ፓኪስታን ከህንድ የተላኩባትን 25 እስራኤል ሰራሽ ድሮኖች መትታ መጣሏን አስታወቀች።

ፓኪስታን ከህንድ የተላኩባትን 25 እስራኤል ሰራሽ ድሮኖች መትታ መጣሏን አስታወቀች።

ሁለቱ የኒውኪሊየር ጦር መሳሪያ ባለቤት ሃገራት በዚህ ሳምንት ወደ ግጭት የገቡ ሲሆን ፓኪስታን ከህንድ ለጥቃት የተላኩባትን 5 የጦር ጀቶች እና 25 እስራኤል ሰራሽ ድሮኖች መትታ መጣሏን ገልፃለች።

የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር 25 እስራኤል ሃሮፕ ድሮኖችን መትተው እንደጣሉ ሲገልፅ የህንድ መንግስት ምንጮች ተመቶ የወደቀው ድሮን አንድ ብቻ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ድሮኖቹ እስራኤል ሰራሽ ሲሆኑ ከዚህ በፊት እስራኤል በሶሪያ እና አዘርባጃን ከአርሜኒያ ጋር ባደረገችው ጦርነት ስለመጠቀማቸው ተነግሯል።

ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ በፓኪስታን ብዙ ሰው በሚኖርባት የፑንጃብ ግዛት ጥቃት የፈፀመችው ህንድ በበኩሏ በሃገሪቱ ሰሜን እና ምዕራብ አካባቢ በሚገኙ 15 ቦታዎች የተቃጡ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶችን ማክሸፏን ተናግራለች።

በተጨማሪ ህንድ በላሆር በሚገኙ የአየር መከላከያ ራዳሮች እና ስርዓቶች ላይ ፈፀምኩት ባለችው ጥቃት ስርዓቶቹን አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረጓን ገልፃለች።

Source : Washington Post, Middle east eye