Blog Archives

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ ተቀሰቀሰ

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ 14 ወረዳዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ መቀስቀሱን ዋዜማ ሰምታለች። ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤው ላይ መሆኑን ያስረዱት ምንጮች፣ ይህንኑ ተከትሎ በቅርቡ እንደ አዲስ በተዋቀረው የምስራቅ ቦረና ዞን መቀመጫ ነጌሌ ቦረና ከተማ እና የቦረና ዞን መቀመጫ በሆነችው ያቤሎ ከተማ፣ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች ከዛሬ ማለዳ አንስቶ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆኑን ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመልክታል። ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ በምክር ቤቱ የተወሰኑት 14ቱ ወረዳዎች በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ቦረና፣ ባሌ፣ ሐረርጌ እንዲሁም ከድሬደዋ አካባቢዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው እንደሆኑ ምንጮች ነግረውናል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 21፣ 2017 ዓ፣ም እኩለ ቀን ድረስ በፌዴራልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ የተባለ ነገር የለም። [ዋዜማ]
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በIMF የተማረሩ ሀገራት! በመጨረሻ IMF ኢትዮጲያ ደርሷል

በIMF የተማረሩ ሀገራት! በመጨረሻ IMF ኢትዮጲያ ደርሷል! በ IMF ድጋፍ ዙሪያ ክርክር አለ! ለሀገራት ይጠቅማል እና ይጎዳል! ከ IMF ድጋፍ ተከትለው ስለሚመጡ የጉዳት ማስረጃዎች ከጥቅሙ ይበዛሉ! ከ IMF ጋር ሪፎርም በማድረግ ከፍተኛ መማረር ውስጥ ስለገቡ ሀገራት እና ምክንያት በምሳሌ እመለከታለን! ኢትዮጲያ ከIMF ጋር የቅርብ ሪፎርም አካል ነች! የአንድ ዓመቱን ምልክት ከሌሎች ሀገራት ጋር እያነጻጸርን እመለከታለን!  https://youtu.be/T631z06d49g
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

በማስተርስ ዲግሪ ተመርቃ ጉሊት የምትቸረችረው የደምቢዶሎዋ መምህርት

አባይነሽ ሐምቢሳ በደምቢዶሎ ከተማ በሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ተመርቃ መንገድ ላይ አትክልት እና ፍራፍሬ በመቸርቸር የምትተዳደረው መምህርት ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቶ በርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል። አባይነሽ ሐምቢሳ የተባለችው ይህች መምህርት ከደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ በሒሳብ የትምህርት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪዋን ያገኘችው በማዕረግ ነው። ይህች መምህርት ላለፉት ዓመታት ትምህርት በሚዘጋበት በክረምት ወቅት እንዲሁም በእረፍት ቀኗ ቅዳሜዎችን መንገድ ላይ በመቸርቸር ነው ኑሮዋን የምትደግፈው። ለ13 ዓመታት በመምህርነት ያገለገለችው አባይነሽ በየወሩ የምታገኛት 7,500 ብር ደመወዝ ካለው የዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ ኑሮዋን መደጎም ስላዳገታት ነው ወደ ጉሊት የወጣችው። “የማገኘው ደሞዝ ልጆቼን ለማስተዳደር፣ ማኅበራዊ ሕይወቴን ለመደገፍ፣ ለትምህርት፤ ለአጠቃላይ ለኑሮዬ በቂ አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ለመንግሥት ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ በቂ አይደለም፤ ያለውን የኑሮ ውድነትን ያገናዘበ አይደለም” ትላለች። ከማስተማር ሥራዋ ጎን ለጎን ትምህርቷን በከፍተኛ ደረጃ መቀጠሉ አስፈላጊ ሆና ያገኘችው አባይነሽ፣ የማስተርስ ትምህርቷን ለመደጎምም ሌላኛው አማራጩ ጉሊት ነበር። “በወር ደሞዜ የትምህርቴን ከፍዬ፣ ኑሮዬን ደግፌ፣ ለልጆቼ አውጥቼ አይሆንም” ስትል የአራት ልጆች እናት የሆነችው አባይነሽ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጻለች። በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ዩብዶ ወረዳ የተወለደችው አባይነሽ የጉሊት ችርቻሮዋን የጀመረችው ከሁለት ዓመታት በፊት ነው። ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ እና አቮካዶ የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን ከደምቢዶሎ ከ20 አስከ 25 ደቂቃ በእግር የሚያስኬድ መንገድ ከሚጠይቀው ስፍራ ተሸክማ አምጥታ በከተማዋ ትችረችራለች። ገበያ በደራበትም ቀንም ከ200 አስከ 500 ብር ታገኛለች። “ከማገኘው ትርፍ 100 ወይም 200 ብር አስቀምጬ ቀሪውን ደግሞ ለቤተሰቤ የሚያስፈልጉ እንደ ሳሙና፣ ስኳር ወይም
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በአዲስ አበባ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ተመልሶ የመጣው መጠነ-ሰፊ የወጣቶች አፈሳ

በአዲስ አበባ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ተመልሶ የመጣው መጠነ-ሰፊ የወጣቶች አፈሳ “ሲቪል ፖሊስ በየመንገዱ እወስድሀለው እያለ ይደራደራል፣ ሌብነቱ ሀላል ወጥቷል። በየቀኑ ከመዝናኛ ቦታ እየወሰዱ በብር ተደራድረው ይለቋቸዋል።” ተጨማሪ ያንብቡ: https://tinyurl.com/6mcu6xfd
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ፋኖ በሱዳን ድንበር ታሪክ ሰራ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

የኤርትራ ጦር በአፋር ድንበር ….. የኢሳያስ ነውር .. የብልጽግና መልስ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ፈተና

የሰሜን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክ (ከማኅደራችን) የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ የገጠመው ፈተና  
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

“የ2010ሩ ተስፋ፣ አምባገነናዊ መንግሥት ለመገንባት በታቀደ ፕሮጀክት ተከድቷል” – ኦፌኮ

የኦፌኮ አመራሮች “የ2010ሩ ተስፋ፣ አምባገነናዊ መንግሥት ለመገንባት በታቀደ ፕሮጀክት ተከድቷል” – ኦፌኮ  
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ

ዘወትር የሚባርቁት የአብይ አህመድ ጥይቶች ( አርበኛ ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ )

