አቡነ ሉቃስ ከታዬ ደንድዓ የተለየ ምን ነገር ተናገሩ ? – ቤተ ክርስቲያንን የማጥቂያ ሰበብ!

ቤተ ክርስቲያንን የማጥቂያ ሰበብ!

ብልፅግና “ቤተ ክርስቲያን ታውግዝ” እያለ ጫና እያሳደረ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የሚጠቀምባቸው የብሔር “ሲኖዶሶች”ም ይህን የብልፅግና ዘመቻ ተቀላቅለዋል። እነ አብይ ዘመቻ ያስጀመሩት ቤተ ክርስቲያን የማውገዝ ግዴታ ስላለባት አይደለም። ሊያጠቋት ሰበብ ፍለጋ ነው። ለምንድን ነው ውግዘቱ?

1) አቡነ ሉቃስ የተናገሩት ሲፈፀም የከረመውን ነው። ሳይፈፀም የጨመሩት ወንጀል አለ?

2) ተታልያለሁ እንዳሉ አባት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ይህን አይደለም የኃይማኖት አባት ከአብይ ጎን የነበሩት እነ ታዬ ደንድኣ የተናገሩት ነው። አብይ ጨካኝ ነው ብሏል ታዬ። አቡነ ሉቃስ ምን ጨመሩ?

3) የግድያው ወሬ የተጋነነ ነው። አብይ ራሱ በየጊዜው ጓደኞቹን ጭምር ልታስገድሉኝ እንደሚናገር ይታወቃል። ባለፈው ወር የቤተ መንግስት ጥበቃዎች ደብረዘይት የተገመገሙት ተፈርተው አይደለም እንዴ? አብይ በግል ጠባቂዎቹን “ልትገድለኝ” ወዘተ እያለ እንደሚጠይቅ ይነገራል። አሁን እንደ አዲስ ምን አስደነገጣቸው? አቡነ ሉቃስ አብይ ዲያብሎስ ነው ሲሉ በዝርዝር ህፃን ከመግደል ጀምሮ ያለውን አሳይተዋል። የኃይማኖት አባት ለዲያብሎስ እንዲራራ ፈልጋችሁ ነው?

ይህ ሁሉ ጫጫታ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት ሰበብ ነው! ብልፅግና ቀሳውስትን ገድሎ ይቅርታ ጠየቀ? ንፁሃንን ጨፍጭፎ ይቅርታ ጠየቀ? አመራሮቹ በህዝብ ላይ ሲለፉደዱ አንዴ እንኳን ይቅርታ ጠይቆ ያውቃል? እና ቤተ ክርስቲያን አንድ አባት ደፈር ብለው የአገዛዙን ወንጀል ስላወገዙ ለምን ታወግዛለች? ቤተ ክርስቲያን የሚወገዝና የማይወገዘውን የምትወስነው በራሷ መንፈሳዊ አሰራር እንጅ በማህበራዊ ሚዲያና በስልክ እየተደወለ በሚደረግ ጫና አይደለም።

ብታወግዝ ማውገዝ የሚገባት ቤተ ክርስቲያን የሚያቃጥለውን፣ ምዕመናን የሚያርደውን፣ ማፍያ ቡድን አደራጅቶ ቤተ ክርስትያን የማከፍለውን ኃይል ነበር።

አባ ሉቃስ እንደ ኃይማኖት አባት ተቀባይነት ስለሚኖራቸው ብቻ ስትደነግጡ ሰበብ ተሸክማችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጣችሁ እንጅ ያልተፈጠረ፣ ሌሎች ያላሉት ነገር አልተናገሩም።

የተረገመ ስራ እየሰሩ አትርገሙኝ ማለት አይቻልም።