Home › View all posts by Meheret Setegn
Blog Archives
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ኩለንታዊት ቀዳማዊት ደኀራዊት፡ ዘመናዊት ናት ስትባል እም ኀበ አልቦ አይደለም፡፡ በብዙ እሴቶቿ ነው፡፡ ኩለንታዊት ከምታደርጋት ከብዙ እሴቶቿ መካከል የጽሑፌ መነሻ የሆኑት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋራ የተሳሰሩት የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ ስንበቴ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የታዘዘች ናት፡፡ የጽዋ ማኅበርም እንደ ሰንበቴው ቀጥታ ከግዚአብሔር ባይሆንም፡ በዮቶር በኩል ለሙሴ የደረሰው የግዚአብሔር ምሪት ናት፡፡ የጽዋ ማሕበርና ሰንበቴ የትርጉማቸው መነሻ፡ መድረሻና የመጨረሻ ዋና ዓላማቸው ሰባዊ ክብርና ነጻነት ነው፡፡
ኢትዮጵያ የተፈታተኗትን ሁሉ ቅኝ ገዥወች ከተከላከለችባቸው ከተዋጋችባቸውና ነጽነቷን ካስከበረችባቸው ዋናወቹ እሴቶቿ ውስጥ የጽዋ ማሕበራትና ሰንበቴወች ናቸው፡፡ በቅኝ ገዥወች ሲቀጠቀጡ ከኖሩት ካጎራባች አገሮች ልዩና የነጻነት ምሳሌ ያደርጓትም የጽዋ ማህበርና ሰንበቴ ናቸው፡፡ የጽዋ ማኅበራትና የሰንበቴ ድርጅቶች እንዴት ተመሰረቱ? ለኢትዮጵያ ምን ጠቀሙ? ትሩፋታቸው ምንድነው? የደርግንና የወያኔን ዘመናት እንዴት ተሻገሩ? በብልጽግና ዘመንስ እንዴት ናቸው? እንዴት ይቀጥሉ ? የሚሉትን ጥያቄወች ለመመለስ ከጽዋ ማኅበር እንጀምር፡፡ ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ያንብቡ።
የጽዋዕ ማህበራት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌDownload
ዘንድሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስታና የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት አካላት በተለይም አማሮችና ተጋሩወች በመልካሙ ዘመን እንደሚያደርጉት ግብረ ሕማማት የሚባለውን መጽሐፍ ዘርግተው ለማንበብ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ የሚያስፈልጋቸው አይደለም፡፡ ራሳቸው ግብረ ሕመም የሚባለውን መጽሐፍ ሆነዋል፡፡ ምድራቸውም ግብረ ሕማማቱ የሚነበበት ወደ ቤተ ክርስቲያንነት ተቀይሯል፡፡ እንዴት? የሚል ጥያቄ መከተሉ ስለማይቀር ተባብረን ለመመለስ የግብረ ሕማማቱን ሐተታ አብረን እንቃኘው፡፡ ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።
ግብረ ሕማማትDownload
አባ ሠረቀ ከእግረኛው ጋራ ያደረጉትን ንግግር አዩት? ሰሙት? ብየ ቀሲስ አስተራየን ጠየኳቸው፡፡ “አዎ ሰማሁት” አሉኝ፡፡ ምን ተሰማዎት? ብየ ጠየኳቸው፡፡ በግረኛውና በአባ ሠረቀ መካከል የተካሄደው ንግግር “በሲኖዶሱ ጸሐፊ በአቡነ ጴጥሮስ እጅ የነበረው ስልጣን በአባ ሠረቀ እጅ ቢሆን ለወደዱት ትልቅ ጥቅም በጠሉት ላይ ትልቅ ጉዳት ያደርሱበት እንደነበርና አባ ሠረቀ ለአመኑለት ነገር እስከ ሞት ለመሄድ የወሰኑ መሆኑን ተረዳሁ። በአማራው ጎን ያሉት ጳጳሳት ለራሳቸው ጥቅምና ክብር ከመቆም በቀር ለምንም የምይጠቅሙ ደካሞች መሆናቸውን በዚህ ንግግር አየሁ። ዳዊት “ጽዋ በግዚአብሔር እጅ ነውና። ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት። ከዚህም ወደ ዚያ አገላበጠው። ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም። የምድር ኅጢአተኞች ሁሉ ይጠጡታል (መዝ 74፡7_10) እንዳለው አባ ሠረቀ የጀመሩትን የኃጢአት ጽዋ ራሳቸውን ከነአተላው እግዚአብሔር ሲግታችሁ ተመለከትኩ” አሉኝ።
ቀሲስን እንድጠይቃቸው ያደረገኝ ከአመታት በፊት ምክር አዘል ደብዳቤ ለአባ ሠረቀ ጽፈውላቸው የነበረውን አንብቤ ስለነበር ነው። “ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅም” እንደሚባለው አባ ሠረቀ በዲያብሎስ የተሰረሩ እርጉም ስለሆኑና ፖለቲካው ደማቸው ውስጥ ስለሚናኝ የሚሰሙና የሚታረሙ አይደሉም። አንድኛውን ከደፈሩ አይቀር ጭምብላቸውን አውልቀው ጥለው የትህነግ ታጋይ መሆናቸው ቢያውጁ ይሻላቸዋል። የትህነግ ታጋይና ቀንደኛ ካድሬ እንደነበሩ በጦርነትም ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው ይታወቃል። እሳቸውስ አንዱ ይዘውታል “የዘሬን ብረሳ ይዘርዝረኝ” ብለዋል። እኔ የሚገርመኝ ከአማራው ወገን ያሉት ጳጳሳትና ቆሞሳት ይህ ሁሉ መርዝ በአባ ሠረቀ ሲረጭ የትግራዩ “መንበረ አሳማ” የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀለብ እየሰፈረች ሆዳቸው በምትሞላላቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ ወንጀል ሲሰራባትና ስትቦረቦር እየተመለከቱ እጃቸውን አጣጥፈው መቀመጣቸው