ዘወትር የሚባርቁት የአብይ አህመድ ጥይቶች ““““““““““““““““““““““““` አብይ “አነጣጥሮ” የሚተኩሰው ጥይት ሁሉ የሚባረቅበት ሰው ነው። ጥቂት ማሳያወችን እንመልከት:- በአግባቡ ወንበሩን ሳያደላድል በጀመረው “የቀንጅብ ፖለቲካው” ከትግራይ የፖለቲካ ኃይል ጋር በገባው እሰጥ አገባ ምክንያት ብዙ እልቂት ያስከተለውን የሰሜኑን ጦርነት አዋለደ። ለግዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ብሎ ኦሮምያ ክልልን ለኦነግ እንደሚሰጥ አስመራ ላይ የገባው ስዉር ስምምነት ዛሬ በአብይ እና በOLA መካከል በወለጋ፣ በሸዋ እና በቦረና አካባቢወች ቀጣይነት ያለው ጦርነት እንዲካሄድ ምክንያት ሆነ። ከህወሃት ጋር ያደረገዉን ጦርነት ለመቋጨት ከአማራ ህዝብ ጀርባ የቆመረው የፕሪቶሪያውን ውል ለመተግበር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ። ከዚህ አጣብቂኝ ለመውጣት 2015 ላይ የጀመረው አማራን ትጥቅ የማስፈታት እቅድ ዓለም በቂ ትኩረት ያልሰጠውን ግዙፍ ጦርነትን ይዞ መጣ። በዚህም ማርኮ የሚታጠቅ፣ መከላከያዉን የሚያንበረክክ የተደራጀ የአማራ ኃይል ተፈጠረ። በራሱ የውስጥ ጦርነት ኤርትራንን የሙጥኝ ካለ በኋላ ፕሮጀክቱን ጨርሻለሁ ብሎ ሲያስብ ሻዕቢያን በመግፋት ይልቁንም የውስጥ ጉዳዩን አጀንዳ ለማስቀዬር ብሎ የቀይ ባህር ጌታ እሆናለሁ ማለት ሲጀምር በቀጠናው ላይ ይፈጠራል ተብሎ ያልተገመተን አዲስ ፀረ-አብይ የኃይል አሰላለፍ ወለደ። ሱዳን ውስጥ መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎን በመደገፍ እና በአሶሳ ኤርፖርት በኩል ሎጅስቲክስ በማቅረብ አልቡራሃንን በማስገደድ ከኤርትራ እና ከትግራይ ኃይሎች እነጥላለሁ ብሎ የገባበት ጨዋታ የፖርት ሱዳንን መንግስት ፀረ-አብይ አሰላለፍ አፀናው። ሱማሊያ ላይ እቀብጣለሁ ብሎ ሶማሊ ላንድን እውቅና ለመስጠት በአደባባይ የገባው ስምምነት ግብፅን ከነ ጦሯ ወደ ሶማሊያ ጎትቶ አመጣ። ከዚህ አጣብቂኝ ለመውጣት አንካራ ሂዶ ሶማሊያን ይቅር በይኝ ብሎ ስምምነት ቢያደርግም
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

ከኢትዮጵያ የባህር በር አጀንዳ ጀርባ የኤምሬቶች ወደብ የማስፋት ፍላጎት አለ ( የኤርትራው ፕሬዝደንት ) ሙሉ ቃለ መጠይቁን ይዘናል

የኤርትራው ፕሬዝደንት የብልፅግና ፓርቲን ‘ርካሽ ውሸት’ በማሰራጨት እና ለጦርነት ዝግጅት በማድረግ ከሰሱ ከኢትዮጵያ የባህር በር አጀንዳ ጀርባ የኤምሬቶች ወደብ የማስፋት ፍላጎት አለ በማለት የኤርትራው ፕሬዝደንት ሲናገሩ ተደመጡ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣብያ ጋር ረዘም ያለ ቃለ-መጠይቅ አድርገው ነበር። በቃለ-መጠይቃቸው አብዛኛውን ከኢትዮጵያ ጋር እየተካረረ ስለመጣው ግንኙነት እና የግጭት ስጋት አንስተዋል። “በግልፅ ሲታይ እነዚህ የብልፅግና ፓርቲ አጀንዳዎች ሳይሆኑ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝደንት [መሐመድ ቢን ዛይድ] በቀጠናው ወደቦችን አስፋፍቶ የመያዝ አጀንዳ አካል ነው።”  https://shabait.com/2025/07/19/highlights-of-president-isaias-afwerkis-interview-with-local-media-outlets-2/    
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሁለት ኮሚሽነሮች የሥራ ዘመናቸው ሳይጠናቀቅ መልቀቂያ አስገቡ

  ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ (በስተግራ) እና ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ (በስተቀኝ) የፎቶው ባለመብት, EHRC የምስሉ መግለጫ, ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ (በስተግራ) እና ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ (በስተቀኝ)   የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር እና የዘርፍ ኮሚሽነር የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር የሆኑት ርግበ ገ/ሐዋርያ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮችች ገልፀዋል። ኮሚሽነሮቹ ለምክር ቤቱ የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠታቸውን ምንጮች የተናገሩ ሲሆን፤ ስለ ሥራ መልቀቂያው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በዋና ኮሚሽነሩ በኩል እንደተነገረ ቢቢሲ ከምንጮቹ ተረድቷል። የከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ የሥራ መልቀቅ ከአዲሱ ዋና ኮሚሽነር “የአመራር ስልት” ጋር በተያያዘ “ተገፍተው” እንደሆነ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። “አሳታፊነትን” ይከተል የተነበረው የተቋሙ አሠራር ባለፉት ወራት ለሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ ውሳኔዎቹን “አለማሳወቅ፣ አለማሳተፍ እና መመካከርን” ወደ ጎን ማለቱ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መልቀቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል። ባለፉት ዓመታት ኮሚሽኑ ገለልተኛነቱን እና ነፃነቱን ለማስጠበቅ ባደረጋቸው መዋቅራዊ እና ተጨባጭ ለውጦች ሲወደስ የነበረ ሲሆን፤ በ2013 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታ “የፓሪስ መርሆዎች” በተሰኘው መለኪያ በተአማኒነቱ ከፍተኛውን ደረጃ ‘ኤ’ ተሰጥቶታል። ኮሚሽኑ ባለፈው ሰኔ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ “የተዛባ” ሪፖርት ያወጣል የሚል ይፋዊ ወቀሳ የገጠመው ሲሆን፤ “እኛ ነፃ ሆነው ይሥሩ ስንል የጠለፏቸው . . .” በማለት
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

ትራምፕ አሜሪካ የኢትዮጵያውን ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በገንዘብ ደግፋለች ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ የኢትዮጵያውን ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በገንዘብ ደግፋለች ሲሉ ርግጠኝነት በሌለው መልኩ ትናንት በድጋሚ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ግድቡ ወደ ናይል ወንዝ የሚሄደውን ውሃ ይዘጋዋል በማለትም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፣ አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ እየሠሩበት መኾኑንና ችግሩ መፍትሄ እንደሚያገኝ በደፈናው ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ “መፍትሄ” ያሉት ምን እንደኾነ ግን አላብራሩም። መንግሥት፣ ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካኹን ቀደምም ይኹን ትናንት ለተናገሩት አወዛጋቢና አሳሳች አስተያየት፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ከመጋቤ ብሉይ አብርሀም ሃይማኖት የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊ/መንበር ጋር

