አንድ ሊትር ቤንዚን 122 ብር ከ53 ሳንቲም ሲገባ አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 116 ብር ከ49 ሳንቲም ገባ።
የኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ዛሬ ለነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ባሰራጨዉ ሰርኩላር ከዛሬ ሚያዚያ 30/2017 ዓ/ም ምሽት 12 ሠዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት ፦
➡️ አንድ ሊትር ቤንዚን 122 ብር ከ53 ሳንቲም
➡️ አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 116 ብር ከ49 ሳንቲም
➡️ አንድ ሊትር ኬሮሲን 116 ብር ከ49 ሳንቲም ገብቷል።
በሌላ በኩል ፦
🔴 የአውሮፕላን ነዳጅ 113 ብር ከ20 ሳንቲም ከነበረበት ወደ 109 ብር ከ56 ሳንቲም ዝቅ ብሏል።
🔴 አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106 ብር ከ75 ሳንቲም ከነበረበት ወደ 104 ብር ከ08 ሳንቲም ዝቅ ብሏል።
🔴 አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 109 ብር ከ22 ሳንቲም ከነበረበት 106 ብር 77 ሳንቲም ዝቅ ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ ከተማ ተዘዋውሮ ስለዋጋው ጭማሪ የጠየቃቸው ማደያዎች ዛሬ ምሽት ቤንዚን 122 ብር ከ53 ሳንቲም፣ ናፍጣ ደግሞ 116 ብር ከ49 ሳንቲም መግባቱን ተናግረዋል።