኢትዮጵያዊነት ተፈትሎ የተሸመነበት ድርና ማግ ስንርቅ የሚበጠስ በለአንድ ቀለም ነጠላ ሳይሆን አውታረ ብዙ ረቂቅ ጥበብ ነው • በይቅርታ ዛሬ እንደመር • ከመቶ ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ስንደመር አንድ ቢሊየን አፍሪካን እንመራለን • ያልተሰጠን የለም ምንም እንደሌለን ያደረገን በጋራ አለመምራቸን ነው • ኢንጂነር ስመኘውን መግደል እንጂ የህዳሴ ግድብን ማቆም አይቻልም
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የልጅ እያሱ እና የዶክተር አብይ እጣ (ጌታቸው ሺፈራው)

የልጅ እያሱ እና የዶክተር አብይ እጣ (ጌታቸው ሺፈራው) በኢትዮጵያ ታሪክ ያልተፃፈላቸው ብዙ መፈንቅለ መንግስቶች ተደርገዋል። የሁለት፣ ወይንም የሶስቱን ብቻ በታሪክ እናገኘዋለን። ~በቀዳሚነት ተፅፎ የምናገኘው የ1953 ዓም መፈንቅለ መንግስትን ነው። ይህ መፈንቅለ መንግስት ስርዓቱ ኮትኩቶ ባሳደጋቸው፣ ለንጉሱ ሰግደው፣ የንጉሱን ትዕዛዝ የቅዱስ መፅሐፍ ቃል ያህል ሲያከብሩ የኖሩ የሞከሩት ነው። በዚህ ስርዓት ውስጥ ያደጉት መኮንኖች የሕዝብ ብሶት፣ የስርዓቱ ድክመቶችና ሌሎች ለውጦችን ሲገነዘቡ ያደርጉታል ተብለው የማይታሰበውን አድርገውታል። ~ሌላኛው በታሪክ ውስጥ የተሻለ ሰነዶች ያሉት የ1981 ዓም መፈንቅለ መንግስት ነው። በ1953 ዓም ቃላቸው የመፅሐፍ ቃል አድርገው የሚወስዱት፣ “ጃንሆን” እያሉ መንበራቸው ላይ እንደተነሱት ሁሉ፣ በአንድ ወቅት ኮ/ል መንግስቱን በማርክሲስም ሽፋን ንጉስ አድርገው ይቆጥሩ የነበሩ፣ ከጓድ መንግስቱ አመራር ሲሉ የነበሩ መኮንኖች የፈፀሙት ነው። ልዩነቱ በአጤው ዘመን መለኮታዊ፣ በደርግ ወቅት ርዮትዓለማዊ መሆኑ እንጅ ሁለቱን መሪዎች መኮንኖቹ ለማምለክ ደርሰዋል። ~ሶስተኛና በክስ ደረጃ ተፅፎ የሚገኘው በ2000 ዓም ተደረገ የተባለው ሲሆን ይህን ሙከራ አደረጉ የተባሉትም ከሁለቱ ስርዓቶች የሚለዩበት አውዶች ቢኖሩም፣ በስርዓቱ ያደጉ “ታጋዮች” አደረጉት የተባለው ነው። የዚህኛው ልዩነት ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ መገፋቱን በዚሁ ማንነት ላይ የመጣ መሆኑ ነው። ~ብዙውን ጊዜ የማይወራለት ልጅ እያሱ ላይ የሆነው ነው። ልጅ እያሱ በወቅቱ በነበረው ፖለቲካ ሕጋዊ ማዕቀፍ የነበረው ቢሆንም አቅም የነበራቸው አካላት ግን ከጎኑ አልነበሩም። ከልጅ እያሱ ይልቅ ለተፈሪ መኮንን ቅርበት የነበራቸው አካላት የልጅ እያሱን በአጤ ምኒልክ የተሰጠ ንግስና (በወቅቱ ሕጋዊ፣ ወይንም ምክንያታዊ) በሀይላቸው ወደ ተፈሪ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረጉት ንግግር ያዳምጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረጉት ንግ ግር ያዳምጡ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ዶክተር ብርሐኑ ነጋ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር ተወያዩ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ዶክተር ብርሐኑ ነጋ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር ተወያዩ Berhanu Nega has just left the Watergate Hotel in Washington D.C., where he met with PM Abiy Ahmed.   ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በዋሽንግተን ዲሲ በዋተርጌት ሆቴል የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር የሆኑትን ደክተር ብርሃኑ ነጋን ተቀብለው ማነጋገራቸውና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ታውቋል። በቅርቡ የትጥቅ ትግሉን ማቆሙን በገሃድ ያወጀው የአርበኞችግንቦት ሰባት መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጋር ሲገናኙ ዶክተር ብርጋኑ ነጋ ሁለተኛው ናቸው ። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ፀሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከተፈቱ በኋላ ከተቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል።
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ መፍጠር ለሃገሪቱ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው- ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ መፍጠር ለሃገሪቱ ሰላም መሰረት የሚጥል ነው- ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች እርቅ በመፈፀማቸው መደሰታቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ። በዋሽንግተን ዲሲ በእርቁ ማብሰሪያ ጉባኤ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አንድ እንድትሆን የምንፈልገው ሀገር ስለሆነች ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለም ሀገር የምትበቃና በሰላም፤ በአንድነት እና ልማት ረገድ ምሳሌ የምትሆንናት ብለዋል፡፡ ይህች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረች ባለታሪክ ቤተክርስትያን ባለፉት አመታት አንድነቷ በለመጠበቁ ገናነታችንን አጥተናል፡፡ ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት ለዚህ እርቅ መሳካት ላደረጉት ጥረት በእኔና በኢትዮጵያ መንግስት ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ አባቶች እንደ ልማዳቸውና ባህላቸው ሀገራችን ሰላም የሰፈነባት እንድትሆን በጸሎት እንዲያግዙም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጠይቀዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኦነግ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ስርዓት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ያዳምጡ

  ኦነግ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ስርዓት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።  ያዳምጡ $bp("Brid_36991_3", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/07/Ethiopia_-የ-ኦነግየኦሮሚያ-ነጻ-አውጪ-ግንባር-ማስጠንቀቅያ-OLF-O.mp4", name: "ኦነግ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ስርዓት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ያዳምጡ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/07/IMG_20180724_162159.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመደመር ተግዳሮቶች!? ( ከኬና ቀኖ)

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከመጡ ወዲህ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው ቃላት ዋነኛው መደመር የሚለው ነው፡፡ ትርጉሙም፤  በጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት ተብራርቷል። በፍቅርና በይቅርታ፣ ወደ አንድነትና መግባባት እንድንመጣ ለማሳሰብ ተጠቅመውበታል፡፡ ይሁን እንጂ መልካም ነገሮች ፈተና እንደሚኖራቸው ሁሉ መደመርም በተለያዩ መንገዶች በእጅጉ እየተፈተነ ይገኛል፡፡ ከፈተናው የጉልህ ድርሻ የሚወስደው የኛ የኢትዮጵያውያን የተቃርኖ ትርክት ነው፡፡ በተቃራኒ የቆሙና ጽንፍ የረገጡ አተያዮቻችን! ይህንን ተቃርኖ ሁልጊዜ በሚያጋጥሙን ትናንሽ ሁነቶች፣ ለምሳሌ እገሌ የሚባል ዘፋኝ እንዲህ አይነት ባንዲራ ያዘ… ልንመልሳቸው በማንችለው የታሪክ ስህተቶች ምክንያት እየተናቆርንና እየተጨቃጨቅን መቀጠል እንደሌለብን አምናለሁ፡፡ ከዚህ አንጻር እንዴት ተቃርነን ሳይሆን ተግባብተን መደመር እንደምንችል  ለመጠቆም እሞክራለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገር ምስረታን ያከናወኑት አፄ ምኒልክ፤ የግንባታውን ዘርፍ፣ ሁሉንም የሀገሪቱን ህዝቦች በሚያረካ መልኩ እንዳልፈጸሙት፣ ብዙዎቹ የታሪክ ምሁራን ይሞግታሉ፡፡  አፄው ከባድ የሆነውንና የመጀመሪያውን ዘርፍ ስላከናወኑ፣ ግንባታው ከሳቸው ይልቅ በተከታታይ ከመጡት ገዢዎች ይጠበቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ፤ አሁን ላይ ቆመን እንድትገነባ በምንፈልግበት ሁኔታ ሳትገነባ ቀረች፡፡ ብዙ ቁርሾዎች እንዲፈጠሩም ዕድል አገኙ። አብዛኛውም ተገለልን ብሎ አማረረ፡፡ ይህም ሄዶ ሄዶ፣ ኤርትራን አስገነጠላት፡፡ ሌሎቹም ይቺን ዳንዲ ተመኙ፡፡ እንዲህ አይነት ስሜቶች አሁንም ድረስ እኛ ዘንድ አሉ፡፡ ጉዳዩን ክደን ወይም ሸሽተን የትም አንደርስም፤ተግባብተን መፍትሔ መፈለግ እንጂ! የኛ ነገር አብዛኛው በተቃራኒ መቆም ሆኖ አልፏል። አሁንም ከዚህ እንዳልወጣን የሚያሳዩን ምልክቶች አሉ። አንድ ሀገር ነው ያለን፡፡ በብሔራዊ ምልክቶቻችን ግን እንቃረናለን! ሀገራችን አንድ ናት፡፡ ነገር ግን በሀገራዊ ጀግኖቻችን አንግባባም! አንድ ሀገር ነው ያለን፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሐሰት መረጃ እየለቀቁ ያሉት ትግራይ ውስጥ የተደበቁ ሰወች ናቸው ሲሉ ዶክተር አብይ ለመምሕራን ተናገሩ።

ጠ/ሚ ዶ/ር አበይ ከምሁራን ጋር በነበራቸው ውይይት ያነሷቸው ዋና ዋና አሳቦች 1.ኢህአዴግ በቅርቡ ፍልስፍናውን እና ምልክቱን ይቀይራል ፡፡ አብዛኛዎቹ የክልል መስተዳደሮችም ይቀየራሉ 2. ብዙ ወንጀል ሠርተው ትግራይ ውስጥየተደበቁ ሠዎች አሉ፡፡ እነሡ ናቸው ያልሆነ መረጃ የሚለቁት። 3. በስልጣን እስከቆው ድረስ የትግራይን ህዝብ ጠቅሜ ነው የምወርደዉ ፡፡ ከጥቅምቹ አንዱ የኤርትራን ጉዳይ መጨረስ ነው ። 4. ኢሳያስን መቀሌ ይዤው ብሄድ ደስ ባለኝ ግን እንደለመዱት የሆነ ነገር አድርገው ያልሆነ ነገር ውስጥ የከቱናል ብዬ ነው ። 5. የኔ ዋና ግብ በሚቀጥለው ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ነው ። 6. የህዳሴው ግድብ በሚቀጥሉት 10 አመታት አይጠናቀቅም፡፡ ብዙው ነገር ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወሬ በቻ ነበር ። 7.ችግሮች እንዲፈቱ ስለፈለኩኝ የጉራጌ ብሔረሠብን በባለፈው የወልቂጤ ውይይት ተጨኜዋለው፡፡ የጉራጌ ዘርማ ታሪክ ሠርቷል ፡፡ ጉራጌ አሁንም ያለ ቀቤና አያምርበትም፡፡ 8. የባንድራው ጉዳይ ልክ እንደ ሀገ መንግስቱ የማይሻሻልበት ምክንያት የለም፡፡ 9. አብዛኛዎቹ ሚዲያዎች የሆነ ቡድን አሳብ ማስፈፀሚያ ናቸው፡፡ የENN ቴሌቪዝን ስለ በደሌ ያቀረበው የተሳሳተ መረጃ የተፃፈውና የተዘጋጀው መንግሰት ቢሮ በባለ ስልጣን ነው፡፡ 10. የት/ት ጥራትን በተመለከተ በሠፊው እየሠራን ነው 11. የመምህራን ደሞዝና ጥቅም በተመለከተ ዝቅተኛ መሆኑን እናውቃለን ስለ እሱም እንወያያለን የውይይቱ ተሳታፊ የነበረው ወንድማችን Daniel Mekonnen ተሳታፊ ከነበሩት ሌክቸረሮች አንዱ ከጻፈው https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2085933348144955&id=100001849297644
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቱ ተባረው የነበሩ 42 መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሱ አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከ50 ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ 3175 መምህራን ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቱ ተባረው የነበሩ 42 መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከብሄራዊና ክልላዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከብሄራዊና ክልላዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከ22 ብሄራዊና 30 ክልላዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አራቱ ክልላዊ የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲዊች መንግስት በቅርቡ ባደረገው ጥሪ መሰረት ከውጭ ሃገር የተመለሱ ናቸው ተብሏል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር አብይ አሕመድ ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አደረጉ

(ሐምሌ 11፣ 2010 ዓ.ም) ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በኢትዮያና በአሜሪካ የሚገኙትን የሀይማኖት አባቶች በማስማማት በቅርቡ የሰላም እና የፍቅር ብስራት በኢትዮጵያ እንደሚመጣ ኮሚቴው እንዲሰራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ለዚሁ ሲባል ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አሜሪካ በማቅናት የእርቅ ምዕራፉ እንደሚቋጭ ይጠበቃል፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር አብይ ቃሉን በልቷል (ጌታቸው ሺፈራው)

ዶክተር አብይ ቃሉን በልቷል (ጌታቸው ሺፈራው ~ክፍል 1)   ዶክተር አብር አህመድ መቀሌ ላይ ስለ ወልቃይት በተናገረው ያልተገባ ነገር ተቃውሞ ሲሰማበት ሚያዝያ ወር መጀመርያ ወደ ጎንደር መጥቷል። ጎንደር ጎሃ ሆቴል በነበረው ስብሰብ ከተነሱለት ጥያቄዎች አንዱ ለሱዳን ስለ ኢትዮ_ሱዳን ድንበር ነበር። በወቅቱ የሰጠው መልስም “ነገ አልበሽርን አገኘዋለሁ። ተገናኝተን እናወራለን።… …በቅርቡ የሕዝቦች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይገታ እናደርጋለን” የሚል ቃል ገባ። ሕዝብም ችግሩን ያውቀዋልና አጨበጨበ። ዶክተር አብይ አልበሽርን ባህርዳር በነበረው የጣና ፎረም አገኘው። በጥቂት ቀን ውስጥ “መፍትሄ እንሰጥበታለን፣ ሕዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ይሆናል” ካለ ከሶስት ወር በኋላም የሱዳን ሰራዊት የአማራ ገበሬዎች ላይ ከባድ መሳርያ እየተኮሰ፣ ድንበር ጥሶ እየገባ ነው። ሰኔ 4/2010 ዓም በተጠናከረ ሁኔታ የጀመረው የሱዳን ወረራ የእነ ዶክተር አብይን ትኩረት አላገኘም። ከሰኔ 4/2010 ዓም ጀምሮ ገበሬዎች ታፍነው ወደ ሱዳን ተወስደዋል፣ አራት ሰራተኞችና አንድ ባለሀብት እርሻቸው ላይ እያሉ ተገድለዋል። የገበሬዎች ማሳ በሱዳን ሰራዊት ወድሟል። ካምፓቸው ተቃጥሏል። ከአስር ቀን በፊት በተደረገ ወረራ ከ7 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በሁለተኛው ቀን መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ቦታው ቢያቀናም “ከቻላችሁ ገበሬውን አረጋጉ፣ ካልሆነ ተመለሱ” የሚል ትዕዛዝ ሲሰጣቸው ገበሬውን ያገዙት ከትዕዛዝ ያፈነገጡ የተወሰኑ አባላቱ ብቻ ነበሩ። የሱዳን ሰራዊት በከባድ መሳርያ፣ የአማራ ገበሬ በነፍስ ወከፍ መሳርያ ጦርነት ሲገጥሙ ዳር ድንበርን ለማስጠበቅ ግዴታ ያለበት፣ ከሶስት ወር በፊት ” በቅርብ ቀን ሕዝብ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር እናደርጋለን” ያለው አብይ መንግስት ያደረገው ነገር አልነበረም። ገበሬው በሱዳን ጦር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሀገር በቀል አዲሱ የኢትዮጵያ ርዕዮተ ዓለም (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

ፍቅራቸው የነካው ሺህ ዓመት ንገሱ ሲላቸው፤ ሌላው እንዴት መንግስት ይሸጋገራል ብሎ ሲያወጣና ሲያወርድ፤ ሌላኛው ደግሞ አምባገነን ስርዓት እየመጣ ነው ብሎ ሲቃወም ይታያል። ለማያስተውል ሰው፤ የዶ/ር ዐቢይ መንግስት ወዴት ይሄድ ይሆን ብሎ ግራ ሊገባው ይችላል። ለእርሳቸው በቂ ጊዜ ሰጥተን ተልዕኳቸውን በሚመጥን መልኩ እንዲመሩን ዕድል ልንሰጥ ይገባናል፡፡ ይህ የእርሳቸው አመራር፣ የለመድነው ፍሬ አልባ የሽግግር መንግስት ሲባል ያየነው ዓይነት አይደለም። የፅሁፌ ጭብጥ ሀሳብ፤ ይህ የእርሳቸው መንግስት ያልነበረ፥ ወደፊትም ሊኖር የማይችል፤ በዓይነቱ በዓለም የመጀመሪያው የሆነ የአዋላጅ መንግስት ስርዓት እንደሚሆን ላስረዳ እሞክራለሁ። ከዚያ በሁዋላ የሐቅ ምርጫ ዳኛ ይሆንልናል። ዶ/ር ዐቢይ፤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከሁለት ምርጫ በላይ መሆን የለበትም ያሉት፣ ያኔ ህግ ስለሚሆን ሀሳብ አይግባን። የዲሞክራሲ ስርዓት አብዛኛው ሰው የመረጠውን መንግስት ይሰጠናል። ይህ ግን በራሱ መልካም መንግስት ያመጣል ማለት አይደለም። በዲሞክራሲ እንደ ምሳሌ የምትነሳው አሜሪካ፤ በጥቂት ቁጥር ልዩነት አንዴ ዲሞክራቲክ ፓርቲ አለያም ደግሞ ሪፐብሊካን ፓርቲ እየተቀያየሩ የሚነግሱባት ሀገር ናት። ሶስተኛ አማራጭ ፓርቲ እስካሁን አቅም አግኝቶ አያውቅም። ስለዚህም የሚመረጠው መንግስት ባብዛኛው ግማሹ ሕዝብ ያልመረጠው ነው። አንዱ ፓርቲ የገነባውን አንዱ እያፈረሰና እርስ በርስ እየተናቆረ ዲሞክራሲ በሀገረ አሜሪካ ይከናወናል። በዲሞክራሲ ጀምረው በአምባገነንነትም የጨረሱ እንደነ ቱርክ ያሉ ሀገራትም አሉ። ስለዚህ ዲሞክራሲ የሚባለው ጉዳይ ጅማሬ ይሆን እንደሆነ ነው እንጂ፤ በራሱ መድሃኒት አይደለም። ስለዚህ ከምናውቀው ዲሞክራሲ የተሻለ ራዕይ ይኖረን ዘንድ ያስፈልጋል። ለዚያ ደግሞ ኢትዮጵያ መንገድ የጀመረች ትመስላለች። ያም ሆነ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሚኒስትሮቹ —- 100 ቀናትስ? ( ከዳግላስ ጴጥሮስ )

የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ዋልታና ወጋግራ አፅንተው ካቆሙት መልህቆች መካከል ሦስቱ በመሠረታዊነት ይጠቀሳሉ፡፡ በሦስቱ ውስጥ በርካታ ዘለላዎች ስለሚተነተኑ፣ ለጊዜው የሃሳቤን ሰንሰለት አንዘልዝዬ ለማራዘም አልሞክርም፡፡ ሠልስቱ መልህቆች የሚባሉት፤ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚውና ማኅበራዊው ሥርዓቶች ናቸው፡፡ ሉዓላዊ ሀገር ያሰኘንም የእነዚህ የሦስቱ መልህቆች ጥምረት ነው፡፡ የትናንቷ ጀምበር ጠቁራብን በነበረበት የአምና ካቻምና ዕለታት ግን ሦስቱ መልህቆች ከታሠሩባቸው ገመዶች ተላቀው፣ “እናት ዓለም ኢትዮጵያ” እንደምን በዐውሎ ነፋስ ወጀብ ልትደፈቅ ዳር ዳር እንዳለች የምናስታውሰው ነው፡፡ የፖለቲካው ገጽታ አስፈሪ ጭምብል ለብሶ እንዳትደርሱብኝ እያለ ብዙዎችን በማግለልና ጥቂቶችን ብብቱ ውስጥ በመሸጎጥ እሹሩሩ እያለ ሲያሞቃቸው ስለመኖሩ ምስክር አያሻውም፡፡ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ወገኖች፤ ወይ ለእስራት፣ ወይ ለስደት፣ አለያም ለመገፋት ስለሚዳረጉ የሕዝባችን አንደበት በዝምታ ነቅዞ ነበር፡፡ በአንፃሩ የፖለቲካውን የጨረቃ ፋኖስ የጨበጡት “ዘመንኛ ልሂቃን” – “የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን” እያሉ ለውጥ እንደማይታሰብ፣ “በመቃብራቸው” ያስፈራሩን እንደነበርም አንዘነጋም፡፡ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አኪርም እንዲሁ ተሰብስቦ ወደ “ኢምንት ልሂቃኑ” ኪስ ውስጥ ተከማችቶ ስለነበር እኛ ብዙኃንና ግፉዓን ዕጣችን፣ የበይ ተመልካች መሆን ብቻ ነበር፡፡ “የሀገራችንን የሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት” እያወደስንም “ተመስገን” በማለት የሁለት አሠርት ተኩል ዓመታትን እያጨበጨብን ማሳለፋችን አይዘነጋም፡፡ ሊዘነጋም አይችልም፡፡ ማስረጃ አምጡ ከተባለም የአንድ ሰሞን ሚሊዮን ነጋዴዎችን፣ የተንጣለሉ ሰፋፊ እርሻ ባለቤት ለመሆን በላብ ሳይሆን በመሳሳብ የገነኑትን፣ ለምድር ለሰማይ የከበዱ የባንክ ተበዳሪዎችን፣ “ለከተማችን ልዩ ውበት ያጎናፀፉ ሰማይ ጠቀስ ምንትሶችን” የገነቡልንን የአንድ ሌሊት ብሩካን መዘርዘሩ አይገድም፡፡ የጠቃቀስኳቸው ምስክሮች ለዋቢነት የማይበቁ መሆናቸው ለጥርጥር የሚዳርግ ከሆነም
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር አብይ በተናገረ ሰዓት ብቻ ማጨብጨብ ሳይሆን ንግግሩ ወደ ድርጊት እንዲለወጥ በግንባር ቀደምትነት ልንሰራ ይገባል።

ትልቅ ነቀርሳ ላያችን ላይ ተተክሏል። አለማዳመጥ ፣ በጥልቀት ያለማንበብ ፣ ችኮላና ብስለት ማጣት ፣ ትችትን መሸሽ ፣ ውይይትን መሸሽ ፣ ዘለፋን መሸሸጊያ ማድረግ ፣ ሮጠን የዘር ስልቻ ውስጥ መደበቅ ፣ በራስ አለመተማመን ፣ እውነትን መሸሽ፣ ሚዛንን አዛብቶ ቡድንና ሕዝብን አለመለየት፣ በሃሳብ ነጻነት አለማመን ፣ ወዘተረፈ ካንሰር ተጠቅተናል። አካሔዶችን መተቸት ማለት መደመርን አሊያም ዶክተር አብይን መቃወም ማለት አይደለም።   የዶክተር አብይ አስተዳደር ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ያሳያቸው መልካም ጅማሮዎች ወደ ተግባር እንዲለወጡ እያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታ አለብን። ዶክተር አብይ በተናገረ ሰዓት ብቻ ማጨብጨብ ሳይሆን ንግግሩ ወደ ድርጊት እንዲለወጥ በግንባር ቀደምትነት ልንሰራ ይገባል። ይህን አይነት የተግባር ተሳትፎ ማድረግ ከቻልን ቃልን ወደ ድርጊት መለወጥ ከቻልን ዶክተር አብይ ብቻውን አይለፋም ፤አይደክምም። መደመር ማለት ይህ ነው። ከዚህ በተጨማሪም መደመር ማለት ለለውጥ በሚደረግ ጉዞ ውስጥ እክል ስለሚያጋጥም የሚመጡ ትችቶችን እንደ ጥንካሬ መውሰድ እንጂ ድንጋጤ ማሳየት ወደአልተፈለገ ዘራፍነት መለወጥ የለውጡን ባቡር ያዳክመዋል። አካሔዶችን መተቸት ማለት መደመርን አሊያም ዶክተር አብይን መቃወም ማለት አይደለም።   እያንዳንዱ ትችት ለእድገት ጠቃሚ ነው። በጭፍንነትና በመንጋ ሆኖ ማጨብጨብ ግን ለሃገርና ለሕዝብ ቀውስ መፍጠር ነው። ሃሳቦች ሲሰበሰቡ የተሻለ ነገር ይፈጥራሉ ፤ የተሰበሰቡ ሃሳቦች ሲዳብሩ ደግሞ የተሻለ ነገር እጅግ የተሻለ ነገር ይፈጥራል። ታሪክ ራሱን እንዳይደግም ተንክረን በመስራት ለትውልዱ አዲስ የስኬት ታሪክ መፍጠርና ማሳደግ ይገባናል። በጭፍንነት እና በመንጋነት እየተጓዝን ስንሔድ ግን ጸሓይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ አለመሆኑንም ልናስብ ይገባል። ካለፈ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለፌደራል ፖሊስ ጠንካራ ትእዛዝ አስተላለፉ።

የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላትን ለህግ የማቅረብ እርምጃ እንዲወስድ ጠቅላይ ሚኒስትረ ዶክተር ዐብይ አህምድ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ እንዲሁም የሰላምና መረጋጋት ስራ በመስራት የህዝቡን አብሮነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን እንዲያከናውኑ አስረድተዋል፡፡ ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ አካልትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር ዐብይ አሳስበዋል፡፡ ባረጀው እና በድሮ አስተሳሰብ በተለይም በሱማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሰው ህይወት እየጠፋ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ህግን የማስከበርና የሰላምና መረጋጋት ስራ በመስራት የህዝቡን አብሮነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ዳር ቆመው ክብሪትና ነዳጅ እያቀበሉ ህዝብን የሚያጣሉ አካላት ከዲርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡ ሰዎችን ቀስቅሶ አንዱን ከአንዱ ማጋጨት የኖርንበት እንጂ ለኛ አዲስ ነገር አይደልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄንን የሚያደርጉ አካላት ያረጃ ፋሽን መሆኑን በመረዳት አዲስ እና ለሀገር የሚበጁ ሃሳቦችን ማቅረብ እንዳለባቸው ዶክተር ዐብይ ጠቅሰዋል፡፡ Source: Ethiopian news agency(ENA)
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት በአፋጣኝ ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳሰቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የውጭ ምንዛሪ በእጃቸው የያዙ አካላት በአፋጣኝ ወደ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሰጡት መግለጫ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ሁኔታ ከውጭ እየገባ በመሆኑ ችግር ከመከሰቱ በፊት ገቢ እንዲያደርጉ ነው ያሳሰቡት፡፡ በቅርብ ቀናትም የውጭ ምንዛሪ ህገ ወጥ ዝውውርን ለመግታት ሲባል አዲስ ዘመቻ እንደሚደረግ ነው የተናገሩት፡፡  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወደአልተፈለገ ነገር ከመግባታችን በፊት የሰላም ጥሪያችንን ተቀበሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግጭቶችን ለሚፈጥሩ አካላትን አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችን ለሚፈጥሩ አካላት የመጨረሻ ነው ያሉትን የሰላም ጥሪ አቀረቡ ፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለሚፈጥሩ አካላት ወደ ሰላም እንዲገቡ የመጨረሻ ነው ያሉትን የሰላም ጥሪ አቀረቡ ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም በሚያሳፍር ሁኔታ ሰዎች ይሞታሉ በማለት ንግግር ያሰሙ ሲሆን ይህ እንዲያበቃም “እባካችሁ ወደ ሰላም ግቡ፤ ይህ የመጨረሻ የሰላም ጥሪዬ ነው” ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ያለው የጥላቻ ግንብ መናዱን አንስተው በአንዳንድ ክልል ያለው “የሳር ቀጤማ ግንቦች ይፍረሱ” በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የዛሬው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይዘው የመጡት ፍቅር በ50 ቢሊየን ብር የማይገዛ ውድ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ የሰላም ዋጋው ያልገባቸው አካላት አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እያስነሱ መሆኑን ጠቅሰው እስቲ ዛሬ እንኳ ስለ ሰላም ተማሩ ብለዋል በንግግራቸው፡፡ ኢትዮጵያ ወስጥ የሰዎች ሞት ማብቃት አለበት ሲሉም የሰላም ጥሪያቸውን አጽንዖት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አልፎ አልፎ የምታውኩን ሰዎች ፍቅራችንን ባታበላሹት መልካም ነው ነግርግን ግጭቶች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ሰውነንና ወዳልተፈለገ ነገር እንዳታስገቡን አደራ እላለው ብለዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አምባገነንነትን የመኮትኮት ክፉ ባህል ይቀየር! ( ሳምሶን ኀይሌ)

አምባገነንነትን የመኮትኮት ክፉ ባህል ይቀየር! ( ሳምሶን ኀይሌ) የሚበዛው የፖለቲካ ታሪካችን እንደሚያሳየው ኢትዮጵያዊያን ለሥልጣን ያለን አተያይ መስመር የሳተ ነው፡፡ ከሥርዓትና ተቋም ግንባታ ይልቅ ግለሰቦቸን እናመልካለን፤ በግለሰቦች ዙሪያ መኮልኮልን እንመርጣለን፡፡ በአገራችን መንግሥት የሁሉም ነገሮች (የጥሩም የመጥፎም) ምንጭ ተደርጎ ነው የሚቆጠረው፡፡ ኅብረተሰቡ ራሱን በራሱ በየደረጃው እያደራጀ የራሱን ጉዳይ የሚፈታበት ባህል በጣም ደካማ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ጠንካራ ሲቪክ ማኅበረሰብ ኖሮን አያውቅም፡፡ ጠንካራ ሲቪክ ማኀብረሰብ አለመኖሩ ደግሞ በሥልጣን ላይ ልጓም ለማበጀትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ጎድቶታትል፡፡ አሁንም እዚያው ነን፡፡ በየደረጃው ራሳችንን በራሳችን እያደራጀን የራሳችንና የአገራችንን ጉዳይ መልክ ለማስያዝ የምናደረግው ጥረት ኢምንት ነው፡፡ ከዚያ ይልቅ አንዱን ጨቋኝ ቡድን በሌላ ቡድን ለመተካት በመረባረብ ላይ ነን፡፡ ሥርዓታትና ተቋማት ስለሚጠናከሩበት ሁኔታ በሙያ ማኅበርም ይሁን በሲቪክ ማኅበራት ተደራጅተን እየታገልን አይደለም፡፡ ሁሉም ሚዲያ ስለ ዶ/ር ዐቢይና የእሳቸው ደጋፊ ናቸው ስለሚባሉ የተወሰኑ የመንግሥት አመራሮች ነው የሚያወራው፡፡ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ዕጣ-ፋንታ በእያንዳንዱ ዜጋ ንቁ ተሳትፎ ሳይሆን በእነ ዶ/ር ዐቢይ መልካም ፈቃድ ይወሰን ይመስል ሁሉም ነገር ለአዲሱ አመራር ተትቷል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ ከሚያደርጓቸው ንግግሮችና ከሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች ተነስተን ብናየው፣ እየተደረገ ያለውን የተክለ-ሰብዕና ግንባታ አዝማሚያ ይፈልጉታል ማለት ያስቸግራል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በአንድ ግለሰብና ቡድን ዙሪያ የመኮልኮል ባህላችን እስካልወጣንና በራሳችን የዜግነት ኀላፊነት እና አቅም ላይ እስካልተማመንን ድረስ የምንፈልገውን ዴሞክራሲያዊና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መገንባት አንችልም፡፡ በጣም ብዙ የቤት ሥራዎች ያሉብን ሕዝብ ነን፡፡ እነዚህን መሠረታዊ ችግሮች መወጣት የምንችውል ደግሞ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የመደመር” የልቀት አስተሳሰብ ግቡን የሚያፋጥነው ባለስልጣናት ለሰሩት በደል ሕዝብን በይፋ ይቅርታ ሲጠይቁ ነው። (ይድነቃቸው ከበደ )

ዶ/ር አብይ እባክዎን! . እርስዎ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ እጅግ በጣም አበረታች የሆነ የለውጥ ሂደት በአገራችን እየታየ ነው። ለዚህም የአንበሳውን ድርሻ እርስዎ እና በእርስዎ ዙሪያ የሚገኙ የለውጥ ኅይሎች ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ። . ሆኖም ግን ! የመንግስት ሹመኞች ከዚህ ቀደም በሥልጣን ዘመናቸው በህዝብ እና በአገር ላይ ለፈጸሙት ወንጀል እና በደል መጠየቅ ሲገባቸው ፤ አንዱን በሹመት ሌላው በክብር እና በማዕረግ በመሸኘት ከሕዝብ ዐይን ለመሰወር የሚደረገው ጥረት የተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚደግፍ ሣይሆን በለወጡ ላይ መጥፎ ጥላ የሚያጠላበት ነው። . እነኚህ ተጠያቂ የመንግስት ባለሥልጣን በሥልጣን ዘመናቸው ሌላው ቢቀር ለሰሩት አስከፊ እና አሰቃቂ በደል በህግ መጠየቃቸው ቀርቶ ሙገሳና ሹመቱ ልጎም ሊበጅለት ይገባል ። ከዚህም ከፍ ሲል ለሰሩት በደል ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል ! ይህ ሲሆን ነው “የመደመር” የልቀት አስተሳሰብ ግቡን የሚያፋጥነው ። . (ይድነቃቸው ከበደ )
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከአብይ ያልተማረው ገዱ (ጌታቸው ሺፈራው)

ከአብይ ያልተማረው ገዱ (ጌታቸው ሺፈራው) ገዱ አንዳርጋቸው በትናንናው ዕለት እነ በረከትንና ትህነግን ሲከላከል ትችት አስተናግዷል። አንዳንዶች ገዱ ያሰበው የማይመስል ሩቅ የፖለቲካ ትንተና አንስተው ሊከላከሉት ሞክረዋል። ገዱን አትውቀሱት የሚሉ አካላት አስተያየት ለለውጡ ካላቸው ቀናኢነት እንደሆነ ይገባኛል። ሆኖም:_ ~ገዱ አንዳርጋቸው ራሱ ባህርዳር ላይ በተደረገው ሰልፍ “የአሮጌው ዘመን ቁማርተኞች……”እግር በእግር እየተለተሉ አላሰሩት እንዳሉ ገልፆ ነበር። ትናንት ሌላ ቋንቋ ተናገረ። ~ትናንት ገዱ ሰልፉ ላይ “ይደገም” ተብሎ ከደገመው ለምን እንዳፈነገጠ ግልፅ አይደለም። ምን አልባት በአማራ ክልል ከተሞች “በረከት መጣ” እየተባለ ሲታደን “እናንተ በምትናገሩት ነው እንዲህ የተጠላነው” ተብለው ከ”አሮጌው ዘመን ቁማርተኞች” ወቀሳ ደርሶባቸው ይሆናል። በረከት ክስ አይነት ወቀሳ ነው የሚያቀርበው። በየ ሰልፉ የተዘለፉት የትህነግ ሰዎችም “አሰደባችሁን” ብለው ይሆናል። እነዚህ ሰዎች ከእጃቸው እርዝመት አንፃር በእነ ገዱ ላይ ምን እንደያዙባቸው ግልፅ አይደለም ~እውነታው ከሆነ ግን ሌላ ነው። እነ ዝማም ከእነ ገዱ ጋር ከመስራት ይልቅ ለትህነግ ወሬ ማቀበል ይቀናቸዋል። ይህን ደግሞ እነ ገዱ በምሬት እንደሚያወሩ በቅርብ የሚያውቁ በግልፅ የሚናገሩት ነው። ትህነግ ብአዴንን እንደፈለገ እየሾረው፣ አላሰራ ብሎት እነ ገዱ ግን ለእሱ ይከራከራሉ! ~እነ ገዱ መማር አይፈልጉም እንጅ መማር ቢፈልጉ የእነ አብይን ያህል ሞዴል ሊኖራቸው አይችልም ነበር። እነ አብይ (ቲም ለማ) “ህዝበኛ” እየተባሉ ክስ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። በትህነግ ሰፈር። ይህን የተባሉት ከምንም አልነበረም። ከሕዝብ የሚያቀራርባቸውን ስራ ስለሰሩ ነው። ትህነግን ከሕዝብ ለመነጠል ስለጣሩ ነው። ለአብነት ያህል ትህነግ ከኦሮሚያ የሚዘርፋቸውን በማጋለጥ፣ ሲያጋልጡም መታወቂያ ሳይቀር
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዘንካታው ጠሚ – ሸላይ ወግ – (ዳንኤል በቀለ )