ኢሕአፓ ከሀገር ከወጣ በኋላ የተለያዩ አንጃዎች ተፈጥረዋል። ከመካከላቸው በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገር ቤት የገባው የኢሕአፓ ቡድን ከዛሬ 6 ዓመት አንስቶ እየተንቀሳቀሰ ነው። መርኁም ሶሻል ዴሞክራሲ ነው። መጋቤ ብሊይ አብርሀም ሃይማኖት የፓርቲው ተቃዳሚ ምክትል ሊ/መንበር ናቸው። ከአንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች  አንዱ ነው። ከተመሰረተ 53 ዓመታት አልፈዋል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ በርካታ ወጣቶችን በማቀፍ ግንባር ቀደሙ ነበር ሊባል ይችላል፤የኢትዮጵያ ህዞቦች አብዮታዊ ፓርቲ በምህጻሩ ኢሕአፓ። 5 የፖለቲካ ድርጅቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ላይ ያነሱት ቅሬታ በማርክሲስት ሌኒኒስት ርዕዮተ ዓለም ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት አልሞ  የተቋቋመው ኢሕአፓ ከደርግ ጋር ባካሄደው የከተማና የገጠር ውጊያ በርካታ አባላትና ደጋፊዎቹ ተገድለዋል፤ ታስረዋል የደረሱበት ያልታወቀም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተወያዩ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዓርማ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢሕአፓ) ዓርማ ምስል፦ Megabe Beluiey Abrham Haimanot/DW አወዛጋቢ ታሪክ ያለው ፓርቲው ከኢትዮጵያ ከወጣ በኋላ የተለያዩ አንጃዎች ተፈጥረዋል። ከመካከላቸው በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ሀገር ቤት የገባው የኢሕአፓ ቡድን፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ከዛሬ ስድስት ዓመት አንስቶ እየተንቀሳቀሰ ነው ። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቤ ብሊይ አብርሀም ሃይማኖት  የዛሬው አንድ-ለ-አንድ ዝግጅታችን እንግዳ ናቸው ።  ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከድምጽ ማዕቀፉ ማዳመጥ ይቻላል።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ይደረጋል የተባለ ማሻሻያ ለምን ሥጋት ፈጠረ?

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ሊደረጉ የታቀዱ ማሻሻያዎችን የመረመሩ ባለሙያዎች ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ ሳለ ዘርፉን ቀፍድደው የያዙ ገደቦች እና አሠራሮች ተመልሰው ተግባራዊ ሊሆኑ ነው የሚል ብርቱ ሥጋት አላቸው። ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት ማሻሻያዎቹን እና ተጽዕኖዎቻቸውን ይፈትሻል። ኢትዮጵያ መንግሥት “አፋኝ” ይባል የነበረውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማኅበራት አዋጅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከያዙ በኋላ በየካቲት 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ሲተካ አድናቆት እና ቅቡልነት አግኝቶ ነበር። የዐቢይ መንግሥት በኢትዮጵያውያን እና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሞገስ የተቸረው ፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ መገናኛ ብዙኃን እና የሲቪል ድርጅቶችን የተመለከቱትን ጨምሮ የኢሕአዴግ አስተዳደር ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግባቸውን ሕግጋትን በማሻሻሉ ነበር። መንግሥት ለስድስት ዓመታት ገደማ ሥራ ላይ የቆየውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ለማሻሻል ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል። ሕጉ የሚሻሻለው ነባሩ አዋጅ “ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል” እንደሆነ የፍትኅ ሚኒስቴር ለውይይት ያቀረበው እና ዶይቼ ቬለ የተመለከተው ሠነድ መግቢያ ላይ ሠፍሯል። ኦፊሴላዊ ባልሆነው ሠነድ “የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቃሴ የህዝብ እና የአገርን ጥቅም ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን ለማድረግ” የሚለው ከማሻሻያው ዓላማች መካከል ተካትቶ ቀርቧል። ሠነዱ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ቦርድ አደረጃጀት፣ የድርጅቶች ምዝገባ፣ የሥራ ነጻነት፣ የሐብት አሰባሰብ እና አስተዳደር በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ለውጦች እንዲደረጉ ምክረ-ሐሳቦች የቀረቡበት ነው። ሠነዱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ቦርድ አባላት ቁጥር ከአስራ አንድ ወደ ሰባት ዝቅ እንዲል ምክረ-ሐሳብ ቀርቧል። ከሰባቱ የቦርድ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የዓመቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲመዘን

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የዓመቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲመዘን የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ እንቅስቃሴማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ ከምዕራባዊያን ሀገራት እና ተቋሞቻቸው ጋር ባላት ግንኙነት “ተቀባይነቷ የጨመረበት” ዓመት መሆኑን የጠቀሱ አንድ የዘርፉ ተንታኝ፣ የገንዘብ ተቋማት እያደረጉት ያለውን የብድር ድጋፍ አስረጂ አድርገዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት “አስጊነቱ አሁንም የቀጠለ” እና በጥቅሉ ሲመዘን “አድገናልም፣ ወድቀናልም የሚያስብል ኹኔታ ያልተፈጠረበት” ነው ብለዋል። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል ዐቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በኩል እንዳለው የተቋሙ የዚህ ዓመት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ “ውጤታማ” ነበር። ቃል ዐቀባዩ ለዚህ ዝርዝር ጉዳዮችን የጠቀሱ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው። “የዲፕሎማሲ ግንኙነታችንን በማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን በማሳደግ፣ ከጎረቤት ሀገሮች እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ትብብር እንዲቀጥል፣ ቀጣናዊ ትስስርን፣ አሕጉራዊ እና አለማቀፋዊ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል”።የሰላም
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የቀይ ባሕር አፋር በኢትዮጵያ ያካሄደው ሕዝባዊ ጉባኤ

