ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለ አቡነ ማትያስ መተኛትና ማንቀላፋት በተከታታይ አውስተው እንቀስቅሳቸው እንጎትጉታቸው በሚል ያቀረቡትን ዝርዝር ትንታኔ በቱምቢ መገናኛ አደመጥኩት፡፡ ሰውም እየተቀባበለ በሰፊው በመደመጥ ላይ ነው፡፡
ቀሲስ አስተርአየ ከዚህ ቀደም የጻፏቸውን እንደኔ ያነበባችሁ፡ የተናገሯቸውን እንደኔ ያዳመጣችሁ ስንት እንደሆናችሁ አላውቅም፡፡ ከደረግ ዘመን ጀምሮ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናቸው ይጽፉትና ይናገሩት የነደነበረው ሁሉ በዘመኑ በነበሩት መገናኛ ድረ ገጾች በሰፊው እየቀረቡ ይነበቡና ይሰሙ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ እስካሁን ድረስ የሚጽፏቸውና የሚናገሯቸው እርስበርስ ሳይጋጩ ወጥ ሆነው ሲቀጥሉ እየተመለከትኩና እየታዘብኩ ነኝ፡፡ በዚህ አቋማቸው በዘመናችን ካሉት መንፈሳዊያን ሰወች ሰባኪወች ጸሐፊወችና ተናጋሪወች ቀሲስን የተለዩ አድርጓቸውል፡፡
ቀሲስ አስተርአየ ሰሞኑን በቱምቢ መገናኛ እየቀረቡ የተናገሩት፡ ከ 12 አመት በፊት በ2005 በየካቲት ወር “ምቱር ፓትርያርክ” በሚል ርእስ ላቀረቡት ጽሑፍ መደምደሚያ መስሎ ስለተሰማኝ ከ archive ውስጥ መዝዠ ለማቅረብ ሳስብ ራሳቸው ደጋግመው የተጠቀሟትን ውጥንቅጥ የምትለውን ቃል መግቢያ እንዳደርጋት አስገደደኝ፡፡
ቀሲስ “የተኙትን ፓትርያርክ እንቀስቅሳቸው” ያሉትን ሲያብራሩ “በኔ በኩል ከመቀስቀስም አልፌ ጎትጉቻለሁ” ያሉትን መነሻ በማድረግ ዲያቆን ዮሴፍ “ፓትርያርኩ ተቀስቅሰውም ተጎትጉተውም ካልነቁ ቀጣዩ ምን ይሁን? ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ በይቆየን አንተርሰውታል፡፡ ዛሬም የሚናገሩት ከዚህ ቀደም “ ምቱር ፓትርያርክ” በሚል ርእስ ላቀረቡት ጽሑፍ መደምደሚያ ስለመሰለኝ ውጥንቅጥ ብለው የተናገሯት ቃል ጎልታ ታየችኝ፡፡ ቀሲስ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥራተ ትምህርትና አስተዳደግ ሲገልጹ ውጥንቅጥ የምትለውን ቃል ደጋግመው መጥቀሳቸውን ያነበበ የሚዘነጋ አይመሰኝም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥራተ ትምህርትና አስተዳደግ ሲገልጹ ውጥንቅጥ የምትለውን ቃል ደጋገመው እንደጠቀሷትና ሶስትም ያንድምታ ትርጉም እንዳለት ተናግረው ነበር፡፡
አንደኛውን ትርጉም ቅልቅል ብለውታል፡፡ ሁለተኛው ትርጉም ዝብርቅርቅ ብለው ሲሆን ሶስተኛውን ትርጉም በሁለት ከፍለው ወጥ እና ቅጥ ብለው ነበር፡፡ አንደኛውንና ሁለተኛውን ያንድምታ ትርጉም የደምን መቀላቀልና የሐሳብን ዝብርቅርቅነት እንዲሚገልጽ ጠቁመው ነበር፡፡ የመጨረሻውን ትርጉም ወጥ እና ቀጥ ብሎ ያደገ የማይወላውል ብለው የኢትዮጵያውነትን አስተዳደግ ገልጸውበታል፡፡ እሳቸውን ከዘመኑ ሰባኪወችና ቀሳውስት ልዩ ያደረጋቸው? ምንድነው ብየ ርሴን ስጠይቅ መልሱን እራሳቸው ከቀሲስ አስተርአየ ውጥንቅጥነታቸው (ወጥቅጥነታቸው) እንደሆነ ተረድቻለህ፡፡
ከልጅነታቸው ጀምረው በዘመናቸው በነበሩት ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ስነ መለኮትና ስነ ሕሊና በማደጋቸው ቀጥ ብለው እንዲዘልቁ ረድቷቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያብነቱ ትምህርት ምን ያህል የማይበገር መሆኑን ትረዱ ዘንድ በሁለት ሺ አምስት የካቲት ወር “ምትሩር ፓትርያርክ” በሚል ያቀረቡትን ጦማር አቀረብኩላችሁ፡፡
ሙሉውን ጽሁፍ እዚህ ላይ ያንብቡ።