የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል፣ አንዳንድ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖች የሚያራምዱት የሉዓላዊ ጎረቤት አገርን ግዛት የመቆጣጠር ፍላጎት፣ “ሊታሰብ ወይም ሊታለፍ የማይችል ቀይ መስመር ነው” በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖች የጎረቤት አገርን ግዛት የመቆጣጠር አጀንዳቸውን የሚያንጸባርቁት፣ ሲያሻቸው “በወታደራዊ ኃይል በማስፈራራት” እና ሌላ ጊዜ ደሞ “ታሪካዊ” ወይም “ሕጋዊ” የሚሏቸውን ምክንያቶች በመደርደር ነው በማለት የማነ ተችተዋል። የማነ አያይዘውም፣ ይኼ ዓይነቱ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና ቡድኖች አካሄድ፣ “ከፍተኛ ፖለቲካዊ ስድብ ነው” በማለት ወቅሰዋል።