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከተማ ምክር ቤት የአድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ አዋጅ እንዲያውጅ አስደርጓል። የአሌክሳንደሪያ ከተማ ምክር ቤት በከንቲባዋ ወ/ሮ አሊያ ጋስኪን ፊርማ ባወጣው አዋጅ 129ኛውን የአድዋ ድል አስመልክቶ ለኢትዮጵያዊያን “የእንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት አስተላልፏል። ከዚህም በተጨማሪ የአድዋ ድል የሚከበርበትን የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. (ማርች 2 ቀን 2025) የአድዋ ድል በዓል ቀን ሆኖ እንዲታሰብ አዋጅ አውጇል። በአዋጁ ላይ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብም ድል መሆኑንና በቅኝ ግዛት ተይዘው ለነበሩ በመላው ዓለም ለሚገኙ ህዝቦችም ለነጻነታቸው እንዲታገሉ መልካም ምሳሌና ማበረታቻ እንደሆናቸው ተመልክቷል። በአሌክሳንደሪያ ከተማ ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንደሚኖሩ የሚታወቅ ሲሆን የወጣው አዋጅ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊያው፣ ባህላዊ መስኮች ያበረከቱትን ገንቢ አስተዋጽኦ ዕውቅና ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የዘንድሮውን የአድዋ ድል በዓል ከአቡጊዳ የቋንቋና ባሕል ተቋም ጋር በትብብር ቅዳሜ፣ ማርች 1 ቀን 2025 እንደሚያከብር አስታውቋል። ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ድረ ገጽ ጎብኙ። www.ehsna.org
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለ አቡነ ማትያስ መተኛትና ማንቀላፋት በተከታታይ አውስተው እንቀስቅሳቸው እንጎትጉታቸው በሚል ያቀረቡትን ዝርዝር ትንታኔ በቱምቢ መገናኛ አደመጥኩት፡፡ ሰውም እየተቀባበለ በሰፊው በመደመጥ ላይ ነው፡፡
ቀሲስ አስተርአየ ከዚህ ቀደም የጻፏቸውን እንደኔ ያነበባችሁ፡ የተናገሯቸውን እንደኔ ያዳመጣችሁ ስንት እንደሆናችሁ አላውቅም፡፡ ከደረግ ዘመን ጀምሮ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናቸው ይጽፉትና ይናገሩት የነደነበረው ሁሉ በዘመኑ በነበሩት መገናኛ ድረ ገጾች በሰፊው እየቀረቡ ይነበቡና ይሰሙ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ እስካሁን ድረስ የሚጽፏቸውና የሚናገሯቸው እርስበርስ ሳይጋጩ ወጥ ሆነው ሲቀጥሉ እየተመለከትኩና እየታዘብኩ ነኝ፡፡ በዚህ አቋማቸው በዘመናችን ካሉት መንፈሳዊያን ሰወች ሰባኪወች ጸሐፊወችና ተናጋሪወች ቀሲስን የተለዩ አድርጓቸውል፡፡
ቀሲስ አስተርአየ ሰሞኑን በቱምቢ መገናኛ እየቀረቡ የተናገሩት፡ ከ 12 አመት በፊት በ2005 በየካቲት ወር “ምቱር ፓትርያርክ” በሚል ርእስ ላቀረቡት ጽሑፍ መደምደሚያ መስሎ ስለተሰማኝ ከ archive ውስጥ መዝዠ ለማቅረብ ሳስብ ራሳቸው ደጋግመው የተጠቀሟትን ውጥንቅጥ የምትለውን ቃል መግቢያ እንዳደርጋት አስገደደኝ፡፡
ቀሲስ “የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸው” ያሉትን ሲያብራሩ “በኔ በኩል ከመቀስቀስም አልፌ ጎትጉቻለሁ” ያሉትን መነሻ በማድረግ ዲያቆን ዮሴፍ “ፓትርያርኩ ተቀስቅሰውም ተጎትጉተውም ካልነቁ ቀጣዩ ምን ይሁን? ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ በይቆየን አንተርሰውታል፡፡ ዛሬም የሚናገሩት ከዚህ ቀደም “ ምቱር ፓትርያርክ” በሚል ርእስ ላቀረቡት ጽሑፍ መደምደሚያ ስለመሰለኝ ውጥንቅጥ ብለው የተናገሯት ቃል ጎልታ ታየችኝ፡፡ ቀሲስ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥራተ ትምህርትና አስተዳደግ ሲገልጹ ውጥንቅጥ የምትለውን ቃል ደጋግመው መጥቀሳቸውን ያነበበ የሚዘነጋ አይመሰኝም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥራተ ትምህርትና አስተዳደግ ሲገልጹ