ዘንካታው ጠሚ – ሸላይ ወግ – (ዳንኤል በቀለ ) መቼስ ዓብይ አህመድን በቁመት የሚስተካከል ኢትዮጵያዊ መሪ የለም። ቢኖርም ምናልባት የቁዋራው አንበሳ፥ አጼ ቴዎድሮስ ብቻ ናቸው። ቆፍጣናው የዘመናይቱ ኢትዮጵያ መስራች ቁመታቸው በዛ ዘመን እንኩዋ ወደ ስድስት ጫማ (1.80m) ይደርስ እንደነበር ያነበብኩ ይመስለኛል። በዛ ዘመን የነበሩ ኢትዮጵየኖች ደሞ ካሁኖቹ ኢትዮጵያኖች አጠር ያሉ ናቸው። ባለፉት 100 አመታት ውስጥ ስልጣን ላይ የነበሩት ግርማዊነታቸው፥ ኮሎኔል መንግስቱም ሆኑ ጠሚ መለስ ዘናዊ፥ ከዓብይ አህመድ ትከሻ ቢደርሱ እንጅ እንብዛም ከፍ አይሉም። እዚህ ላይ ዋናው የሚያሳዝነው ነገር በ100 አመት ውስጥ ያየነው መሪ ሶስት ብቻ መሆናቸው ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን በመዝለሌ እንደማትቀየሙ ተስፋ አለኝ። ፖለቲካ በዚህ ፖስት ስለማናወራ ወደ ቁመቱ እንመለስ። በዓብይ አህመድ የኤርትራ ጉብኝት ከታዘብኩዋቸው አንዱ ነገር የኢሳያስ አፈወርቂ ቁመት ነው። ፕሬዚዳንቱ ረጅም እንደሆኑ ባውቅም ይሄን ያህል ረጅም እንደነበሩ ግን አላስተዋልኩም ነበር። ረጅም ከሚባሉት ጠሚም ዘለግ ብለው ሳያቸው ገርሞኛል። ምን ያህል እንደሚመትሩ ለማወቅ ግን ጉግል አድርጌያቸው አልተሳካልኝም። ዶክተር ጎልጉልም ብዙ መረጃ ያስፈልጋቸዋል። ያሜሪካ አርባ አምስቱንም ፕሬዚዳንቶች ቁመት ጎልጉሎ ለማወቅ ግን ምንም አይነት ችግር የለም። ልዩነቱ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤት ብቻ አይመስለኝም። አንድ አሜሪካዊ ሰለ አሜሪካ ፕሬዚዳንት መጀመርያ የሚያውቀው የቆዳ ቀለሙን እና ቁመቱን ይመስለኛል። ባሁን ዘመን ሜትር ከሰማንያ በታች ሆኖ ያሜሪካ ፕሬዚዳንትነት የማይታሰብ ነው። ማጁም ሆኑ፥ መንጌና፥ መለስ በዚህ እጥረታቸው፥ የፈለጉትን ያህል የሰከኑ አገር ወዳድ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ቢሆኑ ዋይት ሐውስ የመግባት
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመቶ ቀናት ቆይታ

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የመቶ ቀናት ቆይታ 1. ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት ነው። መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣ እዚህም እዚያም ግጭቶችና ትርምሶች የሚፈሉበት፣ በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … ነበር። ይህንን ነባራዊ እውነታ ከመቀየር አንጻር ባለፉት 100 ቀናት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው። 1.1. ተስፋን የሚያጭሩ ንግግሮች ገና ወደ ስልጣን ከመምጣታቸውም በፊት “ቃል ይገድላል፥ ቃል ያድናል” ይሉ የነበሩት ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ፣ ባለፉት 100 ቀናትም ይህን እምነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። በበዓለ ሲመታቸው ያደረጉት ንግግር ከላይ የነበረውን የጭንቀት መንፈስ ከመግፈፍ አንጻር ከፍተኛ ሚና ተወጥቷል። በዚህ ንግግራቸው ስለአንድነት፣ ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለዴሞክራሲና የሃሳብ ብዝሃነት ያነሷቸው ሃሳቦች እና ባልተለመደ ሁኔታ እናታቸውንና ባለቤታቸውን ለማመስገን የሄዱበት ርቀት ሰዎች ለውጡን ከምር (seriously) እንዲያዩት ያስቻለ የመጀመሪያው እርምጃ ነበር። እስካሁንም ድረስ እንደ ጥቅስ የሚነሱ ዓ/ነገሮች (ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞት ኢትዮጵያዊ)፣ ለቀጣይ ስራዎቻቸው መነሻ የሆኑ አቅጣጫ አመላካቾች (የኤርትራ ግንኙነት)፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የምር የማስፋት እርምጃዎች፣ … የተንፀባረቁበት ንግግር ነበር። ከዚህም በኋላ በየክልሉ ባደረጓቸው ንግግሮች የየአካባቢውን ቋንቋ በመቀላቀል፣ የአካባቢውን ባህል በማንጸባረቅ፣ የምር የሚያማቸውን ጉዳይ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሳያስ ኢሳያስ ነው! — (ጌታቸው ሺፈራው)

ኢሳያስ ኢሳያስ ነው! (ጌታቸው ሺፈራው) ጀብሃ የሚባል ግብፅ ኢትዮጵያ ለማፈራረስ የጠፈጠፈችው ቡድን ነበር። አሜሪካ ሙስሊሞች የበዙበትን ይህ ቡድን እንደስጋት አየችው። አጤ ኃይለስላሴ ከግዛት አንድነት አንፃር አደጋ ነው አሉ። ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መንግስት በድሎት ያስተምራቸው ከነበሩ የዛ ዘመን ተማሪዎች አንዱ ነው። ይህ ሰው ጀብሃን ለመበተን በሰላይነት እንደተመረጠ ይነገራል። አጤ ኃይለስላሴ የሀገር አንድነት ለማስጠበቅ አምነውት ነበሩ አሉ። እናም ሰላይ አደረጉት! አምነውት ነው። ኢሳያስ ጀብሃ ላይ የታቀደውን ሰራበት። ጀብሃ ውስጥ ሻዕቢያ ፈጠረ። ቡድኑ ህልውና ያለው ሲሆን የተባለውን የሀገር አንድነት ሕልውና ማስጠበቅ ሳይሆን የሀገር አንድነት ለማፍረስ የመጀመርያው ሰባኪ ሆኖ አረፈው። በኢትዮጵያ በጀት የኢትዮጵያ ጠላት ሆነ። ኢሳያስ አዲስ ሀገር ለመመስረት የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ያላቸው ጋር ተወዳጀ። የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ይረብሻሉ ካላቸው ጋር ተወዳጀ። የመጀመርያው ትህነግ/ህወሓት ነበር። በዚሁ ሂደት አንድ ትልቅ ጠላት አድርጎ የፈረጀው ሕዝብ ነበር። አማራ! አማራን እንደጭራቅ ማሳየት የመጀመርያው የእነ ኢሳያስ የፖለቲካ ቅስቀሳ ሆነ። ይህ ሕዝብ ላይ በዓለም ላይ ያለ ውንጀላን ሁሉ አቀረበ፣ የቻለውን ሁሉ ስድብና እርግማን አወረደ። ትህነግ/ህወሓት የተከተለው የእሱን ፈለግ ነበር! ኢትዮጵያ በሻዕቢያና በትህነግ እጅ እንደወደቀች “የመቶ አመት የቤት ስራ እንሰጣቸዋለን” በሚለው ኢሳያስና የትህነግ ሰዎች እርስ በእርስ ማጋጨት ስልት እንደዋነኛ ስልት ተያዘ። አማራና ኦሮሞን ማባላት የመጀመርያው ስልት ሆነ። አማራን ማጥላላት፣ ማሰርና መግረፍ የኢሳያስና የመለስ ዋና ስራ ሆነ። የቻሉትን አደረጉ። እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በታሰሩበት ወቅት አብዛኛዎቹ ገራፊዎች የሻዕቢያ ደሕንነቶች ነበሩ።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኤርትራ የሚገኘው ደምሕት ምነው ድምፁን አጠፋ ? እውን ወያኔ ለክፉ ቀን ያስቀመጠው ነው ?

በኤርትራ የሚገኘው ደምሕት ምነው ድምፁን አጠፋ ? እውን ወያኔ ለክፉ ቀን ያስቀመጠው ነው ? (ምንሊክ ሳልሳዊ) የደምሕት ጦር በኤርትራ የሚገኘው ለዶክተር አቢይ ጥሪ ምላሽ አለመስጠቱ እያነጋገረ ነው። የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና የፖለቲካ ሰዎች በጎ ምላሽ ያጎረፉለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር አላማን ደምሕት ለመደገፉ እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም ። የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግም አልታየም። ከአስር ሺህ እስከ አስራ አምስት ሺህ የሚገመት ሰራዊት እንዳለው የሚነገርለት ደምሕት የተባለው ድርጅት ሰራዊቱ የመበተን አሊያም ከመከላከያ ሰራዊት የመቀላቀል ሃሳብ ይኑረው እስካሁን ግልጽ አላደረገም። ካሁን ቀደም ይህ ጦር ወያኔ ለክፉ ቀን ያስቀመጠው ጦር መሆኑንና ወደፊት በወልቃይትና በአፋር አከባቢዎች ሊሰፍር ይችላል የሚል መረጃዎች ሲወጡ ነበር። ድምጹን አጥፍቶ እንደተባለው ከ ኤርትራ ተነስቶ ትግራይ በመግባት በተባሉና በተዘጋጁ የስትራቴጂ ካምፖች ላይ ሊሰፍር እና ቅልብ ጦር ሊሆን ይችላል። መሪው የነበሩት ሞላ አስገዶም ቅይጥራቸው ጥቂት ከሆኑ ጭፍሮቻቸው ጋር ሕወሓት ጋር ከተደመሩ በኋላ ድርጅቱ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የመሰረተው ሕብረት መፍረሱ ይታወቃል። የደምሕት ጦር በተለይ ፕሬዝዳንት ኢሳያስንና የመንግስት ተቋሞቻቸውን በትጋት በጥበቃ እያገለገለ መሆኑ ይነገራል። ይህ ከፍተኛ ኮማንዶውች ድረስ የሰለጠኑ ወታደሮች እንዳሉት የሚወራለት ደምሕት ቀጣዩ እጣ ፈንታውን የሚወስኑለት ሕወሓትና ሻእቢያ እንደሆኑ ይነገራል። በወልቃይት አከባቢ ከባድ መሳሪያ ታጥቆ ይሰፍራል ፤ በአፋር አከባቢ እስከ ገዋኔ ድረስ እንዲሁ ከባድ መሳሪያዎች ታጥቆ ይሰፍራል የሚባለው መረጃ እንደተጠበቀ ሆኖ የድርጅቱ አመራሮች ግን ለጊዜው መረጃ ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸውን ይናገራሉ። የሰራዊቱ አባላት እጣ ፋንታ በረሃ ላይ መንከራተት መሆኑ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ትብብራቸው ተጠየቀ ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2011 በጀት ዓመትን አስመልክተው ከፓርላማ አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ከመለሱ በኃላ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት ፍሬ ሀሳብ ፡ • ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚልከውን ገንዘብ በባንክ በኩል በማድረግ የመንግስትን የለውጥ እንቅስቃሴ ደግፉ፡ • ዲያስፖራዎች ከቀን ወጨያቸው አንድ ዶላር በመለገስ በገጠር አካባቢ ያለውን ህዝብ ችግሮች መቅረፍ የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርግልን እለምናለሁ፡፡ • ይህን የሚያንቀሳቅስ ቦርድ ሽራፊ ሳንቲም ሳትባክን ለታሰበለት አላማ እንዲውል ይደረጋል፡፡ • ሙህራን ልምድና ክህሎታችሁን በበጎፈቃድ መልክ እያበረከታችሁ አግዙን • ወጣቶች የበጎ ፈቃድ ባህልን በማዳበር ተጨማሪ የበጀት አቅም ሁኑን • ባለሃብቶች ታክስ በመክፈል ግዴታችሁን ከመወጣት ባሻገር የሞራል ልዕልናችሁን ጠብቃችሁ የአገር አለኝታ ልትሆኑ ይገባል፡፡ • የመንግስት ሹሞች የተጣለባችሁን ኃላፊነት በአግባቡ እንድትወጡ የሚሉና ሌሎች ተማፅኖ አዘል የአብረን እንስራ ጥሪን አስተላልፈዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል ምረቃ ላይ ተገኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል ምረቃ ላይ ተገኙ በ340 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባውን የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። በምረቃው ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦመር ሀሰን አልበሽር፣ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ፣ የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበርና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፈቂ ማሃማት ተግኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በምረቃው ላይ፥ ጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕከል በማስገንባቷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ማእከሉ ለጅቡቲ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሀገራትም የጋራ ሀብት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ኢትዮጵያ ማእከሉ እንደራሷ ፕሮጀክት ትቆጥራለች ብለዋል። #FBC
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት ይሻገር (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

ሕወሓት ይሻገር ዶ/ር ዘላለም እሸቴ የኢትዮጵያ አምላክ ስጦታ የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ የተነሱለት ራዕይ ከእኛ ኢትዮጵያውያን ተርፎ ለአፍሪካም በረከት የሚሆን ጭምር ነው። ፈጣሪ የሕዝብን የዘመናት ልመና ሰምቶ፤ ዛሬ በፍቅር ደስታ ተዐምር በሚያሰኝ ሁኔታ መላውን ሕዝብ አንድ እያደረገ ይገኛል። እኚህ ሰው ዲሞክራሲን አዋልደውና የአፍሪካን አንድ የመሆን ራዕይ ፈንጥቀው ከስልጣናቸው ዞር የሚሉ “ጉደኛና ታሪከኛ” መሪ እንጂ፤ አምላክ የሰጣቸውን የማያልፈው የኢትዮጵያ አባትነት ክብር፥ ለሚያልፈው የስልጣን ጥማት የሚሸጡ አይመስለኝም። ስለዚህ እኚህን የፍቅር ስብዕና የተካኑትን ጠ/ሚ፤ ለሁሉ ፍቱን መድሃኒት የሆነውን ተወዳጅ የመደመር አስተሳሰብ ማደናቀፍ በታሪክ የማይሽር ጠባሳ በራስ ላይ ያመጣል። ይህ ዓይነት ጠባሳ ኢትዮጵያዊ በሆነ ሁሉ ላይ እንዳይመጣ ሁላችንም የቻልነውን ያህል የማሻገር ስራ እንድንሰራ እንነሳሳ። የሕወሓት አመራር ዶ/ር አብይ አህመድን ከመምረጥ ሂደት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፤ ራሱን በለውጡ ባቡር ላይ ሙሉ በሙሉ መቀላቀል ተስኖት፤ በመጀመሪያ ደረጃ ለራሱ፥ ቀጥሎም ለሀገሪቱ አስቸጋሪ ፈተና እንዳይሆን በሚያስፈራበት ሁኔታ ላይ እያለ መሆኑ ለሁሉም ግልፅ ነው። አስተውሉ፥ የትግራይ ሕዝብ አላልኩም። ደግሞም ሕወሓት አላልኩም። የሕወሓት አመራር ነው ያልኩት። የሕወሓት አመራር እስካሁን ለሁሉ መፍትሄ የሆነውን የዶ/ር አብይን የማሻገር ዕድል ሊገነዘቡት አልቻሉም። አሁንም ከተኙበት ነቅተው ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የለውጥ አራማጆች ለመሆን እንዲቀላቀሉና እንዲሻገሩ ሁላችንም በትዕግስት እየጠበቅናቸው ነው። የሆኖ ሆኖ የሕወሓት አመራሮች፤ ሕወሓትን ለጥፋት እንዳይዳርጉና የትግራይን ሕዝብ ትግል ታሪክ በዜሮ እንዳያስኬዱ፤ የትግራይ ወገኖቻችንና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ተሻገሩ የሚል ድምፅ እናሰማቸው። የሕወሓት አመራሮችም ራሳቸውን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ኦሞ የሚኖሩ ብሄረሰቦች አግላይ የዘር ፖለቲካ በምንም መልኩ ውጤቱ ዜሮ ነው! ተደምረናል ብለዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ ናት። ጂንካ በጣም የምታምር፣ የተለያዩ ብሄረሰቦች የሚነግዱባት ከተማ ናት። በባህር ዳር ሕዝብ ድምጹን ባሰማበት ወቅት ይች ከተማም ድምጿንም አሰምታለች።፡ኮከብ አልባ የሆነው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅን በማውለብለብ፣ ጂንካና ደቡብ ኦሞ የፍቅርን፣ የአንድነት፣ የኢትዮጵያዊነት ድምጽ በማስተጋባት፣ ዶ/ር አብይና ጓደኞቻቸው ለጀመሩት ለውጥ ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ጂንካ፣ ደቡብ ኦሞዎች እኛ ተደምረናል ብለዋል። በደቡብ ኦሞ የሚኖሩ ብሄረሰቦች ካልተያያዙ፣ ካልተሳሰሩ ካልተገመዱ መኖር እንደማይችሉ ያውቃሉ። አንድነት ሃይልና ብልጽግና እንደሆነ ያውቃሉ። የሚገመዳቸውም፣ የሚያተሳስራቸውም ኢትዮጵያዊነት ነው። በመሆኑም በኢትዮጵያዊነት ፣ በሰንደቋ ቀልድ አያውቁም። በጂንካ በተደረገው ሰልፍ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነትን የሚያወድሱ መፈክሮች ከማሰማትና የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርጎ ከማወለብለብ ባሻገር “አግላይ የዘር ፖለቲካ. . . በምንም መልኩ. . . ውጤቱ ዜሮ ነው!” እያለ ዘረኝነት የዘር ፖለቲካን አውግዟል። ቀደም ሲል በተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች በሸገር፣ በድሬዳዋ፣ በጂጂጋ፣ በወልቂጤ፣ በእንሙር፣ በቡታጅራ፣ በወራቤ፣ በዱራሜ፣ በሆሳና፣ በባህር ዳር፣ በደብረ ብርሃን፣ በደብረ ታቦር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣ በኮምቦልቻ፣ በቆቦ፣ በመርሳ፣ በግንደወይን፣ በወረታ፣ በቡሬ፣ በቢቸና በደንበጫ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በመሃልሜዳ መንዝ፣ በበደሌ/ኢሊባቡር ..ዶ/ር አብይን በመደገፍና የኢትዮጵያን ባንዲራ በማውለብለብ የድጋፍ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን፣ በመቀሌ ህወሃት፣ በነቀምቴ ደግሞ ኦነግ በመደገፍ ሰልፎች ተደርገዋል። በመቀሌው ሰልፍ የኢትዮጵያ ባንዲራ የተውለበለበ ሲሆን (ኮከብ ያለበትም ቢሆን) በነቀምቴ ግን ምንም ነገር አልነበረም።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረገ ላለው ድጋፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች ሆይ ምስጋና ከሚቀበል ሰው ይልቅ ምስጋና የሚሰጥ ታላቅ ነው፡፡ ያለ ጥርጥር ይህንን እንረዳለን፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በሀገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ጭላንጭል፤ አሁን የሀገራችን ህዝብ እየሰጠን ካለው ወሰን አልባ ድጋፍ እና ፍቅር ጋር የሚወዳደር እንዳልሆነ ብንገነዘብም መንግስት ይሄንን ድጋፍ ፣ ፍቅር ፣ ክብር እና አለኝታነት ለተሰሩ ስራዎች እንደተሰጠ ምስጋና ብቻ ሳይሆን በቀጣይ እንሰራቸው ዘንድ ለሚገቡን በርካታ ስራዎች ተግባራዊነት የተላለፈ የአደራ መልእክት እንዲሁም የአጋርነት ማሳያ አድርጎ በመቁጠር ከምን ጊዜውም በላይ በፍጹም ቁርጠኝነት እና ትጋት ለማገልገል በጽናት ይሰራል፡፡ እስካሁን የታየው የለውጥ ወጋገንም ሆነ ወደፊት የምናስመዘግበው ድርብ- ድርብርብ አንፀባራቂ ድል ባለቤት ህዝብ እና ህዝብ ብቻ ነው፡፡ አሁን ከጀመርነው የፍቅር ፣ የይቅርታ፣የመደመር፣ የአንድነት እና እንደ ሀገር የመለወጥ ጉዞ ሊያደናቅፈን የሚችል መሠናክል – ሊያናጥበን የሚችል ስጋትአይኖርም በሚል መንፈስ ተነስተን በጽናት እየተደመርን የምንገኘውም ህዝብ ታግሎ ያላሸነፈበት ምንም የትግል አውድ የፍልሚያ ግንባር እንደሌለ እና እንደማይኖርም ጭምር በውል ስለምንገነዘብ ነው፡፡ ከምስራቅ እስከ ምእራብ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከሰራነው ስራ እጅግ ለሚልቀው እና ትርጉም- አንድምታውም ፍጹም ለሚረቀው ወሰን አልባ ድጋፋችሁ እና ፍቅራችሁ በያላችሁበት ሆናችሁ እነሆ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ የቸራችሁን ምስጋና የኛ ብቻ ሳይሆን የናንተም ድምር ውጤት ነውና እናንተ አመስጋኞቹ ዋናዎቹ ተመስጋኞች መሆናችሁን ለአፍታም ቢሆን አንዘነጋም፤መዘንጋትም አይቻለንም፡፡ እናም ተመስጋኞቹ አመስጋኞች የለገሳችሁንን አብሮነት በፍቅር – አደራ ያላችሁንን የነገ ትግል በክብር ተቀብለን ታላቂቱን ሀገር ወደ ቀድሞ እና
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሃት ወደ ኩርፊያ ማዘንበሉን ተከትሎ፣ ጠሚሩ አዲስ ፈተናዎች እያቆጠቆጡባቸው ይመስላል [ዋዜማ ራዲዮ]