DW Amharic : የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ በኤርትራ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና በሌሎች የሲቪክ ማህበራት አዘጋጅነት ኢትዮጵያ ውስጥ ትናንት እሁድ ተዘጋጀ በተባለው የቀይ ባሕር አፋር ጉባኤ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተገኝተዋል፡፡ የቀይ ባሕር አፋር በኢትዮጵያ ያካሄደው ሕዝባዊ ጉባኤ   የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ በኤርትራ በተቃዋሚነት የምንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና በሌሎች የሲቪክ ማህበራት አዘጋጅነት ኢትዮጵያ ውስጥ ትናንት እሁድ ተዘጋጀ በተባለው የቀይ ባሕር አፋር  ህዝባዊ ጉባኤ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የማህበረሰቡ አካላት ታዳሚ ነበሩም ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሽኩቻ መሰል ዉጥረት በጎላበት ባሁን ወቅት በኤርትራ መንግስት በቀይ ባህር አፋር ህዝብ ላይ ይፈጸማል የተባለው ሰቆቃ መጉላቱን ያሳወቀው ጉባኤው ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ የትኩረት ጥሪ አሰምቷልም።ትግራይ ክልል የእርስበርስ ግጭት እንዳይከሰት ሥጋት መፈጠሩን የሲቪክ ተቋማት ገለጹ የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ ድርጅት አመራሮች፣ የስደተኞች ተወካዮች፣ የጎሳ መሪዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ተሳትፈውበታል የተባለው ትናንት በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ ከተማ ላይ የተካሄደው ህዝባዊ ኮንፌረንስ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለስልጣናት መካከል የቃላት ጦርነትን ተከትለሎ ባሁኑ ወቅት በድንበር አከባቢዎች ላይ ውጥረት መንገሱን ያመለከተው አንዱና ዋነኛው የጉባኤው ተሳታፊና አዘጋጅ የቀይ ባህር አፋር ህዝብ ድርጅት ((RSADO) የቀይ ባሕር አፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል ይላል፡፡ ከአከባቢው ድንበር ዙሪያ የህዝብ ማፈናቀል ብሎም እሰከ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) ቢዘጋም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈጸሙ “የሁለትዮሽ የእርዳታ ስምምነቶች” በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስር በተዘረጋው አዲስ መዋር እንደሚቀጥሉ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ዋነኛ ናቸው ያላቸው የሰብአዊ እርዳታ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሮች በአዲሱ መዋቅር እንደሚቀጥሉ ዛሬው ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። አሜሪካ በእነዚህ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ እንደሚቀጥል ኤምባሲው ማረጋገጫ የሰጠው፤ የሀገሪቱ ተራድኦ ደርጅት የሆነው USAID ባለፈው ምንት በይፋ መዘጋቱን ተከትሎ ነው። ላለፉት 64 ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሰብአዊ እና የልማት እርዳታ ሲያቀርብ የቆየው ይህ ተቋም የተዘጋው፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ድርጅቱን ቀስ በቀስ ሲያዳክመው ከቆየ በኋላ ነው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፤ ድርጅቱ የነበሩትን ኃላፊነቶች ካለፈው ሰኞ ሰኔ 24፤ 2017 ጀምሮ በይፋ ተረክቧል። ሽግግሩ “ድግግሞሽን ለመቀነስ”፣ “ተጠያቂነትን ለማጠናከር” እና የእርዳታ መርሃ ግብሮችን ከዩናይትድ ስቴትስ “የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና የብሔራዊ ደህንነት ዓላማዎች ጋር ለማጣጣም የሚያስችል” ሆኖ እንደተቀረጸ የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው መግለጫ ጠቁሟል።
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

ከፋኖ ጋር ጦርነቱ ይቀጥላል ( ጄኔራሉ )……. ;አደጋው የከፋ ይሆናል (አቡነ ማትያስ)


Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የአዲስ አበባው ታላቅ ‘የማፊያ ስራ’!

(መሠረት ሚድያ)- አራት ኪሎ የሚገኘው ‘አምባሳደር ህንፃ’ ላይ ይገኝ የነበረው የድርጅቱ ቢሮ ውስጥ ሲገባ በመጀመርያ ቀልብን የሚስበው በብዙ የመንግስት ቢሮዎች ውስጥ እንደሚደረገው በትልቁ ታትሞ እና በፍሬም ተዘጋጅቶ የተሰቀለው የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ፎቶ ነው። ድርጅቱ ቢሮው ብቻ ሳይሆን ማስታወቂያውም ቀልቢ ሳቢ ነበር። “ልጄ ውጭ ሀገር ሄዳ ነው ትምህርቷን መከታተል የምትፈልገው፣ አገሯን የምታስጠራ ምሁር እንድትሆንልኝ እፈልጋለሁ” ትላለች ዝነኛዋ የማስታወቂያ ባለሙያ ሙሉአለም ታደሰ ከሌላኛዋ ታዋቂ የሚድያ ሰው ዳናይት መክብብ ጋር በመሆን በጋራ የሰሩት የዚህ ድርጅት ማስታወቂያ። ይህ ዛሬ የምናቀርብላችሁ የከባድ ማጭበርበር ድርጊት ዋና ተዋናይ ቀላል ሰውም አይደለችም። ከጥቂት አመታት በፊት በአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ላይ ከ ‘ተስፋ ሰጪ’ ‘እና ‘ስራ ፈጣሪ’ አምስት የሀገራችን ግለሰቦች አንዷ ሆና ቀርባለች፣ በተጨማሪም ከሴቶች እና ህፃናት ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጌጎ ተስፋዬ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላታል። ግለሰቧ ቤተልሄም ታደሰ ይማም ትባላለች፣ ታድያ ተሸላሚ ያረጋት ስራዋ ምን ይሆን? ድርጅቷ ከ120 ሚልዮን በላይ ብርስ ከህዝብ እንዴት ማጭበርበር ቻለ? ቤተልሄም ታደሰ ይማም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለስራ ወይም ለትምህርት ወደ ውጪ ሀገር ሰው እንልካለን በማለት ገንዘብ የሚሰበስቡ ድርጅቶች መብዛታቸውን ብዙ ሰው ታዝቧል፣ ከነዚህም አንዱ Aim Ultra Consultancy የተባለው ድርጅት ነው። “እኔ Aim Ultra ን ለደቂቃ እንኳን አልተጠራጠርኩም። ማስታወቂያውን ታዋቂ ሰዎች በቲቪ እና በሶሻል ሚድያ ሲሰሩ ስላየሁ እውነት ይሆናል ብዬ ከቤተሰብ ያገኘሁት ገንዘብ ላይ ከብድር እና ቁጠባ ተጨማሪ በመበደር 520,000 ብር ከፈልኩ”
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

ዋና አዛዦቹ ተገደሉ፤ መከላከያ ለቆ ወጣ !

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ወንድም ከወንድም መገዳደል ይብቃን፣ …ካላጠፋናቸው ያጠፉናል ….. አፋብኃ ህዝባዊ ውይይት ላይ የተላለፉ መልዕክቶች

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

አብይ አሕመድ እና በአውሮፓ የገጠመው ተቃውሞ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የአብይ አህመድ አቀባበል በለንደን ……. የአማራ ፋኖ በእንግሊዝ !

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አዉሮጳ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

ሻዕቢያና ህወሓት ወደ ትብብር ? ፤ አስመራና መቀለ ከጌም ኦቨር ወደ ፅምዶ? ”እናንተ አታስቆሙትም” ዐቢይ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በነፃነት በዓል ላይ ምን አሉ?

