አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ በኢትዮጵያ ከተሞች ከሚካሄደው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ለጊዜው እንዲቆም የሚጠይቁ ደብዳቤዎችን ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የመላክ ዘመቻ ትናንት መጀመሩን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ፣ ለዐቢይ የሚላኩ ደብዳቤዎች በኮሪደር ልማቱ ሳቢያ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው የግዳጅ ማፈናቀልና በፕሮጀክቱ የሰብዓዊ መብት ተጽዕኖ ላይ ጥልቅ ግምገማ እስኪደረግና በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ሳቢያ ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይደርሱ የሚያስችሉ የመከላከያ ሥርዓቶች እስኪዘረጉ፣ ፕሮጀክቱ እንዲቋረጥ የሚጠይቅ እንዲኾን ጥሪ አድርጓል። ድርጅቱ፣ ደብዳቤዎቹ የማፈናቀል ድርጊቶች ከዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕግጋት ጋር መጣጣማቸው እስኪረጋገጥ የኮሪደር ልማቱ እንዲቋረጥ እንዲኹም ጠቅላይ ሚንስትሩ በግዳጅ ማፈናቀል ላይ አንድ ሕግ እንዲያወጡ የሚጠይቅ ይዘት እንዲኖራቸው ጭምር አሳስቧል።