[ዋዜማ ራዲዮ] ሕወሃት ወደ ኩርፊያ ማዘንበሉን ተከትሎ፣ ጠሚሩ በገዥው ፓርቲ ከተጋረጠባቸው ፈተና ሌላ ከአጋር ድርጅቶች እና ታዳጊ ክልሎችም አዳዲስ የፖለቲካ እና ጸጥታ-ነክ አዲስ ፈተናዎች እያቆጠቆጡባቸው ይመስላል-ዝርዝር አለን-  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በቅዳሜው ሰኔ 16 ዶክተር አብይን ለመደገፍ በወጣ ሕዝብ ላይ የደረሰው የቦምብ አደጋ የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን እጁ እንዳለበት ታወቀ።

* በቅዳሜው ሰኔ 16 ዶክተር አብይን ለመደገፍ በወጣ ሕዝብ ላይ የደረሰው የቦምብ አደጋ የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን እጁ እንዳለበት ታወቀ።   * የአዲስ አበባ ፖሊስ በሸጎሌ ቀይ ሽብር የተካሄደበትን ቤት ለግድያና ለድብቅ ማሰቃያ ይጠቀምበታል የሚሉ መረጃዎች ተገኙ።   * ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ከነቤተሰቦቻቸው ወደ ሃገር ቤት እንዲገቡ የሚረዳ ንግ ግር ተጀመረ።   * በዛሬው እለት የተካሔዱ ሰልፎች በሰላም የተጠናቀቁ ሲሆን በባሕር ዳር የሚደረገው ሰልፍ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ   የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን ሃላፊዎች በሰኔ ለዶክተር አብይ ድጋፍ በተደረገው ሰልፍ ላይ ለፈነዳው ቦምብ ተባባሪ መሆናቸው መረጃ ተገኘ ፤ በዚህም መሰረት የመምሪያው ሃላፊዎች ኮማንደር አማኑኤል እረዳና ሃዲሹ ገእግዚያብሄር ሰልፉ ከመጀመሩ በፊት በመስቀል አደባባይ ቀድመው በአራቱም ማእዘናት መገኘት የነበረባቸውን አስራ ስምንት አምቡላንሶች እንዳይንቀሳቀሱ ከማገዳቸውም በተጨማሪ ከቄራ አከባቢ መምጣት የሚችሉ የእሳት አደጋ አምቡላንሶችን እንዳይንቀሳቀሱ ማገዳቸው ታውቋል ተረኛ የሆኑ ሹፌሮችንም በመበተን አንድ ሹፌር ብቻ አስቀርተው አንድ አምቡላንስ ብቻ እንዲንቀሳቀስ አዘው እንደነበር የምርመራ ውጤቱ ያሳያል።   ኮማንደር አማኑኤል እረዳ የአዲሥ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል መምሪያ ባለሥልጣን ዋና ዲሪክተር ሲሆን ሃዲሹ ገእግዚያብሄር የባለሥልጣኑ የአንቡላንሥ አሥተባባሪ ያለሙያ በዘመድ የተመደበ አጅግ አደገኛ የደሕንነት አባል መሆኑን ሰራተኞቹ ይናገራሉ። በትክክለኛው አሰራር ለህዝባዊ በአል ለሙሥሊም ለክርሥቲያን በአል ለሰልፎችም ይሁን ለሌሎች ፕሮግራሞች ከግቢ አንቡሊንሶች ወጥተው በአራት መአዘን ወተው ይቆማሉ ፤ ለአንድ ምድብ 4 አንቡላንሥ አለው።ሁሉም ሠራተኛ በተጠንቀቅ
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ዐብይ አህመድ ላመጧቸው ሀገራዊ ለውጦች ምስጋና ለማቅረብ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ላመጧቸው ሀገራዊ ለውጦች ምስጋና ለማቅረብና ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት በማውገዝ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ጠቃሚ ምክር (ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ)

ለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አስቸኳይ ምክር ************************************ ለ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ትንሽ ጠቃሚ ምክር ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ ውድ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን በአለዎት ፍቅር የተነሳ ስልጣን ከያዙ ሶስት ወር እንኳን ሳይሞላ እርስዎና ባልደረቦችዎ የፈፅማችሁአቸውን ታላላቅ ተግባሮች አሁን እኔ እዚህ አልዘረዝራችውም። እርስዎ፣ እቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የለኮሳችሁት ኢትዮጵያዊነት እሁን ወደ ፍቅርነት አየተለወጠ እየነደደ ነው። በፍቅር ላይ ደሞ እርስዎ መደመርን፣ እንዲሁም ይቅርታ እና ምህረት ማድረግን ጨመሩባቸው። በጣም ደስ ይላል። ዳሩ ግን የእርስዎ ፍቅር፣ መደመር፣ ይቅርታና ምህረት የማይስማሟቸው የጭለማ ሰራዊቶች መኖራቸውን በቀደም እለት ለእርስዎ አነጠጥረው በህዝብ መሀል ያለርህራሄ ባፈነዱት ቦንብ እና በአፈሰሱት ንፁህ ደም ይፋ አድርገዋል። ከቡር ጠቅላይ ሚንስትር ሆይ፡ የምንኖረው አብሪት፣ ትእቢት፣ጭካኔ፣ ሴራ እና ግድያ በሞሉበት ዐለም ውስጥ ነው። ይህ የጭለማ ዐለም የፍቅርን፣ የይቅርታን እና የምህረትን ብርሃን ጠልቶ ሊያጠፋው እንደሚጥር አሙን ነው። ሆኖም ቦምቡ የተወረወረው ከላይ ለእርስዎ ቢሆንም ከውስጥ መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጥቃት እና አሁን የተቀዳጁትን ፍቅር፣ አንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ለመንጠቅ የታቀደ እኩይ ሴራ ነው። እርስዎ የአበሰሩቸው ይቅርታና ምህረት በመሰረቱ መልካም ቢሆኑም ይቅርታ እና ምህረት የሚደረጉት ስለበደሉ ተፀፅተው ይቅርታን እና ምህረትን ለሚጠይቁ ሰዎች ብቻ ነው። አጥፍቻለሁ ይቅር በሉኝ፣ ማሩኝ የሚሉ ሳይኖሩ ይቅርታ እድርጌላችኋለሁ፣ ምሬአችኋለሁ ማለት ትርጉም የለውም። በዳዮቹ ስንትና ስንት ግፍ ፈፅመው ሳይፀፀቱ በቀላሉ ምሬአችኋለሁ ሲባሉ ስላልተቀጡ ታብየው አዲስ ጥፋት ሊያደርሱ ይችላሉ። ለማድረስም ሲጥሩ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ የባለስልጣናቱ የግድያና አፋኝ ቡድን ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የባለስልጣናቱ የግድያና አፋኝ ቡድን ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ) የፖሊስ ባለስልጣናቱን መታሰር ተከትሎ የማሰቃያ እስር ቤቶች ስቃይ መቀነሱ ተገለጸ። የኮማንደር ግርማ ካሳን ጉዳይ ማንሳቴን ተከትሎ በውስጥ መስመር የተለያዩ መረጃዎች በተለይ ከፖሊስ አባላት ደርሰውኛል። እነሆ ተስተካክሎ ቀርቧል። ብልት ላይ የሃይላንድ ውሃ እንዲንጠለጠልና ጥፍሮች እንዲነቀሉ ትእዛዝ የሚሰጡ የፖሊስ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋል እስር ቤቶች እፎይታን አግኝተዋል። በተለይ ኮማንደር አስፋወሰን የኮሚሽነር ግርማ ካሳ ታዛዥና ታማኝ ባርያ በምርመራ ወቅት በጣም ብዙ ወገኖቻችንን እግራቸዉን በጥይት እየመታ ሽባ አድርጓቸዋል ።ሱቆችን ማቃጠል ፣ የገበያ ማእከሎችንና የግለሰቡ ሃብቶችን መዝረፍ ፣ ከሌቦች እና ማጅራት መቺ ቡድኖች ጋር በጋራ መስራት ፣ የውጪ ዜጎችን መዝረፍ ፣ በከተማዋ መኒይ ላውንደሪግ የሚሰሩ የሕወሓት ሰዎችን ከለላ መስጠት ወዘተ በርካታ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ወንጀሎች የፈጸሙ ናቸው ፤ እነዚህ ወንጀለኛ የፖሊስ ባለስልጣናት እንዲፈቱ የሕወሓት አመራሮችና የጦር ጄኔራሎች ጫና ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በቅዳሜው የሰኔ አስራ ስድስቱ ለዶክተር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ መፈዳቱን ተከትሎ የፖሊስ ባለስልጣናት የግድያ የ አፈናና የእስር ማዘዣ ኔትወርክ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። በተለይ ብልት ላይ የሃይላንድ ውሃ እንዲንጠለጠልና ጥፍሮች እንዲነቀሉ ትእዛዝ የሚሰጡ የፖሊስ ባለስልጣናት የሚያሰቃዩ ባለስልጣናት መታሰራቸው የተለያዩ መረጃዎች ይፋ እየሆኑ ነው። የሕወሓት አመራሮች የሚከራከሩላቸው በእስር ላይ ያሉ የፖሊስ ባለስልጣናት በቶርች ብዛት አእምሯቸውን የሳቱ ዜጎችን ከነሕይወታቸው ጫካ ውስጥና በረሐ ላይ ወስደው ለአውሬ እንደሚሰጧቸው ተጋለጠ ።በርካቶች ማንነታቸው የማይታወቅና ከተለያዩ የሐገሪይ ክፍሎች ታፍነው የመጡ ዜጎች የዚህ ቡድን ተጎጂ ናቸው።
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያውያን ዶክተር አብይን በመደገፍ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ለዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ መግለጫ አወጣ ።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በሂውስተን ቴክሳስ በ1984 በአራት ቡድኖች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ዘንድሮ 35ኛ ዓመቱን በዳላስ ከተማ ያከብራል። ድርጅቱ በሰሜን አሜሪካ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙት ከፖለቲካ፣ ከዘርና ከሀይማኖት ነጻ የሆነ ድርጅት ነው። ከግብር ነጻ የሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ የተመዘገበው በካሊፎርኒያ ክፍለ ሀገር ሲሆን ዓላማው ኢትዮጵያውያንን ከያሉበት ለማሰባሰብና ስፖርትን ተጠቅሞ የአገራችንን የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ውጭ ተወልደው ለሚያድጉት ልጆቻችን ለማስተማርና ለማውረስም ጭምር ነው። ፌዴሬሽኑ በተለያዩ ጊዜያት በአምባገነኖችና በዘረኞች ታፍኖ ለኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሟገት ለመብት ተቆርቋሪዎችም የመገናኛ መድረክ ሆኖ ኖሯል። በርሀብና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የገንዘብ አስተዋጾ ያደርጋል። በትምህርታቸው ጎበዝ ለሆኑ ተማሪዎች እርዳታ መስጠቱን ቀጥሏል:: በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካና በካናዳ የሚገኙ በአጠቃላይ 31 ክለቦች አሉት። በየዓመቱ የሚካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያንን የሚያገናኝ መዲና መሆኑ እርግጥ የሚያኮራ ነው። ፌዴሬሽናችን አሁን በአገራችን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካዊ ለውጥ ይደግፋል። በተጨማሪም ድጋፋቸውን የወደፊት ብሩህ ተስፋቸውንና ምኞታቸውን ለጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነፃነት ለመግለጽ በወጡት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ በጣም አዝነናል። ይህን በመልካም የተጀመረውን የሠላም የአንድነትና የፍቅር ጉዞ ለማደፍረስ ታስቦ የተደረገውን አፀያፊ ተግባር አጥብቀን የምናወግዘው መሆናችንን እንገልፃለን። ፈጣሪ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንለምናለን። ዶክተር አብይ አሕመድ የብዙ አመታት የፍትህ እና የዴሞክራሲ መስዋትነት ለወቅቱ የላካቸው የለውጥ አቀንቃኝና የኢትዮጵያውያን መቃተት መልስ ናቸው ብሎ ተረድቶታል:: ከ40 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከዶክተር አብይ ጋር የሚደረገው የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ውይይት እውነተኛ አርቲስቶችን አግልሏል የሚል አቤቱታ ቀረበበት።

*** እውነተኛ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ያገለለው የነገው የቤተ መንግስት ጥሪ *** ( የኋላሸት ዘሪሁን ሺፈራው) ከዚህ ቀደም ማቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዘናዊ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ባናገሩበት ወቅት እጅግ አስቂኝ ና አሳፋሪ ነገሮች ተከስተው ነበር ።የፕሮግራሙ አስተባባሪ የነበሩት “ልማታዊ አርቲስቶች” በነገራችን ላይ እነዚህ ባለሞያዎች በሁለት ይከፈላሉ የመጀመሪያዎቹ በፊት ለፊት መንግስትን እሚደግፉና ከቤተ መንግስት ድርጎ እሚሰፈርላቸው ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ደግሞ የህዝብ ወገንተኛ ነን እሚሉ ህዝብ እሚወዳቸውን ታሪካዊ ሁነቶችን እያነሱ “ከኔ የበለጠ ኢትዮጵያዊ የለም” እሚሉ ከህዝብ ና ከ እውነት ጋር ወግነናል እሚሉ ነገር ግን በጓሮ በር ሄደው እሚሞዳሞዱ (እሚንጎዳጎዱ) ወይም ደግሞ ከባለስልጣናት ጋር በጥምረት እሚሰሩ ናቸው ወደ ዋናው ነጥቤ ቶሎ ልግባ የዛኔ …አቶ መለስ ዜናዊ “የተለያዩ ባለሞያዎችን ማናገር እፈልጋለው” ሲሉ በፍጥነት ኮሚቴ ተቋቋመ ኮሚቴው ሆድ አደሮቹንም እውነተኛ ባለሞያዎችንም በጋራ የያዘ ነበር ። ምን ያደርጋል… እውነተኛ ባለሞያዎችን ሆን ተብሎ ከኮሚቴ አባልነታቸው እንዲወጡ ተደረገ የቀሩትንም አቅም አሳጥተዋቸው መወሰን እንዳይችሉ አደረጓቸው በመቀጠል በወቅቱ ከ ኢሃዲግ ፅህፈት ቤት ከተወከሉ ሰዎች ጋር በጋራ በመሆን “ማን ይጠራ ማን ይቅር ማን ምን ይጠይቅ ” በሚል ከብዙ አተካሮ በኋላ ጥያቄ ጠያቂዎቹ ሰዎች(የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች) የተመረጡ ጥያቄዎች ተሰጧቸው ልምምዱም ቀጠለ ቤተ መንግስት ጥያቄ እንዴት መቅረብ እንደሚገባ እንደ ተውኔት በቃል ተሸመደደ… አይደርስ የለም ቀኑ ደረሰ የተውሸለሸሉ ጥያቄዎች ቀረቡ: “ደሞዝ ይጨመርልን, ካሜራ እናስገባ, የተከለከሉ ቦታዎች ላይ ፎቶግራፍ እንድናነሳ ይፈቀድልን…” ወዘተ ብዙዎችን ያሸማቀቀው ጥያቄ አሳፋሪ በሆነው
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደም ለገሱ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ደም ለገሱ (ኤፍ ቢሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመስቀል አደባባዩ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት ለተጎዱ ዜጎች አጋርነታቸውን ለማሳየት ዛሬ ደም ለገሱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥቃቱ በኋላ የተለያዩ ሰዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ደም ለጋሾች እና በጎ ፈቃደኞች ላሳዩት ትክክለኛ አጋርነትም በትናንትናው ዕለት ማመስገናቸው ይታወቃል። በዚሁ ወቅትም ለተጎጂዎች ተጨማሪ ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለውንም ጥረት አድንቀዋል።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮችና የጦር ጄኔራሎች የታሰሩ የደሕንነትና የፖሊስ ባለስልጣናት እንዲፈቱ ጫና መፍጠር መጀመራቸው ታወቀ

* በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ቁጥር 30 ደረሰ፡፡ * የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮችና የጦር ጄኔራሎች የታሰሩ የደሕንነትና የፖሊስ ባለስልጣናት እንዲፈቱ ጫና መፍጠር መጀመራቸው ታወቀ * ለዶክተር አብይ አሕመድ እየተደረገለት ያለው ጥበቃ አሳሳቢ ነው ። ይህ ደግሞ እንደሃገር አስጊ ነውና ጥንቃቄ ያሻዋል ። ( ምንሊክ ሳልሳዊ  ) በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ ከፈነዳው ቦንብ ጀርባ እጃቸው አለበት ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ቁጥር 30 ደረሰ፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል እንዳስታወቁት ፖሊስ ከአደጋው ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ለመለየት የሚያደረገው ክትትል እንደቀጠለ ነው፡፡ ፖሊስ  6 ጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልፆ ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው አደጋ ክፍተት አሳይተዋል የተባሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ ዘጠኝ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 21 ዶክተር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆኑ ጀምሮ የሰሩትን የለውጥ ስራ ለማበረታታትና ለማመስገን በተጠራ ሰልፍ ላይ ሚሊዮኖች በተገኙበት የፈነዳውን ቦምብ ተከትሎ በፖሊሶችና በደሕንነቶች ሴራና ንዥላልነት የሆነ ነው በሚል ጥርጣሬ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣናትና የደሕንነት ሓላፊዎች ለምርመራ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል። ከፍተኛ የፖሊስና የደሕንነት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ምርመራው ላይ ተፅእኖ ከመፍጠር ጀምሮ የታሰሩት እንዲፈቱ ጫና እስከማድረግ ድረስ ሕገወጥ ተግባር መጀመሩን ለጉዳዩ ቅርብ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓቶች በአፋር ክልል እኩይ ተግባራቸውን ለመፈፀም እያሴሩ ነው ሲሉ የአፋር ታጋዮች ገለፁ።