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ኢትዮጵያ ተናገሩ

የኤርትራው ፕሬዝደንት በትናንት ምሽት ብዙዎችን ባስደመመ ንግግራቸው ስለ ኢትዮጵያ ምን አሉ? – “የውጭ ሀይሎች በብልፅግና ወኪላቸው አማካኝነት የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ላለፉት አምስት አመታት ያወጁት ጦርነት ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጡ ያሳያል” – “ሊያቀርቡ የሚፈልጓቸው ምክንያቶች; ናይል እና ቀይ ባህር፣ የባህር በር ማግኘት፣ የኦሮሞ ህዝብን የማይወክል የኦሮሙማ አስተሳሰብ፣ የኩሽ እና የሴም ግጭት… ናቸው” – “የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱን ምርጫ መርጧል፣ ተቃውሞውን ለማጠንከር እየተዘጋጀ ነው” ሙሉ ዜናውን ያንብቡ፣ የሚድያችን ቤተሰብ ይሁኑ ⤵️ https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/3bf?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ፋኖ ቅድመ ሁኔታዎችና ድርድሩ

Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

በደብረብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ላልተፈለገ እርግዝና እና በአባላዘር በሽታ እየተጠቁ ነው

” በደብረብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ላልተፈለገ እርግዝና እና በአባላዘር በሽታ እየተጠቁ ነው ” የተፈናቃይ ሴት ወጣት ተወካዮች ⚫ ” የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ድርጅቶች አሁን ላይ ሁሉም ወጥተዋል ” የቻይና ካምፕ ተፈናቃይ አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ በደብረብርሃን መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚሰጠው የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን የተፈናቃዮቾ ሴት ወጣት ተወካዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። በህክምና ባለሙያዎች ዘንድም ሚስጥር ጠባቂ አለመሆን አገልግሎት ለማግኘት በምንሄድበት ወቅት የማሸማቀቂያ ቃላቶችን የሚጠቀሙ በመሆኑ አገልግሎቱን ማግኘት ከብዶናል ብለዋል። “የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት እየሰጠ ያለው ዩኒሴፍ ብቻ ነው፣ አገልግሎት የሚሰጠውም ግቢ ውስጥ ቢሆንም ሴት ልጅ ስትገባ የእንትና ልጅ የወሊድ መቆጣጠሪያ ልትጠቀም ገበች ይላሉ፣ ስንወጣ ደግሞ ወጣት ወንዶች ይጠብቁና ያሸማቅቁናል” ሲሉ ችግራቸውን ይገልጻሉ። በተጨማሪም ” የህክምና ባለሙያው ወንድ ነው፣ ይህ ደግሞ ሴቶች በነፃነት የሚፈልጉት እንዳይናገሩ አድርጓል፣ በከተማው ጤና ጣቢያዎች ስንሄድም በነፃ ስለሆነ የሚሰጠው ምን ልታደርጊ ትመጫለሽ ውጪ ይላሉ። እነሱ የሚፈልጉት ብር የሚከፍለውን ሰው ብቻ ነው” ሲሉ አክለዋል። ወጣት ሴቶችም በየፋርማሲው መድሀኒት እየገዙ ይውጣሉ፣ አብዛኞቹም ለህመም እየተዳረጉ ነው ብለዋል። በስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት እጥረት በርካታ ወጣቶች ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለአባላዘር እና ለመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች መጋለጣቸውንም አስረድተዋል። “በተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ያሉ ወጣት ወንዶች ተስፋ እየቆረጡ አልኮል እየጠጡ ሴት ልጆችንን አስገድደው እየደፈሩን ነው፣ ስንጠይቅም በቸልተኝነት ሁሉም ይስተካከላል ይላሉ” ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርቧል። በዚህ ጉዳይ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቻይና ካምፕ የተፈናቃይ ኮሚቴ
Posted in Amharic News, Ethiopia News, News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

” መንግስታት ውጤት አልባ ከሆነ የIMF የበጀት መቀነስና ዕዳ መክፈል ፖሊሲ ወጥተው ትኩረታቸውን ዜጎቻቸው ላይ ማድረግ አለባቸው ” – አክሽን ኤድ

” መንግስታት ውጤት አልባ ከሆነ የIMF የበጀት መቀነስና ዕዳ መክፈል ፖሊሲ ወጥተው ትኩረታቸውን ዜጎቻቸው ላይ ማድረግ አለባቸው ” – አክሽን ኤድ በአፍሪካ ስድስት ሃገራት በጤና እና ትምህርት ዘርፉ በጀት በመቀነሱ ሰራተኞች የከፋ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን አዲስ ጥናት (https://actionaid.org/sites/default/files/publications/The%20Human%20Cost%20of%20Public%20Cuts%20May%202025.pdf) አመላከተ። ጥናቱን አክሽን ኤድ የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት የሰራው ሲሆን ፦ – በኢትዮጵያ – በጋና – በኬንያ – በላይቤሪያ – በማላዊ – በናይጄሪያ 600 የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራንና የማህበረሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ነው ተብሏል። በጥናቱ ከተሳተፉት መሃል 97 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች የሚያገኙት ደመወዝ መሰረታዊ የሚባለውን ወጪያቸውን ለመሸፈን እንደማያስችላቸው ተናግረዋል። 97 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች በደመወዛቸው የቤት ኪራይ መክፈል፣ የምግብ እና ሌሎች ወጪዎችን መሸፈን እንዳልቻሉ አንስተዋል። በጥናቱ በ6ቱ ሀገራት የሚገኙ የጤና ተቋማት ተገልጋዮች በሃኪሞች እጥረት እና በዋጋ መጨመር ደስተኛ አይደሉም ሲል ያስቀመጠ ሲሆን መንግስታት ውጤት አልባ ከሆነ የIMF የበጀት መቀነስና ዕዳ መክፈል ፖሊሲ ወጥተው ትኩረታቸውን ዜጎቻቸው ላይ ማድረግ አለባቸው ብሏል። ህመምተኞች ወደ ጤና ተቋማት ለመሄድ ረጅም መንገዶችን እንደሚጓዙ፤ የወባ መድኃኒትም በ10 እጥፍ ዋጋው መጨመሩ በጥናቱ የተካተተ ነው። ለአብነትም በኢትዮጵያ ሙያከላ ቀበሌ የምትኖር ሴትን በመጥቀስ ከ5 አመት በፊት የወባ መድሃኒት በ50 ብር ትገዛ እንደነበር እና አሁን ግን ከግል ተቋማት በ500 ብር እንደሚገዛ መናገሯን ገልጿል። በሌላ በኩል ፥ በጥናቱ ከተሳተፉት 87 በመቶ የሚሆኑት መምህራን የክፍል ውስጥ ቁሳቁሶች /የማስተማሪያ ቁሳቁሶች እንዳልተሟሉላቸው ሲገልፁ ፤ 73 በመቶ ያህሉ የትምህርት ማስተማሪያ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ

አስፈሪው ኮማንዶ ወደ አዲስ አበባ…

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

በምርመራ ክፍል ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በአብይ አሕመድ መርማሪዎች ስለተገደለው ኢሳያስ በላይ የተሰራ የምርመራ ዘገባ

