“የአዲስ አበባ ህዝብ እግርኳስ እንዳይመለከት ተፈርዶበታል”- አቶ ተካ አስፋው
የቀድሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመታት ቆይታ ስትሳተፍ የፌዴሬሽኑ ም/ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ተካ አስፋው በትላቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የክብር አባል በመሆን ተገኝተው የሰጡት አስተያየት ብዙዎች ሐሳብ እየሰጡበት ይገኛል።
አቶ ተካ አስፋው ትላንት የሰጡት ሃሳብ መጀመሪያ ስለ ሴቶች እግር ኳስ ሲሆን ለወንዶች የሚሰጠው ትኩረት ለሴቶች ስፖርት እየተሰጠ አይደለም ብለዋል። ሌላኛው በጉባዔው የተገኙትን ያስደመመ ንግግር የአዲስ አበባ ስታዲምን በተመለከተ የተናገሩት ነበር።
አቶ ተካ በዚህ መልኩ ገልፀውታል “የአዲስ አበባ ህዝብ እግርኳስ እንዳይመለከት ተፈርዶበታል” ካሉም በኃላ በትክክል የአዲስ አበባ ስታዲየም መቼ ወደ አገልግሎት ይመለሳል በሚል ጠይቀዋል።
በመቀጠልም የአዲስ አበባ ስታዲየም እግር ኳስ ባለማስተናገዱ ሦስት የሚያገኛቸውን ነገሮችን አጥቷል ብለዋል።
🕳እንደ አቶ ተካ አገላለጽ የአዲስ አበባ ስታዲየም ያጣቸው ሦስት ነገሮች
◼አንደኛው ከስታዲየም ገቢ ጋር በተያያዘ በጣም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም አሳጥቶታል ።
◼ሁለተኛው ጉዳት /ችግር የማህበራዊ ህይወት አጥቷል። እንደሚታወቀው በአዲሰ አበባ ስታዲየም የእግርኳስ ጨዋታ ብቻ መመልከቻ ሳይሆን የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን ተመልካቹ የሚነሳበት ፣ ሰዎች ከሰዎች የሚገናኙበት ጓደኝነት የሚመሠርቱበት ብሎም ትዳር ሁሉ የሚመሠርቱት ያንን
◼ሦስተኛው መንግሥት ከፖለቲካ አንፃር ችግር ውስጥ ከቶታል በማለት ተናግሯል።
ምንጭ ኢትዮ ኪክኦፍ የስፖርት ገፅ