የአፋር ሕዝብ ለዶክተር አብይ ያለውን ድጋፍ በነቂስ አደባባይ ወጥቶ ገልጿል። በዚህ የተበሳጨው የክልሉ መሪ ፓርቲ አለቃውን ሕወሓትን ይዞ በሕዝቡ ላይ ማሴር መጀመሩ ታውቋል። ለቅድመ ጥንቃቄ የህወሓት ቡዱኖች ሽንፈታቸውን ባለመቀበል በየቦታው እኩይ ተግባር ለመፈፀም ስሯሯጡ ይታያሉ፡፡ በተለይ በአፋር ክልል ዋና ዋና ከተሞች በየሳምንት ምስጢራዊ ስብሰባ በማድረግ በአፋር ክልል ላይ ተቃውሞ ሠልፍ ለማስኬድ ከፍተኛ ዝግጅት በማደረግ ላይ መሆናቸው ትክክለኛ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በተለይ በአይሳኢታ፡ በሎግያ፡ በዲቾኦቶ፡ ገዋኒ፡ ሚሌ፡ አዋሽ፡ዱብቲ፡ አብዓላ ወዘተ ከተሞች ላይ የሠልፍ ኘሮግራም ለማድረግና ከመንግስት ፍቃድ ለመውሠድ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ህወሐት ለ27 አመታት በአፋር ህዝብና ንብረት ላይ ያደረሰው ብዝበዛና ጭቋና ከምንም ሳይቆጥረው ነገም ወደፊትም በአፋር ህዝብ ላይ የጭቋና ቀንበር ማስቀጠል መፈለጉን የሚያሳይ እብሪት መሆኑን ያሳያል፡፡ አብዴፓ ለአፋር ወጣቶች በየቦታው የሠልፍ ፍቃድ ጥያቄዎችን ውድቅ እያደረገ በልዩ ሐይልና በፖሊስ አካላት ለሰልፍ የሚወጣውን ወጣት እየደበደበ፡እያሰረ ባለበት ወቅት ለመንፈስ እባቱ ለህወሓት ካድሬዎች የሰልፍ ኘሮግራም ፍቃድ የሚሠጥ ከሆነ በክልሉ ለሚፈጠረው ችግር ከወዲህ የህወሓት መራሹ አብዴፓ መሆኑ ከወዲሁ መታወቅ መቻል አለበት፡፡ ሰለዚህ እንዲህ አይነት ችግር ሆን ተብሎ በህወሓት የተሴረ ሥራ በመሆኑ ህይወሐትና የትግራይ ህዝብ ለይቶ የማያት እይታችን መፍስቶ መገኘት መቻል አለበት፡፡ ለማንኛውም ነገሩ ከመከሠቱ በፊት የክልላችን ሠላም በኛው በራሳችን እጅ ነውና በጠንቀቅ እንጠብቅ፡፡ አብዴፓ ለህወሓት እኩይ ተግባር ለሚደረገው ሠልፍ እውቅና መሰጠት የለበትም ባይ ነኝ፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በነገው ሰልፍ ላይ ይገኛሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በነገው ሰልፍ ላይ ይገኛሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍ እና እውቅና መስጠትን ዓላማ ባደረገው በነገው የአዲስ አበባ ሰልፍ ላይ ይገኛሉ። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሰልፉ ላይ እንዲገኙ የተጋበዙ ሲሆን እሳቸውም ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ። (ፋና ብሮድካስቲንግ)
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቅዳሜው የድጋፍ ሰልፍ ብዙ እንድምታ ያለው ነው። ( ያሬድ ኃይለማርያም )

የቅዳሜው የድጋፍ ሰልፍ ብዙ እንድምታ ያለው ነው። ከ1997ቱ የቅንጅት ሰልፍ ለየት የሚለው በተሳታዊዎች ስብጥር አይነት ይመስለኛል። በነገው ሰልፍ ሦስት አይነት የማህበረሰቡ ክፍሎች የሰልፉ ታዳሚ ይሆናሉ። የመጀመሪያው በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ እና የኢህአዴግ አባል የሆኑ ሚሊዮኖች፤ ሁለተኛዎቹ ኢህአዴግን አጥብቀው የሚቃወሙ እና በቅንጅት ሰልፍም ተሳታፊ የነበሩ ብዙ ሚሊዮኖች እና ሦስተኞቹ በቅንጅት ግዜ ከመንግስት ሊደርስብን ይችላል ያሉትን ጥቃት ፈርተው ጎመን በጤና በማለት ሰልፉን እቤታቸው ሆነው በቲቪ ያዩና ዳር ተመልካች የነበሩ እጅግ ብዙ ብዙ ሚሊዮኖች። ስለዚህ ይህ ሰልፍ ባጭሩ የሁሉም ሰው እና አቃፊ ነው። በዚህ ሰልፍ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት የሚገለል የህብረተሰብ ክፍል አይኖርም። ይህ ከሆነ ሰልፉ በቅንጅት ጊዜ ከታየው ታላቅ ሰልፍ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ እጥፍ የሚያስከነዳ ነው የሚሆነው። ይህ ክስተት ለአገሪቱ ፖለቲካ አዲስ ምዕራፍን ይከፍታል ብዮ አምናለሁ። በአንድ ወገን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘር፣ ኃይማኖት፣ ጾታ እና የፖለቲካ አመለካከቶች ግንብ ሆነው ሳይከልሏቸው በጋራ የሚቆሙበት አገራዊ መድረክ መሆኑ ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ዜጎች ሳይሸማቀቁና ሳይፈሩ ደስታቸውን እና ስሜታቸውን ሊገልጹ ወደ አደባባይ መውጣት መቻላቸው የሚፈጥረው የመነቃቃት ስሜት ነው። እንደ እኔ ሰልፉ ዶ/ር አብይን እና ቡድናቸውን ከማወደስ እና ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ ለራሳችንም ቃል ኪዳን የምንገባበት ቢሆን ጥሩ ነው። የሰልፉ ዋና መልዕክትም ከዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች ቢያካትቱ መልካም ነው። 1. ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከውስጡ የዘር ጥላቻን አውጥቶ ሌላኛውን ወገኑን ልክ እንደራሱ ወንድም እና እህት እንዲቆጥር እና ከእንግዲህ ወዲህ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመነጋገር ወደ አስመራ ያቃናሉ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር  አብይ አህመድ በቅርብ ወደ አስመራ እንደሚጏዙ መረጃዎች እየወጡ ነው ። የኢትዮጵያን የኤርትራን ግንኙነት ለማሻሻል በሁለቱም ሀገሮች በኩል ፈቃደኝነት በተገኘበት በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመነጋገር ወደ አስመራ ያቃናሉ ተብሏል። ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች እንደሰማችው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአስመራ ቆይታቸው የድንበር ጉዳይን ጨምሮ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የአለመግባባት ምክንያት ናቸው ተብለው በተለዩ ጉዳዮች ላይ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት ቀን ይፋ አልተደረገም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለኤርትራ እንዲሰጡ በፍርድ ቤት ከተወሰኑ አካባቢዎች በተለይም ከባድመ ለቆ የሚወጣበትንና አጠቃላይ ግንኙነትን ማሻሻል ስለሚቻልባቸው መንገዶች ዝርዝር ይነጋገራሉ ተብሏል። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን የሰላም ስምምነት ያለቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ ኤርትራ የልዑክን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ መወሰኗን አስታውቃለች። የኤርትራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ እንደሚገባ እየተጠበቀ ሲሆን በቆይታውም ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የአስመራ ጉብኝት ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። እስካሁን ሁለቱ ሀገሮች በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ውይይት ያላደረጉ ሲሆን በውይይቱ ልዩነቶቻቸውንም ሆነ ፍላጎታቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኤርትራ በአዲስ አበባ ለአፍሪቃ ህብረት ተጠሪ ከሆኑ ዲፕሎማቶቿ መካከል አንጋፋውን አምባሳደር አርአያ ደስታን ታሳትፋለች ተብሏል። ኤርትራ ማናቸውንም ዝርዝር ድርድር ከማድረጓ በፊት የኢትዮጵያ ወታደሮች “ከግዛቴ” መውጣት አለባቸው የሚል ቅድመ ሁኔታ ስታቀርብ መቆየቷ ይታወቃል። ከሁለቱ ሀገሮች ጀርባ ዩናይትድ ስቴትስ ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትና ሳዑዲ አረቢያ በአግባቢነት ሚና
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር አብይ አህመድ ለመከላከያ ሰራዊት ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ።

ዶክተር አብይ አህመድ ለመከላከያ ሰራዊት ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ። – ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ – ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በመከላከያ የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ – ሌተናል ጀነራል ሞላ ኃማርያም የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዘርፍ አስተባባሪ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጎሹ ወልዴ የዶ/ር አብይን ለውጥ ደገፉ

SBS Amharic የቀድሞው የኢትዮጵያ የትምህርትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሳይቀጭ ዳር እንዲደርስ፤ ኢትዮጵያውያን ሙሉ ልባዊ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ያቀርባሉ። የግል ድጋፋቸውንም ይቸራሉ።  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና እና ቀቤና ዞንና ወረዳዎች የበላይ አመራሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

በወልቂጤ ከህዝብ ጋር እየተወያዩ ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በደቡብ ክልል በተከሰተው ግጭት የበላይ አመራሮች ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ጠየቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመድረኩ ላይ እንዳሉት በደቡብ ክልል ለተከሰተው አሳዛኝ ነገር ሆን ብሎ በቸልተኝነት በመመልከት አልያም በማቀነባበር የክልሉ ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው እንደገለፁት ግጭቱ የተነሳባቸው የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና እና ቀቤና ዞንና ወረዳዎች የበላይ አመራሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ይድረስ እስረኞች ለምን ተፈቱ ይፈታሉ ለምትሉ (እስረኞች ሲፈቱ አይነናችሁ ለሚቀላ)

ማሕሌት ፋንታሁን በእስር ላይ እያሉ በደረሰባቸው ድብደባ እና ተገቢ ህክምና ሳይሰጣቸው ህይወታቸው እዛው እስር ቤት ሆነው ላለፉት፤ ኢንጅነር ተስፋሁን ጨመዳ ፣ ኒሞና ጥላሁን፣ ሙባረክ ይመር፣አየለ በየነ፣ አብደታ ኦላንሳ እና ሌሎችም በእስር እያሉ ሳይገባ ህይወታቸው ላለፉ እስረኞች ቤተሰቦች/ወዳጅ ዘመዶች የእስረኞች መፈታት ምንድነው? ምርመራ በሚል ሰበብ አካላቸው ለጎደለባቸው ለእነ አበበ ካሴ፣ ከፍያለው ተፈራ፣ አስቻለው ደሴ፣ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን እና ሌሎች በርካቶች ከእስር መፈታት ምንድነው? ተፈቱ የተባሉት እስረኞች ከሚደርስባቸው አካላዊ እና አእምሯዊ ጉዳት በተጨማሪ ህገ መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን ከቤተሰብ የመገናኘት እና ክሳቸውን የመከላከል መብታቸውን በሚጋፋ መልኩ (አብዛኛዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ተገናኝቶ ጠበቃ ለማቆም እና መከላከያቸውን ለማሰባሰብ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ስለማይችሉ ሳይከላከሉ ነው የሚፈረድባቸው)። ከመኖሪያ ቤታቸው እና ቤተሰቦቻቸው በርካታ ኪሜ ርቀት ላይ ነው ክስ የተመሰረተባቸው፤ ታስረውም እንዲቀመጡ የተደረገው። በሁለት እና ሶስት አመት ፍርድ ቤት መመላለስ ብቻ ፍርድ ማግኘት እድለኝነት ነው። ፍርድ ቤቶች የሚሰጣቸው ቀጠሮ በጣም ረጃጅም ነው። ሌላም ብዙ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን የሚፃረሩ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው በደሎች ደርሶባቸዋል። እየደረሰባቸውም ነው። ይህን ሁሉ አሳልፈው ለምን ተፈቱ ይባልልኛል። ከተፈቱ በኋላ ወደ ስራቸው ለመመለስ ፣ ጤናቸውን ለመመለስ (መመለስ የሚቻለውን)፣ እና ሌሎች የሚገጥሟቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው። የእስረኞቹ መፈታት እስረኛ የነበሩ ቤተሰቦቻቸውን በሞት ላጡት ምንም ነው። በህይወት ለወጡትም ቢሆን መፈታታቸው የደረሰባቸውን በደል፣ ያሳለፉትን ስቃይ፣ ያጡትን አካል … አይመልስላቸውም። የቤተሰቦቻቸውን አንግልት እና ስቃይም አይመልስም። ታስረን ስንፈታ ፤ እስረኞች
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ እና ሰሞነኛው “ተቃዋሚ” (ጌታቸው ሽፈራው)

ዶ/ር አብይ እና ሰሞነኛው “ተቃዋሚ” (ጌታቸው ሽፈራው) ዶ/ር አብይ አህመድ INSA ምክትል ዳይሬክተር በነበረበት ወቅት፣ አንድ የኢህአዴግ ካድሬ “ጥናታዊ ሪፖርት አቅርብ” ሲባል የሚያቀርበው መወድስ የበዛበት ሪፖርት ነበር። መግለጨ አይነት! አብይ ምን አለው? “ይህን ይህንማ አዲስ ዘመን ይፅፈዋል! እኔ የምፈልገው ድክመቱንና ክፍተቱን ነው። ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ክፍተቱን ማወቃችን ነው” ተቃዋሚ የሚባል ሁሉ ሰሞኑን አንድ ለአምስት እየተጠረነፈ ነው አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ:_ ~ አብይ አንድ ለአምስት የተጠረነፈውን የሴት፣ የወጣት፣……ሊግ አያጣውም። ሰልፍ የሚወጣ ሞልቶታል! አብይ የሚፈልገው ጥሩ ተቃዋሚ እንጅ የሴትና የወጣት ሊግ ላይ የተለጠፈ ተቃዋሚ አይመስለኝም! ~ከመለስ ዘመን ጀምሮ በማጨብጨብ የሚከፈላቸው አሁንም የአብይ ናቸው። እንዲያውም ዛሬ አንገታቸውን በአድናቆት እየነቀነቁም ቢሆን ያጨበጭባሉ። ~አብይ የሚፈልገው ጠንካራ ተቃዋሚ ይመስለኛል። ለሰማይ ጠይቆ፣ አብይ ለጣራ እንዲመልስ፣ መልስ እንዲያሰጥ የሚያግዘው። አብይ “ሕዝብ እንዲህ እያለ ነው” ብሎ ስለተለጠጠ ጥያቄ ሲያነሳ መካከለኛ መንገድ ላይም ቢሆን ብዙ መልስ እንዲሰጥለት የሚያስችል ጥያቄ የሚያነሳ ተቃዋሚ! ~የሽግግር መንግስት ብቻ አይደለም። ትህነግ/ኢህአደግ አሸባሪ ነው፣ ወንጀለኛ ነው ይፍረስ የሚል ተቃዋሚ ያስፈልጋል። ለድርድር የሚሆነው “ፈርቅ” የሚይዝ ተቃዋሚ ያስፈልጋል። ካድሬ የማይጠይቀውን የሚጠይቅ ተቃዋሚ ያስፈልገዋል። ~አብይን ተከትሎ መግተልተል ብቻ ሳይሆን አማራጭ ማቅረብ ወይንም ቀድሞ መንገድ የሚዘጉትን፣ ወይ ከኋላ የሚመቱትን/ ወደኋላ የሚጎትቱትን መያዝ ያስፈልጋል። ይህ ግን በመግተልተል አይሆንም። መግተልተል ከፊት ያለውን መከተል ብቻ ነው። ከፊት ያለውን መንገድ መጥረግ ወይንም ወደኋላ ዞሮ መመከት ሌላ ስራ ነው። ከመግተልተል ይለያል። መግተልተልን ካድሬ ይሰራዋል። ተቃዋሚ ቦይ መቅደድ፣
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለቅዳሜ ሰኔ 16 ለዶ/ር አብይ ድጋፍ በመስቀል አደባባይ የተጠራው ሰልፍ አስተባባሪዎች መግለጫ ሰጡ

ሰኔ 16 በአዲስ አበባ የድጋፍ ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚ/ር ዓብይ አህመድ የወሰዷቸውን የማሻሻያ ሀሳቦች በመደገፍ ሰኔ 16 ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደው ሰልፍ ጭብጥ ምክንያት አድርጎ የሚካሄድ ነው ሲል የሰልፉ አስተባበሪ ኮሚቴ ዛሬ በኢሌሌ ሆቴል ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድቷል። ሰልፉን ለማድረግም ከመንግስት ፍቃድ እንዲሰጣቸው በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ የሰልፉ አስተባበሪ አቶ ጉደታ ገላልቻ አበሰጡት መግለጫ ሰልፉ የፓርቲ አጀንዳን አያስተናግድም፡፡ በሰልፉ የአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ዓላማውም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ ሙሉ ቪዲዮና ዘገባ ይመልከቱ

https://youtu.be/tvcb5-cjkh0 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፓርላማው በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ አለመግባባቶችና ግጭቶች እንዲሁም በወሰንና ድንበር ዙሪያ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጧቸው መልሶች መካከል፡ • አሁን ያለው የወሰን አስተዳደር ችግር እየፈጠረ በመሆኑ ዳግም መለስ ብለን ከችግሩ የምንወጣበትን መንገድ መቀየስ ያሻል፡፡ • ክልልን ከክልል ብቻ ሳይሆን አገርን ከአገር የሚከልል ድንበር ከጎረቤቶቻቸን ጋር ሳይቀር ማስተናገድ የሚያስችል አሰራር ያስፈልገናል፡፡ • ኢትዮጵያ ያለ ቪዛ እንግዶቿን ለመቀበል የሚያስችል አሰራር ለመተግባር እየተጠና ነው፡፡ • እንኳንስ በክልሎች መሃል ያለው ወሰንና አንድ የሆኑ ህዝቦችን ከፍሎ ያለው ድንበር እንኳን ሰው ሰራሽ በመሆኑ በጋራ መኖር የሚያስችል ሂደት መከተል አለብን ፡፡ የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሃት ማለት አይደለም ። በትግራይ ህዝብ ስም የተወሰኑ ሰወች ተጠቅመው ሊሆን ይችላል እንጂ የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ጥቅም ያላገኘ ህዝብ ነው ። የትግራይ ህዝብ መደገፍ፣ መታገዝ እንጂ ከህወሐት ጋር ተደምሮ በጥላቻ መታየት የለበትም። • እንደ ቴሌ፡ አየር መንገድ ፣የኃይል አቅርቦት ዘርፉ እና አንዳንድ የመንግስት ተቋማት የተወሰነው ድርሻቸው የሚሸጠው እዳቸውን ጭምር መክፈል ስላቃታቸው ነው፡፡ • በውድድር ላይ የተመሰረተ ጥራት ያለው አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል፡፡ • ሽግግሩ ጥንቃቄ የሚፈልግ ስለሆነ እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ ይችላል፡፡ • የሀብት ብክነትን ያስቀራል፡፡   ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛው ልዩ ስብሰባ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት መንግስታቸው በዲፕሎማሲ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረጉንና ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የጎረቤትና የመከከለኛው ምስራቅ አገራት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ቅዳሜ፣ ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን የለውጥ እርምጃዎች ለመደገፍ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን የለውጥ እርምጃዎች ለመደገፍ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 27 አመታት በጥቂቶች የጭቆና አገዛዝ ስር ወድቃ ዜጎቿ ለሞት፣ ለእስር፣ ለአካል ጉዳት፣ ለቶርቸር፣ ለስደት፣ የሀገራችን ሀብት እና ማዕድናት ተዘርፎ ለጥቂቶች የተንደላቀቀ ኑሮ እና ምቾት እየዋለ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ። በአጠቃላይ የሀገራችን ህዝቦች በገዛ ሀገራቸዉ ተንቀዉ እና ተዋርደዉ ለመከራ ኑሮ የተዳረጉበት፣ የሀገራችን ወጣቶች በሀገራቸዉ ተስፋ አጥተዉ ለስደት የተዳረጉበትና በየበረሃዉ በዉሃ ጥም እና በረሀብ እየረገፉ፣ በባህር የዓሳ እራት እየሆኑ እንደሆነ ይታወቃል። የሀገራችን ህዝቦች በተለይም ወጣቱ አንድም ቀን ለዚህ ለዉርደት ለዳረጋቸዉ የጥቂቶች የጭቆና አገዛዝ ተንበርክከዉ አያዉቁም። በኦሮሚያ የቄሮ፣ በአማራ የፋኖ፣በጉራጌ ዘርማ በሌሎች የሀገራችን አከባቢዎችም ወጣቶች በተደራጀ እና በተበታተነ መልኩ ገዢዎችን እየተፋለሙ ዉድ ህይወታችዉን እና አካላቸዉን ገብረዋል። ትኩስ የወጣትነት ዕድሜያችዉንም በማዕከላዊ፣ በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በከርቸሌ እና ሌሎች ማጎሪያ ካምፖች ዉስጥ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ወጣቶች መስዋዕትነት እና የደም ፅዋ ሞልቶ መፍሰስ ጀምራል። በሀገራችን ወጣቶች ትግል የህዝብ ልጆች የሆኑ፣ ህዝብ ህዝብ የሚሸቱ፣ የህዝቡ ስቃይ የሚያማቸዉ አመራሮች ወደ ፊት በመዉጣት ትላልቅ እርምጃዎችን መዉሰድ ጅምረዋል። በዶ/ር አቢይ አህመድ የሚመራዉ አዲሱ መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞችን ነፃ አዉጥቷል። በተለያዩ ሀገራት ተሰድዉ በእስር የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዉያንን አስፈትተትዋል። ሲደረጉ የነብሩ ዝርፊያዎችን በማስቆም ላይ ይገኛል። አይነኬ የማይመስሉ የገዢዉ መደብ ደም መጣጭ ፈርኦኖች ከስልጣን በማሰናበት ተስፋ የሚሰጥ የለዉጥ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመስቀል አደባባይ ለዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ሊደረግ ነው ።

