አባ ሠረቀ ከእግረኛው ጋራ ያደረጉትን ንግግር አዩት? ሰሙት? ብየ ቀሲስ አስተራየን ጠየኳቸው፡፡ “አዎ ሰማሁት” አሉኝ፡፡ ምን ተሰማዎት? ብየ ጠየኳቸው፡፡ በግረኛውና በአባ ሠረቀ መካከል የተካሄደው ንግግር “በሲኖዶሱ ጸሐፊ በአቡነ ጴጥሮስ እጅ የነበረው ስልጣን በአባ ሠረቀ እጅ ቢሆን ለወደዱት ትልቅ ጥቅም በጠሉት ላይ ትልቅ ጉዳት ያደርሱበት እንደነበርና አባ ሠረቀ ለአመኑለት ነገር እስከ ሞት ለመሄድ የወሰኑ መሆኑን ተረዳሁ። በአማራው ጎን ያሉት ጳጳሳት ለራሳቸው ጥቅምና ክብር ከመቆም በቀር ለምንም የምይጠቅሙ ደካሞች መሆናቸውን በዚህ ንግግር አየሁ። ዳዊት “ጽዋ በግዚአብሔር እጅ ነውና። ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት። ከዚህም ወደ ዚያ አገላበጠው። ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም። የምድር ኅጢአተኞች ሁሉ ይጠጡታል (መዝ 74፡7_10) እንዳለው አባ ሠረቀ የጀመሩትን የኃጢአት ጽዋ ራሳቸውን ከነአተላው እግዚአብሔር ሲግታችሁ ተመለከትኩ” አሉኝ።
ቀሲስን እንድጠይቃቸው ያደረገኝ ከአመታት በፊት ምክር አዘል ደብዳቤ ለአባ ሠረቀ ጽፈውላቸው የነበረውን አንብቤ ስለነበር ነው። “ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅም” እንደሚባለው አባ ሠረቀ በዲያብሎስ የተሰረሩ እርጉም ስለሆኑና ፖለቲካው ደማቸው ውስጥ ስለሚናኝ የሚሰሙና የሚታረሙ አይደሉም። አንድኛውን ከደፈሩ አይቀር ጭምብላቸውን አውልቀው ጥለው የትህነግ ታጋይ መሆናቸው ቢያውጁ ይሻላቸዋል። የትህነግ ታጋይና ቀንደኛ ካድሬ እንደነበሩ በጦርነትም ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው ይታወቃል። እሳቸውስ አንዱ ይዘውታል “የዘሬን ብረሳ ይዘርዝረኝ” ብለዋል። እኔ የሚገርመኝ ከአማራው ወገን ያሉት ጳጳሳትና ቆሞሳት ይህ ሁሉ መርዝ በአባ ሠረቀ ሲረጭ የትግራዩ “መንበረ አሳማ” የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀለብ እየሰፈረች ሆዳቸው በምትሞላላቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ ወንጀል ሲሰራባትና ስትቦረቦር እየተመለከቱ እጃቸውን አጣጥፈው መቀመጣቸው ነው። ኢትዮጵያ ያሉትም እንዲሁም አሜሪካ፣ እውሮፓና በተለያዩ አገሮች ውስጥ ያሉትም ወጧ እንዳማረላት ሴት በየአውደ ምሕረቱ ቀሚሳቸውን አሳምረው ላይ ታች ሲሉ ከመዋል በፊት ቁም ነገር ሲሰሩ አይታዩም። የነሱ የዘወትር ተግባር ገንዘብ ማጋበስና ከህዝብ በተቀፈፈ ገንዘብ መምነሽነሽ ነው።
ቄሶች በተለይም የትግራይ ሰዎች ይህን ደብዳቤ ተመልከቱት፡፡ ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን የቀረበ ሀሳብና ርሕራኄ ያላቸው ቀሲስ አስተራየ ናቸው ወይስ አባ ሠረቀ? የራሳችሁ ግንዛቤና ትዝብት እንዲኖራችሁ እኔን ያስገረመኝን ቀሲስ አስተርአየ ቀደም ሲል ለአባ ሠረቀ የጻፉላቸውን ደብዳቤ እንድትመለከቱት ከዚህ በታች አቀርብኩላችሁ፡፡ ቀሲስ ደብዳቤውን የደመደሙበት ቅኔው ጥልቅ ትምህርት ሰጭ እንደሆነ እገምታለሁ። “ቆሞስ ነን” “ጳጳስ ነን” የምትችሉ የአውደ ምህረት ግስላዎች እስቲ ሰው ሁኑና የቅኔውን ይዘት ጽፋችሁ አብራሩልን።