በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ፣ ወጣቶች በጸጥታ ኃይሎች ድንገት ከታፈስን በሚል ስጋት ለጉቦ ገንዘብ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ጸጥታ ኃይሎች ምን ያህል ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል እንዳለባቸው ከወረዳ አመራሮች ተተምኖ እንደሚሠጣቸው ምንጮች መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። ኢሰመኮ ኅዳር ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ከመከላከያ ሚንስቴር የምልመላ መስፈርቶች ውጪ በግዳጅ ለተያዙ ሰዎች ማስለቀቂያ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፍሉ በምርመራ ማረጋገጡን አስታውቆ ነበር።