ልክ የዛሬ አመት በዚህ ወር በምርመራ ክፍል ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለተገደለው ኢሳያስ በላይ የተሰራ የምርመራ ዘገባ!ለስድስት አመታት ያህል በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ውስጥ ከፍተኛ የሳይበር ደኅንነት ባለሙያ ሆኖ አገልግሏል።በ2014 ዓ/ም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉ ሰላምና ደኅንነት የሚጠቀምበት ወታደራዊ ሬዲዮ የመለያ ኮዱ በቀላሉ ተጋላጭ ሆኖ ተገኘ። ይህንን የሬዲዮ ትስስር እንደ አዲስ ማስተሳሰር ግድም ሆነ።ኢሳያስ በላይ የወታደራዊ ሬዲዮ ትስስሮች እንዲሁ በቀላሉ የሚከወኑ አይደለም። በዘርፉ ልምድ ያላቸው አለም አቀፍ ተቋማት ተወዳድረው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚጠይቁበት ስራ ነው።አገርን ለከፍተኛ ወጪ የዳረገ የሬዲዮ ግንኙነት መረብ እንዲሁ በቀላሉ የይለፍ ቃሉ ተሰብሮ ሚስጥሮች የሚባክኑ ከሆነ ደግሞ ሌላ የአገራዊ ደኅንነት ስጋት ነው። ይህ ስጋት በ2014 ዓ/ም በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የሰላም እና ደኅንነት የሬዲዮ መገናኛ ላይ በግልፅ ታየ።ችግሩ እንዴት ይቀረፍ? በሚል ኢንሳ መፍትሄ ሲያፈላልግ ኢሳያስ በላይ በተቋሙ ውስጥ ያገኘውን አለም አቀፍ ልምድ በመውሰድ የክልሉን የሬዲዮ አውታር እንደ አዲስ ለማቀናጀት ሀሳቡን አቀረበ። ኢንሳ ሰባት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን አዋቅሮ ኢሳያስን የቡድኑ መሪ አድርጎ ወደ አማራ ክልል ሸኘው።ቡድኑን በማስተባበር የአማራ ክልልን ከወረዳ ጀምሮ እስከ ዋናው ቢሮ ድረስ ያለውን የሬዲዮ ትስስር በዘመናዊ መልኩ አቀናጅቶ ለክልሉ መንግስት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አስረክቧል። ኢሳያስ ዛሬ በሕይወት ባይኖርም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና የሰላምና ደኅንነት ቢሮ እስከ ወረዳ ድረስ የሚጠቀሙበት የሬዲዮ መገናኛ መረብ በዚህ ድንቅ ወጣት የተሳሰረ ነው።ኢሳያስ በላይ ለምን ተገደለ?የአማራ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

አጥብቀን ስንጠይቅ ‘ይህ እኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግላቸው የሚከታተሉት ፕሮጀክት ነው’ የሚል ማስፈራርያ አዘል ማሳሰቢያ ይሰጠናል

ከኢግል ሂልስ ‘ላጋር ዋን’ ሳይት ቤት የገዙ ደንበኞች ገጠመን ያሉት አነጋጋሪ ክስተት – “ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ቅድሚያ የከፈልነው ገንዘብ እና ቤቱ ራሱ እንደሚወሰድብን ማስጠንቀቂያ ደርሶናል” – “አጥብቀን ስንጠይቅ ‘ይህ እኮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግላቸው የሚከታተሉት ፕሮጀክት ነው’ የሚል ማስፈራርያ አዘል ማሳሰቢያ ይሰጠናል” https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/fda?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ፋኖ የአማራ ሕዝብን ያድናል፣ያሸንፋልም” አመራሩ ……… የህወሓት ጥሪና ማስጠንቀቂያ

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ከመረብ ወንዝ አቅራቢያ የተሰማው አዲስ መረጃ!”ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥና አጃቢዎች ተደመሰሱ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የጎጃሙ ጥቃትና የፈረስ ቤት ድል ወልዲያ ላይ በፋኖ ስም የተሴረው..

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

አፋብኃ ከባድ ውጊያ እያደረግን ነው አለ፤ አቡነ ማትያስ “ሀገሪቱ ተንገላታች፣በቃ በሉ” ብለዋል

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

በጎንደር የብልጽግና ሰዎች ተጫረሱ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በኢትዮ-ሱዳን ኮሪደር ተዘጋጅተናል ፋኖ

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል

በመላው አዲስ አበባ የሚገኙ መምህራን ለነገ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻልበት ቀጠሮ ተጠርተዋል – ስልክ እና ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ይዘው እንዳይመጡ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል “በየትኛውም ሴክተር የሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ ተምሮ እንዳልተማረ በመሃይም ካድሬዎችና የቢሮ ኃላፊዎች መብቱ እየተረገጠ፤ እንዳይረጋጋ በመንግስት የታቀደ ኢኮኖሚያዊ ጫና እየደረሰበት ይገኛል። የሰሞኑ የጤና ባለሙያዎችም ጥያቄ የሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ጥያቄ ነው፤ ከእንግዲህ መሃይም ሹመኞች እራት እንዲበሉ ሻማ ይዘን የምንቆምበት ወቅት አልፏል”- መምህራን https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/73e?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደኤታው ለቀቁ! የሐኪሞች ዐድማ ቀጠለ!

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች “በዘረፋ እና በሰዎች ንግድ ላይ ተሳትፈዋል

አቶ ጌታቸው ረዳ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች “በዘረፋ እና በሰዎች ንግድ ላይ ተሳትፈዋል” ሲሉ ወነጀሉ የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ሶስት ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች “በወርቅ ቁፋሮ እና ንግድ”፣ “የመንግስት ገንዘብ በመዝረፍ” እንዲሁም ”በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፈዋል” ሲሉ ወነጀሉ። አቶ ጌታቸው ረዳ ከፋና ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በስም ጠቅሰው የወነጀሏቸው ሶስቱ አመራሮች፤ ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ፣ ብርጋዴር ጀነራል ሃይለስላሴ ግርማይ እና ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ ናቸው። ትላንት ሰኞ ግንቦት 4፤ 2017 ምሽት በፋና ቴሌቪዥን የተላለፈው የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ክፍል አንድ ቃለ መጠይቅ፤ ስለ እርሳቸው የፖለቲካ ተሳትፎ አጀማመር፣ በትግራይ ክልል ስለ ተካሄደው ጦርነት፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች እና የትግራይ ሰራዊት አዛዦች “ፈጽመዋቸዋል” ስላሏቸው ወንጀሎች የዘረዘሩበት ነበር። አቶ ጌታቸው ተፈጽመዋል ካሏቸው ወንጀሎች ቅድሚያውን የሰጡት ለወርቅ ንግድ ነው። በትግራይ ክልል በህገወጥ መንገድ የሚካሄደው የወርቅ ንግድ የተጀመረው፤ ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነትን ከተፈራረሙ ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. በኋላ የሚመስለው በርካታ ሰው እንዳለ አቶ ጌታቸው በቃለ መጠይቃቸው ላይ አንስተዋል። ሆኖም በክልሉ ህገወጥ የወርቅ ቁፋሮም ሆነ ንግድ የተጀመረው፤ የትግራይ ጦርነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ጭምር እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ይፋ አድርገዋል። 🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15872/
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ጎንደር! በትናንቱ ውጊያ ወታደራዊ አመራሮቹ እርስበርሳቸው ተፋጠጡ! …. “የውጊያው እቅድ እንዴት በፋኖ እጅ ሊገባ ቻለ?”