ለዶ/ር አብይ የአዲስ አበባ ሕዝብ በሰልፍ ድጋፉን ለመግለፅ ቅድመ ዝግጅት ተጀምሯል። #AbiyAhmed #I_stand_With_Ethiopian_PM_Abiy_Ahmed ከቄሮ እና ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር በመጣመር ለዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲጠራ አስተባባሪ አዘጋጅ ግብረኃይል ተቋቁሟል ። ህዝባዊ ሰልፉ ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መሰቀል አደባባይ እንዲከናወን ባዘጋጅ ኮሚቴዉ ተወስኗል፡፡ የዝግጅት ዋና አስተባባሪዎች … 1-ክንፈሚካኤል ደበበ(አበበ ቀስቶ) 2-ስንታየሁ ቸኮል ተሰይመዋለል ~ ንዑስ ኮሚቴዎች -አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ -አቶ ተፈራ ተስፋዬ -ስለሺ ደሳቻ -ወጣት ኤፍሪዬም ሰለሞን በአስተባባሪነት ይገኛሉ፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል የማሳወቅ ተግባሮች ይደረጋል፡፡ #MinilikSalsawi
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶክተር አብይ አሕመድ ግጭት ወደባሰበት ደቡብ ክልል ሕዝቡን ለማነጋገር ሊያቀኑ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከህብረተሰቡ ጋር ለመወያየት ቀጣይ ሳምንት ወደ ደቡብ ክልል ያቀናሉ በአገሪቱ አንዳንድ አከባቢዎች በተለይም ደግሞ በሀዋሳና ወላይታ ሶዶ የተነሱትን ግጭቶች ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ገለጹ፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን በሰላምና ፍቅር የምትታወቀው የትንሿ ኢትዮጵያ የደቡብ ክልል ነዋሪዎች፣ የአከባቢው ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ለአካባቢያቸው ሰላም በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡ የጸጥታ አካላትም ህብረተሰቡን ባሳተፈና እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ የየአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክልል እንሁን በሚል ለሚነሱ ጥያቄዎች ሕገ መንግስቱ ስርዓት ያስቀመጠ በመሆኑ ሁሉንም ነገር በሰላም መጠየቅና ማስተናገድ እንደሚቻልም ገልጸዋል፡፡ ከወሰን ጋር በተያያዘ በተለያዩ አከባቢዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በጥናት መመለስ ይቻል ዘንድ ይህንን የሚከታተል ኮሚሽን ለማቋቋም መንግስት እያሰበ መሆኑንም ዶ/ር አብይ ገልጸዋል፡፡ ይህ ኮሚሽን ከየአከባቢው የሚነሱ ጥያቄዎችን በመቀበል ስር ነቀል መፍትሔ እንደሚሰጥም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ምንጭ Ebc
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ በዶክተር አብይ ላይ ግልጽ የማጥላላት ዘመቻ ጀምሯል።

በዶክተር አብይ ላይ ግልጽ የማጥላላት ዘመቻ ተጀምሯል። ከጀርባ በህወኃቶች የሚዘወረው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ አብዲ ኢሌ “ላይቭ” ቪዲዮ ገብቶ ሲፎክር ውሏል። “አብይን ከመለስ ጋር ማነጻጸር አይቻልም።መለስ በጣም ትልቅ መሪ ነው። አብይ ካጠገቡም አይደርስም” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በግልጽ በማጥላላት የጌታቸው አሰፋ የመፈንቅለ ሥልጣን ቡድን አካል መሆኑን ያመለከተው አብዲ ኢሌ” አሁን የተገኘውም መረጋጋት በሁላችንም እንጂ በአብይ ብቻ አይደለም።”ሲል ተደምጧል። አንድ ሚሊየን ሰው ያፈናቀለና ብዙዎችን የጨፈጨፈ ሰው፣ገና የተፈናቀሉት ከተበተኑበት ሜዳ ተጠቃለው ሳይሰባሰቡ እንዲህ መደንፋቱ ይገርማል። የክልሉን ምሁራን ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና እና ከውጭ የመጡ የሶማሌ ተወላጆችን እያስደበደበና እያሳሰረ ያለው ዱርዬው አብዲ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አፉን እስከማላቀቅ የደረሰው በነማን አይዞህ ባይነት እንደሆነ ግልጽ ነው። አክሎም ፦”ግዛታችን ጅግጅጋ ላይ አይቆምም።አዋሽ ድረስ ይዘልቃል። ህልማችንን እናሳካለን!” እያለም ፎክሯል። ጅምር ለውጡ እንዳይቀለበስ የምትሻ ሁሉ፣ ትንታኔ ሳታበዛና ሳትፈላሰፍ፣ ሳትግደረደርና ሳትሽኮረመም … ግልጽ ድጋፍህን ለዶክተር አብይ የምትሰጥበት አስገዳጅ ጊዜ ላይ ደርሰሃል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ የኢምሬቱን አልጋ ወራሽ እራሱ መኪና እየነዳ አዲስ አበባን አስጎብኝቷቸዋል ።

  ዶክተር አብይ ዛሬ በእንግድነት የተቀበላቸውን የአረብ ኤሜሬቱን ልዑል አልጋ ወራሽ ሼኽ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን እራሱ መኪና እየነዳ አዲስ አበባን እንዲህ አስጎብኝቷቸዋል!!! የተባበሩት አረብ ኤመሬትሱ ልዑል 3ቢሊዩን ዶላር ድጋፍ አድርገዋል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያ ሶስት ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ሰጠች። አንድ ቢልዮን ዶላሩ በቀጥታ ለብሔራዊ ባንክ የሚገባ ሲሆን ሁለት ቢሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።  
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሕአዴግ በሆዳም ካድሬዎቹና በጥቅም በገዛቸው ወሮበሎች ሃገር እየበጠበጠ ነው።

ተአምር ከሰማይ የወረደ ያሕል ስናጋንን አገራችን ወደ ከባድ አደጋ እያመራች ነው። ልንክደው የማንችለው = አትኩሮት የነፈግነው = በራሳችን ድክመት ኢሕአዴግ የፈጠረው – የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርጉት ግድያና ማሳደድ – የኦሕዴድ ካድሬዎች አማራውን እያፈናቀሉ ቤቱን እያቃጠሉ እየገደሉ ማሳደድ – በቤንሻንጉል ጉምዝ በአማራው ላይ አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል እስከ ብልት መስለብ – በአፋር ሕዝብና በ አማራ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ግጭት – በጌድዎ ሕዝብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ግጭት – በኦሮሞና በሲዳማ ሕዝብ መካከል የሚደረገው ግጭት – በሲዳማና በወላይታ ሕዝብ መሓል የተከሰተው ግጭት – በጉራጌና በቀቤና መካከል የተከሰተው ግጭት – በሀረር በክልሉ ካድሬዎች መካከል የተለኮሰው እሳት – በትግራይ በሀጋር ሉአላዊነት ስም የተሰራጨው አደንዛዥ አጀንዳ … ወዘተረፈ … አደግመዋለሁ ስለ እውነት እንቁም ስለሕግ እንቁም ስለ ሕዝብ መብት እንቁም። ከላይ በዝርዝር የተከሰቱና የቀተሉ ወደፊትም የሚከሰቱ ግጭቶች በዋናነት ስፖንሰር ሆኖ የሚያካሂደው የሚያስፈጽመው ኢሕአዴግ የተባለ ስልጣኑን መነጠቅ የማይፈልግ ስለ ሕዝብ ደንታ ቢስ የሆነ ድርጅት ነው። ኢሕአዴግ በሆዳም ካድሬዎቹና በጥቅም በገዛቸው ወሮበሎች ሃገር እየበጠበጠ ነው። ሕዝብን እየገደለ እያፈናቀለና እያሳደደ ነው። ለዚህ ደግሞ የተቃዋሚውን መዘናጋት ተጠቅሞበታል። ተቃዋሚው ከመታገልና በሕዝብ ውስጥ ስራ ከመስራት ይልቅ ተዓምር የወረደ ያሕል የኢሕአዴግን አጀንዳ በቅንነት ሲያስፈጽም ሕዝብ አደጋ ላይ ሆኗል።ተአምር ከሰማይ የወረደ ያሕል ስናጋንን አገራችን ወደ ከባድ አደጋ እያመራች ነው። የስርዐቱ የጎሳ ፌዴራሊዝም ችግር ብቻ ሳይሆን ኢሕአዴግ ስልጣኑን ላለመነተቅ የሸረበው
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው

የሕወሓት ሳቦታጅ አንዱ ክፍል የመረጃ ቀውስ መፍጠር ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ውጥረት ከኢሕአዴግ የፖለቲካ ባሕሪይ አንጻር መለካት መጭውን ጊዜ ለማወቅ ይረዳል። ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው ፤ ለሕዝቡ የድንበር ውሳኔውን አጀንዳ ስለሰጠው ይህን ያሕል አይሰጋም ፤ አጃቢው አረና አጀንዳውን በሰላማዊ ሰልፍ ያደምቅለታል። በሰበር ዜናና በተባራሪ ዘገባዎች የመረጃ ቀውስ ተፈጥሮ የተቃዋሚዎች ትግል የእንቅልፍ ላይ የቅዠት መወራጨት አድርጎታል ። ለኤርትራ ይሰጣሉ የተባሉት መሬቶች ሕጋዊ የውሳኔና የማስረከብ ፕሮሰሳቸው መስመሩን የተከተሉ አይደሉም ፤ ስለዚሕም ኤርትራ የሚፈለገውን ከመናገር ተቆጥባለች ፤ ሕጋዊ መስመሩ ኢሕአደግ ውሳኔው ለተመድ ቀጥታ ማሳወቅ ነበረበት ፤ ተመድም ለኤርትራ መንግስት ያስተላልፍና የኤርትራን መልስና መግለጫ ተከትሎ ሕጋዊ አግባቡ ይተረጎማል ። ወያኔ ግን ይህንን ሕጋዊ መስመር ካለመከተሉም በላይ የወሰነው ውሳኔ የሐገር ውስጡን ትኩሳት ለማብረድና በሰበር ዜናና በሰልፎች ሐገሩን ማመስ ይዟል። ወያኔ ኢሕአደግ በተከታይነት ሕዝቤ በውሳኔው ስላልተስማማ ተመልሼ ላጢነው የሚል ተመሳሳይ መግለጫዎችን ይለቃል ። #MinilikSalsawi
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግብፅ ያሰረቻቸውን ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ፈታች ።

ግብፅ በሀገሪቱ ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ለቀቀች።ከአመታት በፊት በሊቢያ በአሸባሪዎች የተገደሉ ዜጎች አፅም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በክብር እንዲያርፍ ግብጽ እገዛ እንደምታደርግም መግባባት ላይ ተደርሷል። ሀገሪቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግብፅ ጉብኝታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤልሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው ኢትዮጵያውያኑን የፈታችው። ኢትዮያውያኑ ወደሀገራቸውም እንደሚመለሱም በውይይት ላይ የተሳተፉት የጠቅላይ ሚኒስቴር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግረዋል።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሃይማኖት ተቋማት – “ሥራቸው የሞራል ልዕልና መፍጠር ነው፡፡ የሌብነት ምሽግ መኾን አይችሉም፤” – ጠ/ሚኒስትሩ

ሃይማኖት ተቋማት ሙስና መንግሥት እርምጃ ይወስዳል! – ጠ/ሚኒስትሩ • “ሥራቸው የሞራል ልዕልና መፍጠር ነው፡፡ የሌብነት ምሽግ መኾን አይችሉም፤” • “ሃይማኖት በመንግሥት፣ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለው ሚዛን ያስፈልገዋል፤” የሃይማኖት ተቋማት በውስጣቸው የተሰገሰገውን የሌብነት ድር በመበጣጠስ፣የሞራል አስተማሪነታቸውን በተግባር እንዲያሳዩ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከእንግዲህ መንግሥታቸው በተቋማቱ ውስጥ የሚፈጸምን ዘረፋና ሌብነት በቸልታ እንደማያልፈው አስጠነቀቁ፡፡ “ሃይማኖት በመንግሥት፣ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም፤”የሚለው የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ ትክክለኛ መርሕ ቢኾንም፣ የሃይማኖት ተቋማት የሚሰበስቡት መባ እና ዘካ የሕዝብ ሀብት እስከኾነ ድረስ መንግሥት አጠቃቀሙን የመቆጣጠር ርምጃ እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ገንዘብ የሕዝብ ሀብት እንደኾነና በየትኛውም ዓለም ኦዲት እንደሚደረጉ የጠቀሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ትንሽ የሌብነት ምልክት ካዩ ፈቃዳቸውን እስከመቀማት እንደሚደርሱ አስረድተዋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ከመሬት ጀምሮ ለመንግሥት ለሚያቀርቡት ጥያቄ ባለሥልጣናቱ በእኩልነት ምላሽ መስጠት የሚገባቸውን ያህል፣ በአጸፌታው የመንግሥት ጥያቄ “ምከሩ፤ ገሥጹ፤ ሰላም አምጡ” በማለት ብቻ እንደማይወሰንና እንደማይቀጥል አስረድተዋል፡፡ “በዕለት ተዕለት የሃይማኖት ሥራ መንግሥት አይገባም፤ በመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ ሃይማኖት አይገባም፤ ግን ደግሞ ቀይ መሥመርና ድንበራችን ሁሌ የቆመና የማይገናኝ አይደለም፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አጠቃላይ መርሑ ትክክል ቢኾንም ዘወትር እንደማይሠራና ሚዛን እንደሚያስፈልገው አስገንዝበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም፣“የሃይማኖት ተቋማት ዋነኛ ሥራቸው፣የሞራል ልዕልና መፍጠር ነው፤ የሌብነት ምሽግ መኾን አይችሉም፤ የለባቸውም፤ አላግባብ መባ እየሰበሰቡ ምን ላይ እንዳዋሉት የማይታወቅ ከኾነ ከእነርሱ የሚጠበቀው የሞራል ልዕልና ይጠፋና የሚያስተምሩትም ምእመን ሌባ ይኾናል፤”በማለት በውስጣቸው የተሰገሰገውን የሌብነት ድር በመበጣጠስ እንዲሁም ሃይማኖት በጥበብና
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈፀመ እንደሚገኝ ተናገሩ። (ቪድዮ)

ሊያዳምጡት የሚገባ የዶ/ር አብይ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የእሳቸው ወደ ስልጣን መምጣትን በመቃወም የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈፀመባቸው መሆኑን ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጉባኤ ላይ ገለፁ ። $bp("Brid_19123_4", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://www.mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/Facebook-917591661745208.mp4", name: "ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈፀመ እንደሚገኝ ተናገሩ። (ቪድዮ)", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/IMG_20180606_135435.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ መሪ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፤የጉልበተኞች ታዛዥ እንዳይሆኑ ግን ምርጫው የርስዎ ነው።

ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ ዶክተር አብይ አህመድ ሥርዓቱ (በሕውሃት) የአጭበርባሪነት ተግባርን ሲፈፅም ብዙ ንፁሃን ሰዎች በደም-ሥልጣን እንዲጨማለቁ አድርጎ፣ “የለሁበትም” “ከደመ-ንፁህ ነኝ” በማለቱ ብቻ ስንቶቹ በተንኮሉ ከንቱ ሆነው ቀርተዋል፤ያበዱትንና አካለስንኩላን የሆኑትን ሳይጨምር። የችግሩን ምንነት ተረድተን እና የሚደርስብንን መከራ ችለን፣የቻልነውን ያህል የሞከርነው ግን እርስዎ አይሮፕላኑ ውስጥ እንዳሉትን ያህል የማይሰማዎትን መብረቅን የመሰለ የሕዝብ የሰቆቃ ድምፅ ከምድር ወደላይ «ዑኡ…ዑኡ!!!»እያለ የግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ ጣር ሲያስተጋባ እየሰማንና በአይናችንም ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ስለምናይ ነው፤ሕውሃት ኢሓድግን አምርረን የምንታገላቸው፤እርስዎ ዶ/ር አብይ አህመድ በፊርማዎ ኖሩበት፣አልኖሩበትም። ይገርምዎታል የችግሩ ግዝፈት ቅጥ አጥትቶ፦«ሰረቀ” የሚባል ነገር የለም፤» ወደ «ዘረፈ»ከተሸጋገረ እና እየባሰም ብሶ“በደም የተነከረ”ነው የሚለው እየበዛ ነው። “በመቶ ሺህ”የሚለው ቀርቶ፤“በሚሊዮን” የተለመደ ሆኗል፤ ብሶም“ብሊዮን አላቸው”የሚባሉትን መቁጠር ከጀመርን ሰነባበተ።   ኮነሬል አብይ አህመድ ይባስ እንዳይገርምዎት፣እነዶክተር መኮንንም ሆኑ እነዶ/ር ፍቅሬ ከስላሳ እና አርባ አመታት በላይ በየሆስፒታል አገልግለው፣እነረዳት ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ስንት ምሁራንን ያፈሩልን፣ሌሎቹም፣እነ እንጂነር እና መምህር አዕምሮ ፈረደ፣ሲስተር አያልነሽ፣እንዲሁም ነጋዴው አባባ ዘርጋው፣ስንቱ ተቆጥሮ ያልቃል ዕድሜ ልካቸውን ለሕዝብ ቀን ከሌት ጥረው ግረው በየሙያቸው ሕዝብን ሲያገለግሉ ያላገኙትን ገንዘብም ሆነ ንብረት፦የዘመኑ ዘራፊዎች ያላቸው ካፒታል ገንዘብና ንብረት ሲታይ ሰርተው ሳይሆን በሕገወጥ ለመምጣቱ ራሱ ሙስና በምሥክርነት ከመቅረብ በስተቀር ምንም ዓይነት ማስረጃ ነፃ ሊያደርጋቸው የሚችል ሊያቀርቡ አይችሉም።የሕዝብም ጥያቄ እና ትግል የሚያርፈው ይህንን ዝርፊያ “ዓይነ-ደረቅ ሌባ ቃጭል ይዞ እንደሚገባ” ዓይነት ጥፋት በደም የተለወስ በደልን በሕዝብ አመፅ ለማስቀረት ነው፤ማንም ደግሞ ሕዝብን አይከለክለውም።እርስዎን አማላጅነት ባያመጡና በገላጋይነት በትግላችን ፊት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የስፖርት ፌዴሬሽኑ ውሳኔ ፤ዶ/ር አብይን እንደዜጋ ተቀብሎ ለማነጋገር አይገታንም፤ (አሰግድ አረጋ)

የስፖርት ፌዴሬሽኑ ውሳኔ ፤ዶ/ር አብይን እንደዜጋ ተቀብሎ ለማነጋገር አይገታንም፤ (አሰግድ አረጋ) ጠ/ሚኒስትሩን ላለመጋበዝ በስሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን የደረሰበትን ውሳኔ እንደየስሜታችን  አስተናግደነዋል። ከመግለጫው እንደተረዳነው ዶ/ር አብይንና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችን ባልመጠነ መስተንግዶ ለመቀበል  እንዳልተዘጋጀ ነው ። ይሁን እንጂ ፤በተለያዩ ሁኔታዎችና አጋጣሚዎች እየወጡ ያሉ መርጃዎችና ( ተዓማኒነት አላቸው ከሚባሉ የሚዲያ አውታሮችና ታዋቂ ግለስቦች ጭምር) እየተነገረ ያለው ዕውነታ ፤ በውሳኔው ላይ ስሜታችን እንዲሻክር ፤ ፌዴሬሽኑ ደረሰበት ለተባለው ውሳኔ አሉታዊ መንፈስ እንዲኖረን የበኩልን ሚና እንደተጫወተ ነው። ለአብነት ለመጥቀስ፤ ጠ/ሚኒስትሩ ጥያቄውን ለፌዴሬሽኑ እንዲያቀርቡ የተሄደበት መንገድ ቀናነትንና ቀጥተኝነትን ያልተላበሰና ፤ በራሱ ጥያቄ ያስጫረ እንደነበር ተመልክቱዋል። የዶ/ር አብይ መስተንግዶም በመሃበረሰቡ የመሪነት ሚና ባልታወቁና አመኔታን ባላተረፉ ግለስቦችና ተቁዋማት እንዲመራ የተሞከረብት ሁኔታና ይህም “ግብዣቸው ፈጠነብን” ፤ “አሁንም ኢሕአድግ ናቸው” ከሚሉ ወገኖች ጋር ተዳምሮ በውሳኔው የድምጽ አሰጣጥ ላይ ጥላውን እንደጣለበትም ተደምጡዋል። በትክክለኛው መንገድ ቢኬድም እንኩዋ ውጤቱ አሁን ካየነው ላይለውጥ ይችላል፤ ነገር ግን የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ያለፈበት ጎዳና  በተቁዋሙ ተዓማኒነት ላይ ሊጥል የሚችለው ጠባሳ በቀላሉ መታየት የለበትም። በእርግጠኝነት ምን እንደተፈጸመ ለመረዳት በጊዜና  ታሪክ ሂደት ውስጥ አልፎ የምናየው ስለሚሆን፤ ወደሁዋላ ላለመመለስ ለራሳቸን ቃል ገብተን፤ እውቀታችንንና ጉልበታችንን ባሰባሰበ ሂደት፤ ወቅቱን በመጠነና የጊዜውን ፍጥነት በአማከለ ሂደት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሩትን የለውጥ ጉዞ በተጨባጭ ለማገዝ  የምንቀሳቀስበት እንዲሆን ጥሪያችን ነው። በመሰረቱ፤ ዶ/ር አብይ እያራምዱ ያሉት ኢትዮጵያዊነት ከፌዴሬሽኑ ውሳኔና እርሱም ካስከተለው በጎም ሆነ በጎ-ያልሆነ ስሜት በላይ ነው። እያሳዩን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከመከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች ጋር በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ ( ቪድዮ )

ሀገራችን ብሄራዊ ጥቅሞችን ለማስከበር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ፣ ዲፕሎማሲ እና ወታደራዊ አቅሞችን አቀናጅቶ ሀገራዊ ክብርና ልዕልናዋን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የመከላከያ ሰራዊት የማይተካ ሚና እንዳለው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡ ብሄራዊ ፍላጎትና ጥቅም በሌላ ቋንቋ የህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ማለት በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊትከ ህገ-መንግስቱ የሚመነጩ ግልጽ ተልዕኮዎችን አንግቦ ለህዝብ ፍላጎት የሚገዛና ለህዝብ ጥቅም የሚሰራ መሆነ አለበት ብለዋል፡፡ የተለያዩ ሀገሮች የመንግሰት ምስረታ ታሪክ እንደሚያሳየው በ19ነኛውና 20ኛው ክ/ዘመን በፊት የሀገር ጥቅምና ፍላጎት የሚመነጨው ከተለያዩ የገዥ መደቦችና እምነት ተቋማት እንደሆነ የጠቆሙት ጠ/ሚሩ ዘመናዊው ብሄራዊ ጥቅምና ፍላጎት አረዳድ ግን ህዝብና ህዝብን ብቻ መሰረት ያደረገነው ብለዋል፡፡ የብሄራዊ አቅማችን ዋነኛ መገለጫ የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግቦች ማሳካት እና የሀገራችን ህዝቦች ክብርና የሀገር ሉዓላዊነት ማስከበር ናቸው ብለዋል፡፡ ዘመናዊው ጦርነት ከመደበኛ የጦርነት አውድ የተለየ ቅርጽና መልክ አለው፡፡ መንግስታትና መንግስታዊ ያልሆኑ የጦርነት ተዋናዮች የሚሳተፉበት፣ የግለሰቦች እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን የማድረግ አቅም ያመጠቀ የቴክኖሎጂ እድገት መኖር እና አለማ-ቀፋዊነት ያመጣው የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና የባህል ትስስር ከፍተኛ የሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የዘመናዊ ጦርነትም ህዳሩን ባህሪያት አስረድተዋል፡፡ የጦርነት ስልቱም አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት ከሚደረግ ጥረት ይልቅ የተፃራሪ ኃይሎችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስርዓቶችን የሚያሳትፍ፣ የተፃራሪ ሀይልን ውሳኔ ሰጪ አካላት ስትራተጂ እቅድ እንዳይሳካ ወይም ውድ ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ እንዲታይ ማድረግን መሰረት ያደረገ የጦርነት ስልት ነው ብለዋል። ዘመናዊ መደበኛ ጦርነቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው)

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው) በኦሮሚያ ክልል በብዙ ዞኖች አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ለምሳሌ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌና ሌሎችም የአዲስ አበባ ዙሪያ ዞንን ጨምሮ አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ አንዱ ሲያቆም ሌላው እየተከተለ ሁሉም ቦታ ተፈናቃይ ብቻ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ የሚፈናቀሉት በሕወሓት ትእዛዝ ነው ማለት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡ ሁሉም አማሮች እየተፈናቀሉ ያሉት ለአማራ ተወላጆች ከ2 ሔክታር መሬት በላይ አይገባቸውም በሚል ከኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በወረደ ትእዛዝ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባና እንግልት ያደርሳሉ፡፡ ለምን ብለው የሚጠይቁ በወንጀለኛነት ይታሠራሉ፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው ከአመያና ኖኖ ወረዳ ቤት ንብረታቸው ወድሞ እንደገና 14 ዓመት በላይ እስር ተፈርዶባቸው በአምቦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አማሮች አሉ፡፡ የሚፈጠሩ አጋጣሚዎችን ሁሉ ወደብሔር ግጭት ለመውሰድ የሚጥሩ አካላት በሁለቱም በኩል እንዳሉ እሙን ነው፡፡ ይህ ችግር የኦሮሞ ሕዝብ ችግር እንዳልሆነ እናምናለን፡፡ ችግሩ የሚያስፈልገው ፖለቲካዊ መፍትሔ ነው፡፡ አቶ ለማና ዶክተር ዓቢይ ለአገር አንድነት እንሠራለን እንደሚሉት የዚህን ጉዳይ በአፋጣኝ መልስ ሊሰጡት ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን የሚከተለውን ቀውስ ለመተንበይ የግድ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡ ስለሆነም በሰከነ አእምሮ የሚያስብ ማንኛውም ፍጡር ሁሉ ይህን ኢሰብአዊ ድርጊት እያወገዘ ውስብስብ ችግር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ልንጠይቅ ይገባል፡፡
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጠ/ሚ አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ኢትዮጵያችን በጎ አጋጣሚ ሆኖላት፣ ቢያንስ ከህመሟ እያገገመች እንደምትገኝ ለማየት በቅተናል።

ካለፉት ሦስት ዓመታት አንስቶ፥ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ወደ ስልጣን እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያችን ክፉኛ ታማ ከርማለች። ሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ህመሟ ሽሮ ከተጣባት ክፉ ደዌ ተፈውሳለች ባይባልም፤ እነሆ የጠ/ሚ አብይ ወደ ስልጣን መምጣት በጎ አጋጣሚ ሆኖላት፣ ቢያንስ ከህመሟ እያገገመች እንደምትገኝ ለማየት በቅተናል። እነኛን የከፉ ሦስት ዓመታት፣ ዛሬ ላይ ቆመን የኋሊት ስናስታውሳቸው፤ ሀገራዊ ስንክሳሮቻችን እጅግ የበዙባቸው፥ ሀገሪቱም የወላድ መካን የሆነች በሚመስል መልኩ ጣሯና ጭንቋ  በዝቶ፥ እንደ ሀገር የመቀጠሏ ነገር ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ገብቶ፥ አደገኛ አዝማሚያዎች በስፋት የተንሰራፋባቸው ጊዜያት ነበሩ ለማለት ያስደፍራል። በእነዚያ ሐገራዊ የመከራና የስጋት ጊዜያት በሐገሪቱ በቆዳ ስፋትም ይሁን በሕዝብ ቁጥር ትልቁ ብሄር ከሆነው የኦሮሚያ ክልል ተነስቶ፤ ወደ ሌላውና ሁለተኛ በርካታ የሕዝብ ቁጥር ወዳለው የአማራ ክልል፤ ብሎም ወደ ደቡብ (ጉራጌ) ክልል በተዛመተና በተደጋጋሚ (domino effect) በተካሔደ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሱናሜ ማዕበላት ስንናጥ መክረማችን፣ በታሪካችን በጉልህ የሰፈረና ከቶውንም ሊዘነጋ የማይችል እውነት ነው፡፡ ይህንን እውነት መሪር የሚያደርገው ኩነት ደግሞ በዚህ አንዴ ጋብ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሰደድ እሳት ሲቀጣጠል በቆየ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሳቢያ፣ በጸጥታ ሀይሎችና አንዳንዴም ምሬታቸው ጫፍ በወጣ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አራማጅ ወገኖች አማካኝነት በተወሰደ ግብታዊና አሳዛኝ እርምጃ፣ ከህጻን እስከ አዋቂ፤ ከምሁር እስከ አርሶ አደር፤ ከሰራተኛ እስከ ነጋዴ ሳይለይ  የበርካታ ዜጎቻችን መተኪያ የሌለው ህይወት ላይመለስ በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል፤ የአያሌ ምስኪን ወገኖች አካል ለጉዳት ተዳርጓል፣ ዜጎች ለፍተው ጥረው ያፈሩት ንብረት ወድሞ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው እስከ ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

(የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው) እስከ ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። ይህ ለፖለቲከኞች ብቻ የማይተው የዜጎች ቀጣይ ተግባር ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሰከነና በሰለጠነ መንገድ መልካም ጅማሮዎች ሊበረታቱ ይገባሉ፤ ነገ ሊያስከትሉ የሚችሉት ጥሩና መጥፎ ነገሮችንም በሰከነ መልኩ አትኩሮት ሰጥቶ ማሰብ ለዘላቂ ስኬት መሰረት ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያላየነውን ጭላንጭል እያየን ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከነበረው አስተዳደር ያተረፍነው ነገር ሞት እስር ስደትና መከራ ነው። ( ፖለቲካው በሴራ እስካልተያዘ ) ድረስ የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ አይወስድም ። ዶክተር አብይ አሕመድ መልካም ነገሮችን ለሕዝብ በማሳየት ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል። በቀጣይነት ደግሞ የኛ ተግባር መሆን ያለበት እየታዩ ያሉ መልካም ጅማሮዎች እንዳይከሽፉ በትግላችን ማረጋገጥ ነው። የዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ብሔራዊ እርቅ የሚደረገውን መንገድ መጥረግም የዚህ መልካም ነገር አካል መሆኑ እያየን ነው። በጥንቃቄና በታታሪነት ሊያዝ የሚገባው የመልካም ፖለቲካ ጅማሮ ሕዝቦች በሃገራቸውና በመንግስታቸው እንዲተማመኑ በሩን ይከፍታል። የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው እስከ ፍንጭ እስካሳየው ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። ፈጥኖ ከማጨብጨብ ይልቅ ፈጥኖ ማበረታታትና የተገኘው ድል እንዳይከሽፍ ከእያንዳንዱ የሰላም ሰው ጎን መቆም ያስፈልጋል። ይህ ሲባል ጎን ለጎንም መልካም ጅማሮዎችን ለማክሸፍ የሚራወጡ እኩያንን እየቀበሩ መሆን ይገባዋል። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያላየነውን ጭላንጭል እያየን ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከነበረው አስተዳደር ያተረፍነው ነገር ሞት እስር ስደትና መከራ ነው። አሁን ግን እነዚህ ስቃዮች በትንታግ የሕዝብ ትግሎች ፈር እየያዙ መልካምነትና ቅንነትን እየደመሩ መስመር ውስጥ ገብተዋል። እነዚህን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተወያዩ

“ጥሩ ነገር እስከሰሩ ድረስ እኛ የመቃወም ሱስ የለብንም። ጠ/ሚኒስትር አብይ ከህዝብ ጋር ያደረጋቸውን የተለያዩ ውይይቶችን ተከታትያለሁ ጥሩ ጅምር ነው። ተስፋ የሚሰጥ ነገር ይታያል።” – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የግንቦት ሰባት ፓርቲ ጸሃፊ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበር ከሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውንና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት የገለጹ ሲሆን በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ ለምን አዜብን ሾመ? (ጌታቸው ሺፈራው)

ዶ/ር አብይ ለምን አዜብን ሾመ? (ጌታቸው ሺፈራው) ትህነግ/ህወሓት ባለፈው 27 አመት ያሳየን “ብቃት” ችግር ያለባቸውን፣ ሕዝብም ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች “አክ እንትፍ” ያሏቸውን እሱ ጋር በማስጠጋት ደካሞችን መጠቀሙ ነው። ለዚህ በምሳሌነት መቀሌ ሄደው “ነፍጠኛ እና ትምክተኛ ብለን የመሳደብ መብታችን ተነፈግን” እያሉ የሚያለቅሱትን የብአዴን ጡረተኞች መጥቀስ ይቻላል። እነ ህላዊ ዮሴፍ በትህነግ የተመረጡት ከሕዝብ የተጣሉ በመሆናቸው ነው። ይሰጡት የነበረው አገልግሎት ሕዝብን መዝለፍ፣ ለህዝብ የቆመውን ማስጠቃት ነበር። ~ዶ/ር አብይ አህመድ አዜብ መስፍንን የሜቴክ ቦርድ አባል አድርጎ ሾመ ሲባል ብዙ ደጋፊዎቹም ቅር ሳይሰኙበት አልቀሩም። ተቃዋሚዎቹም “ብለናችሁ ነበር” ብለዋል። አዜብን በእውቀቷ ሾማት የሚል አይገኝም። አዜም ከሰራተኞች ጋር ተግባብታ ትሰራለች ማለት አይቻልም። መለስ ዜናዊ በመተ ማግስት አንድ የውጭ ጋዜጠኛ የመለስ ዜናዊ አድናቂ መሆኑን ፅፎ ነበር። መለስን የሚያደንቀው ለኢትዮጵያ በሰራው መልካም አይደለም። በጎ አሰራም ብሎ ይመሰክራል። መለስ ዜናዊ ለጉብኝት ወደ ውጭ ሀገር በሄደበት ወቅት ጋዜጠኛው ለቃለመጠይቅ ቀጠሮ አስይዞ እየጠበቀ ነው። አንደኛው ክፍል ውስጥ። በወቅቱ ባልና ሚስቱ ይጨቃጨቃሉ። በአብዛኛው የሚሰማው የአዜብ ድምፅ ነበር። በመጨረሻ በሩን መለስ ጆሮ ላይ ጠርቅማበት ወጣች ይላል ጋዜጠኛው። እናም ጋዜጠኛው መለስ ዜናዊ ይችን ሴት ችሎ በመኖሩ ብቻ ጀግና ነው ይላል። በአጭሩ አዜብ ፀባይ የራቃት ሴት ነች። ለባሏ እንኳ ክፉ ናት። ~አዜብ የባሏን ስልጣን ተጠቅማ ብዙውን ባለስልጣን ከፍ ዝቅ አድርጋለች። በባሏ ስልጣን ተመክታ ብዙውን አዝዛለች። ሀብት አካብታለች። ባለስልጣናቱን ለባሏ ከማሳጣት ባሻገር ስልጣንና ገንዘብ የመስጠትና የመቀማቱ ስራ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ትልቅ ፈተና እጁ ላይ አለ። (ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ)

የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ትልቅ ፈተና እጁ ላይ አለ። ይህን ተቋም ከመለስ ወአላሙዲ ደባ ጠብቀው እዚህ ለማድረስ የታገሉ ሁሉ ዛሬ ደስ ሊሰኙ ይገባል። ማኅበሩን ቢቻል ለማፍረስ ባይቻል ለማዳከም የሞከረው መንግሥት መሪ በፌዴሬሽኑ በዓል ላይ ለመገኘት መጠየቃቸው ለፌዴሬሽኑ መልካም አጋጣሚ ነው። ጠሚ ዐቢይ የመንግሥታቸውን የኖረ የቂምና የበቀል ጎዳና ትተው፣ በትህትና ጥያቄ ማቅረባቸው የሚያስመሰግናቸው ነው፣ የፖለቲካ አጀንዳ ቢኖራቸውም እንኳን። እዚህ ድረስ ሁለቱም አካሎች ባለክብር ናቸው። ይህ የሁለቱም አካላት አመለካከትና አቋም የዛሬው የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ምንም ቢሆን ሳይቋረጥ እንዲቀጥል እመኛለሁ። ብዙዎች እንደሚያስቡት ወሳኔው ለፌዴሬሽኑ ቀላልና ግልጽ አይደለም። ቀላሉና ዘላቂው፣ በመርህና በሕግ ላይ ብቻ ተመስርቶ ውሳኔ መስጠት ነው። ሆኖም መርሖችና ሕጎች ወደፊት የሚመጡ ጥያቄዎችን በሙሉ ለማስተናገድ የማይችሉበት አጋጣሚ መኖሩ የታወቀ ስለሆነ፣ ነገሩን በልዩ ሁኔታነት ማስተናገድ ይገባ እንደሆነ መጠየቅ አግባብ ይሆናል። ለእኔ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ቁልፍ ጥያቄ መሆን ያለበትም ይኸው ነው። ይህ ጥያቄ ባለው ሕግና አሰራር ይመለስ ወይስ በልዩ ሁኔታ ይታይ? (የፌዴሬሽኑን ሕግ በሙሉ ስለማላውቅ ብዙ ማለት አልችልም።) በየትኛውም መንገድ ቢኬድ ግን ፌዴሬሽኑ፣ በዐቢይ (አለ)መምጣት የሚያገኘውን ትርፍ ማስላቱ ተፈጥሯዊ ነው። አሁን እንደማየው በሌሎች መንገዶች ማግኘት የሚገባንን ፖለቲካዊ መፍትሔዎች በፌዴሬሽኑ ላይ አብዝቶ መጫን ትክክል አይደለም። ይህን ስል፣ ፌዴሬሽኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሆነውን ነገር አያገባኝም ብሎ ማለፍ አለበት ማለቴ አይደልም። ፌዴሬሽኑ እንደተቋም፣ ከዚያም አባላቱ ከጠሚ ዐቢይ ግብዣ የበለጠ ትርፍ የሚያገኙበትን ስሌት ማግኝት ወሳኙ ስራ ነው። ለምሳሌ፣ አሁን ባለበት ሁኔታ፣ ፌዴሬሽኑ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶላሩና አጭሩ ዲፕሎማት! (ስዩም ተሾመ)

ዶላሩና አጭሩ ዲፕሎማት! (ስዩም ተሾመ) እንዲህ ሆነ! በምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳለው የሚነገርለት ቁመተ አጭሩ አሜሪካዊ ዲፕሎማት ያማማቶ አዲስ አበባ መጣ፡፡ የያማማቶ ዋና ትኩረት በደቡብ ሱዳን መሪዎች ላይ ስለሚጣለው ማዕቀብ የኢትዮጲያን መሪዎች ለማማከር ነበር፡፡ አያይዘውም ማዕቀብ የሚጣልባቸው መሪዎች በራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም በውጪ ሀገር በሚገኙ ባንኮች የከፈቱትን አካውንትና ያስቀመጡትን የገንዘብ መጠን በቀላሉ ማወቅ እንደሚቻል ይገልፃሉ፡፡ ይህን ግዜ ጠ/ሚ አብይ “ቆይ…ቆይ እኛ የተቸገርነው ይሄን አይደለም እንዴ?” በማለት በተመሣሣይ መንገድ የኢትዮጲያ ባለስልጣናት በየትኛው ሀገር የባንክ አካውንት እንዳላቸውና ያጠራቀሙትን የገንዘብ መጠን የሚያሳይ መረጃ በማሰባሰብ እንዲያግዟቸው ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ያማማቶ ደግሞ እኔ ምን ገዶኝ በማለት የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናትን ጉድ በCIA በኩል ጎልጉለው እንሆ በረከት ይሏቸዋል፡፡ ከደሃው የኢትዮጲያ ህዝብ ላይ የተዘረፈው ብር በአንደኛ ደረጃ የሚገኘው በጀርመን ሀገር እንደሆነ ታወቀ፡፡ ከሚታወቁት ቱባ-ቱባ የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በላይ ኤልክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ዋና ሃላፊ የሆነችዋ ሴትዮ $180,000,000 ዶላር በውጪ ሀገር ባንክ ማስቀመጧ ሁሉም አስገርሟል፡፡ ይህቺ ጀማሪ ባለስልጣን 180 ሚሊዮን ዶላር ከዘረፈች ነባሮቹ ምን ያህል እንደሚዘርፉ መገመት ይቻላል፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጡረታ ከተገለሉ የቀድሞ ባለስልጣናት መሀከል ከአቶ ታደሰ ሀይሌ በስተቀር ብዙዎቹ አኩርፈዋል።

ትናንት ምሽት በብሄራዊ ቤተመንግስት ለትግራይ ክልል ተወላጅ አርቲስቶች፣ባለ ሀብቶች፣ታዋቂ ሰዎች ፖለቲከኞችና ሌሎች ተጋባዦች ከምሽት 12፡00 ጀምሮ ጠ/ሚ/ሩ ግብዣና ነጻ ውይይት አድርገው ከተናገሩት የተወሰዱ አብይ ጉዳዮች :- “በየብሄራችሁ ለየብቻ የምጠራችሁ በአንድነት ከመሰባሰባችን በፊት በተናጠል ቅድመ ህክምና መስራት ስላለብኝ ነው።” “አቶ አንዳርጋቸውን በማሰራችን የተጠቀምነው ነገር የለም።የተረፈን ጥላቻና ከእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊዮን ዶላር ማጣታችን ብቻ ነው።” “በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ግብጽ ተጉዤ በሊቢያ ታርደው በግብጽ የተቀበሩ ኢትዮጵያውያንን አስክሬን ይዤ እመለሳለሁ።ሰዎች እንደ እብድ ቢያዩኝም ይህንን ማድረግ አለብኝ።” “በጡረታ ከተገለሉ የቀድሞ ባለስልጣናት መሀከል ከአቶ ታደሰ ሀይሌ በስተቀር ብዙዎቹ አኩርፈዋል።አይዟችሁ አትታሰሩም ብለናቸዋል።ስራም እየፈለግንላቸው ነው።” ዛሬ ምሽት 12:00 ላይ ብሔራዊ ቤተ -መንግስት ጥሪ ለተደረገላቸዉ እንግዶች በተለይ ከወትሮ የግብዥ ዝግጅቶች በርካታ መኪና ማቆሚያ ስክንቸገር ነበር ዛሬም ቪዲዮ ሞባይል ባልተፈቀደበት ምሽት የዛሬዉ ጥሪ አንዳንድ አርቲስቶች ቢያካትትም የበዛዉ ባለሀብቶች ነበሩ ምንም እንኳን የአርቲስቶቹን ስም እንዳይጠቀስባቸዉ ስለጠየቁን የመጡት ባለሀብቶችና አርቲስቶች ስም ለግዜ እንዝለለዉና ወደ ዋነኛዉ ጉዳያችን ብዙዉ ታዳሚዎቹን ያስገረሙ ንግግሮች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ አንድ ስንሆን ያምርብናል ስለብሔር ከምናወራ አንዲት ኢትዮጲያ እናዉራ አንዳንድ ባለስልጣናት ፀሐፊዋ ትግሬ ሱፌሩ ትግሬ ጋርዶቻቸዉ ትግሬ ሰራተኞቹ በዘመድ እነዚህ የትግራይን ክልል ተወላጆችን ሌሎችም ብሔራቸዉን መሰግሰግ የተለየ ጥቅም እንዳገኙ ህብረተሰብ ዉስጥ የተሳሳተ መረጃ አለ። ለምሳሌ ሸሬን አዉቃለሁ መቀሌ ብትሄድ የዉሃ ችግር አለ የተወሰኑ ለሆዳቸዉ ያደሩ ባለሥልጣናት ህዝብን በትግራይ ህዝብ የሚነግድ አሉ ስልጣን ልቀቁ ሲባሉ ሞት የሚመስላቸዉ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከዶ/ር አብይ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በሁለት ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻው ነው (ዶ/ር ብርሐኑ ነጋ)

“አንደኛ፡ ዶክተር አብይ በቃላት ደረጃ ለማድረግ እፈልጋለሁ የሚሏቸው ነገሮች አብዛኛዎቹ እኛም የምንፈልጋቸው እና እስከ ዛሬ የታገልንላቸው አላማዎቻችን ስለሆኑ የሚሉት የምራቸውን ከሆነ እንዲሳካላቸው ከልብ መመኘት ብቻ ሳይሆን በተቻለን መጠን ልናግዛቸው እንፈልጋለን። እኛ እነኚህን ውጤቶች ነው እንጂ የምንሻው የግድ እኛ ካላመጣናቸው አንልም። እንደ ድርጅት እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ የማገዝ እንጂ ስልጣን የመያዝ ፍላጎት ኖሮን አያውቅም። በርግጥም ይህን የሚጠራጠሩና መጠራጠርን ብቻ በራሱ ትልቅ የፖለቲካ እውቀት አድርገው የሚያዩ ሀይሎች እንዳሉ እናውቃለን። እነሱ ተጠራጠሩም አልተጠራጠሩም ግን በድርጅታችን ውስጥ ስር የሰደደውና በፍጹም የማያወላውለው ዕምነታችን ይኸው ነው። በሌላ በኩል ግን አሁን ያለውን የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ ከስሜት በወጣ መንገድ ካየነው ከመጀመሪያው ቢሆንስ (እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ሽግግር) ይልቅ የሁለተኛው ቢሆንስ (ጥገናዊ ለውጥ)እውን የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ዶክተር አብይ ወደ ጥገናዊ ለውጥ እያመሩ ላለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት እንሻለን። ጥገናዊ ለውጥ ውሎ አድሮ ወደ ትርምስ እና እልቂት ይወስደናል እና ይህንን መፍቀድ አንችልም። እነኚህ ሁለት ሁኔታዎች ተቃራኒዎች በመሆናቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ መራመድ ይኖርብናል።”
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመንጋ ማጨብጨብ እርግማን ነው። ለማጨብጨብ ምክንያታዊ መሆን ያስፈልጋል

አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ ። ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች አሉ ። ለማጨብጨብ ምክንያታዊ መሆን ያስፈልጋል። ስሜታዊነትና ምክንያታዊነት ሲደበላለቁ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው። በስኬት የሚጓዘው የዲያስፖራው ፖለቲካ በክምር ወሬ ተከፋፍሎ ለክሽፈት እንዳይዳረግ ከፍተኛ ስጋትን አጭሯል። መንገኝነት እርግማን ነው። ነገ ላይ ሆነን ዛሬን መመለስ የማንችልበት ጸጸት ውስጥ ከመግባት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ሊተገበሩ የሚገቡ ጉዳዮችን ማጤንና ወደ ተግባር እንዲለወጡ መታገል ዋናና አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በፖለቲካ ጥላቻ የታወረው ኢሕአዴግ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በወሕኒ እየማቀቁ ነው። እነዚህ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች ተፈትተው ወሕኒው ነጻ መውጣት አለበት። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እኩል ስልጣን አለው። ይገላል ያፈናቅላል ፣ ያስራል ፣ ያንገላታል ወዘተ ፤ የስርዓቱ ቁንጮ የደህንነትና የጦር ባለስልጣናት የሚመሩት ኮማንድ ፖስት ከሕግ በላይ ሆኖ በሕዝቦች ላይ መንግስታዊ ሽብር ይፈጽማል። ይህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነስቶ ኮማንድ ፖስቱ መበተን አለበት። ሌላው በዋናነት የሚያስፈልገው ዐለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ኮንቬክሽንን ኢትዮጵያ እንደመፈረሟ ሁሉ የሰብዓዊ መብቶች ሊከበሩ ፣ የዜጎች በገዛ አገራቸው ተዘዋውረው የመኖር የመስራት መብታቸው እንዲረጋገጥ ፣ የመደራጀት የመሰብሰብና ዜጎች ከመንግስታዊ ሽብር ስጋት ተላቀው በነጻነት እንዲኖሩ ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና ስርዓቱን የመቃወም መብቶች እንዲፈቀዱ ፣ በግልና በቡድን አመለካከቶች ላይ መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር መደረግ አለበት። ነገ ላይ ቆመን በቁጭትና በጸጸት ዛሬን ከምንረግም ፤ በተግባር ሊተረጎሙና ልናያቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ ጠንክረን ብንሰራ ተመራጭ ነው። በመንጋ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠ/ሚ አብይ አህመድ በሚሊኒየም አዳራሽ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ያደረጉት ሙሉ ንግግር – ቪዲዮ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ በውጪ አገራት ባንኮች የሚገኙ የባለስልጣናት አካውንቶች እየተመረመሩ ነው አሉ

ዶክተር አብይ ዛሬ ፅ/ቤታቸው ለሰበሰቡት ለካቢኔያቸው ከተናገሩት…… “በውጪ አገራት ባንኮች የሚገኙ የባለስልጣናት አካውንቶች እየተመረመሩ ነው” “በካቢኔ ስብሰባ ስም የሚባክን ጊዜ እንዳይኖር ስብሰባችን ቅዳሜ ቅዳሜ ይሆናል::” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዛሬ ለመንግስት ባለስልጣናት ማሳሰቢና ገለጻ ሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ረፋዱን(ግንቦት 7) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለተሰበሰቡ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በስራዎቻቸውና አሰራር ዙሪያ ገለጻና ማሳሰቢያ ሰጡ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መድረክ ላይ የራሳቸውን ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ በዚሁ ጽሁፋቸውም የአመራር ጥበብን በተመለከተ ገለጻ አድረገዋል። የህዝበ አገልጋይ ምን አይነት ሰብዕና ሊላበስ እንደሚገባና ምነ አይነት አገልግሎት በምን አይነት ጊዜና ቦታ መስጠት እንዳለበትም በተለያዩ አብነቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ገለጻቸው ወቅት እንዳሉትም፤ ሳምንታዊው የካቢኔ ስብሰባ ከአርብ ወደ ቅዳሜ መለወጡንና ሚኒስትሮች አርብ በስብሰባ ስም ጊዜ ማባካን እንደሌለባቸውና መደበኛ ስራቸውን እንዲሰሩ አሳስበዋል። አገሪቷ እያደገች መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ አድጋለች ከማለት ባሻገር በተጨባጭ ህዝቡ ምን ያህል ተጠቅሟል የሚለውን መፈተሽና ማረጋገጥ አለብን ሲሉም አስታውቀዋል። እያንዳንዱ የመንግስት አመራርም አሰራሩን ግልጽና ለህዝብ የማይደበቅ ማድረግ እንደሚገባውም ዶክተር አብይ አሳስበዋል። እያንዳንዱ ሚኒስትር ከዚህ በኋላ ለስብሰባ ሲመጣ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ሚኒስትር ሃሳብ አመንጪ እንጂ አቃቂር አውጭ አይደለም” ሲሉም ነው አጽንኦት የሰጡት። ከባለስልጣናት ጉዞ ጋር በተያያዘም ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይም በውጭ አገራት ባንኮች አካውንት ያላቸው ባለስልጣናት በአካውንቶቻቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና ለዚህም አገራት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ስብሃት ነጋና ካሱ ኢላላን ጨምሮ 5 ባለስልጣናት ጡረታ እንዲወጡ ተደርጓል

አገራችን እያካሄደች ያለችው ሪፎርም የተሳካ እንዲሆን የማድረጉ ሥራ እንዲሁም ለሕዝቡ የልማትና ለውጥ ፍላጎት ተገቢ ምላሽ የመስጠቱ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያግዙ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እያካሄዱት ያለው የካቢኔ ለውጥ ይገኝበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት በአዳዲስ ኃላፊዎች እንዲመሩ በማድረግ ላይም ይገኛሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለበርካታ ዓመታት በመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በጡረታ እንዲያርፉ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በጡረታ እንዲያርፉ የተደረጉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት ክቡር አቶ ስብሐት ነጋ/አቦይ ስብሐት/፣ ክቡር ዶ/ር ካሱ እላላ ከፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ ክቡር አቶ በለጠ ታፈረ ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት፣ ክቡር አቶ ታደሰ ኃይሌ ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል፣ እና ክቡር አቶ መኮንን ማን ያዘዋል ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል ሲሆኑ በቀጣይም ረዥም ጊዜ በመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ እንዲያርፉ የማድረጉ ሥራ ይቀጥላል፡፡ ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ ሲባል የሚያማቸው የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ዘርዓይ አስገዶም ከስልጣን ተባረሩ

ከሕወሓት የማይወግኑ ሚዲያዎችን የሚዘልፉት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ሲባል የሚያማቸው የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ከስልጣን ተባረሩ። ለረዥም ዘመን የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ በመሆን ስልጣኑን እንደ ግል ንብረታቸው በመቆጣጠር የቤት ልጅና የእንጀራ ልጅ የሚሉ ሚዲያዎችን በመፍጠር በነጻነት መስራት በሚፈልጉ ሚዲያዎች ላይ ስድብና ዛቻ ሲያዘንቡ የነበሩት አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከስልጣን ተባረሩ። በምትካቸው አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ተሹመዋል። አቶ ዘርዓይ የኢትዮጵያና የባንድራዋ ስም ለምን ተጠራ በማለት በሚዲያዎች ላይ የሚደነፉ ሲሆን ሸገር ኤፍ ኤም ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር በማለቱ ከተወሰኑ ወራቶች በፊት በዓንድ ስብሰባ ላይ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂ ብለው መዘርጠጣቸው ይታወሳል። በሕወሓት የሚደገፉትን እንደ ሪፖርተርና ሚሚ ስብሃቱ የመሳሰሉትን ሚዲያዎች በማንቆለጳጰስ ይታወቃሉ።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሎች አራት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን ሹመት አነሱ

አቶ አባይ ፀሐዬ – የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የነበሩ አቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ – የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዚደንት የነበሩ አቶ ጌታቸው አምባዬ- ጠቅላይ አቃቢ ህግ የነበሩ ኮሎኔል ታዚር ገ/እግዚአብሄር – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት (ኢንሳ) ም/ዋና ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን ከሚያዚያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሀላፊነታቸው መነሣታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ የደረሣቸው መሆኑን ተገልጿል፡፡ ህጋዊ ተጠያቂነትን ችላ በማለት በከፍተኛ ደረጃ የሃገርንና የሕዝብን ሃብትና ንብረት ሲዘርፉ የነበሩት የገዢው ፓርቲ አባላት ከስልጣን እየተነሱ በስርዓቱ ፉሮጎ ውስጥ በመሸሸግ ለተከታይ ዘረፋ መዘጋጀታቸውን ያሳያል፡፡ የሙስና ኔትወርክ በመዘርጋት ላለፉት ሃያሰባት አመታት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ገድለውታል፣ እንዲሁም በፖለቲካው መስክም በርካቶችን ገድለዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል፣ ፍትሕ እንዲጓደል ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News