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

አቶ ጌታቸው እነ ጀነራል ምግበ በወርቅ ንግድ ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ በስም ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል።

” እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል ” – አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ያለው ህገወጥ የወርቅ ንግድ  ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ የጀመረ ሳይሆን በጦርነቱ ጊዜም ሳይቀር ሲሰራ የነበረ እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ። አቶ ጌታቸው፤ “ብዙ ሰው የወርቅ ንግድ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረምን በኃላ የጀመር ይመስለዋል” ያሉ ሲሆን ግን ጦርነቱም እየተካሄደ ንግዱ ነበር ብለዋል። “እኔ የማምንበትን ትግል ነው ያካሄድኩት ብዬ አምናለሁ በዛ በማምንበት ትግል ውስጥ የትግራይን ህዝብ አጀንዳ ይዘው የታገሉ ብዙ የጦር መኮንኖች አሉ ለሰሩት ስራ ያለኝ ክብር በፍጹም አይቀንስም ግን ደግሞ ገና ገና ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይበላ በነበረበት ወቅት ሳይቀር ምሽግ ለመቆፈር ብለን የወሰድነው ኤክስካቫተር ወርቅ ለመልቀም ይጠቀሙበት የነበሩ አዛዦችም ነበሩ” ሲሉ አጋልጠዋል። “ሲዋሹ በጣም ነው የሚገርመኝ” ያሉት አቶ ጌታቸው “እኔ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል እስካሁን የታገስኩትም ይበቃኛል” ብለዋል። አቶ ጌታቸው “የኤርትራን ሰራዊት እናፍርሰው” በሚል አላማ ዘመቻ የጀመረና ዘመቻውን የሚመራው አመራር ሰዎችን እያፈነ ገንዘብ ሲበስብ እንደነበር ተናግረዋል። “ሰው ሲሸጡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፤ ኤርትራዊ መሸጥ ‘ ንብረት ‘ ነው የሚባለው ወርዷል ወይ ? ይባላል፤ ታፍንና ይዘህ 27 ወጣት አንድ ቤት ትዘጋና ቤተሰቦች አላቸው ውጭ ሀገር የሚባሉት ሰዎች አካውንት እየተጠየቀ እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 4000 ዶላር እንዲያስገባ ተደርጎ (20 ሰው ካፈንክ 80 ሺህ ዶላር ታስገባለህ) በዚህ የውጭ አካውንት ከፍተው በሺዎች የሚቆጠሩ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል 1ኛ ክፍለ ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ የቅንባባ ሻለቃ የጦር ዝግጁነትና ቁመና

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ

ዶ/ር በርናባስ ሳሙኤል፣ ዮናታን ዳኛው፣ ዶ/ር ሀብታሙ ጌታቸው እና ዶ/ር መላኩ አልማው የፎቶው ባለመብት, sm የምስሉ መግለጫ, ዶ/ር በርናባስ ሳሙኤል፣ ዮናታን ዳኛው፣ ዶ/ር ሀብታሙ ጌታቸው እና ዶ/ር መላኩ አልማው   የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኛው እንዲሁም ሦስት የአርባ ምንጭ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተሮች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በአማራ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በቀናት ልዩነት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር አምስት ደርሷል። በአዲስ አበባ ከተማ ሌሎች አምስት የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከሁለት ቀን እስር በኋላ ተለቅቀዋል። የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ ድጋፉን የገለጸው የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዮናታን የታሰሩት ትናንት እሁድ ግንቦት 3/2017 ዓ.ም. እንደሆነ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መለስ ባታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በ2015 ዓ.ም. የተመሠረተውን ማኅበር የሚመሩት አቶ ዮናታን፤ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን በሚገኘው ቢቸና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ መሆናቸውን አቶ መለሰ ገልጸዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንደሚናገሩት አቶ ዮናታን እሁድ ከሰዓት የተያዙት ከመኖሪያ ቤታቸው ነው። “ከመያዙ በፊት ከትናንት ወዲያ [ቅዳሜ] የሚሠራበት ሆስፒታል አካባቢ እና በሚኖርበት ሰፈር [በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ] ለምርመራ እንደሚፈለግ ደውለው እንዳስታወቁት ነግሮኝ ነበር” የሚሉት አቶ መለስ፤ ይህ ከሆነ ከአንድ ቀን በኋላ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። ከማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጋር አጭር የስልክ ንግግር ማድረጋቸውን የሚጠቅሱት አቶ መለስ፤ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝ እና “ብዙ ችግር እንዳልደረሰበበት” ከራሱ መስማታቸውን ገልጸዋል። ይሁንና የስልክ ጥሪው በመቋረጡ ምክንያት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የታሰሩበትን ምክንያትም ሆነ ስለተደረገባቸው ምርመራ በዝርዝር መነጋገር እንዳልቻሉ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

ፊ/ማ ብርሃኑ “ለግዳጅ ተልእኮ ተዘጋጁ”/ “ሰራዊቱ ወደ ፋኖ እየገባ ነው” አፋብኃ

Posted in News, VIDEO ቪዲዮ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ውጊያውና የወታደሩ ፍልሰት!በአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ!

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ጫንጮ ላይ የከተሙ ‘ሪጴ ሎላ’ የተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት አነጋጋሪ ድርጊት ላይ ምርመራ አርገናል

የምርመራ ዘገባ ጫንጮ ላይ የከተሙ ‘ሪጴ ሎላ’ የተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት አነጋጋሪ ድርጊት ላይ ምርመራ አርገናል   (መሠረት ሚድያ)- ከአዲስ አበባ 40 ኪ/ሜ ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የጫንጮ ከተማ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰላም ርቋታል። ተስማሚ አየር እና መልካም ገፀ ምድር ያላት የኦሮሚያ ክልሏ ጫንጮ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) እና በመንግስት ሀይሎች መካከል በሚደረግ ግጭት ምክንያት ፀጥታዋ ደፍርሷል። ታድያ በከተማዋ ተወልደው ያደጉትም ይሆን ከሌላ ቦታ ወደ ከተማዋ ሄደው የሚኖሩ ነዋሪዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ‘ሪጴ ሎላ’ በተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት አበሳቸውን እያዩ እንደሆነ መሠረት ሚድያ ባደረገው ክትትል ደርሶበታል። “የምኖረውም ተወልጄ ያደኩትም እዚሁ ጫንጮ ከተማ ነው፣ ለስራ የተሰማራሁትም በሞባይል ሽያጭ ላይ ነው” የሚለው አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከተማውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ እነዚህ ‘ሪጲ ሎላ’ የተባሉት የመንግስት ሀይሎች የጫንጮን ነዋሪ እያሰቃዩ እንደሆነ ይናገራል። “እኔ ላይ የደረሰውን ለመናገር፣ አንድ ቀን ሶስት ሆነው መጡና ብር አምጣ አሉኝ። ካሽ የለኝም ስላቸው ‘ካዝና ውጥ ይጠፋል? እናየዋለን!’ ሲሉኝና ሲቆጡ የእቁብ ብር ነው ስል አንዱ በጥፊ መታኝና 3,000 አርግ አለኝ፣ ሰጠኋቸው። የሆነውን ለጓደኞቼ ስናገር እኔንም፣ እኔንም 4,000 ብር ምናምን ወሰዱብን አሉኝ” በማለት ሁኔታውን አስረድቷል። ይህን ተከትሎ የጫንጮ ከተማ የፀጥታ ሀላፊ ጋር ሄደው ሲያመለክቱ “ከአቅማችን በለይ ነው፣ የኛን ፖሊስ ራሱ ደበደቡብን፣ ዝም በሉ በቃ” ብሎ ምላሽ እንደሰጣቸው አክሎ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 47 ቢሊዮን ብር ከሰርኩ አለ

ዘንድሮ 47 ቢሊዮን ብር የከሰረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ትርፋማነት እንደሚሸጋገር የኩባንያው ኃላፊዎች ገለጹ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ኪሳራ ቢያጋጥመውም፤ በሁለት ዓመታት ውስጥ ወደ ትርፋማነት ይሸጋገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የእናት ኩባንያው ኃላፊዎች ተናገሩ። መቀመጫውን በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ያደረገው ሳፋሪኮም ኩባንያ፤ እስከ መጋቢት ወር ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካገኘው 3 ቢሊዮን ዶላር የአገልግሎት ገቢ 10 በመቶ ገደማ የሚሆነው የኢትዮጵያ ገበያ ድርሻ እንደሆነ አስታውቋል። ኩባንያው የሚመራበት በጀት ዓመት መጠናቀቁን በማስመልከት ባለፈው ሐሙስ ይፋ የተደረገ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ባለፈው ዓመት 2.7 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን ዘንድሮ 7.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ270 ፐርሰንት እድገት ቢያሳይም፤ 47 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኪሳራ እንደገጠመው ዋና ስራ አስፈጻሚው ዊም ቫንሔለንፑት ገልጸዋል። “ይህ ኪሳራ በአብዛኛው ኩባንያው በሚገኝበት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ ከምንጠብቀው ጋር የተስማማ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በሐምሌ 2016 ዓ.ም. ተግባራዊ ያደረገው የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት ለውጥ በኩባንያው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ጠቁመዋል። የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት ለውጡ፤ በአጭር እና መካከለኛ ጊዜ የሚያሳድራቸውን ተጽዕኖዎች ለመቋቋም “እርምጃዎች መወሰዳቸውን” የሳፋሪኮም ኃላፊዎች አብራርተዋል። እርምጃው በውጭ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተቀጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን መቀነስን የካተተ ነው። 🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15849/
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ

መተማ ከባድ የደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ ወታደሩ ከነ መኪናው ወደመ! ቃሊም ወልድያ ከባድ ትንቅንቅ!

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የነበሩ ባለሀብቶች ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ እያቀረቡ ነው ተባለ

በዘጠኝ ወራት ከ37 ሺሕ በላይ ሠራተኞች መልቀቃቸው ተነግሯል በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩ ጦርነት ሸሽተው የወጡ ባለሀብቶች፣ ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ  እያቀረቡ መሆናቸውን፣ የኢንዱስትሪ ፖርኮች  ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ ይህንን የገለጸው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ ሲያቀርብ ነው፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከአገር ሸሽተው የሄዱ ባለሀብቶችን ለረዥም ጊዜያት በኢንተርኔትና በአካል በመገናኘት ኩባንያዎቻቸው ተመልሰው ወደ ልማት እንዲገቡ ጥረቶች ቢደረጉም ፍላጎት አለማሳየታቸውን፣ በኢንዱስትሪ ፖርኮች  ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ኩባንያዎቹ  ወደ ሌላ አገር ሄደው ለማልማት ማሽናቸውን ከአገር ይዘው ለመውጣት ጥያቄ በማቅረባቸው፣ እኛ እንደ መፍትሔ እያቀረብንላቸው ያለው አገር ውስጥ የገባና በአጠቃላይ አገራዊ ምርት የተመዘገቡ ማሽኖችን ወደ ሌላ አገር ከሚወስዱ፣ በአገር ውስጥ ወደ ሌላ አካባቢ  በማዘዋወር ለማሠራት ጥያቄ አቅርበን እየጠበቅን፤›› ነው ብለዋል። ነገር ግን ወ/ሮ ሶስና ጌታሁን የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል፣ መቀሌ የነበሩ ኢንቨስተሮች እዚያው መቆየት ካልፈለጉ ቦሌ ለሚ ወይም አዳማ እንዲያለሙ ለማድረግ እየተሠራ ነው የሚለው ምላሽ ትክክል አለመሆኑን፣ ኢንቨስተሮች በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምን እንደጎደላቸው መጠየቅና ችግሩን መፍታት እንጂ ከአንድ አካባቢ አስነስቶ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ መሞከር ትክክል አይደለም ብለዋል። አክለውም ያልተመቹ ጉዳዮች ካሉ ኢንቨስተሮቹ ተጠይቀው መፍትሔ በማፈላለግ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እዚያው ማቆየት እንጂ፣ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ማዘዋወር አግባብ አይደለም በማለት አሳስበዋል፡፡ ይህ በዚህ
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

የፋኖ አንድነት ተከትሎ የተቀሰቀሰው ውጊያ

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የፋኖ አንድነትና ውጊያው

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ከአንድነቱ ባልተናነሰ ብልጽግናን ያስደነገጠው ጉዳይ! …………….. አነጋጋሪው የዐቢይ ቃለ መጠይቅ!

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

የቋራ ቃልኪዳን የመሪዎች ማብራሪያ ቀጥታ ከግንባር

Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ፖለቲካ

ለትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች አዲስ ቀለም እና ኮድ ለሹፌሮቹም ዩኒፎርም ሊዘጋጅ ነው

መንግሥት፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደየአገልግሎታቸው ዓይነት “ወጥ ቀለም” እና መለያ ኮድ እንዲኖራቸው እቅድ መያዙን ዋዜማ ሠምታለች። የተሽከርካሪዎች ቀለምና መለያ ኮድ ከከተማ ከተማ የተለያየ ይሆናል ተብሏል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችም፣ ወጥ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ ዋዜማ ተረድታለች። የትራንስፖርት ሚንስትር ዓለሙ ስሜ፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ ለማድረግ እንደተወሰነ ሰሞኑን ባንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸውንም ዋዜማ ተረድታለች።
Posted in News, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, ኤኮኖሚ, ፖለቲካ

ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪቃ በሕገ ወጥ የሰዎች አዛዋሪዎች የሚፈጸምባቸው በደል ከፍቷል

አቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል ለወጣት ኢትዮጵያውያን የተስፋይቱ ምድር ተደርጋ በምትታየው በደቡብ አፍሪቃ በደላሎች የሚፈጽምባቸው በደል መክፋቱን ገልጸዋል።። በሕገ ወጥ መንገድ ደቡብ አፍሪቃ ከደረሱ በኋላ ለእገታ የሚዳረጉት አስቀድሞ ከደላሎች ጋር የተስማሙበትን ውል በጊዜው አላሟሉም የሚባሉት ኢትዮፕያውያን መሆናቸውንም ተናግረዋል።
Posted in አፍሪቃ